እትዮ መጽሐፍት መደብር
118 subscribers
39 photos
1 video
10 files
4 links
ማንኛውንም መጽሐፍት እዚህ ግሩፕ ላይ መለቀቅ ይቻላል ።
በእውቀት አዕምሮ ማዳበር ብልጠት ነው ።
ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋል ።
Download Telegram
Yoo ati na jaalattee

Yoo ati na jaalattee,
Dhugaan na amate,
Garaa kee natti himte,
Miiltoosaanii koo siin jedheen
Fedhii koo siif ibsa.
Anis si abdadheen
Karoora koo cimsa.

Waliin karoorfannee
Jireenya ijaarranna
Rakkina injifannee
Guddinaaf xaarranna
Qilleensi nuu hin raasuu
Humna waliif taana
Homtuu nu hin deebisuu
Galma milkii dhaqna

Situ yaadaan na gorsa
Humnaa ol hin xaaru
Si abdadheen obsa
Jechaa Ormaaf hin aaruu

Yoo ati kiyyaa taatee,
Lafattan ulfaadha
Gammachuun giutameen
Namummaa gonfadha
Akka callee teetiin
Mormaati sii hidheen
Lapheerra kaawwadhee
Jaalalaan si baadha
Urgaa kee uladheen
Nadhii kees unadha!

Yoo ati naa jaalatte
Abdii guddaatu jira
Muuxannoon kiyyaaf kee
Dhaloota jijjiira
Yaadannoo galmeesseen
Nama hundaaf hira!
Barri Fidee

Barri fidee kafana
Huccuu haguugduu dhaqnaa
Kan saala ittiin dhokfannee
Uffannee baanu manaa

Huccuu kaayyoo hanqatte
Dhaqnatti nama hin ulfaatu
Nutti haa himtu ishiin godhatte
Akkamitti akka uffattu
Akkamitti akka of amantee
Ganama abdattee baatu
Akkamitti nama jidduus ooltee
Akka deebitee galtu.

Barri fideen midhaani
Sanyii baargamaa dhufu
Tokkicha facaasanii
Kan lammata axhiin hafu

Biqilli tokko ol baanaan
Raamoo torbatu dhalata
Sanyii namni alaa bitu
Raamoo tola dabalata
Qoricha raammicha ajjeesuu
Baargamatti oomishama
Yookaan sanyii facaasan
Odoo hin daraariin shama.

Barri fideen jireenya
karoora ormi baase
Shira diina fageenya
Duula alagaan bobbaase
Aadaa uummataa gatee
Kan safuu wallaalchisu
Akka namni of dagatee
Alagaa of dhaalchisu

Barri fideen qalbiidha
Gaangee luugama hin qabne
Humna meeqan harkisnee
Mataa qabuu dadhabne!
የማይግሬን ራስ ምታት

ማይግሬን ከከፍተኛ ራስ ምታት የበለጠ ነው። ይህ የነርቭ በሽታ ለቀናት በአልጋ ላይ ሊያውልዎት የሚችል የሚያዳክም የሚረብሽ ህመም ነው! ማይግሬን ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ እና ብርሃን መጥላትን ይኖራቸዋል። ህመሙ ለሰዓታት ወይም ለቀናት ሊቆይ ይችላል።

የማይግሬን ምልክቶች

የማይግሬን ዋና ምልክት ራስ ምታት ነው። ህመሙ በአንድ ጎን ጀምሮ ወደ ሌላው ሊዞር ይችላል ፣ ወይም የፊትለፊት የግንባር ህመም ፣ የጭንቅላትህ ጀርባ ላይ ህመም ሊኖር ይችላል ወይም የሙሉ ጭንቅላትን ህመም ሊኖር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ዓይናቸውን ወይም ዓይናቸው አካባቢ ህመም ይሰማቸዋል፡፡

ሌሎች የማይግሬን ራስ ምታት ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

🔺 ለብርሃን ፣ ጫጫታ እና ሽታዎች ስሜታዊነት።
🔺 ማጥወልወል ፣ ማስመለስ እና የሆድ ህመም።
🔺 የምግብ ፍላጎት ማጣት.
🔺 የሰውነት ሙቀት መሰማት(ላብ) ወይም ቅዝቃዜ (ብርድ ብርድ ማለት) ።
🔺 የቆዳ መገርጣ
🔺 የድካም ስሜት
🔺 መፍዘዝ
🔺 ተቅማጥ (አልፎ አልፎ)።
🔺 ትኩሳት (አልፎ አልፎ)።
🔺 ማይግሬን ለአራት ሰዓታት ያህል ሊቆይ ይችለል ሆኖም ግን ከባድ ማይግሪን በጣም ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል።

ህመሙ ሊጀምር ሲል ያሉ ምልክቶች

🔺 ትኩረት ለማድረግ መቸገር
🔺 ከወትሮ በተለየ መነጫነጭ ወይም ድባቴ
🔺 ለማውራትም ሆነ ለማንበብ መቸገር
🔺 እንቅልፍ ማጣት እና በተደጋጋሚ ማዛጋት
🔺 ማጥወልወል
🔺 ድካም
🔺 የምግብ አምሮት
🔺 የጡንቻ ህመም

Aura symptoms (ለትንሽ ጊዜ የሚቆይ የስሜት ህዋሳት መዛባት)

🔺 ለሰው የማይሰማ ድምጽ መስማት ወይም ለሰው የማይሸት ሽታ መሽተት
🔺 ጆሮ መጮህ
🔺 ሰውነትን መደንዘዝ እና መንዘር
🔺 የእይታ መዛባት
🔺 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እይታ ማጣት
🔺 በአንድ በኩል የሰውነት መድከም

የእራስ ምታት ምልክቶች

🔺 የአንገት ህመም እና መጨምደድ
🔺 ድባቴ እና ስጋት
🔺 ድምጽ ፣ሽታ እና ብርሃን አለመቻል ወይም መጥላት
🔺 የአፍንጫ መታፈን
🔺 እንቅልፍ ማጣት
🔺 ማጥወልወል እና ማስመለስ

ከህመሙ በሆላ የሚኖሩ ነገሮች

🔺 የስሜት ዝቅ ማለት (የድባቴ ስሜት)
🔺 ድካም

ማይግሪንን የሚያስነሱ ነገሮች

🔺 ጭንቀት
🔺 ምግብ ባግባቡ አለመመገብ ወይም ርሃብ
🔺 አንዳንድ የምግብ አይነቶች እነዚህም የስንዴ ዳቦ ቸኮሌት
🔺 የአልኮል መጠጦች
🔺 የወር አበባ
🔺 ድካም ከልክ በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
🔺 ብርሃን የቴሌቭዝን ወይም የኮምፒውተር እና የፀሃይ ጨረር
🔺 በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ

አጋላጭ ሁኔታዎች

🔺 ይህ አይነት ችግር ቤተሰብ ውስጥ ካለ በዘር የመተላለፍ እድል አው
🔺 ጾታ ብዙውን ጊዜ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ የመጋለጥ እድል አላቸው
🔺 እድሜ 15-55 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች
🔺 ሲጋራ ማጨስ

የቤት ውስጥ መድሃኒቶች

🔺 በጨለማ ፣ ጸጥ ባለ ፣ በቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ ማረፍ።
🔺 በግንባርዎ ወይም በአንገትዎ ጀርባ ላይ ቀዝቃዛ ነገር ወይም በረዶ መያዝ ህመሙ ሲኖር። (አንዳንድ ሰዎች ሙቀትን ይመርጣሉ ስለዚህ ለብ ያለ ውሃ መያዝም ይችላሉ።)
🔺 የራስ ቆዳዎን ማሸት።
🔺 ዮጋ
🔺 በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እራስዎን መጠበቅ።

መፍትሄዎች

🔺 ቤት ውስጥ ለማከም መሞከር
🔺 የሚያስነሳቦት ነገር ማስወገድ
🔺 ይህን አድርገው ካልተሻለዎት ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ
#ይብላኝ_እንጂ_ላንተ 🚶‍♀
#በስደት_ላይ_የተከሰተ_እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ ✍
ድንገት ባጋጣሚ በቅፅበት ትውውቅ
በጋራ ቋጠርን  የአብሮነትን ስንቅ 
ትኩሱ  ፋቅራችን  ያስቀና  እንደነበር 
  ዛሬም ትዝ  ይለኛል የነበረን ነገር 
ታዲያ ያንን ጊዜ  አመልህ ጨዋታህ 
ቅን አስተሳሰብህ  እርጋታና  ለዛህ
ማረከና  ሳበኝ  ውስጤን  ተቆጣጥሮ 
ልቤም  ለሂዎቱ  ተመኜህ  አምርሮ 
በቃ አመንኩህ ወዲያው አይቼ እንደራሴ
አብልጨም ወደድኩህ ደስ አለው መንፈሴ
  ከዛማ  ምን  አለ  ሀሳቤም ስራዬም
አንተው  ሁነህ አረፍክ  በውሎም ባዳሬም
      የብቻ   ሂዎቴ  ያንጊዜ  ተቀርፎ
      ባንድ መደብ ተኛ ጎኔ ጎንህ አርፎ
   ባልና ሚስት ሆንን ጎጆም መሰረትን
   በሰው ሀገር ሁነን ትዳርን "ሀ"  አልን 
አዎ አስታውሳለሁኝ ዛሬም እንደትናንት
ያኔ  ያለፍኩትን   የኖርኩትን  ጊዚያት
  ጎጇችን እንዲደምቅ ነገንም አልሜ  
  ስላንተ  ለመኖር  ከራሴ አስቀድሜ
ለኔው ቃል ገብቼ  ልሆንህ እመቤት
   ወረት የማያውቃት ሁኜልህ  አመቤት
    ለደስታህ ልለፍ ቃል ገባሁ ያን ሰአት
  ታስታውስው የለ •••• 🤔
ልጅ  እፈልጋለሁ  ውለጅልኝ  ስትል
ሰው ሀገር መሆኔ  ሳይለኝንኳ ውል
የምኞትህ ይሁን አንተን ደስ ይበልህ
በማለት ወስኜ  እቅድህ ይሙላልህ
ሳልቆይ ፍሬ ቋጠርኩ
ከዚህ ወዲያ ያለው ቀጥዬ ምፅፈው
በብእሬ ሳይሆን በንባየም ቀለም ነው 
አንተም ታውቀዋለሁ  ያለፍኩትን ፍዳ
የኖርኩትን  ችግር  ሁኜ  ከዛች   ጓዳ
ከስራ  ተባረህ  ተቀምጠህ  እቤት
እኔዋ ብቻዬን ስደክም ስንከራተት
በሆዴ ልጅ ይዤ ሊያውም በሰው ሀገር
ላይ ታች እየኳተንኩ  ቤቴን  ለማሳደር 
ካጠገቤ  ሳይኖር  በወጉ  የሚያርሰኝ
ከዘመድ  እርቄ እንዴትነሽ   ከሚለኝ
በዛ   በበርሀ  የኖርኩትን  ኑሮ
ሁሉም ቢዘረዘር አያልቅም ተቆጥሮ
ያን ሁሉ መሆኔ እንደዛ መልፋቴን
ከምንም ሳትቆጥር  አቅለህ ጥረቴን
ይባስ ልትጎዳኝ  ቁስል ልትጨምር
በላዬ ላይ ጀመርክ ከሌላ ሴት ፍቅር
ወልዳለች  እንግዲህ ምንም አታመጣም
ብበድላት  እንኳ  የላትም  መሄጃም
በማለት አስበህ አርክሰህ መውደዴን
ገደል አስገባኸው እምቁን  እምነቴን
እኔ ግን ሚስኪኗ 😢
ያ ሁሉ ሳያንሰኝ  የበደልከኝ  በደል
ዳግም ይቅር አልኩህ ሳላስብ መበቀል
ፍቅሬን መውደዴን ስል  በመዋጥ እንባዬን
በሚያነክስ እግሬ ጀመርኩ መንገዴን 
ቢታይህ በማለት  የኖርኩለት ፍቅሬ
ያለፈውን  ስተት  ብተፋው  አንቅሬ
አንተ ግን  አሁንም  ከሰውነት ወርደህ
ትንሽ እንኳ ሳትቆይ ይቅርታዬን ይዘህ
ከዛው ከለመድከው  ከጥፋቱ አሮንቃ
ተዘፍቀህ አየሁህ  አስጠላኸኝ በቃ  
ከዛ እለት ጀምሮ 🚶‍♀
አንተን ላንተው  ትቼ ስለራሴ ልኖር
አንተ በሄድክበት አይኔንም ላላዞር
          ወሰንኩኝ ከልቤ 
           እኔው ጋር አስቤ
ላንተ ይብላኝ እንጂ ግፍ ለተሸከምከው
እድሜ  ለደግነት ቢያመኝም ሽሪያለው
እናም እልሀለሁ አንተን  ጥዬ አርቄ 
መኖር  ጀምሪያለሁ    ከራሴ   ታሪቄ 
//////// 🌹🌹 //////////
  #ባለታሪኳ_የፌስቡክ_ጓደኛዬ_ነች ✋
#ሼን ✍
_Karooran yoo deman
Karaan hin fagatuu
_Obsaa yoo qabtaan
Kan hawwan argatuu
_Abdi yoo qabtaan
Arguuf tattafatu
_Qalbii yoo qabtaan
Kan darbe yaadatu
_Har'aa yoo rakkataan
Kan boruuf jabaatu
የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ!
**********
ዉድ የተከበራቹህ የዶክተር አለ 8809 ቤተሠቦች ይህ መረጃ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ አጋርነቶን ያሳዩን

👉በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል!!!

👉ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል!

በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጠቅላላ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታዬ አለማየሁ እንደሚናገሩት፤ ሙዝ በስትሮክ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ሞት በግማሽ መቀነስ ይችላል፡፡

ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል። ሁለት ሙዝ በልተን በምናገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ሥራዎችን መሥራት እንደምንችል ዶ/ር ታዬ ይናገራሉ፡፡
ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡

♦1. ለአእምሮ እድገት
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

♦2. ለስትሮክ
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡

♦3. ለደም ግፊት
ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

♦4. ለጨጓራ ህመም
አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡

♦5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡

♦6. ለሆድ ድርቀት
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡

♦7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡

♦8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

♦9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

♦10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡

♦11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች
በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡

👉 ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል።

👉 ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡

👉 ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡

በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡፡

ታዲያ ይህን የግል ሐኪምዎ የሆነ ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው አያበላሹት፡፡ ንፋስ ያለበት ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና - በዚያ ያኑሩት፡፡

------👌 #መረጃ_ሐይል_ነው!
👉 #በሽርፍራፊ ሰከንድ የተሰራች #ስህተት የሰውን ህይወት እንደምታጠፋ ሁሉ፡ #በሰከንዶች ቅፅበት የደረሰች መረጃ ህይዎትን ለማትረፍ ሰበብ ትሆናለችና እባከዎት በዚህ ቻናል የሚለቀቁ #ጤናነክ_መረጃዎችን ለሌሎች ወገኖች ለማድረስ #ሼር ቢያደርጉላቸው መልካምነት ነው፡፡
✍ #ራስ ምታት ያስቸግሮታል? እነዚህን ምግቦች ቢሞክሩስ?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #የአበባ ጎመን፦ የነርቭ ስርዓትን ፣ ጡንቻንና ደም ግፊትን በማስተካከል የራስ ምታትን ይቀንሳል

⏩ #ወተት፣ ስኳር ድንች፦ በቫይታሚን ቢ2 ይዘታቸዉ የነርቭ እና ቀይ የደም ሴሎችን እድገትና በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራሉ

⏩ #ገብስ ፦ በቫይታሚን ቢ6 ይዘቱ ሄሞግሎቢንን (የሰዉነት ኦክስጂን ተሸካሚ ንጥረ ነገር) በመገንባት የነርቭ ስርዓት እንዲገነባ እና በሽታ ለመከላከል ያግዛል

⏩ #የዶሮ ስጋ፦ በያዘዉ ቪታሚን ቢ3 የደም ዝዉዉርን በማፋጠን የደም ቧንቧን ክፍት ያደርጋል፣ በወር አበባ ጊዜ ለሚከሰት ራስ ምታት፣ ለድብርት እንዲሁም ለተያያዥ የህመም ስሜቶችም ፍቱን ነዉ

⏩ #እንቁላል፦ ሰዉነታችን በራሱ ማምረት የማይችለዉን ኦሜጋ 3 የተሰኘ አሲድ የያዘ ሲሆን ፤ ለአእምሮ ስራና እድገት እጅግ ተቃሚ ነዉ ፤ በተጨማሪም በድብርት እና ምክንያት አልባ ጭንቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚነቱ ተረጋግጧል።
"እግረኛ ነው ድሀ" ማለትሽን ሰምቼ፣
ይቻትልሽ አቶዝ እንዳቅሜ ገዝቼ፤
የሰው ልክ ይከብዳል አይሆን በግምት፣
ነይ እስቲ ልለካሽ? ነድቼው ልሙት!!!
"A little about Gyni"

የአራተኛ አመት ተማሪዎች እያለን ለመጀመሪያ ጊዜ በምጥ ላይ ያለች እናት ስመለከት የተሰማኝን ስሜት ሁሌም አስታውሰዋለው፡፡ በሕክምናው ቋንቋ second stage (ህፃኑ ከእናቱ ማህፀን የሚወጣበት) የሚባለው የምጥ ደረጃ ላይ የነበረች እናት ነበረች፡፡

በፍፁም የማላውቀው ሕመም ቢሆንም እስከ አጥንቶቼ ድረስ ዘልቆ ተሰምቶኛል፡፡ ከአመታት በፊት በእናቶቻችን ላይ የፈጠርነው ሕመም ተሰምቶን ይሁን ነግ በኔ ብለን እንጃ እኔና አብረውኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዩ ሴት ጓደኞቼ እንዳለቀስን አስታውሳለው፡፡ የእናቶቻችን ጉዳት ለይቅርታም ለምስጋናም የማይመጥን ነው፡፡

የዛን ዕለት ማታ ይህቺን ስንኝ ለእናቴ ቋጠርኩ፡፡

እንደ ዘበት ኖሬ እድሜ እየሰፈርኩኝ
ገና ዛሬ አወቅኩት
ለካ በሕመምሽ ነው መኖር የጀመርኩኝ፡፡

በእናትየው ፊት ላይ የሚታየው የሕመም ስሜት ፤ ድካም ፤ ጭንቀት ፤ ተስፋ መቁረጥ፡፡ በሌላ በኩል ልጁ ታፍኖ ይሞት ይሆን የሚለው የሐኪሙ ፍርሃት ሁሉም አሉታዊ ስሜቶች ያሉበት ቅፅበት ነው ምጥ፡፡ ቅፅበት ለማለት ያስደፈረኝ ይሄን ሁሉ የአሉታ ስሜት ተከትሎ የሚመጣው ደስታ የሕመሙንም ፤ የጭንቀቱንም ፤ የድካሙንም፤ የፍርሀቱንም ፤ የእዬዬውንም ጊዜ የማስረሳት አቅም እንዳለው ስለተረዳውኝ ነው፡፡

በምጥ ህመምና በእናትነት ደስታና ፍቅር መሀል የጊዜም ፤ የቦታም ፤ የሁኔታም የምንም የምንም ድንበር የለም፡፡ ብዙ ጊዜ እናትነት በትክክል የሚጀምረው መቼ ነው ብዬ እንድጠይቅ ሆኛለው፡፡

ሰውነቷ ሁሉ በላብ ተነክሮ ለረዠም ሰዓታት እግሮቿ እዚህና እዚያ ተለያይተው አቅሟ እስኪሟጠጥ ድረስ ያማጠች አንድ አንዴም ህፃኑ እንዳይታፈን ተብሎ በሰውነቷ ላይ ስለት አርፎባት የሕመምን የመጨረሻ ጥግ ያየች ሴት የልጀዋን የለቅሶ ድምፅ ስትሰማ በፊቱዋ ላይ የሚታየው ደስታ ፤ ሕፃኑ ትንሽ ጉዳት የደረሰበት ሆኖ ሐኪሙ አንድ ነገር ያለ እንደሆነ የራስዋንሕመም ረስታ ስለ ልጅዋ መጨነቅ እና ማልቀስ ስትጀምር ሳይ እውነት ተፈጥሮ ለሴት ልጅ የሸለመቻት ድንቅ ፀጋ ነው እናትነት እላለው፡፡

በጊዜ ሂደት ሁሉንም እየለመድነው ሄድን፡፡ እኛም ባለ ድርሻ ሆነን መስራት ጀመርን፡፡ በሁለቱም የክሊኒካል የትምህርት አመቶች እየተደሰትኩ የተማርኩት የማሕፀንና ፅንስ ትምህርትን ነበር፡፡ ቦታው በተለያዩ የተፈጥሮ ድንቅ ነገሮች የተሞላ መሆኑ እና ከሁሉም ቦታ ይልቅ የፈጣሪን አሰራር በመገረም እንድናደንቅ የሚያደርገን መሆኑ ቀልቤን ይስበዋል፡፡

በሁለቱ አመታት (በዘንድሮም ጥቂት ቆይታዬ) ብዙ የሚገርሙ ፤ የሚያሳዝኑ ፤ የሚያዝናኑ እስከ ስሜት ጉዋዳ የሚጠልቁ ነገሮች ቢገጥሙኝም ስለ Gyni ሳስብ እነዚህ እውነቶች ይገርሙኛል፡፡

1.ምንም አንኩዋን የምጥ ህመም የነብስ ውጪ የነብስ ጊቢ አጣብቂን ቢሆንም ምጥ ያለ ህመምና ያለ ጩኀት አለማማሩ፡፡

አንድ ጊዜ አስታውሳለው አንዲት ለመጀመሪያ ጊዜ የምመትወልድ (ከሏ በስተቀር ምንም ቤተሰብ ያልነበራት) ከመጀመሪው አንስቶ ልጁ እስኪወጣ ድረስ አንዲትም የሚረብሽ ድምፅ ሳታወጣ የወለደች ሴት፡፡ ለወትሮ ለመጀመሪ ጊዜ የሚወልዱ ሴቶች በጩኸታቸው ነበር የሚለዩት ፤ የዛን ቀን የምጥ ውበት ሕመሙ ነው ብዬ አስቤ ይህችን አሰፈርኩ፡-

ሕመሙ በርትቶ እዬዬ ካልመጣ
ምጥ ሰውነት ሰቅዞ እምባን ካላወጣ
እንጃልኝ ለደስታው እርባና ነው ሚያጣ

2.ሰው እያለቀሰ ምድርን የመቀላቀሉ እውነት ሌላ ግርምት ሆኖ እያለ ሕፃኑ እንደተወለደ የለቅሶ ድምፅ ካላሰማ የሚከፈጥረው ጭንቀት እና ወዲያው ካለቀሰ ወይም የተለያየ የሕክምና እርዳታ ተደርጎለት ሲያለቅስ (በሕክምና እርዳታ ማልቀስ) የሚፈጥረው ደስታ ሌላኛው የሚያስገርም ነገር ነው፡፡ ይኼኛውን ስሜት በዚህ መልኩ አይቼዋለው፡፡

ለቅሶህ ደስታ ሆነን ሳቅ ፈጠረ ለኛ
እንዳትቆጥርብን እንዳትሆን ቂመኛ

3. ከምጥ ክፍሉ ደጃፍ ያለው ሌላኛው ምጥ፡፡ ከደጅ ሆነው የህፃኑን መወለድ የሚጠባበቁት ቤተሰቦች ጭንቀት ከምንም በላይ የአንድ አንድ አባቶች ሁኔታ ሌላው ትልቁ ግርምቴ ነው፡፡

አንድ አንዱ እኩል ከህመሙ የሚካፈል ይመስላል፡፡ከእናትየው እኩል ያልበዋል ከእሱዋ እኩል ሆዱን ያመዋል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ በሌላ ጊዜ በሌላ ቦታ የገጠመኝ አጋጣሚ ትዝ ይለኛል፡፡ በመንገድ እየሄድኩኝ ከአንድ ጎልመስ ካለ ሰውዬ ጋር ለብቻችን ተገናኘን፡፡ ከየት መጣ ሳልለው እላዬ ላይ ተጠምጥሞ አቀፈኝና "ልጅ ተወልዶልኝ ደሰ ብሎኝ ነው አሁን ነው በስልክ የሰማሁት መጀመሪያ አንቺን ነው ያገኘሁሽ"አለኝ፡፡ እኔም ከተረጋጋው በኋላ በፈገግታ እንኳን ደስ አለህ አልኩት፡፡ የሚስቱን ምጥ ለማቅለል ወገቡን አላልቶ እንደነበር ያኔ አስተዋልኩኝ፡፡

ብቻ GYNI ደስ ይላል

Dr. Rediet Ararsa, Intern
#እራሴን_ታዘብኩት 🤔
ሳቅና ደስታውን ከሰው በመጠበቅ
ከብሶት ጓዳው ውስጥ ተክዞ ሲደበቅ
ሲያጨበጭቡ ከፍ ሲተቹት ደግሞ ዝቅ
እያለ ከላይ ታች እንዲሁ ሲዋዥቅ

እራሴን ታዘብኩት ••••

ባለፈ ትናንቱ ዛሬው ላይ ሲበሳጭ
የዃሊት በማሰብ ከራሱ ጋር ሲጋጭ
መተው እየቻለ መወሰን ሲያቅተው
መሄድ እያለበት እዛው ቁሞ ሳየው

እራሴን ታዘብኩት ••••

ምንም ለማይፈይድ እርባና ቢስ ነገር
በከንቱ ሲደክም ቆጥሮ እንደ ቁምነገር
የሂዎት ገፁ ላይ አንዳች ሳይጨምር
አመት እያሰላ ልደቱን ሲጨፍር

እራሴን ታዘብኩት ••••

መጥቀም እየቻለ ለመጉዳት ሲዳዳ
በማስታረቅ መድረክ ለፀብ ሲሰናዳ
ከእግር እስከራሱ በጥፋት ተሞልቶ
ሌላው ላይ ሲፈርድ የራሱን ዘንግቶ

እራሴን ታዘብኩት ••••

ለማይሆነው መውደድ ለማይዘልቅ ፍቅር
እኔነቱን ጥሎ አንሶ ሲያቀረቅር
የቀኑ ሳያንሰው መሽቶም ያን በማሰበ
ከንቅልፉ ሲጣላ ሀሳብ በመሰብሰብ

እራሴን ታዘብኩት ••••

ምን ይሉኛል በሚል ታጥሮ በይሉኝታ
መተንፈስ ሲያቅተው የልቡን እውነታ
ካለው ነገር በላይ ያጣውን አማትሮ
ከማመስገን ይልቅ ሲቀናው እሮሮ

እራሴን ታዘብኩት ••••

እኔ ብቻ በሚል እራስ ወዳድነት
ለማያቀው ነገ ሲያንስ ከሰውነት
ያደፈ እኔነቱን በልብስ ሊደብቅ
ውስጡን አቆሽሾ ላዩን ሲያሸበርቅ

እራሴን ታዘብኩት ••••

መሄድ ቻልኩ ብሎ መድረሻውን ሳይለይ
በስሜት ሲነዳ በጭፍን መንገድ ላይ
ድንገት ተሰባሪ ይዞ ፈራሽ ገላ ፣
መሞቱን ዘንግቶ ሲያልፍ ከምነት ኬላ፣

እራሴን ታዘብኩት ••••
#ሼን ✍
#ናፈቀኝ_አሁንስ 🚶‍♂
የሰው ዋጋ ወርዶ፣ ኑሮ ሳይወደድ
በዘር በጎጥ ሀሳብ ፣ ማንም ሳይታረድ
የግፍ በደል ግንዱ ፣ከስሩ ተነቅሎ
የፍትህ ባንዲራ ፣ከፍ ብሎ ተሰቅሎ
ሀገሩን የሚሸጥ ፣ ለሆዱ የሚያድር
ጠላት ባንዳ ጠፍቶ፣ከእምዬ ምድር
ከተራ መግለጫ ፣ፖለቲካው አልፎ
ያጠላብን ሀዘን ፣ ፅልመቱ ተገፎ
ገደለው ሰቀለው ፣ ቆረጠው ፈለጠው
አንደዜ ተያዘ ፣ አንደዜ አመለጠው
ከሚል ሽብር ወሬ ፣ጆሯችን እርቆ
ትንሹም ትልቁም ፣ ያላሳብ ቦርቆ
ሀዘን ዋይታ እሪታ ፣ሳይሰማ መርዶ
ማንም ሳይሰቃይ፣ ከቀየው ተሰዶ
የሚስኪን ደም እንባ፣ በከንቱ ሳይፈስስ
መች ነው የምኖረው ናፈቀኝ አሁንስ
#ሼን ✍
ከማን በልጠህ ነው- ከማን ተሽለህ
ኢትዮጵያ ትውደም- ብለህ የመጣህ
አፋር፣ አማራው ኦሮሞ፣ ደቡብ
ከመጤፍ ቆጥረህ- የኢትዮጵያን ሕዝብ
ልታንበረክክ- ከያዝክ ግብግብ
ይሄን ጠጣና- አንተው አሸልብ፡፡

የእናት አገሬን- ክብሯን የነካ
አይድንምና-
በግብጽ ድጋፍ- በእነ አሜሪካ
እጣ ፈንታህን- ሞትህን እንካ፡፡

ባንዳ አስገብሮት- አገር ከሚናቅ
ባንተ ሕልፈት ላይ
AGOWA ከስሞ- ዓድዋ ይድመቅ፡፡
የሪህ በሽታ ምልክት እና መፍትሄዎቹ
#Gout

ሪህ ምንድንነው?
➡️ሪህ በመገጣጠሚያዎች ውስጥ በተከማቸ የዩሪክ አሲድ ክሪስታሎች የሚፈጠር የአርትራይተስ አይነት ነው። ይህም በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል የህመም ዓይነት ነው፡፡
ሪህ በአንድ ወይም በብዙ መገጣጠሚያዎች ላይ ህመም እና እብጠት ያስከትላል. በተለምዶ በትልቁ ጣት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ነገር ግን ጉልበት ቁርጭምጭሚት እግር እጅ የእጅ አንጓ እና ክንድ ጨምሮ በሌሎች መገጣጠሚያዎች ውስጥም ይገኛል.
ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ንጥረ ቅመም ሲሆን ይህ ንጥረ ቅመም በሰውነት ውስጥ በተወሰነ መጠን መገኘት ያለበትና በሽንት በኩል የሚወገድ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲሆን ሰውነታችን ለማስወገድ አቅም ያጣል፡፡ በዚህን ጊዜ ካልሼም ፎስፊት ወደሚባል ጠጣር ንጥረ ነገርነት ተቀይረው ወደ መገጣጠሚያ ቦታዎች ይሰበሰባሉ፡፡ ከዚህም ሌላ የተከማቸው ዩሪክ አሲድ በኩላሊት ውስጥ እና በሽንት ማመላለሻ መስመሮች ውስጥ በመዝቀጥ የኩላሊት ጠጠር ሊፈጥር ይችላል ፡፡
➡️መንስኤው:-
ለሪህ የጤና ችግር በመንስኤነት የሚገለፁ የተለያዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡
▶️የዕድሜ መጨመር
▶️በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው በላይ የንጥረ ነገሮች መፈጠርና መከማቸት
▶️በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አማካኝነት
▶️ከቤተሰብ መካከል የጤና ችግሩ ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድል ይኖረዋል
ምክንያታቸው በውል የማይታወቅ ጉዳዮች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች ለሪህ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
▶️ለምሳሌ:-በአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ቀይ ሥጋ፣ ጉበት ኩላሊትና የጭንቅላት ስጋን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም አልኮል መጠጣት ለሪህ በሽታ ተጋላጭ የመሆን ዕድልን ያሰፋሉ፡፡
ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ
▶️የሰውነት ክብደት መጨመር፣
▶️በቁጥጥር ስር ያልዋለ ደም ግፊት፣
▶️ውሃ በብዛት ያለመጠጣት፣
▶️የኩላሊት በሽታና ለተለያዩ በሽታዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለሪህ በሽታ ተጋላጭ ያደርጋሉ፡፡
➡️የህመሙ ምልክቶች
▶️ከትንሽ የጣት ጫፍ እስከ ትላልቆቹ የሰውነት ክፍሎች አካባቢ ያሉ መገጣጠሚያ ቦታዎች ያብጣሉ
▶️የሰውነት ትኩሳት መከሰት
▶️ከቁርጥማት ጀምሮ መላ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በመንካት እስከሚቸግር ድረስ ህመም
▶️ከፍተኛ ስቃይ ያለው ህመም
▶️መገጣጠሚያ አካባቢዎች በተለየ መልኩ መቅላት
▶️በመገጣጠሚያ አካባቢዎች የማቃጠል ሁኔታ ይከሰታል
▶️የጡንቻ መዛል በተለይ ጠዋት ጠዋት እጅና እግርን ለማንቀሳቀስ መቸገር ይኖራል
▶️የጤና ችግሩ ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆየ በመገጣጠሚያ ቦታዎች ጠጣርየሆኑ ነገሮች ይፈጠራሉ
▶️ቁርጥማት
▶️በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ፡፡
➡️ህክምናው
አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ የሪህ በሽታ ከተከሰተበት ከፍተኛ ስቃይ ሊኖረው ይችላል::ስቃይን ለማስታገስ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ::
አንዳንድ መድሃኒቶች እንደ ፀረ-ብግነት መድኃኒቶች (ibuprofen እና naproxen), colchicine እና corticosteroids ያሉ የሪህ ጥቃቶችን ህመም እና እብጠት ይቀንሳሉ::
በእነዚህ መድሃኒቶች ለውጥ ካልመጣ Corticosteroids የሚባሉ መድሃኒቶችን በመርፌ ወይም በሚዋጥ መልክ ይሰጣል ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የህመም ስቃይን ከማቃለል በተጨማሪ መገጣጠሚያ ከጥቅም ውጭ እንዳይሆን ለጊዜው ፋታ ይሰጣሉ፡፡
ሌላኛው የህክምና ዘዴ Uric acid ከሰውነት ውስጥ እንዲቀንስ ማድረግ የሚችሉ መድሃኒቶች ነው፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለማከም ጥረት ይደረጋል፡፡ እጅና እግር መንቀሳቀስ ካቆመ በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡

መልካም ጤንነት!
ላጤ ተዋረደ ተናቀ ተረገጠ ተሽሟጠጠ ወገን 😥😥

ላጤ ትስእር✊!

እኚያ የትልቅ ፍንዳታ ተንከሲስ አከራዬ ገና በጠዋቱ እየጦለቡኝ ነው
"ዋትሳብ ተከራዬ..."
"ኧረ መአት ይሳቦት እቴ.."
"ምናልክ አንት ጢንዚዛ..."
"ኧረ ወደዛ ... ይልቅ የሽንት ቤት ቁልፍ..."
"ሊመጠጥ ነው ፖፖህ ላይ ተጠቀም..."
"ባለፈው ሳምንት አይደል እንዴ የተመጠጠው?.."
"የዝጋሉ ሽንትቤት ወርቅ መሰለህ እንዴ የሚቀበርበት!...ሞላ...በቃ ጥቅጥቅ ብሎ ሞላ ...ዩዝ ኤንድ ስሩአችሁን ተጠቀሙአ..." ኧረ እኚህ ሞት እምቢ አፈሉ!..
"ምንድነው እሱ ደሞ?"
"ፍሬሽ ላጤ ነሽ መሠለኝ....ፌስታልና ሀይላንድ አታርፍም?..."
"እ..."
"አጣድፎሻል መሠለኝ ደፈነብሽ...!"
"ኧረ ስለፈጠረዎ..."
"እንካ ወዲያ ... " ቁልፉን የመንጠቅ ያህል ተቀብዬ ሮጥኩ ። ጨራርሼ ስወጣ አልተውኝም "አዘናነጥህና አተኳኮስህ ግን ማች አያደርጉምኮ... ለነገሩ ዝነጣውም ቢሆን የነፍስ ይማር ነው 'ሚመስለው... ይሄን ጃኬት ብታስቀንሰውኮ ሌላ ተቀያሪ ጃኬት ይተርፍህ ነበር... "
ከዚህ በላይ አልችልም ቤት ፈልጉልኝ!🤔
ተፃፈ በጌታቼው ረዳ!
//...........................//
ጋሸና ላይ ሆኖ ይታያል መቀሌ:
ተቀብሬ ቀረሁ አለመታደሌ::
ስዋልል ስፏልል
ስፎክር ከርሜ
ይሄው ቀረሁልሽ
መከነብኝ ህልሜ::
#ለአዲስ_አበባ_መሆኑ ነው
የዛሬው ሌሊት ስም
"አይጥ ስትጠግብ ስታበዛ ሩጫ
ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ
ሲባል የነበረው እስከነ ተረቱ
ባንቺ ላይ ደረሰ በክልፍልፊቱ፤"
ተብሎ ይጠራል(ከ.ሚካኤል)
ልጅቷ የቤታቸው በር ይንኳኳና ስትከፍተው ፍቅረኛዋ ነው ፥😳😳ግን አባቷ በቅርብ እርቀት ስለነበሩ በስነ ስርአት ሰላም አላለችውም ወዲያውኑም ልጁ እንዳይቀባጥር በኮድ

# እሷ ፦ ሀይ ሰላም ነው አባቴ ቤት ነው የሚለውን የበውቀቱ ስዩም መፅሐፍን ልትወስድ መጥተህ ነው ?

# ልጁ ወዲያው ይነቃና እረ እኔስ የበአሉ ግርማን ታዲያ የት ልጠብቅሽ የሚለውን መፅሐፍ ልወስድ ነበር።

# እሷ ውይ እሱን መፅሐፍ እንኳን ቶሎ አላገኘውም ባይሆን የአዳም ረታን ከማንጎ ጥላ ስር "የሚለውን መፅሐፍ ልስጥህ

# ልጁ ጥሩ እዛው እንደደረስኩ እደውላለሁ የሚለውን መፅሐፍም እንዳትረሺው

# እሷ እረ ምንም ችግር የለም የይስማክ ወርቁን ቶሎ መጣለሁ የሚለውንም ይዤልህ መጣለሁ ።

# አባት የሚገርም ነው ይሄ ሁሉ መፅሐፍ ያነባል ?
# እሷ አው አባቴ እንዴት ያለ እስማርት ልጅ መሰለህ
# አባት በጣም ደስ ይላል እንደዛ ከሆነማ እኔም አንድ መፅሐፍ ልስጥሽና ትወስጂለታለሽ

እሷ እሺ አባቴ የቱን መፅሐፍ ?

እዛ መደርደርያ ላይ ሀዲስ አለማየው የፃፈው በናንተ ቤት በኮድ አውርታቹ ልባቹሁ ውልቅ ብሏል የሚለውን 🤦🏼‍♀🤦🏼‍♀🤦🏼‍♀

ስንቶቻቹ አራዳ አባት አላቹ 😌😌😌😌