Ethiopia Customs Commission
5.41K subscribers
2.85K photos
3 videos
51 files
325 links
Download Telegram
ከ371 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***********
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 03 ቀን 2016 ዓ.ም )
የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 23 ቀን እስከ ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 128 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 243.7 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 371.7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተያዙ፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የተለያዩ የምግብ አይነቶች፣ አደንዛዥ እፆች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሞያሌ እና አዋሽ ጉ/ቅ/ፅ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ እንደ ቅደም ተከተላቸው 225 ሚሊዮን፣ 58 ሚሊዮን እና 31 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረገው የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሰባት ተጠርጣሪዎች እና አስር ተሽከርካሪዎችንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የፌደራልና የክልል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ አፈፃፀም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
የጉምሩክ ወንጀል በሃገር ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ተደራራቢ በመሆኑ ጥፋተኛ በሆኑ አካላት ላይ ተመጣጣኝ እና አስተማሪ የሆነ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ተገለጸ
#######################

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም)

የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት የጉምሩክ ወንጀሎች ምንነት፣ የሚያስከትሉት የወንጀል እና አስተዳደራዊ ተጠያቂነትን በሚመለከት ከምስራቅ ሸዋ ዞን የፍትህ እና የጸጥታ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡ ፡

በውይይቱ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ተወካይ አቶ ኃይሉ ድሪባ፤ ኮሚሽኑ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ እንዳይተገብር ከሚያደርጉ ችግሮች መካከል በጉምሩክ አሰራር ላይ የሚፈፀም ወንጀል ዋነኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በተለይም በወንጀል ምርመራ እና በክስ አመሰራረት ሂደት የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን ለመቀነስ ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው መስራት እንደሚገባቸው አቶ ሀይሉ ተናግረዋል።

የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ጌቱ አለሙ በበኩላቸው፤ በ2016 የበጀት ዓመት በኮሚሽኑ ከተያዘው 210 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ውስጥ የቅ/ጽ/ቤቱ ድርሻ 62 ቢሊዮን ወይም 30 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል ። ባለፉት 11 ወራትም 57 ቢሊዮን ብር ገቢ በቅ/ ጽ/ቤቱ መሰብሰቡንም ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጁ አክለውም፤ ባለፉት ወራት በገቢ አሰባሰብ እና በሌሎችም ስራዎች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስረድተው የጉምሩክ ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ መልካቸው በመቀያየር ፈተና እንደሆኑም አስረድተዋል።

የፌደራል የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው ፤ ኮሚሽኑ በታክስ አከፋፈል የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመመርመር ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ውሳኔ እንደሚሰጥ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም የጉምሩክ እና የታክስ ቅሬታዎች ውስብሰብ በመሆናቸው ችግሩን ለመቀነስ ውይይቱ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ምድብ ችሎት አስተባባሪ ወ/ሮ አሻ አሚኒ በበኩላቸው የጉምሩክ ወንጀሎች በሃገር ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ተደራራቢ መሆኑን በመጥቀስ ጥፋተኛ በሆኑ አካላት ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በውይይት መድረኩ የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት የህግ ተገዢነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅር ታምሬ የጉምሩክ ወንጀሎች ምንነት፣ የሚያስከትሉት የወንጀል እና አስተዳደራዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት :-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsommission

Facebook (https://www.facebook.com/ecczena)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ባለፉት 11 ወራትት 171 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል
*********

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም )
በጉምሩክ ኮሚሽን የዋናው መስሪያቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት እድገት ያለበትን ደረጃ እንዲሁም የኮሚሽኑን የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ ቀናት ስራዎች ክንውንን በሚመለከት ውይይት አድርገዋል፡፡

አጠቃላይ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ተስፋና ስጋቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ የ11 ወራት ዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብዲሳ ዱፌራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ፣ እንደ ሀገር ባለፉት ዓመታት በሁሉም መስኮች ተጨባጭ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገባቸውን ገልጸው ይህ ውጤት እንዲቀጥልም የጋራ ጥረትና ርብርብ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

ውይይቱ በ2016 የበጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያጋጠሙ ችግሮችንም መፍትሔ ለማበጀት እንዲሁም ለ2017 የበጀት ዓመት እቅድ ግብዓት ለመሰብሰብ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት እንደተመላከተው፣ በ2016 የበጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት 191 ነጥብ 96 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 171 ነጥብ 4 ቢሊዮን ወይም የእቅዱን 89.3 በመቶ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወይም በ6 ነጥብ 4 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን በሪፖርቱ የተቀመጠ ሲሆን ባለፉት 11 ወራትም 9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የወጭ በድምሩ 14 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በውይይቱ ሀገራዊ እና ተቋማዊ አስቻይ ሁኔታዎች እንዲሁም ፈተናዎች የተነሱ ሲሆን በተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission