ኢትዮ ቴክኖሎጂ ( Ethio technology )
7.14K subscribers
1.56K photos
57 videos
101 files
965 links
✔️በቻናላችን✔️
📲 የAndroid መተግበሪያ
💻 የPC SoftWare
📌 አዲስ ለሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች ልዩ ዘገባ

👉ለአስተያየትና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለማግኘት ይቀላቀላሉ
Download Telegram
#በቫይረስ የተጠቃ ፍላሽ ዲስክ ሶፍትዌር ሳንጠቀም እንዴት ማፅዳት እንችላለን ?
በቫይረስ የተጠቃ ፍላሽ ዲስክ እንዴት ያለአንቲ ቫይረስ እንደምናጸዳውና ስንገዛው እንደነበረው አዲስ እንደምናደርገው እናያለን።
እባክዎ ከመጀመርዎ በፊት ፍላሹ ላይ ጠቃሚ ፍይል ካለዎት ወደ ሌላ ቦታ ኮፒ ያድርጉ። ምክንያቱም ፋይሉ ሙሉ በሙሉ ስለሚጠፋ!
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ '#command_prompt' ወይም '#cmd' እንከፍታለን።
( '#cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ #cmd ብለን #search እናደርጋለን. #Cmd
ሲመጣልን right click አድርገን run as #administrator የሚለውን በመጫን cmdን
እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች በቅደም ተከተል እናስገባለን። እያንዳንዱን
ትእዛዝ ከጻፍን በኋላ ENTER ቁልፍን እንጫናለን
1. #DISKPART
2. #LIST DISK
(አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት
የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)
3. SELECT DISK *
(በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን)
4. CLEAN
(በዚህ ጊዜ ፍላሹ ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር ያጠፋዋል)
5. CREATE PARTITION PRIMARY
(ለፍላሹ ይዘት ይፈጥራል)
6. SELECT PARTITION 1
7. ACTIVE
(ይህ ፍላሹን ዝግጁ ያደርገዋል)
8. FORMAT FS=FAT32 Quick
(ይህ ፋላሹን በጥልቀት በመሰረዝ በውስጡ ያሉትን
ማንኛውም ቫይረስ ወይም ሌላ ችግር ያጠፋል። ሂደቱ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ
እስከሚጨርስ ወይም 100 % እስኪሞላ በትዕግስት እንጠብቀዋለን)
9. ASSIGN
(አዲስ ለፈጠርነው ፍላሽ የፊደል ስም ይሰጥልናል)
10. EXIT
(ፕሮሰሱን ይጨርስልናል)
አሁን አዲሱን ፋላሻችንን መንቀልም ሆነ መጠቀም እንችላለን። ይህንን መንገድ በመጠቀም
ማንኛውንም ቫይረሱ ያለበት ፍላሽ
ማስተካከል እንችላለን።