ጥበብ ፍልስፍና
⁶“#Love_is_a_serious_mental_disease” ሲንደሬላ አንድ ጫማ አውልቃ ፍጹም ፍቅር አገኘች። አንቺ ግን ሙሉ ልብስሽን አውልቀሽ ፍቅረኛ አጣሽ..🤓
⁷"#Love_is_a_serious_mental_disease" አይደለምን???
ፍቅር መልቀቅ ነው ( Love is a Detachment )
ፍቅር እና መጣበቅ (Love vs. Attachment)
ጭንቀት ፍቅር ሊሆን አይችልም።
የመልቀቅ ኃይል (The Power oiletting Go)
አሳዳጅ እና ተሳዳጅ ( he chaser and the Pursued )
ማጠቃለያ
እውነተኛ ፍቅር እንደ ክፍት እጅ ነው። እጅህን ጨብጠህ አሸዋ ብትይዝ አሸዋው በጣትህ መሃል ይፈስሳል። እጅህን ከፍተህ አሸዋውን ብታስቀምጠው ግን በቦታው ይረጋል። ፍቅርም እንደዚሁ ነው፤ ሳትይዘው ይኖርሃል፤ ልትይዘው ስትታገለው ግን ታጣዋለህ። የምትወዱትን ሰው ተዉት" ማለት እምነታችሁን በራሳችሁና በተፈጥሮ ፍሰት ላይ አድርጉ ማለት ነው። የፈቀዳችሁለት ነፃነት የእውነተኛ ፍቅራችሁ ልክ ነው።
#Explore_ur_mentality
ፍቅር መልቀቅ ነው ( Love is a Detachment )
ጭንቀት ፍቅር ሊሆን አይችልም፡፡ ፍቅር ከሁኔታዎች ወይም ከስሜታችን ጋር መጣበቅ አይደለም ነገር ግን ስሜታች እና ጥልቅ ፈታኝ ፍላጎቶችን በራሳቸው ፍሰት እንዲጓዝ መፍቀድ እንጂ። ስለሆነች ሴት አጥብቀህ የምትጨነቅ እና የምተብሰለሰል ከሆነ ዕውነቱን ልንገር አትወዳትም። የዕውነት የምትወዳት ከሆነ እንድትሄድ እና ለገዛ ፍቃዷ ተላልፋ እንድትሰጥ ፍቀድላት። ያኔ ጥልቅ የታከመ ስሜቷን ታስተውላለህ። እንድሄድ የፈቀድክለት ሰው ተመልሶ ካልመጣ መጀመሪያውንም አይጠቅምህም እንኳንም ሄደ። ለገዛ ፍቃዱ ታልልፎ የተሰጠ የፈቀድክለት እና ነፃነት የሰጠህው ሰው ተመልሶ ከመጣ የሕመሙን መታከም አስተውለህ ተቀበለው ፍቅር የራሴ የምትላትን ሴት አለማጣት አይደለም! ፍቅር የራሴ ያልካትን ሴት ለገዛ ውሳኔዋ ሙሉ ሐላፊነትን መስጠት እንጂ። መልቀቅ እና መተው የተተወውን ሰው ልቦና ይፈትናል። በስሜት መጣበቅ እና ማሳደድ ግን የአሳዳጁን ልቦና እንደ እሳት ያነዳል። የምትወዱትን ሰው ተዉት። የእውነት የሚወዳችሁን ታገኛላችሁ።
ፍቅር እና መጣበቅ (Love vs. Attachment)
ብዙዎቻችን ፍቅርን የምንረዳው ሰውን አጥብቆ በመያዝ ወይም የእኔ በማድረግ መስታወት ነው፡፡ ነገር ግን መጣበቅ የሚመነጨው ከፍርሃት ( የመታጣት የብቸኝነት ወይም የባዶነት ፍርሃት) ነው። ፍቅር ግን የሚመነጨው ከነፃነት ነው። መጣበቅ ( Attachment ) ያለ እሷ መኖር አልችልም ይላል፡፡ እዚህ ጋር ትኩረቱ እኔ ላይ ነው፡፡ የገዛ ስሜታችንን ለማርካት ሌላውን ሰው እንደ መቆጣጠሪያ እንጠቀማለን!!። ፍቅር እሷ ደስተኛ እንድትሆን እፈልጋለሁ ይላል። እዚህ ጋር ትኩረቱ እሷ ላይ ነው። ደስታዋ በእኔ እጅ ካልሆነ እንኳ ምርጫዋን ማክበር የፍቅር ነው። ምሳሌ አንድን ቆንጆ ወፍ ድምፅዋን እና ውበቷን ወደህ ቀፎ ውስጥ ብታስገባት፣ የምትወደው ወፏን ሳይሆን ወፋ የምትሰጥህን ስሜት ነው። ወፏን ግን ነፃነቷን ስታጣ ዝማሬዋ ይቆማል እወነተኛ ፍቅር ግን ወፍ በሰማይ ላይ ስትበር ማየትና ከነፃነቱ መደሰት ነው። ብትበርም ትመለስም፤ አንተ ነህ የበረራዋ ውበት ደስ ያሰኝሃለ
ጭንቀት ፍቅር ሊሆን አይችልም።
አንድን ሰው ለማጣት የምትጨነቀ ከሆነ ያ ስሜት ፍቅር ሳይሆን ስጋት ነው። ሌላውን ሰው ነፃነት ይነሳዋል የት ነሽ ከማን ጋር ነሽ፣ ለምን አልመለስሽም የሚል ጥያቄዎች ፍቅር ሳይሆኑ የራስን የውስጥ አለመረጋጋት በሌላው ላይ መጫን ናቸው። ስለሆነች ሴት አጥብቀህ የምትጨነቅ ከሆነ አትወዳትም ፍቅር መተማመን ነው። መተማመን ደግሞ አትከዳኝም ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን፣ “ብትሄድ እንኳ ለራሷ ምርጫ ክብር አለኝ ብሎ ራስን ማሳመን ነው
የመልቀቅ ኃይል (The Power oiletting Go)
ካንተ ጋር ሰውን እንዲሄድ ስትፈቅድለት፣ ያ ሰው ካንተ ጋር የሚቆየው ተገዶ ሳይሆን መርጦ ይሆናል። በፍላጎትና በምርጫ የሚሰጥ ፍቅር ደግሞ ፈውስ አለው፡ አንድን ሰው ልቀቀው ሲባል አትውደደው ማለት አይደለም ይልቁንም ካንተ ጋር እንዲሆን አታስገድደው ማለት ነው። በግዴታ የታሰረ ሰው ውስጡ ይቆስላል፣ ያምፃል ነፃነት የሰጠኸው ሰው ግን ወደ አንተ ተመልሶ ከመጣ፣ የመጣው ካለው ጥልቅ ፍቅርና ካገኘው ሰላም የተነሳ ነው። ያኔ ግንኙነቱ ከጭንቀት የፀዳ እና ጤናማ ይሆናል።
አሳዳጅ እና ተሳዳጅ ( he chaser and the Pursued )
በስሜት መጣበቅ አሳዳጅ ያደርጋል። አሳዳጅ በሆነክ ቁጥር ሌላው ሰው ተሳዳጅ ሆኖ እንዲሸሽ ታደርገዋለህ። አሳዳጁ ሁልጊዜ በጥርጣሬና በመታጣት እሳት ይቃጠላል። ሰውን ማሳደድ ማቆም፣ ወደራስ መመለስ ነው። የራስህን ሰላም ስትፈልግ የራስህን ማንነት ስታከብር፣ አንተን የሚመጥንና የእውነት የሚወድህ ሰው በራስ ጊዜ ወደ ህይወትህ ይመጣል።
ማጠቃለያ
እውነተኛ ፍቅር እንደ ክፍት እጅ ነው። እጅህን ጨብጠህ አሸዋ ብትይዝ አሸዋው በጣትህ መሃል ይፈስሳል። እጅህን ከፍተህ አሸዋውን ብታስቀምጠው ግን በቦታው ይረጋል። ፍቅርም እንደዚሁ ነው፤ ሳትይዘው ይኖርሃል፤ ልትይዘው ስትታገለው ግን ታጣዋለህ። የምትወዱትን ሰው ተዉት" ማለት እምነታችሁን በራሳችሁና በተፈጥሮ ፍሰት ላይ አድርጉ ማለት ነው። የፈቀዳችሁለት ነፃነት የእውነተኛ ፍቅራችሁ ልክ ነው።
#Explore_ur_mentality
❤10👍4🔥3👏3
ጥበብ ፍልስፍና
#Aboundenmenttrauma part6 1/ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች ውስጥ መግባት በየትኛውም ግንኙነት ውስጥ የሆነ Expectation አለ። በወላጅና ልጅ ግንኙነት ውስጥ፣ በፍቅር ግንኙነት፣ በስራ ባለደረባም ሆነ በጓደኝነት ውስጥም ሆነ በሌሎች ግንኙነቶቻችን እንዲደረግልን ወይም ለማግኘት የምንፈልጋቸው Expect የምናደርጋቸው ነገሮች አሉ። በተለይም ልጆች እያለን ከወላጆቻችን…
#Identity_Fragility የማንነት መሰባበር / የማንነት ደካማነት
አንድ ሰው ስለራሱ ማንነት፣ እሴቶች፣ እምነቶች እና ቦታ ያለውን ግንዛቤ ምን ያህል ደካማ፣ ያልተረጋጋ እና በቀላሉ ሊናወጥ እንደሚችል የሚገልጽ የስነ-ልቦና ሁኔታ ነው። ፤ ይህ ሁኔታ ያለባቸው ሰዎች የራሳቸውን ማንነት በግልጽና በፅናት ከመግለጽ ይልቅ፣ በውጫዊ ሁኔታዎች፣ በሌሎች ሰዎች አስተያየት ወይም በሚያጋጥሟቸው ክስተቶች በቀላሉ ይወሰናሉ። ፤ የማንነት መሰባበር ያለበት ሰው የራሱን ማንነት የሚገነባው ከውስጥ በሚመነጩ እሴቶችና እምነቶች ሳይሆን፣ በውጫዊ ማረጋገጫዎች (external validation)ነው።
ዋና ዋና ባህሪያት:
— በራስ አለመተማመን (Lack of Self-Confidence):
— የውጭ ማረጋገጫ ፍለጋ (Constant Need for External Validation)
— የማንነት አለመረጋጋት (Unstable Sense of Self)
— ለለውጥ መሸነፍ (Vulnerability to Influence)
— የ-መተው ፍርሃት (Fear of Abandonment)
— የድንበር አለመኖር (Lack of Boundaries)
የማንነት መሰባበር መንስኤዎች
— የልጅነት ልምዶች፡ በልጅነት ጊዜ በቂ ያልሆነ ፍቅር፣ ትኩረት ወይም ማረጋገጫ ካለማግኘት። ወላጆች ወይም ተንከባካቢዎች የልጁን ስሜት ወይም ማንነት ያለማክበር።
— አሰቃቂ ገጠመኞች #Trauma: በህይወት ውስጥ ያጋጠሙ ከባድ አሰቃቂ ገጠመኞች የሰውን ማንነት ሊያናውጡ ይችላሉ።
— ማህበራዊና ባህላዊ ግፊቶች: ማህበረሰቡ የሚያስቀምጣቸው የውበት፣ የስኬት ወይም የባህሪ መስፈርቶች ግለሰቡ የራሱን ማንነት እንዲጠራጠር ሊያደርጉት ይችላሉ።
የማንነት መሰባበር የሚያስከትላቸው ውጤቶች
— ሥር የሰደደ ስሜታዊ ጥገኝነት: ደስታን፣ ዋጋን እና ደህንነትን ለማግኘት በሌሎች ላይ ሙሉ በሙሉ መደገፍ።
— የግንኙነት ችግሮች: በቅናት፣ በጥርጣሬ፣ በራስ አለመተማመን እና በድንበር እጦት ምክንያት ጤናማ ግንኙነቶችን መገንባት አለመቻል ወይም ማቆየት አለመቻል።
— የአእምሮ ጤና ችግሮች: ጭንቀት፣ ድብርት፣ ዝቅተኛ በራስ መተማመን እና የድንበር ስብዕና መታወክ (Borderline Personality Disorder) የመሳሰሉ ችግሮች።
— የግል እድገት መቀዛቀዝ: የራሱን ማንነት ለመፈለግ እና ለማዳበር ከመሞከር ይልቅ፣ የሌሎችን ፍላጎት በማሟላት ላይ ማተኮር።
ምሳሌ

• ሰውየው ስለራሱ ማንነት፣ ችሎታዎች እና ዋጋ ጥልቅ የሆነ ጥርጣሬ አለው። ይህ ጥርጣሬ የሌሎችን አስተያየት እና ፍርድ ከመጠን በላይ እንዲያሰላስል ያደርገዋል።
— የውጭ ማረጋገጫ ፍለጋ (Constant Need for External Validation)
• የራሱን ዋጋ የሚያገኘው ሌሎች ሲያመሰግኑት፣ ሲቀበሉት ወይም ሲያደንቁት ብቻ ነው። ፤ የሌሎች ሰዎች አሉታዊ አስተያየት በቀላሉ ያናውጠዋል እና የራሱን ማንነት እንዲጠራጠር ያደርገዋል። "እኔ ጥሩ ነኝ ወይስ አይደለሁም?" የሚለው ጥያቄ ሁልጊዜ በአእምሮው ውስጥ ይኖራል።
— የማንነት አለመረጋጋት (Unstable Sense of Self)
የራሱን ማንነት በየጊዜው ይለውጣል። ከማን ጋር እንዳለ ወይም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ በመመስረት፣ የራሱን አስተያየት፣ እምነት ወይም ባህሪ ሊቀይር ይችላል። "እውነተኛው እኔ ማን ነኝ?" የሚለው ጥያቄ ግልጽ መልስ የለውም" ።
— ለለውጥ መሸነፍ (Vulnerability to Influence)
ለቡድን ግፊት (peer pressure) ወይም ለሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ በቀላሉ ይሸነፋሉ። የራሱን አቋም አጥብቆ መያዝ ይቸገራል፤ ምክንያቱም የራሱ አቋም ጠንካራ መሠረት የለውም።
— የ-መተው ፍርሃት (Fear of Abandonment)
የራሱ ማንነት ደካማ ስለሆነ፣ ሌሎች ሰዎች ቢተዉት ወይም ግንኙነቱ ቢቋረጥ ሙሉ በሙሉ ባዶ እንደሚሆን ይሰማዋል። ይህ ፍርሃት ግንኙነቶችን ከመጠን በላይ እንዲጣበቅ ወይም የሌሎችን ፍላጎት ከራሱ ፍላጎት በላይ እንዲያስቀድም ያደርገዋል።
— የድንበር አለመኖር (Lack of Boundaries)
በራሱ እና በሌሎች መካከል ግልጽ የሆኑ የስሜት ወይም የአካል ድንበሮችን ማስቀመጥ ይቸገራል። ሌሎች ሰዎች ድንበሩን ሲጥሱ በቀላሉ ይፈቅዳል።
የማንነት መሰባበር መንስኤዎች
— የልጅነት ልምዶች፡ በልጅነት ጊዜ በቂ ያልሆነ ፍቅር፣ ትኩረት ወይም ማረጋገጫ ካለማግኘት። ወላጆች ወይም ተንከባካቢዎች የልጁን ስሜት ወይም ማንነት ያለማክበር።
— አሰቃቂ ገጠመኞች #Trauma: በህይወት ውስጥ ያጋጠሙ ከባድ አሰቃቂ ገጠመኞች የሰውን ማንነት ሊያናውጡ ይችላሉ።
— ማህበራዊና ባህላዊ ግፊቶች: ማህበረሰቡ የሚያስቀምጣቸው የውበት፣ የስኬት ወይም የባህሪ መስፈርቶች ግለሰቡ የራሱን ማንነት እንዲጠራጠር ሊያደርጉት ይችላሉ።
የማንነት መሰባበር የሚያስከትላቸው ውጤቶች
— ሥር የሰደደ ስሜታዊ ጥገኝነት: ደስታን፣ ዋጋን እና ደህንነትን ለማግኘት በሌሎች ላይ ሙሉ በሙሉ መደገፍ።
— የግንኙነት ችግሮች: በቅናት፣ በጥርጣሬ፣ በራስ አለመተማመን እና በድንበር እጦት ምክንያት ጤናማ ግንኙነቶችን መገንባት አለመቻል ወይም ማቆየት አለመቻል።
— የአእምሮ ጤና ችግሮች: ጭንቀት፣ ድብርት፣ ዝቅተኛ በራስ መተማመን እና የድንበር ስብዕና መታወክ (Borderline Personality Disorder) የመሳሰሉ ችግሮች።
— የግል እድገት መቀዛቀዝ: የራሱን ማንነት ለመፈለግ እና ለማዳበር ከመሞከር ይልቅ፣ የሌሎችን ፍላጎት በማሟላት ላይ ማተኮር።
ምሳሌ
አንድ ሰው በልጅነቱ ወላጆቹ ሁልጊዜም "ጎበዝ ስትሆን ብቻ ነው የምንወድህ/ሽ" ወይም "የምትፈልገውን ሳይሆን እኛ የምንፈልገውን ስታደርግ ብቻ ነው ጥሩ ልጅ የምትሆነው" እያሉ ያሳድጉት እንበል። ይህ ልጅ ሲያድግ የራሱ የሆነ አስተያየት ወይም ፍላጎት ቢኖረውም፣ ወላጆቹ የሚፈልጉትን በማድረግ ብቻ ነው ፍቅርና እውቅና የሚያገኘው።
ይህ ሰው ሲያድግ የራሱ የሆነ ጠንካራ ማንነት አይኖረውም። ከማን ጋር እንዳለ በመመስረት የራሱን ባህሪ ይለውጣል። ከጓደኞቹ ጋር ሲሆን እንደ እነሱ፣ ከባልደረባው ጋር ሲሆን እንደ እሱ/ሷ ይሆናል። የራሱ አስተያየት ሲኖረው እንኳ፣ ሌሎች ካልተስማሙበት ወዲያውኑ ይቀይራል። "እኔ ማነኝ?" የሚለው ጥያቄ ሲመጣበት ግልጽ መልስ አይኖረውም። ይህ የማንነት መሰባበር ምልክት ነው። የማንነት መሰባበር አንድ ሰው ስለራሱ ያለውን ግንዛቤ ደካማ የሚያደርግ የስነ-ልቦና ሁኔታ ነው። ይህ ሁኔታ ያለባቸው ሰዎች በሌሎች አስተያየት እና ውጫዊ ሁኔታዎች በቀላሉ ይወሰናሉ። ይህንን ችግር ለመፍታት የራስን ማንነት መገንባት፣ በራስ መተማመንን ማዳበር እና የውጭ ማረጋገጫ ፍላጎትን መቀነስ ያስፈልጋል።
#Explore_ur_mentality
❤4👍2😢2🤔1
ጥበብ ፍልስፍና
⁷"#Love_is_a_serious_mental_disease" አይደለምን??? ፍቅር መልቀቅ ነው ( Love is a Detachment ) ጭንቀት ፍቅር ሊሆን አይችልም፡፡ ፍቅር ከሁኔታዎች ወይም ከስሜታችን ጋር መጣበቅ አይደለም ነገር ግን ስሜታች እና ጥልቅ ፈታኝ ፍላጎቶችን በራሳቸው ፍሰት እንዲጓዝ መፍቀድ እንጂ። ስለሆነች ሴት አጥብቀህ የምትጨነቅ እና የምተብሰለሰል ከሆነ ዕውነቱን ልንገር አትወዳትም።…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከህልሜ ፍቅር ያዘኝ
በጣም በተደጋጋሚ ፈፅሞ አግኝቻት በማላቃት ልጅ ሃሳብ ፈገግ እያልኩ እተክዛለሁ ጸጥታ በሰፈነባቸው የምናቤ ጥጋጥግ ውስጥ የተወሸቀች አንዲት ሴት። ሃሳቤ ወደዛ ምናብ ውስጥ በገባ ቁጥር እራሴን በሷ ፍቅር ደጋግሞ እየወደቀ አገኘዋለሁ። በተጋራነው ጊዜ፣ ባሳለፍናቸው ሰዓታት፣ ባወጋናቸው ቃለት፣ በመገናኘት የተጸነሰ ፍቅር አይደለም። በብቸኝነት ሃሳቤ ውስጥ የሚያድግ ፍቅር ነው፣ እኔ ውድ ብዬ በምጓጓላቸው ባህሪያት የሚያብብ: ቅንነት፣ የዋህነት፣ ለዚህ ሸካራ ዓለም በጣም ስስ የሆነ ልብ። አንዳንዴ አዕምሮዬ ውስጥ ብቻ ከምትኖር ሴት ጋር በፍቅር መውደቄ ትንሽ ወፈፍ እያረገኝ ይሆን እያልኩ አስባለሁ። ግን ራሴን ምናብ ከእውነታ በላይ ሃያል መሆኑን አስታውሰዋለሁ። ምናቤ ተስፋን የምዘራበት መቅደስ እንድገነባ ይፈቅድልኛል የእውነታው ሻካራ ገጾች ወደ የዋህ ጉጉት የሚለሰልሱበት ስፍራ። በዛ ስፍራ ውስጥ እሷ የምሳሳላቸው ማንነቶች ሁሉ መገላጫ ናት፣ ከአስቀያሚው እና ጨካኙ የህይወት ገጽታ በታች በብርሃን እና ርህራሄ የተሞላ ዓለም እንዳለ ማስታወሻዬ ናት። አውቃለሁ የሆነን ሰው በምናብ ብቻ ማፍቀር የቀውስ ሃሳብ እንደሚመስል። ሆኖም ግን በሃሳብ ከሷ ጋር የማደርገው ውይይት ከመቼውም በላይ እውነተኛ ሆኖ ይሰማኛል። እነዛ ሃሳቦች፣ መጪው ጊዜ እውነታው በምናቤ የሳልኳትን ልዕልት ያንጸባርቅ ይሆናል እያሉ በሹክሹክታ ቃል ይገቡልኛል። ያ ቀን እስኪመጣ ከምናቤ ውስጥ መውጣት፣ ከህልሜ መንቃት አልፈልግም። ህይወት በፈተናዎች ብትሞላም ልቤ አሁን ካለው መከራ በላይ ለሆነ ነገር የመሳብ፣ የመተማመን እና የመውደድ አቅም እንዳለው ያስታውሰኛል። እዛ... የሆነ ቦታ ወይም ምናልባት በውስጤ ...ንጹህ፣ ያልረከሰው፣ ለህይወት በትንሹም ቢሆን ብርሃን የሚሆነው እውነተኛው ፍቅር እንዳለ ተስፋ አለኝ።
❤13
ማብሰልሰያ - ፩
ሰይጣን አለ ብለን ብናስብና እንደተነገረን ክፋቱን ብንቀበል፣ maximum ሊያደርግብን የሚችለው ነገር ምንድነው?... ስቃይ ማብዛት?፣ መከራ መቆለል?፣ ለሞት መዳረግ? ወይስ ሌላ?... ታዲያ ሰይጣን የሚያደርገው እኛ እስካሁን ያላደረግነው ምን ነገር አለ?...
መንደሮችን አቃጥለናል... ሕፃናትን በቦምብ ደብድበናል... አፍላጋትን መርዘናል... ድንበር ፈጥረን ተቋስለናል... በረሃብ ሰው ፈጅተናል... ፍቅርን ሸቅጠናል... ሃቂቃን አፍነናል... ጨቅላ ሕፃን ደፍረናል... እርጉዝ ሴት በሳንጃ ዘንጥለናል... ሰውን በቁሙ አቃጥለናል... ስጋውን ቀርጥፈን ከርስ ሞልተናል... ከመሰዊያ ላይ አርደናል... በስልጣናችን ባልገናል... ዘርፈናል፣ ቀጥፈናል፣ ሰስነናል - ይህች ምድር በእኛ ምክንያት ያላየችው ምን ቀሪ መከራ አለ?...
[ለኢጎአችን እስከ-ጠቀመ ድረስ ጆሮ አደንዛዡን፣ ዓይን አፍዛዡን ሁሉ አድርገናል - እስካሁን ካደረግነው የሚበልጥ ምንም ሌላ ነገር ወደፊት አናደርግም... ከኛ በላይ የሚያደርግ ሌላ 'ሰይጣንም' የለም]
እውነት ሰይጣን ካለ ግን በእርግጠኝነት በዚህ ሰዓት ጡረታ ወጥቷል... አልያም መዝገብ ይዞ ክፋታችንን እየከተበ ነው... ወይም ደግሞ ከከፋው ተግባራችን ልምድ እየቀሰመ ይሆናል...
ያን የ Desert father's wisdom ታስታውሱት የለ?...
እርሱ ማንነታችንን ይገነባል... እርሱ ግንኙነታችንን ይመራል... እዚያ ቅይጥ መልካችን ይከተባል... እዚያ መሻት መጥላታችን ይቀመራል... ደግነት ክፋታችን፣ ርህራሔ ተንኮላችን፣ ጨዋነት ወራዳነታችን፣ ንቃት ድንዛዜያችን የመንታ አንድ ሆኖ ይላቆጣል...
ሰይጣን የሰው ልጅ ባሕሪያዊ ጽላሎት (Inner shadow) ትዕምርት ሲሆን ያልተፈተነ ፍርሐት፣ ስግብግብነትና ድብቅ ጭካኔያችን ነጸብራቅ ነው... ከእውነት፣ ከፍቅር እና ከሕላዌ ነቅዕ (Being) የመለያየት ተምሳሌት፤ እንዲሁም ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን ለማምለጥ የምንከለልበት ዓይነ-ርግብ (mask) ነው...
"The devil is the personification of the shadow side of human nature."
- Carl Jung
ማብሰልሰያ - ፪
ንድፈ ሃሳባዊውን መለኪያ ትተን በተግባር ብንፈተሽ 'ሰይጣን' ከሚባለው 'ትርክት' የሚለየን ምንድነው?...
ለምሳሌ - ሰይጣን 'ፈታኝ ነው' እንላለን... እኛም በአባይ ቃል፣ በአታላይ ጥቅም ሌሎችን በማማለል እንፈትናለን...??.. ፤ ሰይጣን 'ከፋፋይ ነው' እንላለን... እኛም 'ልዩነትን' የጥላቻ ምንጭ፣ 'ማንነትን' የጦር መስበቂያ ሰበብ አድርገን የሰውን ልጅ ስንበልት እንኖራለን...??.. ፤ ሰይጣን 'ሐሰተኛ ነው' እንላለን... ነግቶ እስኪመሽ ቅጥፈት፣ መሽቶ እስኪነጋ እብለት አሽሞንሙነን ወገናችንን እንወጋለን...??..ሰይጣን ለመባል ቀንድ አያስፈልገንም - ከቀንድ በላይ የሚወጋ ምላስ አለን... ገሃነመ እሳት አያስፈልገንም - ከጥይት አረር እስከ ከፋው ኒውክለር ሁሉን ታጥቀናል...!
አንድ ጥንታዊ የሱፊ ወግ ልንገራችሁ...
Mister Eckhart እንዲህ ይላል...
“The devil is simply that which pushes you away from your own center.”
ማዕከል (center) የሰው ልጅ ለሕላዌው ጣዕም የሚፈጥርበት፣ እንዲሁም በመኖር ወጀብ ከመናወጥ የሚድንበት መልህቁ ነው... ፍቅሩ፣ አገልጋይነቱ፣ እሴቱ፣ የሕይወት ፍቺው... ሻገር ብሎ ደግሞ ከነፍስያው፣ ከምንጩ፣ ከምልዓተ ዓለሙ የሚዋደድበት እትብቱ... ከዚህ ማዕከል የሚገፋውን ነገር ነው ማላዩ ኤካርት 'devil' ሲል የጠራው...
መውጫ - መወጣጫ
[ሰይጣን ከአካላዊ ማንነት ይልቅ ከፍቅር የመፋታት ምልክት ቢሆንስ?... ምናልባትም የንቃት ስንጥቃት አልያም ከአማናዊው የማንነታችን ምንጭ የመለያያት ጥልቀት ቢሆንስ?...]

በአንድ ገዳም ውስጥ፣ አንድ ወጣኒ መነኩሴ እንቁላል ይሰርቅና ተደብቆ ሲጠብስ ይገኛል...ጎበዝ ሰዋዊ ጉዳዮቻችን የሚመሩት በግላጭም በስውርም ነው... እኛ - አስበን፣ ወስነን የምንከውነው ብቻ አይደለንም... ከማለዳ ዕድሜያችን ጀምሮ በልቡሰ-ጥላ (subconscious mind) ሲሞላ የኖረው ፕሮግራምም በድብቅ ይመራናል፤ ይቆጣጠረናል...
'ምን እያደረግህ ነው?' ያገኙት አባት ይጠይቁታል...
'አይ አባ... ሰይጣን አስቶኝ...' ወጣቱ ይርበተበታል...
ጉዳዩን ከመስኮት በኩል ሆኖ ሲከታተል የነበረው 'ሰይጣን' ታዲያ እንዲህ ሲል ራሱን ነፃ አወጣ...
'አባ ውሸቱን ነው... ይህችን መላ ያለዛሬም አላየሁዋት'...
እርሱ ማንነታችንን ይገነባል... እርሱ ግንኙነታችንን ይመራል... እዚያ ቅይጥ መልካችን ይከተባል... እዚያ መሻት መጥላታችን ይቀመራል... ደግነት ክፋታችን፣ ርህራሔ ተንኮላችን፣ ጨዋነት ወራዳነታችን፣ ንቃት ድንዛዜያችን የመንታ አንድ ሆኖ ይላቆጣል...
ሰይጣን የሰው ልጅ ባሕሪያዊ ጽላሎት (Inner shadow) ትዕምርት ሲሆን ያልተፈተነ ፍርሐት፣ ስግብግብነትና ድብቅ ጭካኔያችን ነጸብራቅ ነው... ከእውነት፣ ከፍቅር እና ከሕላዌ ነቅዕ (Being) የመለያየት ተምሳሌት፤ እንዲሁም ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን ለማምለጥ የምንከለልበት ዓይነ-ርግብ (mask) ነው...
"The devil is the personification of the shadow side of human nature."
- Carl Jung
ማብሰልሰያ - ፪
ንድፈ ሃሳባዊውን መለኪያ ትተን በተግባር ብንፈተሽ 'ሰይጣን' ከሚባለው 'ትርክት' የሚለየን ምንድነው?...
ለምሳሌ - ሰይጣን 'ፈታኝ ነው' እንላለን... እኛም በአባይ ቃል፣ በአታላይ ጥቅም ሌሎችን በማማለል እንፈትናለን...??.. ፤ ሰይጣን 'ከፋፋይ ነው' እንላለን... እኛም 'ልዩነትን' የጥላቻ ምንጭ፣ 'ማንነትን' የጦር መስበቂያ ሰበብ አድርገን የሰውን ልጅ ስንበልት እንኖራለን...??.. ፤ ሰይጣን 'ሐሰተኛ ነው' እንላለን... ነግቶ እስኪመሽ ቅጥፈት፣ መሽቶ እስኪነጋ እብለት አሽሞንሙነን ወገናችንን እንወጋለን...??..ሰይጣን ለመባል ቀንድ አያስፈልገንም - ከቀንድ በላይ የሚወጋ ምላስ አለን... ገሃነመ እሳት አያስፈልገንም - ከጥይት አረር እስከ ከፋው ኒውክለር ሁሉን ታጥቀናል...!
አንድ ጥንታዊ የሱፊ ወግ ልንገራችሁ...
አንድ ቀን አንድ ደርቪሽ መምህሩን እንዲህ ሲል ጠየቀ...
"መምህር ሆይ፣ ሰይጣንን ማሸነፍ የምችለው እንዴት ነው?"
መምህሩ መለሱ...
"በቅድሚያ የእርሱን ጫማ መዋስ አቁም"
መምህሩ በጫማ ነጽሮት ውስጥ ውስጠ ቅኝታችንን ነው ያጠየቁት... አሳባቢ፣ ጥሩር ቀጥቃጭ፣ ኃላፊነት ካጂ ውስጠ ማንነታችንን...
ያመሰጠሩት ስለ ዓይነ ትልልቅ፣ ባለ ጨልጨሌ፣ ቀንዳም ሰይጣን ሳይሆን - ልናይ ስላልፈቀድነው ማንነታችን ነው...
Mister Eckhart እንዲህ ይላል...
“The devil is simply that which pushes you away from your own center.”
ማዕከል (center) የሰው ልጅ ለሕላዌው ጣዕም የሚፈጥርበት፣ እንዲሁም በመኖር ወጀብ ከመናወጥ የሚድንበት መልህቁ ነው... ፍቅሩ፣ አገልጋይነቱ፣ እሴቱ፣ የሕይወት ፍቺው... ሻገር ብሎ ደግሞ ከነፍስያው፣ ከምንጩ፣ ከምልዓተ ዓለሙ የሚዋደድበት እትብቱ... ከዚህ ማዕከል የሚገፋውን ነገር ነው ማላዩ ኤካርት 'devil' ሲል የጠራው...
መውጫ - መወጣጫ
[ሰይጣን ከአካላዊ ማንነት ይልቅ ከፍቅር የመፋታት ምልክት ቢሆንስ?... ምናልባትም የንቃት ስንጥቃት አልያም ከአማናዊው የማንነታችን ምንጭ የመለያያት ጥልቀት ቢሆንስ?...]
እንደ እውነቱ ከሆነ ክፉ አስፈፃሚ አይደለም ያለው - ፈፃሚው ራሱ እንጂ... በሌላ አነጋገር ወይ እኛ ሰይጣን ነን - አልያም ብቅ እልም የምትል ስይጥንና አለችብን...✍ ደምስ ሰይፉ
ጨለማን ሁልጊዜ ሻማ በመለኮስ አንፋታውም... አንዳንዴ ጨለማነቱን መቀበልም ይኖርብናል... በተለይ የውስጣችን ኑባሬ ሲሆን በዓይኖቻችን ልናየው መድፈርም ግድ ይሆናል... ልክ ራሳችንን በመስታወት ፊት እያየን እንደምናወራው ሁሉ - "አንተ - እኔን ነህ... ያልተፈቀርከው፣ ያልተጎበኘኸው፣ ያልተደመጥከው እኔ... አሁን አጠገብህ ነኝ፣ እያየሁህ ነው..." ልንለው ይገባል
❤5👍2🔥2👏2
ጥበብ ፍልስፍና
<unknown> – ፈራሁ Teddy Afro🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹
ቴድሮስ ካሳሁን
<unknown>
ክርስቶስ ወ ገብረክርስቶስ
✍️የክብር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሣኹን ገርማሞ-ታኅሣስ 2001
✍️የክብር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሣኹን ገርማሞ-ታኅሣስ 2001
ጥበብ ፍልስፍና
ፈራሁ ወፎችም ጠፍተዋል እንደ ድሮ አይመጡም ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ሸንጎ አይቀመጡም ያልጠኑ ጥጃዎች እየፈነጠዙ መስክ ለይ አይሮጡም ልጆች ሲቆጧቸው ቶሎ አይደነግጡም ህፃናት አውቀዋል እንደ ልጅ አይፈሩም በሳት ዙሪያ ከበው ተረት አያወሩም ከለታት አንድ ቀን አይባልም ቀረ ያልኖረውን እድሜ ልጅም እየኖረ ወንዝኦችም ደርቀዋል እያሉ አይፈሱም ወጣቶች ደክመዋል ለሽበት አይደርሱም ክርምት አና በጋ ተናፍቀው…
ጎልጎታ - ገብረ-ክርስቶስ ደስታ - 1963
ክርስቶስ ወ ገብረክርስቶስ
(✍️የክብር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሣኹን ገርማሞ - ታኅሣስ 2001)
ዕዩት ይኼን ጠቢብ፥ ሸራው እስኪደማ
በቀይ እየወጋ፥ በደም እየሣለው
እንጨት አመሳቅሎ፥ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው።
ቀራንዮ ኾነ፥ የወጠረው ሸራ
ጎልጎታ ኾነ፥ የወጠረው ሸራ
አሁን እስኪመሥል ሥቃዩ እያስፈራ (2×)
ደም በደም አ’ረገው፥ አበዛበት ጣር
ብሩሹን አሹሎት፥ እንደ፡ጎኑ ጦር
እየወጋ ሣለው፥ እየሣለ ወጋው
በጣም ጨከነበት፥ ገብረ-ክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ፤
የቆዳው ዓይነቱ በደም ተከልሎ፥ ዘሩ እስከሚጠፋ።
እየወጋ ሣለው፥ እየሣለ ወጋው
ዘሩ እስከማይለይ፣
መልኩ ዝም ብሎ፥ ደሙ እስከሚናገር
የትም ያለ ፍቅር፥ እንዳይኖረው ሀገር
እንዳንለው ፈረንጅ፥ እንዳንለው ጥቁር እንዳንለው ቀይ፣
በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ሥቃይ፣
በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው፣
በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው።
ከቀናት ባንዱ ዕለት፣
ሰዎች ሲሟገቱ፥ በቀለሙ ጉዳይ ሲከራከሩበት
በተመጻዳቂ የምሁር አንደበት፣
በአንዱ አፍ ሲጠቁር፥ ባንዱ አፍ ሲነጣ
መታገስ አቃተው፥ ሠዓሊው ተቆጣ
ሥሜቱ ገንፍሎ፥ በቡርሽ ጫፍ ወጣ።
ሐሳቡን የሚገልጽ ቀለም እስከሚያጣ፣
ሸራ ላይ ሰቀለው፥ እንጨት አመሳቅሎ
አልወጣልኽ አለው፥ ፍቅርን ሥሎ ሥሎ።
ሥሎ ሥሎ ሥሎ፥ ፍቅርን ሥሎ ሥሎ
በሣለው እየወጋ በደማው እየቀባ፣
'ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀለም፣
እንጨቱ ላይ ያለው ዕውነት ይኼ አይደለም።'
እያለ እስኪናገር፥ የሥዕሉ አንደበት
ገብረ-ክርስቶስም ለክርስቶስ የሚኾን፥ ቀለም እስኪያልቅበት
በነጩ ሸራ ላይ፥ እስከአሁን የሚወርድ ደም አፈሰሰበት።
ቀለም፣ ቀይ ቀለም! የደም ቀለም። የጥላ ቀለም
የኹሉም ነው እንጂ የማንም አይደለም፣ ፍቅር ዘር አይደለም።

❤10🔥9
ጥበብ ፍልስፍና
"እንደወደደ ይሁን እግዚአብሔር ቢሰጠኝ ሁሉን ልገዛ አሣብ ነበረብኝ። እግዚአብሔር ቢነሳኝ አልሞት ኣሳቤ ይህ ነበረ፡፡ ከተወለድሁኝ እስካሁን ወንድ እጄን ጨብጦት አያውቅም፤ ሰዎቻ ሲሸሹ ተነስቼ ተነስቼ ማራጋት ልማድ ነበረብኝ። ነገር ግን ጨለማ ከለከለኝ፡፡ እንደኔ አያድርጋችሁ። እንኳንስ የሀበሻ ጠላቴን ኢየሩሳሌም ዘምቼ ቱርኮችን አስለቅቃለሁኝ መስሎኝ ነበር። ወንድ ያቀፈ ወንድ ተመልሶ አይታቀፍም ።…
የአፄ ምኒልከ አዋጅ
መልካም በዓል
እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፋፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በ እግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። ከንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፡፡ ከእንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም። አሁንም አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት ፤ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር። አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስልኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ጉልበት ያለሀ በጉልበትሀ እርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ ለ ልጅህ ለ ሚስትህ ለ ሃይማኖትህ ስትል በሐዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለሀ፡፡ አልተውህም። ማርያምን ለዚሀ አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላገኝህ፡፡
መልካም በዓል
❤7🔥5👍2👎1
ጥበብ ፍልስፍና
ማብሰልሰያ - ፩ ሰይጣን አለ ብለን ብናስብና እንደተነገረን ክፋቱን ብንቀበል፣ maximum ሊያደርግብን የሚችለው ነገር ምንድነው?... ስቃይ ማብዛት?፣ መከራ መቆለል?፣ ለሞት መዳረግ? ወይስ ሌላ?... ታዲያ ሰይጣን የሚያደርገው እኛ እስካሁን ያላደረግነው ምን ነገር አለ?... መንደሮችን አቃጥለናል... ሕፃናትን በቦምብ ደብድበናል... አፍላጋትን መርዘናል... ድንበር ፈጥረን ተቋስለናል... በረሃብ…
"ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት ወንድ አለ የሚያመነዝርና የማመንዘር እድሉን ያላገኘ!"
ለምንድነው በምግባር የታጠርከው? ለምን ለሰዎች ጥሩ ትሆናለህ? ታማኝነትህስ ከየት የመጣ ነው? የሚለውን ጥያቄ የያዘ ነው። አጋጣሚውን ያጣ የስነ-ምግባር ሰውና አጋጣሚው ኖሮት በስነ ምግባር መታነፅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ለምንድነው የበደሉህን የማትገድላቸው? ወይ መልሰህ የማትበድላቸው? እውን ምግባር ስላለህ ነው? ሀይማኖትህ ስለከለከለህ? ወይስ አቅሙን አጥተህ? የሆነ የሆነ ቦታዎች ላይ አቅሙን አጥተህ የተውከው ነገር በሰዎች ዘንድ ግን በጣም ጥሩ ስነ ምግባር ያስብልሀል።
ከዚህ ታሪክ የምንረዳው በስነ ምግባር የታነፅን የመሰልነው አማራጭና አቅም የማጣት እንጂ በስነ ምግባር መኖሩ ፅድቅ እንዲሆንልን አይደለም እንደማለት ነው!??። የ በውቄም ጨዋታ እዚህ ትመጣለች እስከዛሬ ያለመነዘሩ ታማኝ የስነ ምግባር ሰው የተባሉት ዕድሉን አጥተው እንጂ እንደዛ ጋይጂ የመሰውሯን ቀለበት ቢያገኙ ምናልባት ዘወትር የሚመኟትን ሴት ከመግለጥ ስነ ምግባራቸው አይይዛቸውም ለማለት ነው። የኛ የምግባር መለኪያ የተዛባ ይመስላል። ዕድሉን አጥቶ ጨዋ የሆነና ጨዋነት ዋጋ እንዳለው አውቆ የታቀበን የምንለይበት መንገድ የለንም። ስለ ምግባርን ለስነ ምግባርነቱ ስትል የምታደርገው ነገር ይመስልሀል?። የማትሰርቀው የሰውየው ላብ አሳዝኖህ ያልደከምክበትን ላለመንካት ነው ወይስ ብትያዝ እስሩና የሰው መጠቋቆሚያ ስለምትሆን? አንተ ታውቃለህ።
Carl Gustav Jung ሁላችንም የየግል ወይ የማህበረሰብ ጭንብል (personal or mask) አለን ይላል። በሰዎች ፊት የማናሳየው ጋጥ ወጥ ክፍል። እርስ በእርስ ስንገናኝ ወይ ከቤት ስንወጣ የምናጠልቀው ምግባረ ብልሹነታችንን ሸፈነን የምንወጣበት የጋይጂን ቀለበት የመሰለች ጭንብል አለችን። እሷን ገልጦ ላየን ግን አፈንጋጭነታችን አድፍጧል። እሷን ግን የሚገልጣት ብዙ ነገር ሊሆን ይችላል። ወይ ስልጣን ወይ ገንዘብ ለዛ ነው አንዳንድ ሰው ድንገት ገንዘብ ሲያገኝ ወይ ስልጣን ሲያገኝ የሚቀየረው ያደፈጠው ማንነቱ ብቅ ይላል ልክ እንደ ጋይጂ ቀለበት።

እዚህ ጋር የ አሪስቶትልን የ እረኛውን ወንድሙን ታሪክ ጋይጂን አንስቶ ስለ ስነ ምግባር ያወራናል። ጋይጂ እረኛ ነው ከ እረኛም የተዘነጋ እረኛ አይነት በሉት በሰዎች ዘንድ ሞኝ ጥሩ ስነ ምግባር ያለው እረኛ። ታዲያ ባንድ ወቅት ከዝናብ ለመጠለል በ አንድ ዋሻ ውስጥ ይገባል። ታዲያ እዚያ ዋሻ ውስጥ አንድ የጥንት ቀለበት ከ ጥንተ ቅሪተ አካል ላይ ያገኛል። ይሄኔ ጋይጂ ቀለበቱን ሲያጠልቅ ከሰው ዘንድ የሚሰውረው መሆኑንን አወቀ። ባለ ጥሩ ስነ ምግባሩ ጋይጂ ምን አደረገ አትሉኝም? ወዲያውኑ ወደ ቤተመንግስቶ ተሰውሮ ገባ ንጉሱን ገድሎ የንጉሱን ሚስት አገባት ወዲያውም ንጉስ ሆነ። ከዚህም ታሪክ አስከትሎ ምን ይላል መሰላቹህ አንተስ የጋይጂ አስማተኛ ከሰዎች የሚሰውር ቀለበት ብታገኝ ምን ታደርጋለህ ይልሀል። ትዘርፋለህ? ወይስ እንደድሮህ ትኖራለህ? ባንክ ቤት መዝረፍ? ስልጣን መገርሰስ? ወይስ እየተደበቅህ የሴት ገላ ልብሷን ስትቀይር ታያለህ? ምን ታደርጋለህ?
ከዚህ ታሪክ የምንረዳው በስነ ምግባር የታነፅን የመሰልነው አማራጭና አቅም የማጣት እንጂ በስነ ምግባር መኖሩ ፅድቅ እንዲሆንልን አይደለም እንደማለት ነው!??። የ በውቄም ጨዋታ እዚህ ትመጣለች እስከዛሬ ያለመነዘሩ ታማኝ የስነ ምግባር ሰው የተባሉት ዕድሉን አጥተው እንጂ እንደዛ ጋይጂ የመሰውሯን ቀለበት ቢያገኙ ምናልባት ዘወትር የሚመኟትን ሴት ከመግለጥ ስነ ምግባራቸው አይይዛቸውም ለማለት ነው። የኛ የምግባር መለኪያ የተዛባ ይመስላል። ዕድሉን አጥቶ ጨዋ የሆነና ጨዋነት ዋጋ እንዳለው አውቆ የታቀበን የምንለይበት መንገድ የለንም። ስለ ምግባርን ለስነ ምግባርነቱ ስትል የምታደርገው ነገር ይመስልሀል?። የማትሰርቀው የሰውየው ላብ አሳዝኖህ ያልደከምክበትን ላለመንካት ነው ወይስ ብትያዝ እስሩና የሰው መጠቋቆሚያ ስለምትሆን? አንተ ታውቃለህ።
Carl Gustav Jung ሁላችንም የየግል ወይ የማህበረሰብ ጭንብል (personal or mask) አለን ይላል። በሰዎች ፊት የማናሳየው ጋጥ ወጥ ክፍል። እርስ በእርስ ስንገናኝ ወይ ከቤት ስንወጣ የምናጠልቀው ምግባረ ብልሹነታችንን ሸፈነን የምንወጣበት የጋይጂን ቀለበት የመሰለች ጭንብል አለችን። እሷን ገልጦ ላየን ግን አፈንጋጭነታችን አድፍጧል። እሷን ግን የሚገልጣት ብዙ ነገር ሊሆን ይችላል። ወይ ስልጣን ወይ ገንዘብ ለዛ ነው አንዳንድ ሰው ድንገት ገንዘብ ሲያገኝ ወይ ስልጣን ሲያገኝ የሚቀየረው ያደፈጠው ማንነቱ ብቅ ይላል ልክ እንደ ጋይጂ ቀለበት።
በውቄ ይሄን ፍልስፍና በቀልድ መልኩ ጣል አድርጎ ያለፈው ይሁን አንጂ ስትተነትነው ሰፊ ነገር ነው የያዘው። ብዙ ጊዜ በቀልድ መልኩ የሚያስተላልፈው መልእክት የሚደንቀኝ ሰው ነው። እና አንተን የስነ ምግባር ሰው ያደረገህ ምን ይሆን? ማህበረሰቡን ፈርተህ? ወይስ አቅሙን አጥተህ? ወይስ የምርም የስነ ምግባር መንገድ ጥሩ እንደሆነ አምነህ? መልሱን ለናንተ ትቼዋለሁ!።
❤3🔥2👏2👍1
ጥበብ ፍልስፍና
⁷"#Love_is_a_serious_mental_disease" አይደለምን??? ፍቅር መልቀቅ ነው ( Love is a Detachment ) ጭንቀት ፍቅር ሊሆን አይችልም፡፡ ፍቅር ከሁኔታዎች ወይም ከስሜታችን ጋር መጣበቅ አይደለም ነገር ግን ስሜታች እና ጥልቅ ፈታኝ ፍላጎቶችን በራሳቸው ፍሰት እንዲጓዝ መፍቀድ እንጂ። ስለሆነች ሴት አጥብቀህ የምትጨነቅ እና የምተብሰለሰል ከሆነ ዕውነቱን ልንገር አትወዳትም።…
ፍቅር ና ወሲብ በ,Objectivism ፍልስፍና
በ,Objectivism ‹‹ፍቅር ያዘኝ›› ማለት ‹‹እኔ የራሴ እሴቶች አሉኝ፤ value system አለኝ፤ የምወደውና የማከብረው አለኝ›› ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ያሉት አእምሯችን ውስጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ የሁለት ነገሮች ውህደት ነው ― የነፍስና የአካል፡፡ አየን ራንድ ‹‹ነፍስ›› የምትለው ‹‹የንቃተ ህሊና (Consciousness) የሆኑትን ነገሮች›› ነው፡፡
የሰው ልጅ የራሱ የሆኑ እሴቶች (values) ላይ አንድ ፍላጎት አለው፡፡ ይሄውም፣ ልክ መስታወት አካላዊ ገፅታችንን እንደሚያሳየን ሁሉ፣ የያዝናቸው ረቂቅ እሴቶችም (abstract values) አካል ነስተው ማየት እንፈልጋለን፡፡ ‹‹አካል መንሳት›› ማለት ከረቂቅነት ወደሚታይ አካላዊ ነገር እንዲቀየሩ መፈለግ ማለት ነው፡፡ ይሄም የሚገለፀው በሌላ ሰው ላይ ነው፡፡ በመሆኑም፣ ‹‹የያዝናቸው ረቂቅ እሴቶች አካል ነስተው ማየት እንፈልጋለን›› ሲባል ‹‹የእኛ እሴቶች በሌላ ሰው ውስጥ ማየት እንፈልጋለን›› ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት፣ ሌላ ሰው የኔን ዓይነት እሴቶች ተላብሶ ሳይ፣ የኔን ነፍስ እሱ ላይ አየዋለሁ፤ እናም በፍቅሩ እወድቃለሁ ማለት ነው፡፡ ይሄ ፍቅር ግን የግድ ፆታዊ ብቻ ሳይሆን ልባዊ ጓደኝነትንም ይጨምራል፡፡
በObjectivism ፍልስፍና፣ ሰው የሚያፈቅረው በሌላ ሰው ውስጥ የሚገኘውን የራሱን እሴቶች ነው፡፡ ‹‹ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል›› የሚባለው ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ባል የራሱን values በሚስቱ ውስጥ ያገኛል፤ ሚስቲቱም እንዲሁ፡፡ ይሄ ነገር objectivist ስለሆንክ ምናምን አይደለም፤ ሁሉም የሰው ልጅ experience የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሂትለር አያፈቅርም ማለት አይደለም፡፡ እሱም የራሱ values አሉት፡፡ ይሄም ማለት፣ ሂትለርም የራሱ ዓይነት values ያላትን ሴት ያፈቅራል ማለት ነው፡፡
በObjectivism ፍልስፍና፣ ፍቅር ስሌት ወይም calculation አይደለም፡፡ ‹‹አፍቃሪ እንድትሆን ወይም ሴቷ እንድታፈቅርህ እንዲህ አድርግ፣ እንዲህ ሁን…›› የሚባል ነገር የለም፡፡ በሰራኸው የነፍስህ ቅርጽ እንደዛ ዓይነት ቅርጽ ያለው ሌላ ሰው ነፍስ ታያለች፡፡ ፍቅር ስሌት አለመሆኑን ለማሳየት አየን ራንድ እንዲህ ትላለች ‹‹አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀላሉ ዘለላ ፀጉሯን ወደ ኋላ ስትመልሰው አይቶ ነፍሷን ሊለየው ይችላል፡፡ ነፍስ ነፍስን ልታስተውል ትችላለች፡፡
© Yonas Tadesse Berhe

እናም ያፈቀርኩት ሰው ‹‹የኔ የእሴቶች መስታወት›› ነው፤ በእሱ ውስጥ የእኔን እሴቶች አይበታለሁ፤ መስታወት ይሆነኛል፡፡ ነፍሴ እሱ ላይ መገለፅ ስትጀምር ማድነቅ እጀምራለሁ፡፡ የኔን ዓይነት ‹‹value system›› ሌላ ሰው ሲያደርገው ወይም ስታደርገው ስናይ ማድነቅ እንጀምራለን፡፡ ነገሩ የሚጀምረው በአድናቆት ነው፡፡ አየን ራንድ፣ ‹‹የዚህ አድናቆት የመጨረሻው ደረጃ ‹‹ፍቅር›› ይባላል›› (the highest form admiration is Love) ትላለች፡፡
በObjectivism ፍልስፍና፣ ሰው የሚያፈቅረው በሌላ ሰው ውስጥ የሚገኘውን የራሱን እሴቶች ነው፡፡ ‹‹ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል›› የሚባለው ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ባል የራሱን values በሚስቱ ውስጥ ያገኛል፤ ሚስቲቱም እንዲሁ፡፡ ይሄ ነገር objectivist ስለሆንክ ምናምን አይደለም፤ ሁሉም የሰው ልጅ experience የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሂትለር አያፈቅርም ማለት አይደለም፡፡ እሱም የራሱ values አሉት፡፡ ይሄም ማለት፣ ሂትለርም የራሱ ዓይነት values ያላትን ሴት ያፈቅራል ማለት ነው፡፡
በObjectivism ፍልስፍና፣ ፍቅር ስሌት ወይም calculation አይደለም፡፡ ‹‹አፍቃሪ እንድትሆን ወይም ሴቷ እንድታፈቅርህ እንዲህ አድርግ፣ እንዲህ ሁን…›› የሚባል ነገር የለም፡፡ በሰራኸው የነፍስህ ቅርጽ እንደዛ ዓይነት ቅርጽ ያለው ሌላ ሰው ነፍስ ታያለች፡፡ ፍቅር ስሌት አለመሆኑን ለማሳየት አየን ራንድ እንዲህ ትላለች ‹‹አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀላሉ ዘለላ ፀጉሯን ወደ ኋላ ስትመልሰው አይቶ ነፍሷን ሊለየው ይችላል፡፡ ነፍስ ነፍስን ልታስተውል ትችላለች፡፡
በሌሎች ውስጥ ያለ የራስን እሴቶች በማድነቅ የሚጀመረው ይሄ ክስተት ወደ ፍቅር ያድግና በስተመጨረሻ በወሲብ Celebrate ይደረጋል፡፡‹‹Sex is the Celebration of this Love›› ትላለች አየን ራንድ፡፡ ትክክለኛው ወሲብ ይሄ ነው ትርጉሙ፡፡ አየን ራንድ እንዲህ ትላለች፣ ‹‹ከአድናቆት ወደ ፍቅር ያደገውን ግንኙነት Celebrate ለማድረግ ፖስት ካርድ ልሰጥህ እችላለሁ፤ እሱ ግን አያረካኝም፡፡ የአንገት ሐብል ልገዛልህ እችላለሁ፤ እሱም አያረካኝም፡፡ የሚያረካውና የመጨረሻው ውዱ ስጦታዬ ርቃን የሆነውን አካሌን እሰጥሃለሁ፡፡ I am happy to give you this naked body in celebration of that administration and love.››
© Yonas Tadesse Berhe
❤13👍6🤔2
[...ደስታ ተረፈ-ምርት እንጂ ግብ አይደለም! / Happiness is a byproduct not a goal by itself...]
ደስታ ትልቅ የሕይወት ግብ የሆነበት ዘመን ላይ እንዴት ደረስን? መጻሕፍታችን ሁሉ ከምሁራዊ ይዘት ወጥተው መፅናናትን ሰባኪዎች ሆነዋል፡፡ ደስታ እንዴት'ስ ይህን ያህል ነገራችንን ያዘው? ብዙ ሰው ያጣው ስለሆነ ነው? መቼም ያለ ነገር አይሰበክም?!
ምክንያት የሚሻው ትርጉምን፥ ሥሜት ደግሞ እርካታን ነው፡፡ ትርጉም ለሚሻ ደስታ ግቡ አይሆንም፡፡ ደስታ'ና ሐዘን በጉዞው እያፈራረቀ የሚኖራቸው እንጂ ለመድረስ የሚጓዝላቸው አይደሉም፡፡
ሥሜት ከምክንያት እግር ሥር ሲውል ግን ይህ ሁሉ የለም ፡፡ በየመንገዱ ለምን? ባዩ አእምሮ የሚገባና የማይገባውን ይጠይቃል፡፡ በአኗኗሩ ስለሚሸምነው ትርጉም እንጅ ሥለ ደስታ አይባዝንምና ለአግበስባሽነት አይመችም፡፡ ምክንያት የሚቻልን ከማይቻል፣ የሚሆንን ከማይሆን ትመዝናለች፡፡ እምነቱ ሥለ ሥራው እንጂ በሥራው ስለሚያገኘው አይደለም፡፡ ደስታዋ ከይዘቷ የሚቀዳ ነው፡፡
ደስታ ትልቅ የሕይወት ግብ የሆነበት ዘመን ላይ እንዴት ደረስን? መጻሕፍታችን ሁሉ ከምሁራዊ ይዘት ወጥተው መፅናናትን ሰባኪዎች ሆነዋል፡፡ ደስታ እንዴት'ስ ይህን ያህል ነገራችንን ያዘው? ብዙ ሰው ያጣው ስለሆነ ነው? መቼም ያለ ነገር አይሰበክም?!
ደስታ ግብ የሚሆነው ሥሜት ከምክንያት ስትበልጥ ነው፡፡
ምክንያት የሚሻው ትርጉምን፥ ሥሜት ደግሞ እርካታን ነው፡፡ ትርጉም ለሚሻ ደስታ ግቡ አይሆንም፡፡ ደስታ'ና ሐዘን በጉዞው እያፈራረቀ የሚኖራቸው እንጂ ለመድረስ የሚጓዝላቸው አይደሉም፡፡
ደስታ ግብ ሲሆን ምክንያት'ና እውቀት ይሸሻሉ፡፡ ግልብ አኗኗር ይገንናል፡፡ በአኗኗራቸው ይዘት አልባነት ፍጹም ደስታን ማግኘት ያልቻሉ ወደ ቁስ አግበስባሽነት ይጓዛሉ፡፡ ደስታቸው ከተጠቃሚነት (CONSUMERISM) የተለጠፈና የተጠለፈ ይሆናል፡፡ ከቁሱ ፋሽንነት ጋር የሚያልፈው ደስታ ግን ባለበት አይቆይምና አዲስ ደስታ ፍለጋ ወደ አዲስ ቁስ ይሸጋገራሉ፡፡
ሥሜት ከምክንያት እግር ሥር ሲውል ግን ይህ ሁሉ የለም ፡፡ በየመንገዱ ለምን? ባዩ አእምሮ የሚገባና የማይገባውን ይጠይቃል፡፡ በአኗኗሩ ስለሚሸምነው ትርጉም እንጅ ሥለ ደስታ አይባዝንምና ለአግበስባሽነት አይመችም፡፡ ምክንያት የሚቻልን ከማይቻል፣ የሚሆንን ከማይሆን ትመዝናለች፡፡ እምነቱ ሥለ ሥራው እንጂ በሥራው ስለሚያገኘው አይደለም፡፡ ደስታዋ ከይዘቷ የሚቀዳ ነው፡፡
❤3🔥2👍1
ህልማለማዊነት(Surrealism)
በ1920ዎቹ በምዕራቡ ዓለም በሥነ-ፁሁፍ ተጀምሮ በኋላም ወደ ሌሎች ጥበቦች(ወደ ስዕል እና ፊልም) ያደገና አሁንም ርዝራዡ ያለ የጥበብ እንቅስቃሴ ነው። በአንድሬ ብሬቶን (Andrè Breton) ተጠናክሮ የተጀመረ ሲሆን ፣ ንቁ ያልሆነውን የአዕምሮ ክፍል ከግብረገባዊ ፣ምክንያታዊ እና አመክንዮአዊ ተጠይቆች እና ሳንሱሮች ነፃ በማውጣት በሚፈጠር የፈጠራ ዓለም ላይ የሚያተኩር ነው። ህልማለማዊነት (Surrealism) በምክንያታዊነት እና በተለመደው አስተሳሰብ ላይ በማመፅ ድንገተኛነትን ፣ሕልምን እና የውስጠ ንቃተ ሕሊናን ኃይል የሚጠቀም ሲሆን የዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች "ምክንያታዊ አስተሳሰብ የሰውንልጅ እንደሚገድብ ከማመን በዘለለ ይሄ ገደብ አልፎ ለመሄድ እና ነፃነቱን ለመመለስ የውስጠ ሕሊናን ምናባዊ ምስሎች (Subconscious Images) ማነቃቃት አስፈላጊ ነው" ባይ ናቸው።
ህልማለማዊነት ፍሬው
ህልማለማዊነት (Surrealism) ከዳዳይዝም (Dadaism) የኪነጥበብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ የፈለቀ ሌላ አመፃ ሲሆን የዳዳይዝም መሠረታዊ ነፀብራቅም የማህበረሰቡን የ'ምክንያታዊነት ጉዞ' የሚነቅፍና የስልጣኔ እርከኑ እንከን እንዳለበት የሚያምን የኪነጥበብ የአመፃ እንቅስቃሴ ነው።ልክ እንዳዳይዝም ህልማለማዊነት (Surrealism) በቅዘቶቻችን ውስጥ የተፈጠሩ ምስሎች በሸራ ላይ ማረፍ እንዳለባቸው የሚያምን የኪነጥበብ ጎራ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ የሳይኮአናሊስቱ ሲግመን ፍሮይድ ከንቃተሕሊና በላይ የሆኑ ፅንሰ-ሀሳቦች ምኞቶች እና ትውስታዎች የሚከማቹበትን የአእምሮ ክፍል ህልማለማዊነት(Surrealism) ስራዎች እንደግበአት የሚሆኑ ናቸው። ውስጠሕሊና ኃይለኛ የፈጠራ ምንጭ እና የሰውን ልጅ ልምድ ጥልቀት ለመመርመር የሚያስችል ዘዴ እንደሚሰጥ ይገልፁ ነበር። ፍሮይድ 'የሕልም አንድምታ ትርጓሜዎች' ላይ ከፃፋቸው መጽሐፍት በተለይም "The Interpretation of Dreams" የተሰኘው መጽሃፍ ለህልማለማዊነት (Surrealism) አዲስ የጥበብ ቋንቋ እና ማዕቀፍ የሰጣቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ውስጠ ሕሊናን እንዲረዱ እና እንዲገልጹ አድርጓቸዋል። ህልማለማዊ ከያኒያን ብዙ ጊዜ ከሕልም ዓለም ለሚመነጩ ሃሳቦች፡ምስሎች ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ። ይህም እንደ እንግዳ እና ምሳሌያዊ ምስሎችን ምንጭ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። ህልማለማዊነት (Surrealism) ቃሉ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ 1917 ዓ.ም ላይ ቢጠራም ነገርግን እስከ አንድሬ ብሬቶን 'Surrealism Manifesto' እ.አ.አ 1924 ድረስ ግን አገልግሎት ላይ አልዋለም ነበር።ከአንደኛው አለም ጦርነት በኋላ ይሄ የኪነጥበብ አመፃ እንቅስቃሴ በከፍተኛ መልኩ እያደገ በመሄድ ታላላቅ ሰአሊያን ባለቅኔ ገጣሚያንን እና ፈላስፎች የፊልም ፀሀፊያን ልብ ያስኮበልል ጀመር ከእነዚህ መካከል Paul Éluard Paul Éluard, Benjamin Péret, René Crevel, Robert Desnos, Jacques Baron, Max Morise, Pierre Naville, Roger Vitrac, Gala Éluard, Max Ernst, Salvador Dalí, Luis Buñuel, Joan Miró, Marcel Duchamp, Jacques Prévert, እና Yves Tanguy, Dora Maar . . .ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው። ፍልስፍናቸውን እያዳበሩ ሲሄዱ ህልማለማዊነት (Surrealism) ተራ እና ገላጭ አገላለጾች አስፈላጊ እና ጠቃሚ ናቸው የሚለውን ሀሳብ ማበረታታ ቢጀምሩም ፤ ነገር ግን የዝግጅታቸው ስሜት በሄግሊያን ዲያሌክቲክስ መሰረት ለሙሉ ምናብ ክፍት መሆን አለመቻሉ እንዲሁም የማርክሲስት ዲያሌክቲክን እና እንደ ዋልተር ቤንጃሚን እና ኸርበርት ማርከስ ያሉ የቲዎሪስቶች ላይ እንከን ሆነውበታል።
ህልማለማዊነት (Surrealism) የሰው ልምድ፣ ግላዊ ዕይታ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ገፅታዎች በመጠቀም ሰዎችን ከሐሰት ምክንያታዊነት፣ እና ገዳቢ ልማዶች እና አወቃቀሮች ነፃ ማውጣት እንደሚችል ለማሳየት የተለያዩ ስራዎችን አራማጆቹ መስራታቸውን ቀጠሉ። ብሬተን የህልማለማዊነት እውነተኛ አላማ "የማህበራዊ አብዮት ለዘላለም እንዲኖር ነው" በማለት ገልፆ ነበር።በዚህ ቆራጥ ግባቸው የተነሳ በተለያዩ ጊዜያት ህልማለማዊያን ከኮምኒዝም እና አናርኪዝም ጋር ይስማሙ እና ይገጥሙ ነበር።ይሄ ጥንካሬ በጊዜው በሙዚቃ፡በስዕል፡በግጥም፡በፖለቲካ፡በስነፅሁፍ እያ በፊልም. . . ወዘተ ዘርፎች ላይ በመግባት ዓለም አቀም የኪነጥበብ ውድመትን በማምጣት የራሱን አዲስ መንገድ ፈጥሯል።ህልማለማዊነት እንደ ምስላዊ እንቅስቃሴ ዘዴን በማበረታታት -የስነ-ልቦና እውነትን ለማጋለጥ እና የተራ ቁሶችን ከመደበኛ ጠቀሜታቸው በማሳለፍ፣ ከተራ መደበኛ ድርጅት በላይ የሆነ አሳማኝ ምስል ለመፍጠር፣ የሞከረ እና አድርጎም ያሳየ እንቅስቃሴ ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ትንሽ መዳከም ቢገጥመውም እስከአሁን ድህረ ዘመናዊ መልከታ ድረስ የዘለቀ በብዙዎች ልብ ውስጥ የቀረ የኪነጥበብ እንቅስቃሴ ሆኖ ቀርቷል።
❤6
ጥበብ ፍልስፍና
ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ ፫፮፱ ሙሉ በሙሉ ውስጥህን ባዶ አድርግ እርጋታ ይኑርህ። ምንም እንኳን ሁሉም ነገር አንድ ለይ ቢነሳም፤ ሲመለስም ተመልከት። ሁሉም ነገር ያብባል፣ ግን ውሎ አድሮ ወደ ስሩ ይመለሳል። በእርጋታ እያንዳንዱ እጣ ፋንታውን ያሟላል ወደ መሰረቱ ሲመለስ እርጋታ ይባላል፣ እርጋታው ደግሞ ወደ ተፈጥሮ ይመልሳል፣ ወደ ተፈጥሮ መመለስ ደግሞ…
what is wisdom?
ጥበብ ምንድነች? የት ነች? ጥበበኛስ ማነው?? ጥበብ ትፅፋለች። ጥበብ በተፈጥሮ ሁሉ ውስጥ ታወራለች፡፡ ጥበብ ታዜማለች። ጥበብ ያላወራችበት ቅፅበት የለም፡፡ የጥበብ ገላጮች ግን የጥበብን ድምፅ ያሰናክላሉ። ፅሁፏንም ያጣምማሉ። ጥበብ ስፍራዋ ዝቅታ ውስጥ ነው፡፡ ጥበብ ከዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠው ንጉስ አይደለችም። ነገር ግን በባርነት ቀንበር ስር እንዳለ አገልጋይ ነች። ዓላማዋ የተነሳውን መጣል አይደል የወደቀውን ማንሳት እንጂ። ስንቱ የጥበብን ድምፅ አጣሞ እንኳን የወደቀውን ሊያነሳ የቆመውን ጥሏል። ዕውቀት ከሰማነው ካነበብነው ሀሳብ ይቀዳል። ጥበብ ግን በሕማም ውስጥ ካለው የጣር ድምፅ በስተጀርባ ያለች አንዳች የምትስብ ጥዑመ ዜማ ነች። በአጭሩ ጥበብ እራሱ የጣር ድምፁ የሙዚቃ "Harmony ሲሆን እንደማለት ነው፡፡ ከሕመማችን ውስጥ የሚወለድ ጥበብ አለ። የሕመማችሁ ጥዑመ ዜማ በጥበብ መልክ የሚገለጠው በልቦናችሁ ንፅህና በኩል ነው፡፡ የልቦና ንፅህና የሌለው ሰው የጥበብን ጥዑመ ዜማ ሊያዳምጥ አይችልም። ክፋት፣ ተንኮል፣ ጥላቻ፣ ቅናት፣ መጠላለፍ፣ መነቃቀፍ፣ ከልክ ያለፈ እራስ ወዳድነት፣ ጦርነት፣ ዘረኝነት፣ አድመኝነት፣ ሐሜት ባለበት ስፍራ ሁሉ የጥበብ መውጫ በሯ ይጋረዳል። የልቦና ንፅህና ግን በጨለማ ውስጥም ቢሆን የጥበብን ብርሃናዊ ምሪት ያጎናፅፈናል፡፡ ቅንነትን ከትልቅ ስፍራ አትጠብቁ። ጥበብ መገኛዋ የተዋረደ ስፍራ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚያ ዘንድ የልቦና ንፅህና አለ! በተዋበ የልቦና ስፍራ ላይ የተሾመ የብርሃን አክሊል አለ።
❤7
ጥበብ ፍልስፍና
ፈጣሪ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ አደገኛው ፍጥረት ማን ይመስላቿል❓❗ ሴት ልጅ ናት !! ሴትን ልጅ በጣም ተጠንቀቅ ወንድሜ ! አለም በሴት ጠፍታ በሴት ብትድንም እናትም እህቶቻችን ሴቶች ቢሆንም ተፈጥሯቸው ግን እጅግ አደገኛና ሀያል እንደሆኑ መፅሀፍ ቅዱስም የታሪክ መዛግብትም ይነግሩናል። የጠቢቡ ሰለሞንን ያህል ማን ጥበበኛ አለ ግን በሴት ተሸነፈ የዳዊትን ያህል በእግዚአብሔር ፊት የተወደደና ሞገስ ያገኘ…
የሴት አምባገነንነት እና የወንድ ሞኝነት
ሐሳብ አስተያዬታችሁን" በተለመደዉ!! ኢትዮጵያዊ ጨዋነት! " አጋሩኝ።
@ethiosecret
የዘመናችን ትልቁ አሳዛኝ ነገር የወንድ ሞኝነት እና የሴት ጥቅመኝነት ጋብቻ መፍጠራቸው ነው። አንተ ወንደ!.. ለማፍቀር መስፈርት የማታዋጣ ሞኝ ነህ! እሷ ግን የጥቅም መስፈርት (Criteria) አውጥታ የወንድን ልብ ሳይሆን የወንድን ኪስ ትመርጥለች!።
1, የሞራል ኪሳራ
— ጥቅመኝነት እና የውሸት ፍቅር ፤ ሴቲነተን በራስ ወዳድነት ( Ego ) ጥቅመኝነት (Advantageousness )እና አጋጣሚን በመጠቀም (Opportunistic)የተሞላ ነው።
— የጥቅም ጋብቻ፡ ሴቶች ወንድ የሚፈልጉት Economical ችግራቸው እንዲቀርፍላቸው ነው። ውላቸውን፣ ህይወታቸውን፣ ፍላጎታቸውን ይነግሩታል፤ የሱ ግን መስማት አይፈልጉም ይህ ፍቅር ሳይሆን የገንዘብ ዝርፊያ ነው።
— የውሸት ገጸ ባህሪ፡ (Artificial Character) ያላቸው Romantic የሚመስሉ አጭበርባሪ ወንዶች ይወዳሉ። ተግባር እና Serious የሆነ የሞራል ሰው አያደንቁም ይባስ ብለው ደባሪ እንደሆነ ያስባሉ። የወንድ ዝምታ ለነሱ አይናፋርነት ወይም ኩራት ነው፤ የባህሪው አካል መሆኑን አይረዱም።
— የጥላቻ ፍቅር፡ በሚያሳዩት የውሸት ፍቅር ውስጥ ጥልቅ ጥላቻ አለ። የወንድ ቤተሰብን እንደ ቤተሰባቸው አይቀበሉም ከልጃቸው ውጭ ያሉትን ልጆች እንደ ልጅ አያዩም። ሴት ለሴት ያላቸው እርስ በእርስ መናከስ አስመሳይነታቸውን ለማየት በቂ ነው።
2, የፌሚኒዝም እና የበታችነት ስሜት ፤ ፖለቲካ ፍልስፍና ሲወራ የሚደብራቸው ሴቶች
— የማይስማሙበት ነገር ከተናገርክ ይጠሉሃል በ logic አይሞግቱህም የ Dialectics አቅማቸው ሲበዛ ትንሽ ነው። ጠጠር ያለ ወሬ ሲወራ ያሳክካቸዋል Serious የሆነ ርእስ ሲነሳ ይደብራቸዋል።
— ( inferiority complex ) ትንሽ ፊደል ሲቆጥሩ ከጥራዝ ነጠቅነት አልፈው ፀረ-ወንድ ( feminism ) የዘመናዊነት አንዱ መገለጫ አድርገው ይወስዱታል። ይህ ሁሉ የሚመጣው ትልቅ የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ነው ። አብዮተኞች (Revolutionary) አይደሉም ለውጥ አይወዱም!
3, የወንድ ስቃይ ትዳር ላይ ሲበዛ ያልተነቃበት ፤ አምባገነናዊ መንገድ ይከተላሉ።
— የወንዱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ በጣም ይጥራሉ። የወንድ ልጅ ስቃይ ለነሱ አንዳንዴ እንደ Orgasm ነው። ባገኙት ትንሽ አጋጣሚ እና ስልጣን ወንድን Abuse ለማድረግ ይፈልጋሉ።
— ልጆች አባት ላይ እንዲነሱ አባት ላይ ጥላሸት እየቀባች ልጆች ከአባታቸው እንዲርቁ እንዲሸሹ ታደርጋለች የወንድ የቤት ተፈጥሯዊ መሪነቱን ለመንጠቅ ይሻሉ።
—ወንድ ሁሌም Open የሆነው የወሲብ ፍላጎት ጆሮ ዳባ ብለው ባይተዋር አድርገው፣ አይኑ ሌላ ኮረዳ እንዲያማትር ይገፋፉታል። ይህ የወንድ ባህሪ ካለመረዳት የሚመነጭ ያልበሰለ አካሄድ ነው።
ማጠቃለያ
አካላዊ፣ ሞራላዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬ በሚፈልገው ነባራዊ አለም፣ ስትወድቅ መነሳት በሚፈልገው የአለም ባህሪ የወንድ አሸናፊነት ግድ ይሆናል የሴት አምባገነንነት እና የወንድ ሞኝነት መቆም አለበት። ወንዶች አትሸወዱ!
ሐሳብ አስተያዬታችሁን
@ethiosecret
❤5😁5👍2😢2👎1🤬1
ጥበብ ፍልስፍና
#Movies🎥 🎥
#Movies🎥 🎥
ፊልሙ እ.ኤ.አ በ 2002 የተሰራ ፊልም ነው። የፊልሙ አርዕስት #Equilibrium የተሰኘ ነው። ፊልሙ በ totalitarian ላይ የተመሰረተ ነው። totalitarian ማለት አገዛዙ የፈቀደልህንና የወሰነልህን ገደብ መኖር እንደማለት ነው።@ethiosecret
ፊልሙ ጭብጡን ያደረገው በ totalitarian ሀሳብ ላይ ሆኖ ስሜታችን feeling, sense and emotion የሚባሉት ነገሮች የማይፈቀዱበት እንደወንጀል የሚቆጠርበት ሀገረ መንግስት ነው። ለነገሮች ያለን ስሜት ነው ጦርነቶችና መገዳደሎችን ያስከተሉብን የሚል ሀሳብን በመያዝ የሀገሬው መንግስት ህዝቡ ሁሉ ምንም አይነት ስሜትን እንዳይሰማው በየቀኑ የሚወስዱት መድሀኒት ይሰጣቸዋል። በርግጥ ህዝቡ ግን ያን መድሀኒት ስሜታቸውን እንደሚገለው የሚያውቁት ነገር የለም መድሀኒቱን በየቀኑ በስሪንጅ መልክ መወጋት ግዴታቸው ነው እሱን ያላደረገ በሽብር ወንጀል ይከሰሳል የሞት ፍርድ ይፈረድበታል።
እዚህ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት ስሜትን የሚቀሰቅስ ነገር ማድረግ አይቻልም እንስሳትን ማሳደግ አይፈቀድም የጥበብ ስራዎችን መመልከትም ሆነ በመፅሐፍ መልክ ማየትም መስማትም የተከለከለ ነው። ስዕል ፣ ሙዚቃ ፣ ጌጣጌጥ ፣ መስታወት ፣ ቤትን ማስዋብ....ምንም ከስሜት ጋር የተገናኘ ነገር ካደረጉ የስሜት ተጠርጣሪዎች (sense offenders) ተብለህ ትገደላለህ። ማልቀስ መሳቅ ማፍቀር ውጉዝ ናቸው።
ፊልሙ ሲጀምር የስሜት ተጠርጣሪዎችን በማሳደድ ሲጀምር ይታያል። ከዛም ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ከገደሉ በኋላ ቤት ውስጥ ያሉትን የጥበብ ስራዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ ያዛል እዛ ቤት ውስጥ የሞናሊዛ ስዕልም አብሮ ሲቃጠል ይጀምራል። የዛ ከተማ ኗሪዎች ሚለብሱት ፣ የሚኖሩበት ፣ የሚመገቡት የሁሉም ተመሳሳይ ኑሮን የሚከተል ነው።
እና ባንድ ወቅት ዋና ገፅ በሀሪው የ ከተማዋ ኤጀንት clierk ጠዋት እንክብሏ ወድቃ ትሰበርበታለች ከዛን በኋላ ነገሮች ይሰሙት ይጀምራሉ። ለእንስሳ ፣ ለሚገላቸው ሰዎች ፣ ለነገሮች ስሜት ይሰማው ይጀምራል እያለ የሚቀጥል ፊልም ነው።
❤2👏2🔥1
ጥበብ ፍልስፍና
#Movies🎥 🎥 ፊልሙ እ.ኤ.አ በ 2002 የተሰራ ፊልም ነው። የፊልሙ አርዕስት #Equilibrium የተሰኘ ነው። ፊልሙ በ totalitarian ላይ የተመሰረተ ነው። totalitarian ማለት አገዛዙ የፈቀደልህንና የወሰነልህን ገደብ መኖር እንደማለት ነው። ፊልሙ ጭብጡን ያደረገው በ totalitarian ሀሳብ ላይ ሆኖ ስሜታችን feeling, sense and emotion የሚባሉት ነገሮች የማይፈቀዱበት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
...የቀጠለ
በርግጥ ይሄን ፊልም ሳይ የሰው ልጅ ለነገሮች ምንም የማይሰማው ከሆነ ከ አውሬ እንደሚብስና ሮቦት እንደሚሆን ያሳያል። ለልጅህ ለቤተሰብህ ለሰው ለ እንስሳ የማታዝን ከሆነ ለ ስነ ጥበብ ግጥም ሙዚቃ ቦታ ከሌለው ሰው ምንድነው? እንድትሉ የሚያደርግ ነው። ይሄን ፊልም አሁን ካለንበት ዘመን ጋር ብናመጣው ለነገሮች ስሜት ያጣበት ዘመን ላይ ነው። ይሄ ማለት በፊልሙ ላይ ያለውን አይነት ከተማ ለመምሰል ብዙ አንርቅም በመንግስት ጫና ሳይሆን አሁን የተጠናወተን አግበስባሽነት (consumerism) ጋር ይገናኛል። ፊልሙ ላይ ያለችው በየቀኑ የሚወስዷት ስሜት አልባዋ እንክብል እዚህ ዘመን ላይ አግበስባሽነት በሏት።
ፊልሙን ኮምኩሙት። ፊልሙን ካጣቹህት ሀሳብ መስጫ ላይ ጠይቁኝ አስቀምጥላቹሀለሁ

አሁን ላይ ሰው ደስታን ፍለጋ የማያግበሰብሰው ነገር የለም ግን ደስታ እንደ ሰማይ የራቀው ይመስላል። ከ 19 ነኛው ክፍለ ዘመን በኋላ materialism የገነነበት አለም ነገሮች በመሰብሰብ የሚያምን ከነገሮች ጋር ግንኙነቱ የተቋረጠ ብዙ ስዕል በቤቱ ቢደረደርም ስሜት ማግኘት የቸገረው ለስሜቱ ብዙ ርቀትም ቢሄድ ስሜት አልባ የሆነው postmodernism ዘመን ይሄ ፊልም ብዙ ጭብጥ ይሰጠናል። ስሜት ማጣት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ፊልሙን ኮምኩሙት። ፊልሙን ካጣቹህት ሀሳብ መስጫ ላይ ጠይቁኝ አስቀምጥላቹሀለሁ
❤6