💊 መሰረታዊ የመድሃኒት መረጃ #1: አስፕሪን (#Aspirin/Acetylsalicylic Acid/ASA)
🟢 አስፕሪን ምንድን ነው?
• የስትሬይድ ይዘት የሌለው ፀረ-ብግነት መድሃኒት (nonsteroidal anti-inflammatory drug/NSAID) ሲሆን ህመም፣ ትኩሳት እና እብጠትን ይቀንሳል። በተጨማሪም ደም መርጋትን የሚቀንስ (antiplatelet) መድሃኒት ነው።
📌 አስፕሪን መቼ ይታዘዛል?
• ህመምና ትኩሳት ላላቸው
• የልብ በር ወይም ግድግዳ ሽፋን ብግነት ለተከሰተባቸው
• የመገጣጠሚያ ብግነት ላለባቸው
• የደም ስር መዘጋትን ተከትሎ የሚመጣ የልብ ጥቃትን (Heart attack) እና ስትሮክን (Stroke) ለመከላከል
• የተዘጋን የልብ ደም ስር ለመክፈት በሚረዱ ሰው ሰራሽ ቀጫጭን ቱቦዎች (coronary stents) ለታከሙ
⚠️ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ለየትኞቹ ሁኔታዎች ነው?
• የአስፕሪን አለርጂ
• የአስም በሽታ
• የጨጓራ ቁስለት
• የደም መፍሰስ ችግር (ለምሳሌ፦ ከጨጓራ ወይም ከአንጀት ግድግዳ ላይ)
• የኩላሊት ወይም የጉበት ችግር
🚫 አስፕሪን መወሰድ የሌለበት መቼ ነው?
• የደም መፍሰስ ካለ
• ከባድ የአስፕሪን አለርጂ ካለ
• የቫይረስ ሕመም ላለባቸው ህፃናት
⚠️ ልዩ ጥንቃቄ
• ከአልኮል ጋር መወሰድ የለበትም።
🤰ከእርግዝና ጋር በተገናኘ
• ከ20 ሳምንት በኋላ ያለሃኪም ትዕዛዝ እንዲወሰድ አይመከርም።
🤱 ጡት ከማጥባት ጋር በተገናኘ
• በዝቅተኛ መጠን ከተወሰደ አብዛኛውን ጊዜ የጤና ችግር አያመጣም።
• በከፍተኛ መጠን ከተወሰደ ግን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
⚡የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ምን ምን ናቸው?
• የጨጓራ ህመም ወይም ማቃጠል
• ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ
• በቀላሉ የሚከሰት የቆዳ መበለዝ
🚨 አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልገው በምን ሁኔታዎች ነው?
• ጥቁር ሰገራ ወይም ደም ማስታወክ ከታዬ
• ያልተለመደ የደም መፍሰስ ካጋጠመ
• ከባድ የማዞር/ግራ መጋባት ሁኔታ ከተከሰት
• ጆሮ ውስጥ ድምጽ (Tinnitus) ከተሰማ
📦 ዋና ዋና መልዕክቶች
✔ ለህመም ማስታገሻነትና እና የልብ ደም ስር መዘጋትን ወይም ስትሮክን ለመከላከል ይረዳል።
❌ ዋና አደጋዎች: የደም መፍሰስና የጨጓራ ቁስለት
⚠️ የቫይረስ ሕመም ላለባቸው ህፃናት መሰጠት የለበትም!
በዶ/ር ጋሻው ሶለላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያና የልብ ህክምና ፌለው)
Telegram: https://t.me/ETMedHeart
Facebook: facebook.com/ETMedHeart
📞 0928084444
በቴሌግራም ለማማከር: @DrGashaw

🙏1
🤰World Preeclampsia Day [May 22, 2026]: (ዓለም ዓቀፍ የእርግዝና ከፍተኛ የደም ግፊት ቀን)
📊 ማወቅ ያለብዎት
• ከፍተኛ የደም ግፊት እርግዝና ላይ የመከሰት እድል ከ 2 - 8% እንደሆነ ይገመታል።
• ብዙ ጊዜ ከ20 ሳምንታት በኋላ ይጀምራል።
• በእርግዝና ወቅት ቀድሞ በመለካት ከፍተኛ ደም ግፊት እንዳለ ማወቅና መታከም ይመከራል።
🟢 ፕሪኤክላምፕሲያ (በእርግዝና የሚመጣ ከፍተኛ ደም ግፊት) ምንድን ነው?
• በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ከፍተኛ ደም ግፊት (ከ 140/90 በላይ) ሲሆን በእናትና እና ልጅ ጤና ላይ የተለያዩ ችግሮችን ሊያመጣ የሚችል ሁኔታ ነው።
⚠️ የተለመዱ ምልክቶች
🩺 ከፍተኛ የደም ግፊት
💧 የፊት፣ የእጅ እና የእግር ማበጥ
🚽 የሽንት ምርመራ ላይ ፕሮቲን መታየት
🚨 አደገኛ ምልክቶች
🤕 ከፍተኛ ራስ ምታት
👀 የእይታ ችግር
🤢 ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
📍 በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም
😮💨 የመተንፈስ ችግር
⚖️ በፍጥነት የሚጨምር ክብደት
🚑 አስቸኳይ ሁኔታ
⚡ መንቀጥቀጥ ወይም እንፍርፍሪት (seizure)
🩸 በጣም ከፍተኛ የደም ግፊት
🚱 የሽንት መጠን መቀነስ
💔 ከባድ የደረት ህመም ወይም የመተንፈስ ችግር
📌 አደገኛ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች
• የመጀመሪያ እርግዝና
• መንታ ወይም ከዛ በላይ እርግዝና
• ስር የሰደደ ከፍተኛ ደም ግፊት
• የስኳር በሽታ
• ውፍረት
• የበፊት እርግዝና ላይ ተመሳሳይ ታሪክ መኖር
🏥 ራስንና እና ልጅን ከከፋ አደጋ እንዴት መጠበቅ ይቻላል?
• ሁሉንም የቅድመ ወሊድ ክትትል ቀጠሮዎች ማክበር
• የደም ግፊትን በየጊዜው መመርመር
• የታዘዘ መድሃኒትን በትክክል መውሰድ
• ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች ችላ አለማለት
🚨 ዋና መልእክት
• ምልክቶቹን ይወቁ! በጊዜ ይተግብሩ! ሕይወትን ይታደጉ!

❤1
💊 መሰረታዊ የመድሃኒት መረጃ #2: ዋርፋሪን (#Warfarin)
🟢 ዋርፋሪን ምንድን ነው?
• ደም መርጋትን (thromboembolism) ለመከላከልና ለማከም አስፈላጊ የሆነ የሚዋጥ መድሃኒት ነው።
📌 ዋርፋሪን መቼ ይታዘዛል?
• የላይኛው የልብ ክፍል ምት መዛባት (Atrial fibrillation)
• ጥልቅ የደም መላሽ ቧንቧዎች (በብዛት እግር ውስጥ) ደም መርጋት (Deep vein thrombosis)
• የሳንባ ውስጥ ደም መረጋት (Pulmonary thromboembolism)
• ሰው ሰራሽ የልብ ቫልቭ (Mechanical valve)
• የታችኛው የልብ ክፍል ውስጥ ደም መርጋት (LV thrombus)
• ተደጋጋሚ የደም መርጋትን መከላከል
🧪 "INR" ምንድን ነው?
• "INR" የደም መርጋት ፍጥነትን የሚለካ ምርመራ ሲሆን ከ 2 እስከ 3 እንዲሆን ይፈለጋል። ለሰው ሰራሽ የልብ ቫልቭ ደግሞ (ከፍተኛ አደጋ ስላለው) ከ 2.5 እስከ 3.5 እንዲሆን ይመከራል።
⚠️ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ለየትኞቹ ሁኔታዎች ነው?
• የጨጓራ ቁስለት ወይም የበፊት የደም መፍሰስ ታሪክ
• የጉበት ወይም የኩላሊት ችግር
• መቆጣጠር ያልቻሉት ከፍተኛ የደም ግፊት
• በተደጋጋሚ የመውደቅ አደጋ
🚫 ዋርፋሪን መወሰድ የሌለበት መቼ ነው?
• አዲስ ወይም የቅርብ ጊዜ ደም መፍሰስ ከተከሰተ
🤰 ከእርግዝና ጋር በተገናኘ
• በእርግዝና ወቅት ከሃኪም ትዕዛዝ ውጭ አይመከርም።
🤱 ጡት ከማጥባት ጋር በተገናኘ
• በአብዛኛው ጊዜ ጡት በማጥባት ወቅት መወሰድ ይችላል። ይሁን እንጅ የሃኪም ምክር ያስፈልጋል።
🥬 ከምግብ ጋር በተገናኘ
• አረንጓዴ አትክልቶችን ለምሳሌ ስፒናች፣ ጎመን፣ ብሮኮሊና አረንጓዴ ሻይ አዝወትሮ መጠቀም አይመከርም። እነዚህ ምግቦች ዋርፋሪን በትክክል እንዳይሰራ በማድረግ የደም መርጋት እድልን ይጨምራሉ።
🧬 የመድሃኒት ግንኙነቶች
• ከአስፕሪን (Aspirin) ጋር
• ከፀረ-ማስታገሻ መድሃኒቶች (NSAIDs) [ለምሳሌ፦ Ibuprofen, Diclofenac) ጋር
• ከአማይዳሮን (Amiodarone) ጋር
• ከብዙ ፀረ-ተዋህሲያን መድሃኒቶች (antibiotics) ጋር
⬆️ ከእነዚህ ጋር ሲወሰድ የደም መፍሰስ አደጋን ይጨምራል።
⚡ የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ምን ምን ናቸው?
• በቀላሉ መበለዝ
• ቀላል የደም መፍሰስ (ለምሳሌ፦ ነስር)
• የድካም ስሜት
🚨 አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልገው በምን ሁኔታዎች ነው?
• የማይቆም ደም መፍሰስ
• ደም ማስመለስ
• የሰገራ ደም መጥቆር
• በሽንት ደም መታየት
• ከባድ ራስ ምታት
• ከባድ ማዞር/ድካም
🔄 በዋርፋሪን የመጣ ደም መፍሰስ እንዴት ይቀለበሳል (Reversal)?
• ቫይታሚን ኬ (Vitamin K)
• Prothrombin Complex Concentrate (PCC) ወይም Fresh Frozen Plasma (FFP)
📦 ዋና ዋና መልዕክቶች
✔ ዋርፋሪን ለሰው ሰራሽ የልብ ቫልቭ እና ለደም መርጋት ችግሮች ወሳኝ መድሃኒት ነው።
✔ INR በመደበኛነት መከታተል አስፈላጊ ነው።
❌ ዋና አደጋ: የደም መፍሰስ
⚠️ በእርግዝና ወቅት ያለሃኪም ትዕዛዝ አይመከርም!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
🔴 የኮሌስትሮል መብዛት ወይም መዛባት (High Blood Cholesterol/Dyslipidemia)
#ኮሌስትሮል ደም ውስጥ የሚገኝ ቅባት ወይም ስብ መሰል ንጥረ ነገር ሲሆን መጠኑ ይለያይ እንጅ በሁሉም ሰው ደም ውስጥ ይገኛል። ኮሌስትሮል በብዛት ጉበት ዉስጥ የሚመረት ሲሆን ከቅባት ምግቦችም በተወሰነ መልኩ ልናገኘው እንችላለን።
ኮሌስትሮል የሰውነታችን ህዋሳት (cells) ስራቸውን በትክክል እንዲሰሩ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ይሁን እንጅ ደም ውስጥ ያለው የኮሌስትሮል መጠን መብዛት በዋነኛነት #ልብና_ደም_ስር በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል።
#የኮሌስትሮል_ጥቅሞች
1. የህዋሳት ሽፋንን (cell membrane) ለመገንባት
2. አስፈላጊ የሆኑ #ሆርሞኖች (ለምሳሌ ኮርቲሶል፣ ቴስቶስቲሮን፣ ፕሮጀስትሮን እና ኢስትሮጅን) እንዲመረቱ
3. ጉበት ውስጥ #ሐሞት እንዲሰራ
4. ለነርቭ ሕዋሳት ሥራ መቀላጠፍ
5. ቆዳችን ውስጥ #ቫይታሚን_ዲ እንዲዘጋጅ
#የቅባት_አይነቶችና_ትክክለኛ_መጠናቸው
ደማችን ውስጥ በዋናነት 4 የሚደርሱ የቅባት አይነቶች አሉ፡፡
1ኛው አጠቃላይ ኮሌስትሮል (#total_cholesterol) ይባላል፤ ይህም ከ200 mg/dL በታች እንዲሆን ይመከራል።
2ኛው ኤል.ዲ.ኤል. ኮሌስትሮል (#LDL_cholesterol) የሚባል ሲሆን ከ100 mg/dL በታች እንዲሆን ይመከራል፡፡ ነገር ግን አይነት 2 የስኳር በሽታ ያለበት ሰው እድሜው 40 ዓመት እና ከዛ በላይ ከሆነ፤ እንዲሁም የደም ስር በሽታ እንዳለ ከተረጋገጠ ከዚህም በታች ዝቅ እንዲል ይመከራል፡፡ ይህ የቅባት አይነት ለልብና ለአንጎል የደም ስር በሽታዎች ያጋልጣል። በዚህም ምክንያት መጥፎ ኮሌስትሮል (bad cholesterol) ይባላል።
3ኛው ኤች.ዲ.ኤል. ኮሌስትሮል (#HDL_cholesterol) ተብሎ ይጠራል። ከኤል.ዲ.ኤል. ኮሌስትሮል በተቃራኒ ይህ የቅባት አይነት ደም ውስጥ ከፍ እንዲል የሚፈለግ ሲሆን ለሴቶች ከ50 mg/dL በላይ እንዲሁም ለወንዶች ከ40 mg/dL በላይ እንዲሆን ይመከራል። የኤች.ዲ.ኤል. ኮሌስትሮል መጠን ከፍ ባለ ቁጥር ለልብ ደም ስር በሽታ እና ለስትሮክ የመጋለጥ ዕድል በተቃራኒው እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ ለዚህም ነው ይህ የኮሌስትሮል አይነት ጥሩ ኮሌስትሮል (good cholesterol) በመባል የሚታወቀው።
4ኛው ትራይግላይሰራይድ (#triglyceride) ይባላል። ይህ የቅባት አይነት ከ150 mg/dL በታች እንዲሆን የሚመከር ሲሆን ብቻውን ለደም ስር በሽታዎች የማጋለጥ እድሉ አነስተኛ ነው፡፡
#ስርጭት
በአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ #40_በመቶ የሚጠጉ አዋቂ ሰዎች በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ ኮሌስትሮል እንዳለባቸው ይገመታል። በየአመቱ ወደ 4.4 ሚሊዮን አካባቢ የሚጠጉ ሰዎች በከፍተኛ ኮሌስትሮል ምክንያት ለህልፈተ ህይወት ይዳረጋሉ። በኢትዮጵያ ሰፋ ያለ የቅርብ ጊዜ ጥናት ባይኖርም በ2015 (እ.ኤ.አ.) በ10,260 ሰዎች ላይ የተሰራ ጥናት 5.2% የሚሆኑት የኮሌስትሮል መዛባት እንዳለባቸው አሳይቷል።
#መነሻ_ምክንያቶች
መሻሻል ከሚችሉት መካከል አንዱ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ነው። ይህም ሲባል የእንስሳት ውጤቶችን፣ ጣፋች ምግቦችን እንዲሁም በፋብሪካ የሚመረቱ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብን ያጠቃልላል፡፡ ሳቹሬትድና ትራንስ ቅባቶች (#saturated እና #trans_fats) በተለየ ሁኔታ ለጤና አስጊ ሲሆኑ ቅቤ፣ አይብ፣ የፓልም ዘይት፣ የኮኮናት ዘይትና ማርጋሪን ይጠቀሳሉ። እንዲሁም እንቅስቀሴ አለማድረግ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል አብዝቶ መጠጣት ፣ የተዛማጅ በሽታዎች መኖር (ለምሳሌ፦ የደም ግፊት መብዛት፣ የስኳር በሽታ፣ የታይሮክሲን ሆርሞን ማነስ፣ የኩላሊት ስራ መስተጓጎልና የኤች አይ ቪ በሽታ) እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ወይም ቦርጭ ለኮሌስትሮል መጨመር ያጋልጣሉ፡፡
መሻሻል ከማይችሉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የመጥፎ ኮሌስትሮል መብዛት በዘር መከሰት (#familial_hypercholesterolemia) ሲሆን ያለእድሜ ለሚከሰት የልብ ደም ስር መዘጋትና እሱን ተከትሎ ለሚመጣ ድንገተኛ የልብ ጥቃት አንዱ ተጠቃሽ ምክንያት ነው። መሻሻል የማይችሉ ሌሎች ምክንያቶች የእድሜ መጨመር እና ጾታ ሲሆኑ፤ ሴቶች ካረጡ በኋላ የመጥፎ ኮሌስትሮል መጠናቸው ስለሚጨምር ለደም ስር በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ይላል።
#ምን_ያስከትላል?
በሂደት በሚመጣ የቅባታማና ፋይበር ንጥር ነገሮች ክምችትን ምክንያት የደም ስር ጥበት ሊያመጣ ይችላል። ይህም ልብ፣ አንጎል ወይም እግር ውስጥ የደም ስር በሽታ እንዲከሰት በማድረግ እስክ ህልፈተ ህይወት የሚያደርስ ጉዳት ለያስከትል ይችላል።
#እንዴት_ይታውቃል?
የኮሌስትሮል መብዛት በራሱ #ምልክት_አልባ ሲሆን ችግሩ እንዳለ የሚታውቅው ከላይ የተዘረዘሩት አጋላጭ ምክንያቶች በሚታዩ ወቅት የደም ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እድሜያችው ከ20 በላይ የሆኑ ሰዎች በ5 ዓመት ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የኮሌስትሮል ምርምራ እንዲያደርጉ ይመከራል። እድሜያችው ከ35 አመት በላይ የሆኑ ወንዶችና ከ45 አመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ 5 አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መመርመር ይኖርባቸዋል።
#የኮሌስትሮል_መብዛት_ህክምናና_መከላከያው
የኮሌስትሮል መጠን በአጋጣሚ ከፍተኛ ሆኖ መገኘት ብቻዉን አሳሳቢ ላይሆን ይችላል፤ ይህም ያለ መድሃኒት #የአኗኗር_ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ለተወሰኑ ወራት ሊታይ ይችላል።
የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ሲባል እንቅስቀሴ ማድረግ (በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ወይም በሳምንት ለ150 ደቂቃ)፣ ክብደትን መቆጣጠር፣ ቦርጭን ማጥፋት፣ አመጋገብን ማስተካከል (ስጋ፣ ቅቤና አይብ የመሳሰሉ የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦችን መቀነስ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ምግቦችን ማዝወተር እና ያልተፈተጉ እህሎችን መጠቀም) ያጠቃልላል፡፡ የምግብ ዘይትን በተመለከተ የእጽዋት (ለምሳሌ፦ የወይራ፣የሱፍ፣የአኩሪ አተር) ዘይቶችን እሳት ሳያበዙ መጠቀም ይመከራል። በተጨማሪም ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠጣትና ጭንቀትን ማርገብ ያስፈልጋል።
መጥፎ ኮሌስትሮል ከ190 mg/dL በላይ ከሆነ #መድሃኒት መጀመር የሚያስፈልግ ሲሆን፤በዘር የሚከሰትበት እድልም ስለሚኖር ቅርብ ቤተሰብን ማስመርመር ያስፈልጋል።
እንዲሁም አይነት 2 የስኳር በሽታ ካለ እና እድሜ 40 እና ከዛ በላይ ከሆነ፣ ለልብና ደም ስር በሽታዎች የመጋለጥ እድል ከፍተኛ ከሆነ ፤ እንዲሁም ልብ፣ አንጎል ወይም እግር ውስጥ የደም ስር በሽታ ከተከሰተ የኮሌስትሮል መጠን ከፍተኛ ባይሆን እንኳ የኮሌስትሮል ማውረጃ መድሃኒት እንዲጀመር በጥብቅ ይመከራል። ይህም ኮሌስትሮል ከማስተካከል ባሻገር ደም ስር ውስጥ የሚካሄደውን ብግነት (ቁጣ) ለማርገብ ይረዳል።
መድሃኒት ከተጀመረ በኋላ የኤል.ዲ.ኤል. ኮሌስትሮል (LDL-cholesterol) በታዘዘበት ምክንያት መሰረት ከ70 ወይም ከ55 mg/dL በታች መሆን ይኖርበታል። የኮሌስትሮል ማውረጃ መድሃኒት ለረጅም ጊዜ ወይም እድሜ ልክ የሚወሰድ ስለሆነ ያለሃኪም ትእዛዝ መቋረጥ የለበትም።
የኮሌስትሮል መብዛት መከላከያ መንገዶች ከላይ የተዘረዘሩትን አጋላጭ ምክንያቶች ማስወገድ ወይም መቆጣጠር ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው።

❤2
🩺 #በደም_ግፊት ዙሪያ የታተመ ጥናት ዳግም ምልከታ (Revisiting a Published Research on #Hypertension)
🫀 በአዲስ አበባ በተደረገ የአጋጣሚ የደም ግፊት ምርመራ ፕሮግራም ላይ ሳይታወቅ የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊትና ተያያዥ ምክንያቶች
የጥናቱ #ርዕስ፦
"Prevalence of newly diagnosed hypertension and its associated factors in an opportunistic screening program in Addis Ababa, Ethiopia"
ደራሲዎች (Authors)፦ Gashaw Solela, Balew Arega, Elias Tewabe, Rediet Ambachew, Samuel Kassahun, Seble Legese
ተጓዳኛ ደራሲ (Corresponding author)፦ Gashaw Solela - gashawsol@gmail.com
📌 #መግቢያ
• ከፍተኛ የደም ግፊት በዓለም ዙሪያ ከልብና ከደም ቧንቧ በሽታዎች ጋር ለተገናኙ የተለያዩ የጤና ችግሮችና ሞቶች ተቀዳሚ ምክንያት ነው።
• ብዙ ጊዜ ምልክት ስለሌለው በርካታ ሰዎች ላይ መኖሩ አይታወቅም።
• በአጋጣሚ የደም ግፊት ምርመራ ማድረግ ቀደም ብሎ ለመለየት አንደኛው ተግባራዊ መንገድ ነው።
🧪 #የጥናቱ_ዘዴዎች
• የጥናት አይነት: ተቋማዊ የአንድ ጊዜ ጥናት
• ቦታ: የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
• ጊዜ: ከኖቬምበር 2023 – ፌብሩዋሪ 2024 (እ.ኤ.አ.)
• ተሳታፊዎችና ብዛታቸው: 301 አዋቂዎች
• መረጃ ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ የዋለ መሳሪያ: WHO STEPS መጠይቅ እና መደበኛ የደም ግፊት መለኪያ
• ትንተና: ባለብዙ ተለዋዋጭ ሎጂስቲክ ሪግሬሽን
📊 #ዋና_ውጤት
• አዲስ የተገኘ (በፊት ያልታወቀ ወይም ያልነበረ) ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ብዛት 36.2 በመቶ ነበረ። ይህም ማለት በአማካኝ ከ3 ሰዎች 1 ሰው ቀደም ሲል ያልታወቀ ከፍተኛ የደም ግፊት ነበረው።
⚠️ #ተያያዥ_ምክንያቶች
👨 ወንድ መሆን (AOR 2.06): በ2 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
💍 ትዳር ያላቸው (AOR 4.8): በ5 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
⚰️ ባል ወይም ሚስት የሞተባቸው (AOR 5.14): በ5 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
🥗 ዝቅተኛ የፍራፍሬ እና የአትክልት አመጋገብ (AOR 2.22–2.88): ከ2 እስከ 3 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
🏃 የእንቅስቃሴ እጥረት (AOR 2.26): በ2 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
⚖️ የውፍረት ለቁመት ንፅፅር [Body Mass Index - BMI] (AOR 1.17 per kg/m²) መጨመር: በእያንዳንዱ 1 kg/m² መጨመር 17 በመቶ ከፍ ያለ እድል
🧠 #መደምደሚያ
• በጤና ተቋም ውስጥ በተደረገ የአጋጣሚ የደም ግፊት ምርመራ ቀድሞ ሳይታወቅ የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ብዙ እንደነበር ታይቷል። እንዲሁም አብዛኞቹ አጋላጭ ምክንያቶች መሻሻል የሚችሉ እንደሆኑ ጥናቱ አመላክቷል።
📌 #ዋና_መልዕክቶች
👉 ከ3 ሰዎች 1 ሰው ቀደም ሲል ያልታወቀ ከፍተኛ የደም ግፊት እንደነበረው ታይቷል።
👉 ከፍተኛ የደም ግፊት መኖሩን ለማወቅ መደበኛ ምርመራ እና የመከላከል እርምጃዎች መጠናከር አለባቸው።
ማጣቀሻ፦ Solela, G. et al. BMC Cardiovasc Disord 24, 492 (2024). https://doi.org/10.1186/s12872-024-04171-9

SpringerLink
Prevalence of newly diagnosed hypertension and its associated factors in an opportunistic screening program in Addis Ababa, Ethiopia:…
BMC Cardiovascular Disorders - Hypertension is a recognized risk factor that underlies the epidemic of cardiovascular diseases. Guidelines, including those from the European Society of...
❤2
🦠 የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ (Bundibugyo Ebola Virus Outbreak)
#ኢቦላ ምንድን ነው?
• በኢቦላ ቫይረስ የሚከሰት ለሰው ልጆች ህይወት አስጊ የሆነ ተላላፊ በሽታ ነው።
• መነሻው ፍራፍሬ የሚበሉ የሌሊት ወፎች (Fruit bats) ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚገመት ሲሆን ከእንስሳት ወደ ሰው ወይም ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
• በተበከለ የሰው አካል ፈሳሾች ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ የበሽታው ስርጭት ይጨምራል።
የኢቦላ ቫይረስ #ዝርያዎች ምን ምን ናቸው?
• ዛየር ቫይረስ
• ሱዳን ቫይረስ
• ቡንዲቡግዮ ቫይረስ
የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ በሽታ #ታሪክ እና #አሁናዊ መረጃ
• የቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ ከዚህ በፊት 2 ገዜ (በ2007 እ.ኤ.አ. በ ዩጋንዳ እና በ2012 እ.ኤ.አ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ) የተከሰተ ሲሆን በቫይረሱ ምክንያት የደረሰው የሞት ምጣኔ ከ30 እስከ 50% ነበር።
• በቅርቡ በ May 15፣ 2026 እ.ኤ.አ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ (DRC) በቡንዲቡግዮ (Bundibugio) ቫይረስ ዝርያ የሚመጣ የኢቦላ ቫይረስ በሽታ መከሰቱ ተረጋግጧል። በመቀጠልም በዩጋንዳም በሽታው መከሰቱ ተረጋግጧል።
• የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በ May 16 ፣ 2026 እ.ኤ.አ ባወጣው መግለጫ መሰረት የቡንዲቡግዮ ቫይረስ በሽታ የዓለም የጤና ስጋት እንደሆነ አውጇል።
#ምልክቶች
• ብዙውን ጊዜ ከ2–21 ቀን በኋላ ይታያሉ። ብዙ ሰዎች በሽታውን ማስተላለፍ የሚጀምሩት ምልክት ከታየባቸው በኋላ ነው።
በመጀመሪያ የሚታዩ ምልክቶች፦
√ በድንገት የሚጀምር ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት
√ ከፍተኛ የድካም ስሜት
√ ራስ ህመም
√ የጡንቻ ህመም
√ የጉሮሮ ህመም
√ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
በመቀጠል የሚታዩ ምልክቶች፦
√ ውሃማ ተቅማጥ
√ ማቅለሽለሽና ትውከት
√ የሆድ ህመም
√ የቆዳ ሽፍታ
√ ደም መፍሰስ (ሁሉም ሰው ላይ የማይታይ)
#እንዴት_ይተላለፋል?
• በቀጥታ ከደም፣ ከትውከት ፈሳሽ፣ ከምራቅ፣ ከሽንትና ከተቅማጥ ጋር የሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ
• ታካሚን ያለ መከላከያ መሳሪያዎች መንከባከብ
• በቫይረሱ የተበከሉ ዕቃዎችን መንካት
• በቫይረሱ የተበከሉ እንስሳት ወይም ጥሬ ስጋ ጋር መነካካት
• የቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ
• ከተበከለች እናት በጡት አማካኝነት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል።
⚠️ በአየር ወይም በትንፋሽ አይተላለፍም።
በሐኪም መታየት የሚያስፈልገው መቼ ነው?
• በኢቦላ ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ሲኖር
• ኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ተከሰተበት አካባቢ በባለፋት 3 ሳምንታት የጉዞ ታሪክ ካለ
• ለኢቦላ ከተጋለጡ በኋላ ትኩሳት ወይም ሌሎች አደገኛ ምልክቶች ከታዩ
#ህክምና
• የቡንዲቡግዮ ቫይረስ ለማጥፋት የሚረዳ መድሃኒት የለም። የሚሰጠው የድጋፍ ህክምና ብቻ ነው። ለምሳሌ፦
√ የኦክሲጅን ድጋፍ
√ በደም ስር የሚሰጥ ፈሳሽ
√ ምልክቶችን (ለምሳሌ፦ መድማትን) መቆጣጠር
• ለተወሰኑ የኢቦላ ቫይረስ ዝርያዎች (ለምሳሌ፦ ለዛየር ኢቦላ ቫይረስ) ክትባት ሲኖር፣ ለቡንዲቡግዮ ቫይረስ ግን ፍቃድ ያገኘ ክትባት እስካሁን የለም።
#የመከላከያ_መንገዶች
• ከተበከለ ፈሳሽ ጋር ንክኪን ማስወገድ
• ቶሎ ቶሎ እጅን መታጠብ
• ታማሚን ለሚንከባከቡ ሰዎች የመከላከያ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙ ማድረግ
• ጥንቃቄ የተሞላበት የቀብር ስርዓት አፈፃፀም
• ከዱር እንስሳት መራቅ
ይህ መረጃ ለጠቅላላ ግንዛቤ የሚውል ሲሆን በግለሰብ ደረጃ የሚሰጥን የሐኪም ውሳኔ ወይም ምክር አይተካም!

👍1
አዲስ የታተመ ጥናት 📄 (በBMC Cardiovascular Disorders መጽሔት፣ እ.ኤ.አ ኤፕሪል 11፣ 2026)፦ አጣዳፊ #የልብ_ደም_ስር በሽታ (Acute Coronary Syndrome [#ACS]) ላይ ያተኮረ ባለብዙ ማዕከል ጥናት (አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 🇪🇹)
የጥናቱ #ርዕስ፦
"Clinical profiles, management, and outcomes of acute coronary syndrome patients in hospitals without reperfusion therapy: a multicentre study in Addis Ababa, Ethiopia"
ደራሲዎች (Authors)፦
Begashaw Belay Abichu; Gashaw Solela; Samson Mulugeta; Nahom Addisu Bekele; Amanuel Zeleke; Roman Negewo; Chala Fekadu Oljira; Yidnekachew Asrat Birhan; Sintayehu Abebe MD; Dejuma Yadeta; Bekele Alemayehu
ተጓዳኝ ደራሲ (Corresponding author)፦ Gashaw Solela - gashawsol@gmail.com
የጥናቱ #መነሻ (Background):
• አጣዳፊ የልብ ደም ስር በሽታ (Acute coronary syndrome) የልብ ደም ስር መዘጋትን ወይም መጥበብን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ሞትን ጨምሮ የተለያዩ የአጭርና የረጅም ጊዜ መዘዞችን ያመጣል። በሽታው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ላይ የበለጠ ጓልቶ ይታያል።
• ይህ ጥናት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በሶስት ትላልቅ የመንግስት ሆስፒታሎች ውስጥ ለአጣዳፊ የደም ስር በሽታ የደም ፍሰትን በፍጥነት ወደነበረበት ለመመለስ የሚረዱ ህክምናዎች (Thrombolysis እና PCI) ያላገኙ ታካሚዎች ላይ የተሰራ ነበር።
• ጥናቱ የታካሚ የበሽታ ባህሪያት፣ የሆስፒታል ውስጥ ህክምና እና ውጤቶችን ለመገምገም ያለመ ነበር።
የጥናቱ #ዘዴዎች (Methods):
• በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሶስት ትላልቅ የመንግስት ሆስፒታሎች የተመረጡ አጣዳፊ የልብ ደም ስር በሽታ ያላቸው አዋቂ ታካሚዎች የተካተቱበት ጥናት ተካሂዷል።
• የጥናቱ መረጃዎች በ "SPSS" የተተነተኑ ሲሆን የባለ ብዙ ተለዋዋጭ ሪግሬሽን ትንተናን በመጠቀም ለሞት የዳረጉ ተያያዥ ምክንያቶችን ለመለየት ተችሏል።
የጥናቱ #ውጤቶች (Results):
• የጥናት መስፈርቱን ያሟሉ በ18 ወራት ውስጥ ለአጣዳፊ የልብ ደም ስር በሽታ ተኝተው የታከሙ 154 ህሙማን ተካተዋል።
• የታካሚዎች አማካይ ዕድሜ 58.4 ዓመት ሲሆን 63.6 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ነበሩ።
• ምልክት ከታየ ጀምሮ ሆስፒታል ለመድረስ የወሰደው አማካኝ ጊዜ 24 ሰዓት እንደነበር ታውቋል። ይህም ከበሽታው አንፃር ሲታይ በጣም መዘግየት እንዳለ ታይቷል።
• የተለመዱ ምልክቶች ደረት ህመም (87.7 በመቶ የታየ) እና ትንፋሽ ማጠር (50.6 በመቶ የታየ) ነበሩ።
• ከፍተኛ ደም ግፊት (Hypertension) 55.2 በመቶ በሚሆኑት እና የስኳር በሽታ ደግሞ 44.2 በመቶ በሚሆኑት ላይ ታይተዋል።
• አብዛኞቹ ታካሚዎች ማለትም 98.7 በመቶ ሁለት ዓይነት ፀረፕሌትሌት መድሃኒት ("Aspirin" እና "clopidogrel") ፣ 94.8 በመቶ የሚሆኑት የኮሌስትሮል ማስተካከያ (statins) እና 90.3 በመቶ የሚሆኑት ደም እንዳይረጋ የሚያደርግ ህክምና (anticoagulation) እንዲወስዱ ተደርጓል።
• የሆስፒታል ውስጥ ሞት 26.6 በመቶ (ከፍተኛ) የነበረ ሲሆን አማካይ የሆስፒታል ቆይታ ደግሞ 8 ቀን ነበር።
• የምት ምጣኔን የጨመሩ ምክንያቶች የእድሜ መጨመር (4 በመቶ)፣ ሴት መሆን (በ4 እጥፍ)፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ (18 በመቶ) እና ዝቅተኛ የሲስቶሊክ ደም ግፊት (3 በመቶ) ነበሩ።
የጥናቱ #ምክሮች (Recommendations):
• ታካሚ ሃኪም ቤት እንደመጣ የበሽታውን አደገኛነት ለመለየት ወሳኝ ምልክቶች (vital signs) ላይ ትኩረት ማድረግና እርምጃ መውሰድ፣ የልብ ደም ስር ውስጥ የረጋን ደም የሚበጣጥሱ መድሃኒቶችን (Thrombolytics) አቅርቦት ማስተካከል፣ በረጅም ጊዜ እቅድ የልብ ደም ስርን በቀጫጭን ቱቦዎች የመክፈት ህክምናን (Percutaneous coronary intervention [PCI]) ማስፋፋት፣ ስለ አጣዳፊ የልብ ደም ስር በሽታ የቅድመ ሆስፒታል ትምህርት ማጠናከር እና የጤና ማዕከላትን ዘመናዊና ወጥነት ያለው የታካሚ እንክብካቤና ቅብብሎሽን መተግበር የተሻለ ውጤት ለማግኘት ወሳኝ ናቸው።
ማጣቀሻ: https://link.springer.com/article/10.1186/s12872-026-05850-5
#አጣዳፊየልብደምስርበሽታ #Acutecoronarysyndrome #የልብደምስርውስጥየረጋደምመበተን
#Thrombolysis
#የተዘጋየልብደምስርመክፈት
#Percutaneouscoronaryintervention (#PCI)
#አዲስአበባጤናቢሮ #AAHB
#ጤናጥበቃሚኒስቴር #MoH
#ኢትዮጵያ #Ethiopia

Clinical profiles, management, and outcomes of acute coronary syndrome patients in hospitals without reperfusion therapy: a multicentre…
BMC Cardiovascular Disorders - Acute coronary syndrome (ACS) is a leading cause of morbidity and mortality worldwide, disproportionately affecting low- and middle-income countries. Although ACS has...
👍2
🔴 በጤና እና በጥንካሬ ረጅም እድሜ የመኖር ሚስጥሮች!
ረጅም ዕድሜን የመኖር ሚስጥር ማለት አስማታዊ መፍትሄ ማግኘት ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በየቀኑ የሰውነት/አዕምሮ ጤና እና ጥንካሬን የሚጠብቁ ትናንሽ ልምዶችን ማዳበር ማለት ነው
🥗 ጤናማ አመጋገብ እና የሰውነት ክብደት
• ላልተቀነባበሩ የተፈጥሮ ምግቦች ቅድሚያ ይስጡ! አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ ሙሉ እህሎች፣ ጤናማ ስቦች (ለውዝ፣ አቮካዶ ...) እና ከእፅዋት የሚገኙ ፕሮቲኖች ላይ ትኩረት ያድርጉ
• የተቀነባበሩ ምግቦችና ስኳርን ይቀንሱ እንዲሁም ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖርዎ ያድርጉ
🏃♂️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
• እንደ ፑሻፕ፣ ክብደት ማንሳት አይነት የጥንካሬ ስፖርቶችን መስራት የጡንቻ መመናመንና የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል
• ፈጣን መራመድ እና ሳይክል መንዳት የመሳሰሉ የትንፋሽና ካርዲዮ እንቅስቃሴዎች ለልብና አዕምሮ ጤንነት ጠቃሚ ናቸው
• የማሳሳብ እና የፍሌክሰቢሊቲ እንቅስቃሴዎች ደግሞ ለመገጣጠሚያዎች ጤንነትና የሰውነት ቅልጥፍናን ለማስጠበቅ ይረዱናል
💤 ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት እና ጭንቀትን መቆጣጠር
• በአማካይ ከ7-9 ሰዐት ጥራት ያለው እንቅልፍ ያግኙ፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዐት መተኛትና መነሳትን ልምድ ያድርጉ
• ስር የሰደደ ጭንቀትን በጥሩ ማህበራዊ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ በአካል እንቅስቃሴ፣ ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ በማሳለፍ በመሳሰሉት መቆጣጠር ያስፈልጋል
👥 ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከርና የህይወት አላማ መኖር
• ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች ወይም ከማህበረሰብ ጋር ጥብቅ ግንኙነት መኖር ለረጅም ዕድሜ ትልቅ ሚና አለው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብቸኝነት ለጤና አደገኛ ነው
• ጠንካራ የህይወት ዓላማ መኖር አእምሮን ንቁ ያደርጋል፣ ጭንቀትን ይቀንሳል እንዲሁም በጤና ረጅም እድሜ ለመኖር አስተዋፅኦ አለው
🚫 ቅድመ ጥንቃቄዎች እና ክትትሎች
• ማጨስን ያቁሙ እና የአልኮል መጠጥን ይቀንሱ
• የሕክምና ምርመራዎችን ያድርጉ! የደም ግፊትን፣ ኮሌስትሮልን እና የደም ስኳርን በየጊዜው መመርመር በሰውነት ክፍሎችዎ ላይ ዘላቂ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ችግሮችን አስቀድሞ ለማወቅና ለመቆጣጠር ይረዳል
በጥንቃቄ ጤናን እየጠበቁ ረጅም ዕድሜ መኖር ወይስ የፈለጋቹትን እየበላችሁ እና እያደረጋችሁ አጭር ዕድሜ መኖር? የቱን ይመርጣሉ❓❔

🧠 የስትሮክ (Stroke) ምልክቶችን ይወቁ – BE FAST
B – ሚዛንን አለመጠበቅ (Balance Loss)
E – የእይታ ችግር (Eye/Vision Changes)
F – የፊት መጣመም (Face Drooping)
A – የክንድ ወይም የእግር ድካም (Arm or Leg Weakness)
S – የንግግር ችግር (Speech Difficulty)
T – ጊዜ አታባክኑ (Time): እነዚህ ምልክቶች በድንገት ከታዩ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ይሂዱ ወይም የአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት ይጥሩ።
ዋና መልእክት፦
• ስትሮክ አስቸኳይ ሕክምና የሚፈልግ ድንገተኛ የጤና እክል ነው! በፍጥነት የሚደረግ ሕክምና የአንጎል ጉዳትን ሊቀንስ እና ሕይወትን ሊያድን ይችላል።

❤️ ለጤናማ ልብና ሰውነት ተፈጥሯዊ መርህ፦ ልባችን ለመምታት፣ ሰውነታችን ደግሞ ለመንቀሳቀስ ተፈጥረዋል።🚶
🏃 የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሳምንት ቢያንስ ለ 150 ደቂቃ ወይም በቀን ለ 22 ደቂቃ መጠነኛ አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ይመክራል።
🌿 ይሁን እንጅ ለጤናማ ህይወት የግድ ከባድ ስፖርት መስራት አያስፈልግም። የጓሮ አትክልትን የመንከባከብ ሥራ፣ አጭር የእግር መንገድ ወይም ደረጃ መውጣትን የመሳሰሉ ቀላል እንቅስቃሴዎች ለጤናችን ትልቅ ጥቅም አላቸው።
❤️ ማንኛውም አካላዊ እንቅስቃሴ የማይተላለፉ በሽታዎችን፣ ካንሰርን፣ የልብና የደም ሥር በሽታዎችን ለመከላከል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል።
✨ ትናንሽ እርምጃዎች ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ፤ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ዋጋ አለው!
Source: https://bit.ly/4oCubNH