እትዮ መጽሐፍት መደብር
118 subscribers
39 photos
1 video
10 files
4 links
ማንኛውንም መጽሐፍት እዚህ ግሩፕ ላይ መለቀቅ ይቻላል ።
በእውቀት አዕምሮ ማዳበር ብልጠት ነው ።
ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋል ።
Download Telegram
በሙከራ ብዛት ቻርጅ ከሚያልቅብኝ
በተሞሉ ካርዶች ጊዜ ከሚየልፍብኝ
እባክህ አምላኬ ያልተፋቀ ስጠኝ

አሜን!!!!!
😀😂😂😂😂
የብዙሀንን አዳፋ...
በንፁህ ነፍሴ ላይ የዘሩ
ጨለማው የሸሸጋቸው..
በሰው ፊት የተከበሩ
የተኙኝ ብዙ ነበሩ

.
.
ግራ እና ቀኙን አማክሮ
እንደ ዳኛ ወግ ለወትሮ
ትወገር ትዳን የሚል ቃል
መሀል ፈራጁ እሱ ያውቃል
.
.
.
ደማቅ ምሽቴን ሊጋሩ
ሰረገላዬን ሊያሰግሩ
የተኙኝ ሹሞች በኔ እርቃን
ምነዋ አብሮ እንዳልነቃን?!

.
.
ከከሳሾቼ አንዳችሁ
ሀጥያት የሌለባችሁ
ውገሯት ቢል በቃሉ
ምነው አንድም አትሉ??
#እየነገርኩሽ_ነው 🤔
መሄድ ቻልኩ ብለሽ እንዲሁ አትጓዢ
ወስኝ መድረሻሽን በቂ ስንቅም ያዢ
ደርሰሽ ስትገሰግሽ እግርሽ ወዳመራሽ
እንደኔ መሽቶብሽ ጠፍቶሽ መመለሻሽ
ከኔነትሽ ጋራ ጠብ እንዳትገጥሚ
አስቢ ቆም ብለሽ
ከራስሽ ጋር አውሪ •• የውስጥሽን ስሚ
የማታፈቅርህ ሴት ባህሪያት (ባጣቆየኝ ያደረገችህ)።
በፍቅር ይበልጣል


1ኛ አትቀርብ/አታስቀርብም: እሷ የአንተን ቤተሰብ እና ጓደኞች መቅረብ መተዋወቅ አትፈልግም እንዲሁም የእሷንም ጓደኞች ቤተሰብ አታስተዋውቅም። እኛ ሴቶች ከልብ ስናፈቅር ለመተዋወቅ ጉጉት ስላለን መቼ ነው የምታስተዋውቀኝ እያለን እንጨቀጭቃለን እንጂ አንሸሽም።

2ኛ አትሰማህም: አንተ የነገርካትን ባህሪያት እዬን ተይ፣ ይሄ አያስፈልግም ያልካትን ነገሮች አትተውም ታረገዋለች አትሰማህም። የአንተ ሃሳብ እሷ ጋር ቦታ የለውም። የምታፈቅርህ ሴት ከሆነች በተቻለ መጥን ባህሪዎቿን በመተው አንተን ለማስደሰት ትሞክራለች።

3ኛ ለራሷ ብቻ ነው የምታስበው: ገንዘብ ስታገኝ ለራሷ ነው፣ ስጦታ ሰጥታክ አታውቅም፣ ልጋብዝ ብላ አታውቅም፣ የኢትዮጵያ ሴቶች እዚህ ጋር ችግር አለብን ሁለታችሁም ደሞዝተኛ ናችሁ ለምንድነው ሁሌ ወንዱ የሚጋብዘው? ምናለበት የሆነ ቦታ ወስደሽ ብትጋብዢው ለምን ሁሌ ከወንድ መጠበቅ። ወሲብ ላይም ለራሷ የሚመቻትን ነው ማድረግ የምትፈልገው የአንተ ስሜት እሷ ጋር ቦታ የለውም።

4ኛ አታማህርም: ቢዝነስ ለመጀመር ስራ ለመቀየር፣ የቤተሰብ ጉዳይ ካለ አንተን አታማክርህም። የምታፈቅርህ ሴት ሁለ ነገሯን ዘርዝራ ነው የምትነግርህ።

5ኛ ከእኛ ይልቅ እኔ ማለት ታበዛለች: ትልቅ ራዕይ ከአንተ ጋር ካሰበች እኛ እያለች ነው የወደፊት እቅዶቿን የምትነግርህ የማታፈቅርህ ከሆነች ግን እኔ እንደዚህ ሆኜ እኔ እኔ እኔ ብቻ ነው ንግግሮቿ።

6ኛ ሁሌ ካንተ ጠባቂ ናት: ደዋይ አንተ ነህ፣ ጋባዥ አንተ ነህ፣ ቴክስት አድራጊው አንተ ነህ አንዳንድ ሴቶች ለመኩራት ነው ይገባኛል ግን እስከ መቼ? ስድስት ወር አብራችሁ ቆይታችሁ አመትም ቆይታችሁ እንድኮራበት ብለሽ ስልክ የማትደውይ፣ ቴክስት የማታደርጊ ሴት አይሰለቸውም እሱስ አንድ ቀን እኮ የምትንከባከበው ሴት ካገኘ ልቡ ሊሸፍት ይችላል ስለዚህ እንደዚህ ባንሆን። ስለዚህ ሁሌ ከአንተ የምትጠብቅ ሴት አትወድህም።

7ኛ ውሸታም ናት: ስለ እሷ እንድታውቅ ስለማትፈልግ አትነግርህም እውነቱን።

8ኛ ይቅርታ ሞቷ ነው: ሴት ልጅ የምታፈቅርህ ከሆነ ላለማጣት ይቅርታ ትጠይቃለች። የምታወድህ ሴት እራሷ በድላ ሁላ አንተን ነው የምትወቅሰው። እራሱ በድሎ እራሱ አለቀሰ እንደሚባለው ዘፈን ነው።

በጣም ብዙ ምልክቶች አሉ እነዚህ ዋነኞቹ ናቸው። ወንዶች እነዚህ ምልክቶች ካያችሁ እንድታስተካከል ነገሯት የማይስተካከል ከሆነ ጊዜያችሁን አታጥፉ በጣም ብዙ እውነተኛ ሴት፣ ንፁ ፍቅር የምትፈልግ ሴት አለች ጊዜችሁን አታባክኑ።
ካፈቀሩ ወዲያ ምን ያደባበብቃል
ወዶ ሟች መሆኔን ሃገር ሁሉ ያውቃል
አውላላው ሜዳ ላይ ሸራ የገጨውሽ
ብዬ ነው
አይቶ ይቁረጥለት ያ የድሮው ወዳጅሽ
የማይግሬን እራስ ምታትን መረዳት


 ማይግሬን በተደጋጋሚ የሚከሰት በአይነቱ  ውስብስብ የራስ ምታት ህመም ነው:: በሽታው የሚከሰተው በተለያዩ ምክንያቶች በሚመጣ የነርቭ ስርአት መዛባት ነው::

 የማይግሬን የራስ ህመም አብዛኛውን ጊዜ ከፍሎ እራስን በአንድጎን የሚያም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ እራስ ምታቱ ከመከሰቱ በፊት ከእይታ ወይም ከስሜት ህዋሳት ጋር የተያያዙ ጠቋሚ የሆኑ ምልክቶች (Aura) ሲኖሩት እነዚህ ምልክቶች በራስ ምታቱ ወቅት ወይም ከራስ ምታቱ በኋላ ሉከሰቱም ይችላሉ::

80 በመቶ ማይግሬን በሴቶች ዘንድ የሚታይ ቢሆንም ወንዶች ላይ በሽታውን ማየት ያልተለመደ አይደለም:: በተጨማሪም የማይግሬን እራስምታት በዘር መተላለፍ የሚችል የበሽታ አይነት ነው፡፡

 

የተለመዱ የማይግሬን ምልክቶች

የሚወጋ (Throbing ) አልያም ትርትር የሚል (Pulsatile) በእንቅስቃሴ ጊዜ ወይም ከአካላዊ እንቅስቃሴ በኋላ መጠኑ የሚጨምር ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የራስ ህመም

 ውስን ቦታ ላይ ያለ ብዙ ጊዜ በአንድ ጎን የሚከሰት በአይን እና በግንባር አካባቢ ያለ ህመም

 ህመሙ ቀስ በቀስ ከ1-2 ሰአት ውስጥ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን እራስ ምታቱ ከ4 ሰአት እስከ 3 ቀን ሊቆይ ይችላል::

 ማቅለሽለሽ ከመቶ ታማሚዎች መሀል ሰማኒያዎቹ ላይ ይኖራል::

 ማስታወክ ከመቶ ታማሚዎች መሀል ሀምሳዎቹ ላይ ይታያል::

 በብርሃን እና በድምጽ መረበሽ (Sensitivity to light and sound)

አንድ ሰው ማይግሬን አለበት እንዲባል ከሚከተሉት ምልክቶች ቢያንስ 2 ሊኖረው ይገባል::

1. በአንድ ጎን የሚከሰት እራስ ምታት

2. ትር ትር የሚል እራስ ምታት

3. ህመሙ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ

4. በእንቅስቃሴ የሚባባስ ወይም ህመምተኛውን ከመደበኛ እንቅስቃሴ ያስተጓጎለ::

በተጨማሪም ታማሚው በህመሙ ወቅት ወይ ወደላይ ማለት/ማስታወክ አልያም በድምፅ/በብርሃን መረበሽ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን እነዚህ ምልክቶች በሌላ በሽታ የመጡ መሆን የለባቸውም::

 

የማይግሬን ራስ ምታት እንዴት ይታከማል?

 የዚህ ህመም ተጠቂ ህመሙን የሚቀስቅስበት ምን ሁኔታ ወይም ነገር እንደሆነ ለይቶ በማወቅ ቀስቃሹን ነገር ወይም ሁኔታ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡

READ  Breast Self Examination (ጡትን እራስን በራስ መመርመሪያ መንገድ)

 የማይግሬንን የራስምታትን የሚቀሰቅሱ የሚከተሉትን ይመስላሉ የሚከተሉት ናቸው::

1. ጭንቀት

2. የእንቅልፍ መዛባት

3. ፆም

4. አብረቅራቂ ነገሮችን መመልከት

5. አንዳንድ ሽታዎች

6. የሲጋራ ጭስ

7. አልኮል መውሰድ- በዋነኝነት ወይን እና ቢራ

8. ካፌን ያላቸው ምግቦች እንደቸኮሌት፣ ቡና ወዘተ…

 ህመሙን የሚቀሰቅሱብንን ነገሮች አውቆ ማስወገድ ህመሙ አስቀድሞ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

 መጠነኛ እና መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የህመሙን መጠን ያወርደዋል::

 ዮጋ እና አንዳንድ ሌሎች ዘና የማያ ዘዴዎች(Relaxation Techniques)

 በቂ ውሃ መጠጣት – አንድ ጥናት እንዳሳየው በቀን ውስጥ የሚጠጡትን የውሃ መጠን በ1.5 ሊትር መጨመር ማይግሬን የእራስ ምታቱን መጠን እና ድግግሞሽ ይቀንሰዋል::

 የማይግሬን የራስምታትን ለማከም፣ እንደ የራስምታቱ ክብደት የተለያዩ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ ቀለል ላለ የ የማይግሬን ራስምታት፣ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ እንደ ፓራሲታሞል፣ አስፕሪን መውሰድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከላይባሉት መንገዶች በሽታውን መቆጣጠር ካልተቻለ ወደሀኪም ጋር በመሄድ መታየት ያስፈልጋል::
እንጨት ተቀምጦ ድንጋዩ ይነዳል፤
ፌርሙዝ በረዶ ይዞ ፍሪጅ ውሃ ያፈላል።

ወፍ እግረኛ ሆና ፍየሏ በረረች፤
በሬዎች እያሉ ዶሮ ለእርሻ ወጣች።

ምርጥ ዘር ፈልገን ምርጥ ዘር ልንዘራ፤
ዘር ከወዴት ይምጣ ዘር እየተበላ?

ዘመኑ ክፉ ነው ጊዜው ተቀይሯል፤
ፖሊሱን ሌባ አስሮት ቅል ድንጋይ ይሰብራል፤

ነፍሰ ገዳይ ሁሉ የነፍስ አባት ሆኖ፤
እንዴት ይጸደቃል ጻድቅ ተኮንኖ?

ጥንቸል ስትቀደም ዔሊ በጣም ሮጣ፤
መጠባበቅ ቀርቶ መቀዳደም መጣ።

ልንጀምር ስንል መንፈሳዊ ጉዞ፤
ሹፌር ወንበር ያጣል በተሳፋሪዎች ወንበሩ ተይዞ።

እውነት ከቦታዋ በግፍ ተፈናቅላ፤
ሀሰት ቁጭ ብላለች ካርታና ፕላኗን መብቷን አስከብራ።

እግር ከላይ ወጥቶ እራስ እያከከ፤
እጅ ግን ከእራስ ጋር በጣም ተራራቀ።

በሬዎች ወደዚህ ገበሬው ወደዛ፤
ምንም ላይታረስ መፋጠጡ በዛ።

ማር እየመረረ ሬት እየጣፈጠ፤
ምላስ ግራ ገባው እንዴት ነው ነገሩ ተገለባበጠ?

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
መ/ገ/ቆ/ አባ ወ/ገብርኤል አበበ
24/10/2013 ዓ.ም
ከሕይወት ተራራ ላይ
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
Bakka garaa kee geessee?

Ani amaluma kooti
Homaadhaafuu hin jarjaruu
Qormaata bara rakkootiif
Karoora koo hin jijjiiruu
Waanan godhe tokkittif
Wannin gaabbuf hin jiru!

Nan beeka karoora kee
Karoora bara dhibaa
Maafan jiruu koo hiikee
Waan hin taneef dadhaba?
Fedha koo siif ibsuufuu
Yeroo gabaabduun qaba

Hammamuu yoo gaabbite
Gatii kee gaara keessee
Meeqaatama darbitee
Gabaa qarqara teessee
Kan qophaahetu si bitee?
Qaamaaf qalbii koo hunda
Jaalala kee itti guuttee
Akkuma sangaa fardaa
Dhaabitti na gurgurtee
Eega gaaf saniin booda
Na dhiistee narraa gorte

Icciitiin dhoksee baadhuu
Sirra kaawwadheen ture
Humnaa ol si jaaladhus
Amma anis abdii mure!
Waaqayyoof haagalatuu
kunoo jira nu lachuu
Namni lama hin dhalatuu
Siif haakennu gammachuu
Kan narra ati jaalatu
Uumankee siif haatolchuu!

Irimmixooyuu nyaatanii
Dhukkubarraa ni fayyuu
Gaafii fedhe baatanii
Yoo bubbulan hin wayyuu?

GALAA DOOCCOO

✍ Dilgaasaa Dirribsaa
ሰው ሲሰራ አትስራና
አስደገሙብኝ በል ስትዞር ዋልና!!
የመኪና ላይ ጥቅስን ፎቶ ማንሳት ይመቸኛል!!
ብርዱ አኮራምቶ ሳያረገኝ ፍንግል፣
ያን ትኩስ ዳቦሽን ላኪልኝ ባገልግል!
📌 አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት!

((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))

በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣

አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡

✨አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፡፡

✨ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው!!

✨አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡

✨በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡

✨ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፡፡

✨ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ

👉እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል፡፡

👉በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም፡፡

👉የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥ የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው፡፡

👉ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፡፡

👉ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፡፡

…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል

👉አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ፣

❣እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፡፡ ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ፡፡

5ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …

☝ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፡፡ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፡፡

☝ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ፡፡

☝የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፡፡

☝"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፡፡

☝ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፡፡

☝በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ፡፡

Via: Dr Beza
Yoo ati na jaalattee

Yoo ati na jaalattee,
Dhugaan na amate,
Garaa kee natti himte,
Miiltoosaanii koo siin jedheen
Fedhii koo siif ibsa.
Anis si abdadheen
Karoora koo cimsa.

Waliin karoorfannee
Jireenya ijaarranna
Rakkina injifannee
Guddinaaf xaarranna
Qilleensi nuu hin raasuu
Humna waliif taana
Homtuu nu hin deebisuu
Galma milkii dhaqna

Situ yaadaan na gorsa
Humnaa ol hin xaaru
Si abdadheen obsa
Jechaa Ormaaf hin aaruu

Yoo ati kiyyaa taatee,
Lafattan ulfaadha
Gammachuun giutameen
Namummaa gonfadha
Akka callee teetiin
Mormaati sii hidheen
Lapheerra kaawwadhee
Jaalalaan si baadha
Urgaa kee uladheen
Nadhii kees unadha!

Yoo ati naa jaalatte
Abdii guddaatu jira
Muuxannoon kiyyaaf kee
Dhaloota jijjiira
Yaadannoo galmeesseen
Nama hundaaf hira!
Barri Fidee

Barri fidee kafana
Huccuu haguugduu dhaqnaa
Kan saala ittiin dhokfannee
Uffannee baanu manaa

Huccuu kaayyoo hanqatte
Dhaqnatti nama hin ulfaatu
Nutti haa himtu ishiin godhatte
Akkamitti akka uffattu
Akkamitti akka of amantee
Ganama abdattee baatu
Akkamitti nama jidduus ooltee
Akka deebitee galtu.

Barri fideen midhaani
Sanyii baargamaa dhufu
Tokkicha facaasanii
Kan lammata axhiin hafu

Biqilli tokko ol baanaan
Raamoo torbatu dhalata
Sanyii namni alaa bitu
Raamoo tola dabalata
Qoricha raammicha ajjeesuu
Baargamatti oomishama
Yookaan sanyii facaasan
Odoo hin daraariin shama.

Barri fideen jireenya
karoora ormi baase
Shira diina fageenya
Duula alagaan bobbaase
Aadaa uummataa gatee
Kan safuu wallaalchisu
Akka namni of dagatee
Alagaa of dhaalchisu

Barri fideen qalbiidha
Gaangee luugama hin qabne
Humna meeqan harkisnee
Mataa qabuu dadhabne!
የማይግሬን ራስ ምታት

ማይግሬን ከከፍተኛ ራስ ምታት የበለጠ ነው። ይህ የነርቭ በሽታ ለቀናት በአልጋ ላይ ሊያውልዎት የሚችል የሚያዳክም የሚረብሽ ህመም ነው! ማይግሬን ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ እና ብርሃን መጥላትን ይኖራቸዋል። ህመሙ ለሰዓታት ወይም ለቀናት ሊቆይ ይችላል።

የማይግሬን ምልክቶች

የማይግሬን ዋና ምልክት ራስ ምታት ነው። ህመሙ በአንድ ጎን ጀምሮ ወደ ሌላው ሊዞር ይችላል ፣ ወይም የፊትለፊት የግንባር ህመም ፣ የጭንቅላትህ ጀርባ ላይ ህመም ሊኖር ይችላል ወይም የሙሉ ጭንቅላትን ህመም ሊኖር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ዓይናቸውን ወይም ዓይናቸው አካባቢ ህመም ይሰማቸዋል፡፡

ሌሎች የማይግሬን ራስ ምታት ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

🔺 ለብርሃን ፣ ጫጫታ እና ሽታዎች ስሜታዊነት።
🔺 ማጥወልወል ፣ ማስመለስ እና የሆድ ህመም።
🔺 የምግብ ፍላጎት ማጣት.
🔺 የሰውነት ሙቀት መሰማት(ላብ) ወይም ቅዝቃዜ (ብርድ ብርድ ማለት) ።
🔺 የቆዳ መገርጣ
🔺 የድካም ስሜት
🔺 መፍዘዝ
🔺 ተቅማጥ (አልፎ አልፎ)።
🔺 ትኩሳት (አልፎ አልፎ)።
🔺 ማይግሬን ለአራት ሰዓታት ያህል ሊቆይ ይችለል ሆኖም ግን ከባድ ማይግሪን በጣም ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል።

ህመሙ ሊጀምር ሲል ያሉ ምልክቶች

🔺 ትኩረት ለማድረግ መቸገር
🔺 ከወትሮ በተለየ መነጫነጭ ወይም ድባቴ
🔺 ለማውራትም ሆነ ለማንበብ መቸገር
🔺 እንቅልፍ ማጣት እና በተደጋጋሚ ማዛጋት
🔺 ማጥወልወል
🔺 ድካም
🔺 የምግብ አምሮት
🔺 የጡንቻ ህመም

Aura symptoms (ለትንሽ ጊዜ የሚቆይ የስሜት ህዋሳት መዛባት)

🔺 ለሰው የማይሰማ ድምጽ መስማት ወይም ለሰው የማይሸት ሽታ መሽተት
🔺 ጆሮ መጮህ
🔺 ሰውነትን መደንዘዝ እና መንዘር
🔺 የእይታ መዛባት
🔺 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እይታ ማጣት
🔺 በአንድ በኩል የሰውነት መድከም

የእራስ ምታት ምልክቶች

🔺 የአንገት ህመም እና መጨምደድ
🔺 ድባቴ እና ስጋት
🔺 ድምጽ ፣ሽታ እና ብርሃን አለመቻል ወይም መጥላት
🔺 የአፍንጫ መታፈን
🔺 እንቅልፍ ማጣት
🔺 ማጥወልወል እና ማስመለስ

ከህመሙ በሆላ የሚኖሩ ነገሮች

🔺 የስሜት ዝቅ ማለት (የድባቴ ስሜት)
🔺 ድካም

ማይግሪንን የሚያስነሱ ነገሮች

🔺 ጭንቀት
🔺 ምግብ ባግባቡ አለመመገብ ወይም ርሃብ
🔺 አንዳንድ የምግብ አይነቶች እነዚህም የስንዴ ዳቦ ቸኮሌት
🔺 የአልኮል መጠጦች
🔺 የወር አበባ
🔺 ድካም ከልክ በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
🔺 ብርሃን የቴሌቭዝን ወይም የኮምፒውተር እና የፀሃይ ጨረር
🔺 በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ

አጋላጭ ሁኔታዎች

🔺 ይህ አይነት ችግር ቤተሰብ ውስጥ ካለ በዘር የመተላለፍ እድል አው
🔺 ጾታ ብዙውን ጊዜ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ የመጋለጥ እድል አላቸው
🔺 እድሜ 15-55 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች
🔺 ሲጋራ ማጨስ

የቤት ውስጥ መድሃኒቶች

🔺 በጨለማ ፣ ጸጥ ባለ ፣ በቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ ማረፍ።
🔺 በግንባርዎ ወይም በአንገትዎ ጀርባ ላይ ቀዝቃዛ ነገር ወይም በረዶ መያዝ ህመሙ ሲኖር። (አንዳንድ ሰዎች ሙቀትን ይመርጣሉ ስለዚህ ለብ ያለ ውሃ መያዝም ይችላሉ።)
🔺 የራስ ቆዳዎን ማሸት።
🔺 ዮጋ
🔺 በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እራስዎን መጠበቅ።

መፍትሄዎች

🔺 ቤት ውስጥ ለማከም መሞከር
🔺 የሚያስነሳቦት ነገር ማስወገድ
🔺 ይህን አድርገው ካልተሻለዎት ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ
#ይብላኝ_እንጂ_ላንተ 🚶‍♀
#በስደት_ላይ_የተከሰተ_እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ ✍
ድንገት ባጋጣሚ በቅፅበት ትውውቅ
በጋራ ቋጠርን  የአብሮነትን ስንቅ 
ትኩሱ  ፋቅራችን  ያስቀና  እንደነበር 
  ዛሬም ትዝ  ይለኛል የነበረን ነገር 
ታዲያ ያንን ጊዜ  አመልህ ጨዋታህ 
ቅን አስተሳሰብህ  እርጋታና  ለዛህ
ማረከና  ሳበኝ  ውስጤን  ተቆጣጥሮ 
ልቤም  ለሂዎቱ  ተመኜህ  አምርሮ 
በቃ አመንኩህ ወዲያው አይቼ እንደራሴ
አብልጨም ወደድኩህ ደስ አለው መንፈሴ
  ከዛማ  ምን  አለ  ሀሳቤም ስራዬም
አንተው  ሁነህ አረፍክ  በውሎም ባዳሬም
      የብቻ   ሂዎቴ  ያንጊዜ  ተቀርፎ
      ባንድ መደብ ተኛ ጎኔ ጎንህ አርፎ
   ባልና ሚስት ሆንን ጎጆም መሰረትን
   በሰው ሀገር ሁነን ትዳርን "ሀ"  አልን 
አዎ አስታውሳለሁኝ ዛሬም እንደትናንት
ያኔ  ያለፍኩትን   የኖርኩትን  ጊዚያት
  ጎጇችን እንዲደምቅ ነገንም አልሜ  
  ስላንተ  ለመኖር  ከራሴ አስቀድሜ
ለኔው ቃል ገብቼ  ልሆንህ እመቤት
   ወረት የማያውቃት ሁኜልህ  አመቤት
    ለደስታህ ልለፍ ቃል ገባሁ ያን ሰአት
  ታስታውስው የለ •••• 🤔
ልጅ  እፈልጋለሁ  ውለጅልኝ  ስትል
ሰው ሀገር መሆኔ  ሳይለኝንኳ ውል
የምኞትህ ይሁን አንተን ደስ ይበልህ
በማለት ወስኜ  እቅድህ ይሙላልህ
ሳልቆይ ፍሬ ቋጠርኩ
ከዚህ ወዲያ ያለው ቀጥዬ ምፅፈው
በብእሬ ሳይሆን በንባየም ቀለም ነው 
አንተም ታውቀዋለሁ  ያለፍኩትን ፍዳ
የኖርኩትን  ችግር  ሁኜ  ከዛች   ጓዳ
ከስራ  ተባረህ  ተቀምጠህ  እቤት
እኔዋ ብቻዬን ስደክም ስንከራተት
በሆዴ ልጅ ይዤ ሊያውም በሰው ሀገር
ላይ ታች እየኳተንኩ  ቤቴን  ለማሳደር 
ካጠገቤ  ሳይኖር  በወጉ  የሚያርሰኝ
ከዘመድ  እርቄ እንዴትነሽ   ከሚለኝ
በዛ   በበርሀ  የኖርኩትን  ኑሮ
ሁሉም ቢዘረዘር አያልቅም ተቆጥሮ
ያን ሁሉ መሆኔ እንደዛ መልፋቴን
ከምንም ሳትቆጥር  አቅለህ ጥረቴን
ይባስ ልትጎዳኝ  ቁስል ልትጨምር
በላዬ ላይ ጀመርክ ከሌላ ሴት ፍቅር
ወልዳለች  እንግዲህ ምንም አታመጣም
ብበድላት  እንኳ  የላትም  መሄጃም
በማለት አስበህ አርክሰህ መውደዴን
ገደል አስገባኸው እምቁን  እምነቴን
እኔ ግን ሚስኪኗ 😢
ያ ሁሉ ሳያንሰኝ  የበደልከኝ  በደል
ዳግም ይቅር አልኩህ ሳላስብ መበቀል
ፍቅሬን መውደዴን ስል  በመዋጥ እንባዬን
በሚያነክስ እግሬ ጀመርኩ መንገዴን 
ቢታይህ በማለት  የኖርኩለት ፍቅሬ
ያለፈውን  ስተት  ብተፋው  አንቅሬ
አንተ ግን  አሁንም  ከሰውነት ወርደህ
ትንሽ እንኳ ሳትቆይ ይቅርታዬን ይዘህ
ከዛው ከለመድከው  ከጥፋቱ አሮንቃ
ተዘፍቀህ አየሁህ  አስጠላኸኝ በቃ  
ከዛ እለት ጀምሮ 🚶‍♀
አንተን ላንተው  ትቼ ስለራሴ ልኖር
አንተ በሄድክበት አይኔንም ላላዞር
          ወሰንኩኝ ከልቤ 
           እኔው ጋር አስቤ
ላንተ ይብላኝ እንጂ ግፍ ለተሸከምከው
እድሜ  ለደግነት ቢያመኝም ሽሪያለው
እናም እልሀለሁ አንተን  ጥዬ አርቄ 
መኖር  ጀምሪያለሁ    ከራሴ   ታሪቄ 
//////// 🌹🌹 //////////
  #ባለታሪኳ_የፌስቡክ_ጓደኛዬ_ነች ✋
#ሼን ✍
_Karooran yoo deman
Karaan hin fagatuu
_Obsaa yoo qabtaan
Kan hawwan argatuu
_Abdi yoo qabtaan
Arguuf tattafatu
_Qalbii yoo qabtaan
Kan darbe yaadatu
_Har'aa yoo rakkataan
Kan boruuf jabaatu
የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ!
**********
ዉድ የተከበራቹህ የዶክተር አለ 8809 ቤተሠቦች ይህ መረጃ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ አጋርነቶን ያሳዩን

👉በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል!!!

👉ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል!

በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጠቅላላ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታዬ አለማየሁ እንደሚናገሩት፤ ሙዝ በስትሮክ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ሞት በግማሽ መቀነስ ይችላል፡፡

ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል። ሁለት ሙዝ በልተን በምናገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ሥራዎችን መሥራት እንደምንችል ዶ/ር ታዬ ይናገራሉ፡፡
ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡

♦1. ለአእምሮ እድገት
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

♦2. ለስትሮክ
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡

♦3. ለደም ግፊት
ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

♦4. ለጨጓራ ህመም
አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡

♦5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡

♦6. ለሆድ ድርቀት
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡

♦7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡

♦8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

♦9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

♦10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡

♦11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች
በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡

👉 ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል።

👉 ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡

👉 ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡

በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡፡

ታዲያ ይህን የግል ሐኪምዎ የሆነ ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው አያበላሹት፡፡ ንፋስ ያለበት ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና - በዚያ ያኑሩት፡፡

------👌 #መረጃ_ሐይል_ነው!
👉 #በሽርፍራፊ ሰከንድ የተሰራች #ስህተት የሰውን ህይወት እንደምታጠፋ ሁሉ፡ #በሰከንዶች ቅፅበት የደረሰች መረጃ ህይዎትን ለማትረፍ ሰበብ ትሆናለችና እባከዎት በዚህ ቻናል የሚለቀቁ #ጤናነክ_መረጃዎችን ለሌሎች ወገኖች ለማድረስ #ሼር ቢያደርጉላቸው መልካምነት ነው፡፡
✍ #ራስ ምታት ያስቸግሮታል? እነዚህን ምግቦች ቢሞክሩስ?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #የአበባ ጎመን፦ የነርቭ ስርዓትን ፣ ጡንቻንና ደም ግፊትን በማስተካከል የራስ ምታትን ይቀንሳል

⏩ #ወተት፣ ስኳር ድንች፦ በቫይታሚን ቢ2 ይዘታቸዉ የነርቭ እና ቀይ የደም ሴሎችን እድገትና በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራሉ

⏩ #ገብስ ፦ በቫይታሚን ቢ6 ይዘቱ ሄሞግሎቢንን (የሰዉነት ኦክስጂን ተሸካሚ ንጥረ ነገር) በመገንባት የነርቭ ስርዓት እንዲገነባ እና በሽታ ለመከላከል ያግዛል

⏩ #የዶሮ ስጋ፦ በያዘዉ ቪታሚን ቢ3 የደም ዝዉዉርን በማፋጠን የደም ቧንቧን ክፍት ያደርጋል፣ በወር አበባ ጊዜ ለሚከሰት ራስ ምታት፣ ለድብርት እንዲሁም ለተያያዥ የህመም ስሜቶችም ፍቱን ነዉ

⏩ #እንቁላል፦ ሰዉነታችን በራሱ ማምረት የማይችለዉን ኦሜጋ 3 የተሰኘ አሲድ የያዘ ሲሆን ፤ ለአእምሮ ስራና እድገት እጅግ ተቃሚ ነዉ ፤ በተጨማሪም በድብርት እና ምክንያት አልባ ጭንቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚነቱ ተረጋግጧል።
"እግረኛ ነው ድሀ" ማለትሽን ሰምቼ፣
ይቻትልሽ አቶዝ እንዳቅሜ ገዝቼ፤
የሰው ልክ ይከብዳል አይሆን በግምት፣
ነይ እስቲ ልለካሽ? ነድቼው ልሙት!!!