⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye)
13.4K subscribers
1.66K photos
7 videos
494 files
818 links
Download Telegram
♧ ሰ.መ.ቁ. 212950 [ቅፅ 27]

♧ ተከሳሽ ይከላከል ከተባለ በኋላ በመከላከያ ማስረጃው ማስረዳት የሚጠበቅበት በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ነው ወይስ ጥርጣሬ መፍጠር ????

♧ በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ የሚታዘዘው በዓቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዲያስተባብል ሲሆን ማስተባበል ማለት ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፋተኝነት አረጋግጠዋል በተባሉት ማስረጃዎች ላይ በእንድም ይሁን በሌላ መንገድ ጥርጣሬ እንዲፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዳት አቅም ላይ መተማመን እንዳይኖር ማድረግ በመሆኑ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን የዐቃቤ ህግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ ስለመሆኑ ተወስኗል
❤12
#ምንጩ #ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በማከማቸት #የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የማስረዳት ግዴታ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን #ብቻ ለፍርድ ቤቱ #በማሳየት የሚወሰን #ሳይሆን፣ #በዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ #ከተረጋገጠው ገቢ #ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት #ትክክለኛ #ምንጭ #ምን #አንደሆነ #የማስረዳት #ግዴታና #ኃላፊነት #ያለበት ስለመሆኑ
🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢🧢

የሰበሩ የውሳኔ ትንታኔ⛑
💦💦💦💦

➤ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 ንዑስ አንቀጽ 1//ሀ/ እና /ለ/ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው ዐቃቤ ሕግ የመንግስት ሠራተኛ የሆነው ወይም የነበረው ሰው ያገኝ የነበረውና የሚያገኘው ገቢ ምን ያህል እንደሆነና የመንግስት ሠራተኛው በራሱ ስምም
ሆነ በቤተሰቡ ስም ከሕጋዊ ገቢው ውጪ ይዞት የሚገኘውን የገንዘብና የንብረት ግምት የማስረዳት ግዴታ ያለበት መሆኑን በመግልፅ ተደንግጓል፡፡

➤በሌላ በኩል የመንግስት ሠራተኛ የነበረው ሰው ከነበረውና ከሚያገኘው ገቢ በላይ ይዞት የተገኘው ገንዘብ ወይም ሀብት ትክክለኛው ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዳት ግዴታ እንዳለበት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 419 ንዑስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፓራግራፍ ፣ “… የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ በእጁ እንዴት እንደገባ ለፍርድ ቤቱ ካላስረዳ በስተቀር” ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ይዞ በመገኘቱ ጥፋተኛ ተብለው በሕጉ የተደነገገው ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል በመግለፅ ይደነግጋሉ፡፡

ከዚህም የምንረዳው ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ከሚታወቀው ሕጋዊ ገቢ በላይ ነው በማለት በክሱ የተገለፀውንና በማስረጃ ያረጋገጠውን ሀብት ትክክለኛ ምንጭ የማስረዳት ግዴታ / Burden of Proof/ በተከሳሾች ላይ የሚወድቅ መሆኑን ነው፡፡

የተከሳሾች የማስረዳት ግዴታም ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን ብቻ ለፍርድ ቤቱ በማሳየት የሚወሰን ሳይሆን፣ በዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከተረጋገጠው ገቢ ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት ትክክለኛ ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዳት ግዴታና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 ንዑስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፓራግራፍ ድንገጌ አቀራረፅና ይዘት ለመረዳት ይቻላል፡፡

➤ስለሆነም #ምንጩ #ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በማከማቸት #የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ክስ የቀረበበት ተከሳሽ የማስረዳት ግዴታ ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሽ ሌላ ገቢ የሚያገኝበት ስራ ወይም የገቢ ምንጭ ያለው መሆኑን #ብቻ ለፍርድ ቤቱ #በማሳየት የሚወሰን #ሳይሆን፣ #በዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ #ከተረጋገጠው ገቢ #ውጭ በእጁ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት #ትክክለኛ #ምንጭ #ምን #አንደሆነ #የማስረዳት #ግዴታና #ኃላፊነት #ያለበት ስለመሆኑ፡- የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 /1//ሀ/ እና /ለ/ መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 137672 ህዳር 25 ቀን 2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።
❤6👌1
"የማህበራዊ ፍርድ ቤት #ሥልጣን_ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ባይሻርም ተፈፃሚነት የለውም!"

በአገራችን የሕግ ሥርዓት ውስጥ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የተቋቋሙት ቀላልና አነስተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ግጭቶችን ለመፍታት ነው። ነገር ግን፣ እነዚህ ፍርድ ቤቶች የሕግ ሥልጣን ከሌላቸው ጉዳይ ውስጥ ገብተው ውሳኔ ቢሰጡ ውጤቱ ምን ይሆናል?

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 256261 (ሰኔ 2017 ዓ.ም) በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚከተሉትን ነጥቦች ግልጽ አድርጓል፦

🔍 ዋና ዋና ነጥቦች፦

የሥልጣን ወሰን፦ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የገጠር የእርሻ መሬትን በሚመለከት ክርክር አይተው የመወሰን የሥነ-ነገር (Subject Matter Jurisdiction) ሥልጣን የላቸውም።

የሕገ-መንግሥት ጥሰት፦ አንድ ፍርድ ቤት በሕግ ያልተሰጠውን ሥልጣን ተጠቅሞ ውሳኔ መስጠቱ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78(5) እና 40(3)ን የሚጥስ ተግባር ነው።

"ሳይሻር የቆየ ውሳኔ" ውጤት፦ የማህበራዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ፣ በወቅቱ በይግባኝ ባይሻርም እንኳ፣ ውሳኔው ከመሠረቱ የሕግ መሠረት የሌለው (Null and Void) በመሆኑ "ውሳኔው አልተሻረም" በሚል ምክንያት ብቻ ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም።

የሰበር ትርጉም፦ ቀደም ሲል በሰ/መ/ቁ 105677 ላይ "የማህበራዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ በይግባኝ ካልተሻረ ይጸናል" ተብሎ የተሰጠው ትርጉም፣ መደበኛ የሥነ-ሥርዓት ግድፈቶችን እንጂ የሥልጣን (Jurisdiction) ጉድለትን አይጨምርም።

💡 ትምህርቱ ምንድን ነው?

አንድ ፍርድ ቤት (በተለይም የማህበራዊ ፍርድ ቤት) በሕግ ያልተሰጠውን የዳኝነት ሥልጣን ተጠቅሞ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ፣ በማንኛውም ጊዜ ሊታረም እንደሚችልና ተፈፃሚነት እንደሌለው ሊታወቅ ይገባል።
"የሥልጣን ጥሰት በዝምታ አይጸድቅም!"

የማህበራዊ ፍርድ ቤት ሥልጣን ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ባይሻርም ተፈፃሚነት የለውም።

(ሰ/መ/ቁ 256261)
❤12
በቤት ሽያጭ ውል ላይ የቤቱ ስመ ሀብት በገዢ ስም ስለዞረ ብቻ ሻጭ ንብረቱን የመሸጥ ሕጋዊ መብት እንደነበረው ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም
🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛🏛

➤በቤት ሽያጭ ውል ላይ ሻጭ ቤቱን ለማስተላለፍ የሚያስችል ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ሕጋዊ መብት እንዳለው ሊረጋገጥ ይገባል።

➤ይህ ካልተረጋገጠ የራስ ባልሆነ ንብረት ላይ የተደረገ ውል ውጤት አይኖረውም።

➤በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1195 መሠረት የማይንቀሳቀስ ንብረት በስሙ የተመዘገበለት ሰው የንብረቱ ባለቤት እንደሆነ ቢገመትም ይህ ግምት ግን በሌላ ማስረጃ ሊፈርስ የሚችል ነው።

➤የቤቱ ስመ ሀብት በገዢ ስም ስለዞረ ብቻ ሻጭ ንብረቱን የመሸጥ ሕጋዊ መብት እንደነበረው ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

➤የቤቱ ስመ-ሀብት በገዢው ስም መዛወሩ ብቻ ውሉን ሕጋዊ አያደርገውም በማለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.208266 ሚያዝያ 24/8/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል። ➡(ቅጽ 26)
❤18👏3
ዋስትና መከልከል
አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ መድብለ ሕግ ዐዋጅ ቁ.1410/2018 የዋስትና መብት ከመከልከል አኳያ ብዙ ለውጦችን አድርጎአል::
ለምሳሌ:-
1. #በሴቶችና ሕጻናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል የተጠረጠረ ሰው በፖሊስ ዋስትና (police bond) ሊወጣ አይችልም::
*መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪውን የግድ ወደ ጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት በማቅረብ በዋስትና ጉዳይ ላይ ዳኛ ብይን እንዲሰጥበት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ (አንቀጽ 117(3)

2. #በሴቶችና ሕጻናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል መጠርጠር/መከሰስ በፍ/ቤት ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት ነው:: አንቀጽ 139(2/መ)
*[በርግጥ ሴቶችና ሕፃናት በመድብለ ሕጉ ውስጥ ልዩ ትኩረት አግኝተዋል::]

3. #ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ቋሚ አድራሻ ከሌለው ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት ነው:: (አንቀጽ 139(2/ሐ)::
*ስለዚህ ቋሚ አድራሻ አለመኖር ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት አይደለም የሚለው የሰበር ውሳኔ ተሽሮአል::
*ያለው አማራጭ "ቋሚ አድራሻ"ን ላይ በሰበር ሰፋ አድጎ ከዋስትና ሕገ መንግሥታዊ መርኅነት አኳያ ማስተርጎም ብቻ ነው::

4. #ተጠርጣሪው/ተከሳሹ የተጠረጠረበት ወይም የተከሰሰበት ወንጀል አፈጻጸም አደገኛ ከሆነ ወይም ወንጀሉ አሰቃቂ በመሆኑ ምክንያት ተጠርጣሪው/ተከሳሹን በዋስትና መልቀቅ ዜጎች በፍትሕ ላይ ያላቸው አመኔታ የሚያሳጣ ነው ፍ/ቤቱ ካመነ ዋስትና ሊከለክል ይችላል::
*ይህም ከPresumption of innocence ጋር የሚጋጭ ይመስላል::

5. #በተደጋጋሚ በጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ወንጀል መፈጸም ዋስትና ያስከለክላል:: (አንቀጽ 139(2/ሀ)
*ያልገባኝ፥ የቀድሞ የወንጀል ጥፋተኛነት ባሕርይ (previous conviction) ከፍርድ በፊት ስለ ዋስትና ብይን ለመስጠት ተገቢነት ሊኖረው ነው?

6. #በሞት ወይም፣ 15 ዓመት እና ከዚያ በላይ ሊያቀጣ በሚችል ሰው በሞተበት ወንጀል የተጠረጠረ/የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት የለውም:: (አንቀጽ 138(2,3)
*ይህ እንኳን ነባር ነው—የቀድሞውን የወ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 63 ያጸና::
❤8👍1
በአዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች ...

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ዘመኑን የዋጁ እና የሰብዓዊ መብቶችን አጠባበቅ የሚያጠናክሩ በርካታ የሕግ ማዕቀፎች ተካተውበታል፡፡

ከ6ዐ ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 በመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።

ከተሻሻሉ ዋና ዋና ሕጎች መካከል የዲጂታል ማስረጃዎች ዕውቅና አንዱ ሲሆን ይህም የቴክኖሎጂ ለውጥን ያገናዘበ የሕግ ማዕቀፍ ነው፡፡

ለአብነትም የቪዲዮ ምስሎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ የኮምፒውተር መረጃዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች እንደ ትክክለኛ ማስረጃ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሕጋዊ መሠረት ሰጥቷል።

ሌላው የተሻሻለው የምርመራ ዘዴዎች እና የሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከት ሲሆን፤ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ያላቸው መብት፣ የምርመራ ጊዜ ገደብ እና በምርመራ ወቅት ጠበቃ የማግኘት መብታቸው በግልጽ ተቀምጧል።

በዚህም መሰረት አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ሲውል ጠበቃው እስኪመጣ ቃሉን ያለመስጠት መብቱ የሚጠበቅለት ሲሆን የተጠርጣሪው የምርመራ ገደብ ከአራት ወር እንዳይበልጥ በማድረግ ተጠርጣሪ ለረጅም ጊዜ በምርመራ እንዳይቆይ ያስችላል።

የተጎጂዎችን መብት በሚመለከት የወንጀል ድርጊት የተፈጸመባቸው ሰዎች በፍትሕ ሂደቱ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ፣ ጉዳታቸው የሚካካስበት መንገድ እና የሚደረግላቸው ጥበቃ ትኩረት አግኝቷል።

ሌላው የዋስትና መብትን እንደ መሠረታዊ መብት መከልከልን እንደ ልዩ ሁኔታ የሚመለከት ሕግ ሲሆን፤ በዚህም ሕጉ ግልጽ የሆኑ የዋስትና ዓይነቶችን አስቀምጧል።

እነሱም በግል ማረጋገጫ በሰው ዋስትና፣ በንብረት ዋስትና ወይም በገንዘብ ማስያዝ የሚልን አካትቷል።

ሌላኛው የምስክሮች እና የጠቋሚዎች ጥበቃ የሚመለከት ሲሆን በከባድ ወንጀሎች ላይ መረጃ የሚሰጡ ጥቆማ ሰጪዎች እና ምሥክሮች ከበቀል ወይም ከጥቃት እንዲጠበቁ የሚያስችል የሕግ ከለላ መስጠትን ይመለከታል።

በተመሳሳይ የዐቃቤ ሕግ የክስ ድርድርን በተመለከተ አንድ ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ ጥፋተኛነቱን አምኖ ከዐቃቤ ሕግ ጋር በመደራደር ቅጣቱ እንዲቀልለት ወይም ክሱ እንዲቋረጥ የሚያስችል ሥርዓት በሕጉ እንዲካተት ተደርጓል።

በዚህም በአዋጁ ዐቃቤ ሕግ ክስ ለማንሳት የሚችልባቸው ምክንያቶችና ቅድመ ሁኔታዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።

የክስ ድርድር በሚመለከት ክስ ከመመሥረቱ በፊት ወይም ክስ ከተመሠረተ በኋላ ፍርድ እስከሚሰጥ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ጥፋተኛነቱን አምኖ ከዐቃቤ ሕግ ጋር ሊደራደር ይችላል።

የድርድር ዓይነቶችን በሚመለከት ከባድ የሆነውን ክስ ወደ ቀለል ያለ የወንጀል ዓይነት በመቀየር መደራደር እንዲሁም በቅጣት ድርድር በክሱ ላይ ተስማምቶ ቅጣቱ እንዲቀልለት መደራደር የሚል ይገኝበታል።

በዚህም በድርድሩ የተደረገው በፈቃደኝነት መሆኑን፣ ተከሳሹ መብቶቹን መረዳቱን እና ድርድሩ የሕዝብን ጥቅም የማይጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ አለበት።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ድርድሩን ውድቅ የማድረግ ሥልጣን ያለው ሲሆን በተለይም ዐቃቤ ሕግ የክስ ድርድር ሲያደርግ የወንጀል ተጎጂዎችን ፍላጎትና ስሜት ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ሕጉ ይደነግጋል።

ተጎጂው ካሳ የሚያገኝበት መንገድም በድርድሩ ውስጥ የተከካተተ ሲሆን ይህም ተከሳሹ የቅጣት ቅናሽ እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ድርድሩ መንግሥት ለምስክሮች እና ለረጅም ክርክር የሚያወጣውን ወጪ ይቆጥባል፣ ተጎጂዎች ደግሞ የፍርድ ሂደቱን ሳይጠብቁ ካሳ ወይም ይቅርታ ሊያገኙ ይችላሉ።

በአጠቃላይ እነዚህ ለውጦች ፍትሕን በፍጥነት ለመስጠት እና የተጠርጣሪዎችንም ሆነ የተጎጂዎችን መብት በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ናቸው፡፡

ይህም በሀገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ አፈጻጸሙም ከሕገ መንግሥቱ እና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

FBC በታሪክ አዱኛ
❤17
7 (ሰባት) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ የሰበር ውሳኔ፤ መዝገብ ቁጥር 271726

ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡

የውሳኔውን ሙሉ ይዘት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከቴሌግራም ቻናላችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
👍14❤4
ከመንፈስ መጫን ምክንያት ዉጪ ስጦታን ለመቀነስ ወይም ለመሰረዝ የሚቀርብ ክስ ይርጋ 10 ዓመት መሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰመቁ 232628 የሰጠዉ የህግ ትርጉም።

የፍ/ሕግ ቁጥር 2441(1) ይዘት ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሰረዝ የሚቀርብ ጥያቄ፣ ስጦታው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ለዳኞች ካልቀረበ በስተቀር ዋጋ የለውም ይላል።

የክርክሩ አመጣጥ

አመልካች በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ሲሆን፣ 1ኛ ተጠሪ በጀርመንኛ የተጻፈ ውክልናን ትርጉም በማዛባት የአመልካችን የውርስ ድርሻ ለ2ኛ ተጠሪ በስጦታ አስተላልፈዋል በማለት የስጦታ ውሉ እንዲፈርስ ክስ አቅርበዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው አመልካች ቀደም ብለው ድርሻቸውን መልቀቃቸውን እና ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ ይታገዳል በማለት ተከራክረዋል።

የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ

የስጦታ ውልን ለመቃወም ያለው የይርጋ ጊዜ 2 ዓመት ነው በሚል ክሱን በይርጋ ውድቅ አድርገውታል።

የሰበር ሰሚ ችሎቱ ውሳኔው

ምንም እንኳን ይህ የሕግ ቁጥር (2441) በስጦታ ላይ የሁለት ዓመት ገደብ ቢያስቀምጥምየሰበር ችሎቱ
በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2441 የተመለከተው የ2 ዓመት ይርጋ የሚያገለግለው በስጦታ ሰጪው ላይ "የመንፈስ መጫን" (Undue Influence) ተፈጥሮ የተደረገን ስጦታ ለማፍረስ በሚቀርብ ክስ ላይ ብቻ ነው።

ከመንፈስ መጫን ውጭ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች (ለምሳሌ በውክልና ሥልጣን ያለአግባብ መጠቀም) የሚቀርብ የስጦታ ውል ለማፍረስ ወይም ለመቀነስ የሚቀርብ ክስ በሕግ ቁጥር 1845 መሠረት በ10 ዓመት የይርጋ ደንብ የሚመራ መሆኑን ችሎቱ ወስኗል።
👇👇
https://t.me/ethiolawtips
❤13👏2
አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ይዞ የመጣ ሰነድ ነው። ይህ ሕግ ከረዥም ዓመታት በኋላ የቆየውን የ1954ቱን የሥነ-ሥርዓት ሕግ በመተካት፣ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሰብአዊ መብት መርሆችን ያካተተ ነው በትክክል ስራ ላይ የሚል ከሆነ በወንጀል የፍትህ ስረአቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥ እጅግ የላቀ ነው ።
1. የሕጉ ዋና ዓላማ
* የፍትሕ ጥራትን ማሻሻል፡ የወንጀል ምርመራ እና የክስ ሂደት ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሆን ማድረግ።
* የተከሳሾችን መብት ማስጠበቅ፡ ሕገ-መንግሥታዊ የሆኑ የተከሳሽ መብቶች በተግባር እንዲተረጎሙ ማገዝ።
* የማስረጃ አቀራረብን ማዘመን፡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች (Digital Evidence) በችሎት ፊት እንዴት ተቀባይነት እንደሚያገኙ ዝርዝር ሥርዓት መዘርጋት።
### 2. በሕጉ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ ለውጦች
* የማስረጃ ሕግ መካተት፡ ቀደም ሲል ራሱን የቻለ የማስረጃ ሕግ ባለመኖሩ ይፈጠሩ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት፣ የወንጀል ሥነ-ሥርዓቱ እና የማስረጃ ሕጉ በአንድ ላይ እንዲጠቃለሉ ተደርጓል።
* የምርመራ ዘዴዎች፡ ሳይንሳዊ እና ዘመናዊ የምርመራ ዘዴዎች (ለምሳሌ የዲ.ኤን.ኤ/DNA ምርመራ እና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎች) አጠቃቀም
እና ሌሎችም
በቅርብ ቀን ሊያውቋቸው የሚገቡ ገሀዳዬች ላይ በቪዲዬ እንመለስበታለን።
❤14👍2👌1
አዳዲስ የጊዜ ገደቦች

አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ ዐዋጅ ቁጥር 1410/2018 ከሚደነቅባቸው አንዱ ነገር ብዙ አዳዲስ የወንጀል ፍትሕ ሂደት የጊዜ ገደቦችን መደንገጉ ነው:: ከእነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹን እንጠቃቅሳለን::👴🏽
(By Hailu Hasena (Lawyer)

1. የተጨማሪ የወንጀል ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በአንድ ጊዜ እስከ 14 ቀን ሊፈቀድ የሚቻል ሲሆን አጠቃላይ የምርመራ ጊዜ ግን #በማናቸውም ምክንያት ከ4 (አራት) ወር ሊበልጥ አይችልም: ተብሎ ትደንግጓል:: አንቀጽ 119(2)

ይሁንና ወንጀሎች ቀላል፣ መካከለኛ እና ከባድ ተብለው የተከፋፈሉ እንደመሆኑ አጠቃላይ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮም በዚህ አግባብ ቢከፋፈል ጥሩ ነበር::👴🏽

2. የወንጀል ምርመራው ተጠናቆ በዐቃቤ ሕግ ክስ እስኪመሠርት ያለው የመሸጋገሪያ ጊዜ ቀጠሮ በመደበኛነት እስከ 20 ቀን ሆኖ በአጠቃላይ ግን ከ 34 ቀን ሊበልጥ አይችልም: ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 119(4)፣ 197(1)፣ 198(2)
* የጊዜ ገደቡ የሚሠራው ተጠርጣሪው ተይዞ ያለ ከሆነ ብቻ ነው::

3. ፍርድ ቤት በዐቃቤ ሕግ የተመሠረተን መደበኛ ክስ አይቶ ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ ተገድቧል:: አንቀጽ 232 (1), (2)::
በዚህ መሠረት:-
*ቀላል ክሶች=3 ወር (+45 ቀን) ማለትም በአጠቃላይ በ4 ወር ከ15 ቀን ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው::
*መካከለኛ ክሶች =6 ወር (+3ወር) ማለትም በአጠቃላይ በ9 ወር ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው::
*ከባድ ክሶች=12 ወር (+6ወር) ማለትም በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ከ6 ወር ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ማግኘት አለባቸው::
~ያልገባኝ በእነዚህ የጊዜ ገደቦች ውስጥ ውሳኔ ካልተሰጠ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለው ነው—ዳኛው መዝገቡን ባለበት ይዘጋል ቢባል ጥሩ ነበር::🙄

4. በዋስትና በመስጠት፣ በመከልከል ወይም በተፈቀደ የዋስትና ዓይነት ወይም መጠን ላይ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው ብይኑ በተሰጠ በ20 ቀን ውስጥ ነው::

*ይህ እንኳን ከጊዜ ገደብ አኳያ አዲስ አይደለም—ከነባሩ የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 75(1) ጋር ተመሳሳይ ነው::
ይሁንና የዋስትና ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ይግባኙ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ በይግባኙ ላይ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ተደንግጓል:: አንቀጽ 152(1), 153

*ይሁንና በተለይ በቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 66 ሥር ማናቸውም ፍ/ቤት የዋስትና ጉዳይ ሲመጣለት በ48 ሰዓት ውስጥ መወሰን አለበት ከሚለው አኳያ ሲታይ አዲሱ ሕግ ያዘገየዋል::

5. ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ ተገድቧል:: ይህም ፍ/ቤት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ ከሰጠ በኋላ ግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየታቸውን አጠቃለው ካቀረቡበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ፍ/ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፍ አለበት ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 301(1)

6. በዋናው የወንጀል ጉዳይ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት ጊዜ ፍርዱ፣ ውሳኔው፣ ብይኑ ወይም ትእዛዙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተደንግጎአል:: አንቀጽ 332(4)

*ይህም በቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 187 (1)፣ (2) መሠረት ይግባኝ ለማለት የሚፈልግ አካል ለይግባኝ የመዝገብ ግልባጭ እንዲሰጠው ውሳኔው በተሰጠ 15 ቀን ውስጥ ለወሰነው ፍ/ቤት ማመልከቻ የማቅረብ እና እና የውሳኔ ግልባጩ በደረሰው 30 ቀን ውስጥ ይግባኝ የማከፈት በድምሩ የ45 ቀን አሳሳች አሠራርን ቀሪ የሚያደርግ ነው::
ስለሆነም የወንጀልና የፍ/ብሔር ይግባኝ አቀራረብ የጊዜ ገደብ ተመሳሳይ ሆነ ማለት ነው::

7. የሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት ጊዜ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ 90 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተደንግጎአል:: አንቀጽ 344(3)
*ያው በቀድሞው የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ ኮድ ውስጥ ባለመጠቀሱ ምክንያት ለፎርማሊቲ ያህል አዲስ ነው ብለን ጠቀስነው እንጂ በተግባር አዲስ አይደለም::

8. የፍ/ቤት መጥሪያ ከቀነ ቀጠሮ 10 ቀን በፊት እንዲደርስ ተደንግጓል:: ማለትም የዐ/ሕግ ክስ ማመልከቻ ፍ/ቤቱ ቀጠሮ ክስ ለማንበብ ከያዘው ቀን አሥር (10) ቀን ቀደም ብሎ ለተከሳሽ ሊደርሰው ይገባል:: አንቀጽ 214(3)

እንዲሁም የተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ፍ/ቤቱ የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ከቀጠረበት ቀን አስቀድሞ ከ10 ቀናት በፊት ለዐ/ሕግ ሊደርሰው ይገባል:: አንቀጽ 288(2)

9. የግል አቤቱታ (private prosecution) እንዲያቀርብ በዐ/ሕግ የተፈቀደለት ሰው ፈቃዱን ባገኘ 15 የሥራ ቀን ውስጥ ክሱን አዘጋጅቶ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ አለበት።
በመሆኑም ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ ክስ ማቅረብ አይችልም:: አንቀጽ 200(3)

10. የግል የወንጀል ምርመራ አቤቱታ (complaint) የሚያቀርብ ሰው አቤቱታውን ባቀረበ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ለመርማሪ ፖሊስ ካላስረዳ የግል አቤቱታው ይሠረዛል::
አቤቱታው ከተሠረዘ በኋላ በጉዳዩ ላይ ድጋሚ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም: ተብሎ ተደንግጓል:: አንቀጽ 64(4)

11. በልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበሰብ በፍ/ቤት የሚሰጥ ጊዜ በመደበኛነት ከሦስት ወር አይበልጥም:: ይሁንና በዚህ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበሰብ በፍ/ቤት የሚሰጥ ጊዜ በማንኛውም ምክንያት ከ12 ወራት ሊበልጥ አይችልም::
አንቀጽ 105 (1)፣ (2)፣ (3)

12. የጥፋተኛነት ድርፍር (Plea bargaing) ማድረጊያ ጊዜም ተገድቧል:: ማለትም ዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጣመ በስተቀር ዐ/ሕግና ተከሳሹ (ጠበቃው) የጥፋተኛነት ድርድር ለማካሄድ ከተስማሙበት ቀን ጀምሮ 45 (አርባ አምስት) ቀናት ውስጥ ድርድሩ መጠናቀቅ አለበት፡፡
አንቀጽ 175(4)
*"ከዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ድርድሩ እስከመቼ እንደሚራዘም ቁርጥ ገደብ ቢቀመጥ ሸጋ ነበረ::

13. ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ ፍርድ ድጋሚ እንዲታይ የሚቀርብ አቤቱታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት:: አንቀጽ 221
*ይህ ጊዜ ከቀድሞው የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ. 198 ጋር ተመሳሳይ ነው::
ይሁንና በቀድሞው ኮድ የአንድ ወሩ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ተከሳሹ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ፍርድ እንደተሰጠበት ካወቀበት ቀን አንሥቶ ሲሆን በአዲሱ ኮድ ግን በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ፍርድ እንዲሰጥበት ያደረገው ምክንያት ከቀረበት ወይም ከተወገደበት ቀን ጀምሮ ነው::

*በነገራችን ላይ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት በመታየት ሂደት ላይ ያለ (ፍርድ ያላገኘ) ከሆነ ተከሳሹ በማንኛውም ጊዜ ክርክሩን መቀላቀል ይችላል:: ማለትም ፍ/ቤቱ በሌለህበት ጉዳዩን ለማየት ብይን (Ex parte ruling) ስለሰጠሁ ወደ ክርክሩ መግባት አትችልም ሊለው አይችልም:: አንቀጽ 218(4)

* አደራ! ተከሳሽ በሌለበት (trial in absentia) የተሰጠ ፍርድን ድጋሚ ማየት [አንቀጽ 218-222] እና ተከሳሽ ባለበት (trial in praesentia) ታይቶ የተሰጠ ፍርድን ድጋሚ ማየት [አንቀጽ 353-357] የተለያዩ ፅንሰ ሀሳቦች ናቸውና አይቀላቀል::
በዚህ መሠረት ተከሳሽ ባለበት ታይቶ የተሰጠ ፍርድ ድጋሚ እንዲታይ (review of judgement) ለመጠየቅ የሚቀርብ አቤቱታ የመጨረሻው ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ፍርዱን ለሰጠው ፍ/ቤት ሊቀርብ ይችላል:: አንቀጽ 355(1)

ነገሮች እየተወሳሰቡ፣ ጽሑፉም እየረዘመ ስለሆነ እዚህ እንቋጨው::😌
❤14👌2
ተሽከርካሪዎ እንዳይወረስ ከሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠ አዲስ የሕግ ትርጉም
*******

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 204922 በሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ፤ አንድ ተሽከርካሪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመደበቅ እንዲያስችል ተደርጎ አካሉ ተለውጦ (ሻግ ተበጅቶለት) ከተገኘ፣ ባለንብረቱ ድርጊቱን "አላውቅም" ቢል እንኳ ተሽከርካሪው ተወርሶ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን አጽንቷል።

ውሳኔው በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 147 (3) ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ ሕጉ ኮንትሮባንድ የጫነ ተሽከርካሪ እንዲወረስ የሚያዝዘው በተሽከርካሪው አካል ላይ የዕቃ መደበቂያ ተሰርቶበት መገኘቱ ሲረጋገጥ ብቻ መሆኑን ይገልጻል።

በዚህ ረገድ ባለንብረቱ ስለ ድርጊቱ አስቀድሞ ማወቁ ወይም አለማወቁ በሕጉ ፊት ዋጋ የማይሰጠው በመሆኑ፣ ተሽከርካሪው የመንግስት ንብረት ሆኖ እንዲመዘገብ የተሰጠውን ውሳኔ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አጽንቶታል።

ይህ ውሳኔ የመኪና ባለንብረቶች ለተሽከርካሪዎቻቸው ጥንቃቄና ክትትል እንዲያደርጉ የሚያሳስብ ጠንካራ የሕግ መልዕክት ያስተላልፋል።
❤14👍7
1776842465240.pdf
1.6 MB
የተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግሥት የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
❤6
👍10❤4
#የተዘጋ_መዝገብ_ለማንቀሳቀስ_አመልካች_በራሱ_ጉድለት_ወይም_ቸልተኝነት_ቀጠሮውን_ሳይከታተል_ቀርቶ_ካልሆነ_በቀር_ፍትህ_የማግኘትና_የመከራከር_መብት_ከግምት በማስገባት አመልካች የገጠመዉ እክል እንደ በቂ ምክንያት በመዉሰድ ለተጠሪ በቂ ወጪና ኪሳራ አስከፍሎ መዝገቡን ማንቀሳቀስ የሚገባ ስለመሆኑ።
በፌ/ብ/ሥ/ሥ/ሔ/ቁ.74 (2) ድንጋጌ መሰረት ‛በቂ ሆኖ የሚገመት እክል“ ምን እንደሆነ የተመከከተ ባይሆንም በቀጠሮ ለመቅረት ምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በቀር፣ ፍትህ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካች የገጠመዉ እክል እንደ በቂ ምክንያት በመዉሰድ ለተጠሪ ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ መደረጉ አግባብ ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ 182136 በቅፅ 24 ላይ የተሰጠ አስገዳጅ ውሳኔ።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.32 (2) እና 74 (1)
❤9
አንድ የመንግስት ሰራተኛ በተከሰሰበት የዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት ከስራ እንዲሰናበት ካልተወሰነበት በስተቀር ከስራ በታገደበት ወቅት ሳይከፈለው የቀረው ደመወዝ የሚከፈለው ስለመሆኑ ። ቅፅ 24 መዝገብ ቁጥር 161880

በአዲሱ የፌዴራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2024 (2025) መሰረት፡

የመንግስት ሰራተኛ በዲስፕሊን ጥፋት ምክንያት ከስራ ሲታገድ፣ በእግዱ ጊዜ ደመወዙ ሊቆም ይችላል።

በመጨረሻ ከስራ እንዲሰናበት ውሳኔ ካልተወሰነበት (ወይም ውሳኔው ካልተረጋገጠ)፣ በእግዱ ወቅት ያልተከፈለው ሙሉ ደመወዝ ያለ ወለድ መከፈል አለበት።
👍13❤2
በዋስትና ከመፈታት አኳያ አዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ ያመጣቸው አዳዲስ ነገሮች መካከል:-
By Hailu Hasena (Legal Advocate)

1. "ያለ ዋስትና መለቀቅ (Release without bail/unconditional release)" የተሰኘ አዲስ ድንጋጌ አምጥቷል::

በዚህ ድንጋጌ መሠረት ተጠርጣሪው የተጠረጠበትን ወንጀል ስለመፈጸሙ ወይም የተባለው ወንጀል ስለመፈጸሙ አጠራጣሪ (doubtful) በሆነ ጊዜ የወንጀል ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፍ/ቤትም ሆነ ቀዳሚ ምርመራ አድራጊ ፍ/ቤት ተጠርጣሪውን ያለ ዋስትና እንዲሁ እንዲለቁት ይገደዳሉ:: አንቀጽ 118(4)፣ 137(2)

*በቀድሞው የወ/መሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 59(1) እና 93 መሠረት የጊዜ ቀጠሮ እና የቀዳሚ ምርመራ ፍ/ቤቶች ተጠርጣሪው ወንጀል ስለመፈጸሙም ሆነ ወንጀሉ ራሱ ስለመፈጸሙ ቢጠራጠሩም ስንኳ ተጠርጣሪውን የግድ ዋስትና እንዲያስይዝ ወይም በማረፊያ ቤት እንዲቆይ እንዲያዙ ይገደዱ ነበር:: በአዲሱ መድብለ ሕግ ያ አሠራር ተሽሯል::

*ይህ ድንጋጌ በተለይ ለሚታፈሱ ወይም በመመሳጠር በፍ/ብሔር ወይም ወንጀል ባልሆነ ጉዳይ ለሚታሰሩ ሰዎች ይህ ትልቅ የሕግ ጥበቃ የሚያደርግ ነው::

*ስለዚህ የተያዙ ሰዎች የሚለቀቁባቸው መንገዶች እነዚህ ናቸው—ያለ ዋስትና መለቀቅ፣ ያለ ገደብ መለቀቅ፣ በራስ ዋስትና መለቀቅ፣ በንብረት ዋስትና መለቀቅ፣ በሰው ዋስትና፣ በገንዘብ ዋስትና መለቀቅ፣ በተጨማሪ ዋስትና መለቀቅ::

*ስለሆነም ከእንግዲህ የጠበቆች ሥራ የታሰረን ሰው በዋስትና ማስፈታት ብቻ ሳይሆን ያለ ዋስትና ማስፈታትንም ይጨምራል::

*Note: በፍ/ቤት መደበኛ ክስ (charge) የተከፈተ ከሆነ ያለ ዋስትና የመለቀቅ ጉዳይ አይነሣም::

2. በሕግ ዋስትና የሚያስከለክሉ ወንጀሎች (non-bailable crimes)
* በሞት የሚያስቀጡ ወንጀሎች፣ ወይም
* በ ≥15 ዓመት ጽኑ እሥራት የሚያስቀጡ ሰው የሞተባቸው ወንጀሎች ብቻ እንዲሆኑ የተደነገገ ስለሆነ በእንደዚህ ዓይነት ወንጀሎች ውጭ ያሉ ወንጀሎች በሙሉ በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎች (bailable crimes) ሆነዋል:: አንቀጽ 138(2,3)

ስለሆነም:-
➡️ስለሆነም በሕግ ዋስትናን በማይከለከልባቸው ወንጀሎች በመሉ ተጠርጣሪዎች/ተከሳሾች በዋስትና የመለቀቅ መብት አለው::

➡️በዕድሜ ልክ ወይም የጽኑ እሥራት ጣሪያ በሆነው በ25 ጽኑ እሥራት የሚያስቀጣ ወንጀል ብቻውን ዋስትናን አያስከለክልም::

➡️በማንኛውም የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ/የተከሰሰ ሰው በሕግ ዋስትናን አይከለከልም—all corruption crimes have become bailable.

ከዚህ ቀደም በዐዋጅ ቁ. 434/1997 (በዐዋጅ ቁ. 882/2007 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 4(1) መሠረት "ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰው በዋስትና አይለቀቅም በማለት ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጡትን ለይቶ non-bailable corruption crimes ተደርጎ የነበረው ድንጋጌ ቀሪ (abolished) ተደርጎአል::

➡️በአደገኛ ቦዘኔነት ዐዋጅ ቁጥር 384/96 አንቀጽ 6(3) "በአደገኛ ቦዘኔነት ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በዋስትና አይለቀቅም:" ተብሎ በወንጀል ዓይነት ዋስትና ይከለከል የነበረው (categorical bail denial) ዘፈቀዳዊ ነው ተብሎ በዚህ ዐዋጅ ተሽሮአል::

➡️በሕግ ዋስትና የማያስከለክሉ ወንጀሎችን (bailable crimes) አስመልክቶ ዋስትና መብት (right) ሲሆን ዋስትና ሊከለከልም ሊፈቀድም የሚችለው በዳኞች ፍቅድ ሥልጣን (judicial discretion) ነው::

ፍቅድ ሥልጣኑ የሚመራባቸው መርኆዎችም ደግሞ "ዳኛው ተጠርጣሪውን/ተከሳሹን በዋስትና ይለቃል የሚል ግምት (presumption of release on bail) ይወሰዳል:"፤ "ዋስትናን በሁኔታ የሚያስከለክሉ ሁኔታዎችም አይኖሩም: ተብሎ ይገመታል::"

"ዋስትናን ለመከልከል የሚያበቁ ልዩ ሁኔታዎች በጠባቡ እና ለተከሳሽ/ተጠርጣሪ በሚጠቅም መልኩ ይተረጎማሉ:" የሚሉ ናቸው—ከተመድ የሰብኣዊ መብቶች የዋስትና መብት ትርጉም አኳያ::

ለምሳሌ:- ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጣ ሌላ ወንጀል ይፈጽማል ወይም ማስረጃ ያጠፋል ወይም በተፈለገ ጊዜ አይቀርብም ወይም ቋም አድራሻ የለውም ወይም መውጣቱ ለኅ/ሰቡ ደኅንነት ያሰጋል ወይም የዋስትና ግዴታውን አይወጣም ወዘተ. የሚል ግምት አይያዝም::

ስለሆነም መርማሪ ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ እነዚህን መርኀዊ ግምቶች ለማስተባበልና ለመሠረታዊ መብቶች (የነጻነት መብት፣ ንጹሕ ሆኖ የመገመት መብት) የሥነ ሥርዓታዊ ጥበቃ የሆነውን የዋስትና መብት ለመቃወም ሕጋዊ፣ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት ያለ መሆኑን በቂ ማስረጃ በማቅረብ ማስረዳት ይኖርበታል::

3. የድኅረ ጥፋተኝነት ፍርድ ዋስትና (Post-conviction bail) የተሰኘ አዲስ ድንጋጌ አምጥቷል::
አንቀጽ 301(2)

ይህ ድንጋጌ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ነህ ተብሎ ከተፈረደበት በኋላ የቅጣት ውሳኔ እስኪተላለፍበት ድረስ ባለው ጊዜ በዋስትና እንዲቆይ የሚያደርግ ነው::
ይሁንና ይህ ዋስትና የሚሠራው ወንጀሉ በመቀጮ ብቻ የሚያስቀጣ ሲሆን ነው::

እንደሚታወቀው በነባሩ የወ/ሕ/ሥ/ሥ መሠረት ዳኞች የፈረዱበትን ማንኛውንም ሰው ቅጣቱ እስኪወሰን ድረስ 'ታስሮ' እንዲቆይ ያዙ ነበር—በጣም ጥቂት ሰብኣዊነት ላይ የተመሠረተ ልዩነት ቢኖርም::

ለዚህ እንደ ምክንያት ይጠቀስ የነበረው የዋስትና መብት ንጹሕ ሆኖ ከመገመት መርኅ ጋር ብቻ የተቆራኘ ስለሆነ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሲባል መብቱም ዐብሮ ቀሪ ይሆናል፣ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ በዋስትና ቢወጣ ሊጣልበት የሚችለውን ቅጣት ፈርቶ ላይቀርብ ስለሚችል የሚጣለው ቅጣት አፈጻጸም ችግር እንዳይገጥመው የሚል ግምት በመያዝ ነበር::

ይሁንና ሁለቱም ምክንያቶች የተሳሳቱ እና የሕግ ፍልስና መሠረት የሌላቸው ስለሆኑ በሥሡ ለማረም ተሞክሯል::

*ለምሳሌ በፌስታል ዐዋጅ ቁ. 1383/2017 አንቀጽ 25(1/ሀ) ሥር ፌስታል በመጠቀም ወይም ለመጠቀም ይዞ በመገኘት ወንጀል ተከሶ የጥፋተኛነት ፍርድ የተሰጠበት ተከሳሽ የቅጣት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በማረፊያ/በማቆያ ቤት እንዲቆይ አዲሱ ሕግ አይፈቅድም
❤16👏3