ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
6.9K subscribers
2.19K photos
74 videos
101 files
1.28K links
✔️በቻናላችን✔️
📲 የAndroid መተግበሪያ
💻 የPC SoftWare
📌 አዲስ ለሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች ልዩ ዘገባ

👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ
Download Telegram
ዲቪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ ሆኗል።

የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2025 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል።

መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ dvprogram.state.gov/ESC/ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት #ብቻ መሆኑን አሳስቧል።

ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም።

N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው።

ምናልባትም  " ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጉ ተብሏል።

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሆንም።

የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም።

@remoteict