Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ
1.14K subscribers
275 photos
756 links
#NewsaboutEthiopia & the #Horn
ይህ የቴሌግራም ቻናል ትኩስ ዜናዎች፣ አዝናኝ መረጃዎች፣ ትንታኔዎች እና የስራ ቅጥር ማስታወቂያ የሚቀርብበት ነው።

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ አድርገው ቤተሰብ ይሁኑ።

http://youtube.com/@ethionegari
Download Telegram
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አስክሬን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባል

የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አስክሬን በህክምና ሲረዱ ከቆዩበት ኬንያ ናይሮቢ ዛሬ ምሽት ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባ የቀብር አስፈጻሚ አብይ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የአብይ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ማርቆስ ሌራንጎ የፕሮፌሰሩ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሐሙስ በአዲስ አበባ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም ተናግረዋል፡፡

የፕሮፌሰሩን ዜና ህልፈት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
በትግራይ ክልል አዲስ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ተቃዎሚ ፓርቲዎች ጠየቁ

በትግራይ የሚንቀሳቀሱ አራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ሁሉን አካታች እና ሲቪላዊ አዲስ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲመሰረት ጠየቁ።

በትግራይ ክልል ያሉ ችግሮች መነሻ ፖለቲካዊ ናቸው የሚሉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፥ መፍትሔውም ሁሉ አካታች ፖለቲካዊ መድረክ ነው ብለዋል።

ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ለዴሞክራሲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ እና ባይቶና በጋራ በሰጡት መግለጫ የትግራይ ሐይሎች እያሳዩት ነው ያሉት ፖለቲካዊ ተሳትፎ ኮንነዋል።

ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና ባይቶና በጋራ መግለጫቸው እንዳሉት የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች በሲቪል አስተዳደር ስር ሆነው፣ በገለልተኛነት መንቀሳቀስ ሲገባቸው፥ በአንድ ፓርቲ ውስጣዊ መሳሳብ ቀጥታ በመግባት፥ መጥፎ ሁኔታ ላይ ያለው የትግራይ ፖለቲካ ይበልጥ እያወሳሰቡት ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

አሁን ላይ በትግራይ ተከስቶ ያለው ችግር መነሻ ፖለቲካዊ ስለሆነ መፍትሄው መሆን ያለበት ፖለቲካዊ ነው የሚሉት እነዚህ ፓርቲዎች፥ ይህ እንዲሆንም ሁሉን አካታች ሲቪላዊ ጊዚያዊ አስተዳደር እንደአዲስ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበዋል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናዬ ከሀገር መሰደዳቸውን ተናገሩ

ከሶስት ወራት በፊት ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናዬ፤ ሀገራቸውን ለቅቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ተናገሩ።

ሁለቱ ጋዜጠኞቹ የተሰደዱት፤ በመንግስት የጸጥታ አባላት በተሰጣቸው “ለህይወታቸው የሚያሰጋ” “ማስጠንቀቂያ” እና ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሚደረግባቸው “ክትትል” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ በላይ እና በቃሉ 11 ቀናት የፈጀ “አስቸጋሪ ጉዞ” በማድረግ ከሀገር የወጡት፤ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጳጉሜ 4፤ 2016 መሆኑን አስረድተዋል።

ሆኖም ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ሀገር፤ “ከደህንነት ስጋት” ጋር በተያያዘ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
በደባርቅ ከተማ የታየውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው አስተዳድር ጸጥታ ምክርቤት አስታወቀ

"በደባርቅ ከተማ ተከስቶ የነበረው ጊዜአዊ የፀጥታ ችግር በፀጥታ ሀይላችን ቅንጅታዊ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል!" ሲል የከተማ አስተዳደሩ ፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል።

የከተማ አስተዳድሩ ጸጥታ ምክር ቤት በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አሁን ላይ የደባርቅ ከተማ ማሕበረሰብ የተለመደ ዕለታዊ ማሕበራዊ እንቅስቃሴውን እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጿል።

ትናንት በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በመንግስትና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል ትላንት በነበረው ግጭት ወደ ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል ቆስለው ከገቡት ውስጥ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ የሶስት አመት ህፃንን ጨምሮ 28 ሰዎች መቁሰላቸውን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አስታውቀው ነበር።

ስራ አስኪያጁ አቶ አለ አምላክ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ ከሟቾቹ ውስጥ አንድ ታጣቂና አንድ ሲቪል ናቸው ብለዋል ::

ወደ ሆስፒታል ሳይደርሱ የህፃኑን አባት ጨምሮ ከ7 በላይ ስዎች መሞታቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ሊሰጥ ነው

የመጀመርያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ስርዓት ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን በውድድር ነፃ የትምህርት እድል ከዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎት ጋር እንደሚሰጥ ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና እንደሚሰጥና እንደሚቀበል ይጠበቃል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የኦሎምፒክ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴን አገደ

መስከረም 8 2017 ዓ.ም ፦በመዝገብ ቁጥር 333122  የዋለው ችሎት በይግባኝ ባዮች በእነ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ (4 ሰዎች) እና መልስ ሰጪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (5 ሰዎች) ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ባዮች  በዋናነት ያነሱት
 
- ግንቦት 5 2016 እና ሰኔ 4 2016 የተከናወኑ ህገወጥ የጠቅላላ ጉባኤ እና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ እንዲታገድ

- የህዝብ እና የሀገር ሀብት እንዳይባክን ከደመወዝ ክፍያ ውጪ የባንክ አካውንት እንዲታገድ ጠይቀዋል

የይግባኝ መነሻቸውን ፍርድ ቤቱ የመረመረ ሲሆን አመልካቾችና ጠበቆች በሰጡት ምልሽ በዋናነት ህግና ስርዓት ተከብሮ ተቋሙን የመታደግ አላማና ወደነበረበት ከፍታ ለመመለስ ከመሻት የመነጨ ፍላጎት እና ቁጭት እንጂ የጥቅምም ሆነ የስልጣን ፍላጎት እንደሌላቸው ለፍርድ ቤት አስረድተዋል፡፡

ከስራ አስፈፃሚዎች ነውጠኝነትና ለስርዓትና ለህግ ያለመገዛት አዝማሚያ በስራ ማስኬጃ ሰበብ ብክነት እንዳይኖር እንዲሁም በሪፎርም በሚል ምክንያት  የታቀዱ ብክነቶች ስለመኖራቸው መረጃ ስላለን ፍርድ ቤቱ አካውንቱን እንዲያግድ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ትእዛዝ ለባንኮችና ለዋና መስሪያ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ 

ሌላኛው ትእዛዝ ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በቀን 04/10/2016 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ የታገደ መሆኑን እንዲያውቁና እግዱን እንዲፈፅሙም ታዟል፡፡ 

የመልስ ሰጪዎችን ምላሽ ለመስማት ለመስከረም20 ፍርድቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

#ethiopia #Olympic
ቱርክ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ባለሥልጣናትን በተናጥል ልታነጋግር ነዉ

ቱርክ የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት ዳግም ግን በተናጥል ለማነጋገር ማቀዷን አስታወቀች።

የቱርክ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊንዳን ከዚህ ቀደም በተደረጉት ተዘዋዋሪ ድርድሮች ሁለቱም ወገኖች መጠነኛ መለሳለስ በማሳየታቸዉ ድርድሩ ዉጤት ያመጣል የሚል «ተስፋ አለኝ» ብለዋል።

በፊዳን መግለጫ መሠረት ቱርክ የወደፊቱን ሽምግልና ለመቀጠል ያቀደችዉ «የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት እዚሕ ብንጋብዛቸዉም ፊትለፊት ሥለማይነጋገሩ እኛ በተናጥል እናነጋግራቸዋል።» ብለዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል የተካረረውን ጠብ ለማርገብ ቱርክ ከዚሕ ቀደም የሁለቱን ሐገራት ባለሥልጣናት አንካራ ዉስጥ ሁለቴ በተዘዋዋሪ አነጋግራለች።

በቱርክ ሸምጋይነት የሚደረገዉ ድርድር ባለፈዉ ማክሰኞ ለሶስተኛ ዙር ይቀጥላል ተብሎ ነበር።
ይሁንና ቀጠሮዉ ተሰርዟል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
በ2017 በጀት ዓመት 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንደሚነሱ ተገለፀ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በዘንድሮው በጀት ዓመት በሚገነባቸው መንገዶች እና ከሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንደሚነሱ አስታወቀ

መስሪያ ቤቱ ባለፈው የ2016 በጀት ዓመት ባከናወናቸው የመንገድ ግንባታ ሳቢያ ለተነሱ መሰረተ ልማቶች እና የመኖሪያ ቤቶች 1.8 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መፈጸሙን ገለጿል።

ያለፈውን አመት የስራ አፈጻጸሙን እና የ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት እቅድ አስመልክቶ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 9፤ 2017 ዓ.ም መግለጫ የሰጠው መስሪያ ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት 1,140 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ማከናወኑን በውይይቱ ላይ ጠቅሷል።

በመንገድ ግንባታ እና ጥገናው ሳቢያ 682 ቤቶች እንዲነሱ መደረጋቸውን የገለጸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ከ1,200 በላይ በሆኑ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።

ቤቶቹ እና መሰረተ ልማቶቹ እንዲነሱ የተደረጉት፤ መንገዶች በሚገነቡበት “ወሰን ውስጥ የሚገኙ” በመሆናው ምክንያት መሆኑን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን መናገራቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት ለመዋዕለ ህጻናት ወይም ኬጂ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዳይማሩ ከልክላ ነበር፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኬጂ ተማሪዎች እንዳይማሩ አግዶት የነበረውን እንግሊዘኛ ቋንቋ በድጋሚ እንዲሰጥ መወሰኑ ተገልጿል፡፡

ቢሮው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ክልከላ የጣለው ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ በሚል እንደነበር በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡

ባለፈው ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቅድመ መደበኛ (ኬጂ) የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በዚህ ሳምንት በተጀመረው የ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሳምንት ለአምስት ጊዜ እንደሚሰጥ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3MSqQYU

#ethiopia #English
አዲስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች

Mercy Corps, International Rescue Committee እና Care Ethiopia በተለያዩ የስራ መስኮች አዲስ ሰራተኞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ አጥተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://ethionegari.com/2024/09/20/latest-ngo-job-opportunities-in-ethiopia-3/

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
የትራንስፖርት ቢሮው አዲስ የስምሪት ውሳኔውን እንዲቀር ማድረጉን ገለጸ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እቅዱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እስከሚደረግበት ድረስ የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ባለበት ይቀጥላል ብሏል።

ቢሮው ከትምህርት መከፈት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ መጨናነቆችን ለመቀነስ የተወሰኑ የከተማዋ መስመሮች ለብዙሀን ትራንስፖርት አግልግሎት ብቻ ክፍት እንዲሆኑ ወስኖ ነበር።

ቢሮው አሁን ከመሸ ባወጣው መግለጫ ይህን ውሳኔውን እንዲቀር አድርጎታል።

እቅዱ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት እስከሚደረግበት ድረስ የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ባለበት ይቀጥላል ብሏል።

ትራንስፖርት ቢሮው ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ 14 መስመሮችን ይፋ አድርጎ ነበር።

ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ተለይተው የነበሩት መስመሮች ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ- ፒያሳ እና ከጀሞ- ሜክሲኮ፣ ከፒያሳ- ቦሌ፣ ከሜክሲኮ- ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ- ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ- ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ- ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ እና ከሜክሲኮ - ጀሞ ነበሩ።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
የስኮላርሺፕ እድል ለኢትዮጵያዊያን

የስዊድኑ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ኢትዮጵያዊያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስኮላርሽፕ እድል ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

ለማመልከት እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ

https://ethionegari.com/2024/09/20/new-scholarship-opportunity-for-africans/

#ethiopia #scholarships
የድቪ 2026 ማመልከቻ ከአንድ ሳምንት በኋላ ይጀመራል

የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1995 ዓመት ጀምሮ በድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ በመውሰድ ለይ ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያ ለዚህ እድል ከተፈቀደላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በየዓመቱ በአማካኝ ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ ያቀናሉ፡፡

የድቪ 2024 እድለኛ ኢትዮጵያዊን የቪዛ ማመልከቻቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚያበቃ ሲሆን የድቪ 2025 እድለኞች ደግሞ ከያዝነው መስከረም ወር መጠናቀቅ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የቪዛ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡

ይህ በዚህ እንዳለም የድቪ 2026 የማመልከቻ ጊዜ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጀመር ሲሆን ለአንድ ወር እንደሚቆይ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜው ከመስከረም 21 ቀን እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 30 ቀናት ይቆያል የተባለ ሲሆን አሸናፊ እድለኞች ደግሞ ግንቦት ወር ጀምሮ ማወቅ እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://bit.ly/3XStXX8

#ethiopia #DV2026
አዲስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች

Care Ethiopia በተለያዩ የስራ መስኮች አዲስ ሰራተኞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ አጥተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://ethionegari.com/2024/09/21/new-ngo-job-opportunities-at-care-ethiopia/

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶች ላይ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ

በሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን በጉብኝት ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶች በነበሩበት በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት አንድ የፖሊስ መኮንን መሞቱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የውጭ አገር ዲፕሎማቶቹ በአካባቢው ያለን ቱሪስት ሥፍራ ለመጎብኘት ሲጓዙ ነው መንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ ጥቃቱ የደረሰው።

“ዲፕሎማቶቹን እየመራ ሲሄድ የነበረው የደኅንነት ቡድን ነው መንገድ ዳር በተቀበረ ቦምብ የተመታው” ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ባወጣው መግለጫ በፓኪስታን ኺቤር ፓኽቱንኽዋ ክልል የደረሰውን “የሽብር ጥቃት” አውግዟል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች የውጭ አገር ዲፕሎማቶች በሥፍራው እንደነበሩ አረጋግጧል።

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በኽርን ጨምሮ በዲፕሎማቶቹ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አልደረሰም።

ሮይተርስ እንደዘገበው በጥቃቱ አራት የፖሊስ መኮንኖች መቁሰላቸውን የግዛቲቱ የፖሊስ ኃላፊ አስታውቀዋል።

የፓኪስታን ፕሬዝደንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሼባዝ ሻሪፍ ጥቃቱን ያወገዙት ሲሆን፣ እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ የለም።

ዲፕሎማቶቹ ስዋት ቫሊ ወደተባለው አካባቢ ለጉብኝት ሲያቀኑ የነበረው በአካባቢው የንግድ ምክር ቤት ግብዣ በስፍራው ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ መሆኑ ተገልጿል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
ግብፅ ለሶማሊያ ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች፣ መድፎች እና ሌሎች አነስተኛ የጦር መሳሪያዎችን ሰጠች

ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧት እና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን አረጋገጡ።

ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩት ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው መሆኑን አመልክተዋል።

ወደ ሶማሊያ የገቡት የጦር መሳሪያዎች ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች፣ መድፎች እና ሌሎች አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው አረጋግጠዋል።

ይህንን ከፍተኛ መጠን ያለውን የጦር መሳሪያ በሞቃዲሾ ወደብ በኩል ወደ ሶማሊያ መግባቱን በተመለከተም የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ሲሆን፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይም ይህንን የሚያሳዩ ምሥሎች ተሰራጭተዋል።

ቢቢሲ ሶማሊኛ ያነጋገራቸው የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣን አሁን ከገባው የጦር መሳሪያ ጭነት በተጨማሪ በቀጣይነት ታንኮችን እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ይህ ዜና የተሰማው ግብፅ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ደርሳ ሠራዊቷን በአገሪቱ ውስጥ ለማሰማራት ፍላጎት እንዳላት መግለጿን ተከትሎ ኢትዮጵያ ተቃውሞዋን ካሰማች በኋላ ነው።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
ሶማሊላንድ ግብፅ ወደ ሞቃዲሹ ከባድ የጦር መሳሪያ ማስገባቷ እንዳሳሰባት ገለፀች

የሶማሌ ላንድ መንግስት ግብፅ ለሶማሊያ የምታቀርበውን ከባድ የጦር መሳሪያ አሳሳቢነት በመግለጽ እርምጃው ቀድሞውንም ደካማ የነበረውን የቀጠናውን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል ስትል አስጠንቅቃለች።

የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ “በተለይ የሞቃዲሾ አስተዳደር በብቃት ለማስተዳደር ወይም ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ስለሌለው የእነዚህ መሳሪያዎች ዝውውር በእጅጉ አስደንግጦናል ብለዋል።

ሶማሊላንድ በተጨማሪም ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር የአፍሪካ ቀንድን ወደ አልተረጋጋ ቀውስ እና የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እድልን ከፍ እንደሚያደርግ አፅንዖት ሰጥታለች።

የጦር መሳሪያዎቹ በቀጠናው ሰላምን ለማደፍረስ በሚጥሩ እንደ አልሸባብ ባሉ እና በሌሎች ፅንፈኞች እጅ እንዳይወድቁ ስጋት እንዳለው ገልጿል።

የሶማሊላንድ መንግስት የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ በዚህ ጉዳይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
አዲስ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች

በተለያዩ የስራ መስኮች የወጡ የNGO ስራዎችን በዝርዝር ለመመልከት እና ለማመልከት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://ethionegari.com/2024/09/24/latest-ngo-jobs-in-ethiopia-7/

ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

�Telegram https://t.me/EthioNegarii

�Twitter https://twitter.com/EthioNegari

� YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ

Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/

Website https://ethionegari.com/

LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari
በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀረበ

በደቡብ እና በምስራቅ የሊባኖስ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ለዜጎቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መረጃ በተለይም በደቡብ እና በምስራቅ የሊባኖስ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መሆኑን ገልጾ÷ በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ከታች በተቀመጠው መሠረት ስማቸውን ፓስፖርት ላይ አንደተፃፈው፣ የፓስፖርት ቁጥር እና ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዚሁ መሠረት በደቡብ ሊባኖስ
ታየር፣ ሱር፣ ቢንት ጅቤል፣ ማርጃዩን፣ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51ወይም 03-87-10-89

እንዲሁም በምሥራቅ ሊባኖስ አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው)የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ አሳስቧል፡፡

በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ በሊባኖስ እና ቀጠናው ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ዜጎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ማሳሰቡ ይታወሳል።

በሊባኖስ በእስራኤል ሃይሎች እና በሂዝቦላህ መካከል የነበረውን ውጥረት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከወር በፊት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቆ ነበር።

የወቅቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ “ህጋዊም ይሁኑ ሕገወጥ፣ ተዘጋጅተው መጠበቅ አለባቸው ፣የጸጥታው ጉዳይ ተባብሶ ከቀጠለ የኢትዮጵያ መንግስት በሊባኖስ ያሉትን ህገወጥ እና ህጋዊ ዜጎቹን ወደ አገራቸው ይመልሳል" ማለታቸው ይታወሳል።

በሌላ መረጃ የአለማቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) እ.አ.አ በኦገስት 2023 ባወጣው ሪፖርት 160,738 የሌላ ሀገር ዜጎች በሊባኖስ እንደሚኖሩ ይገልጻል። ከነዚህ ውስጥም 119,154 የሚሆኑት በከተማ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።

በተለያዩ ቁጥራዊ መረጃዎች በአጠቃላይ በሀገሪቱ ካሉ ስደተኞች ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት የኢትዮጵያ ዜጎች ሲሆኑ አብዛኞቹ ደግሞ ሴቶች ናቸው።