እትዮ መጽሐፍት መደብር
118 subscribers
39 photos
1 video
10 files
4 links
ማንኛውንም መጽሐፍት እዚህ ግሩፕ ላይ መለቀቅ ይቻላል ።
በእውቀት አዕምሮ ማዳበር ብልጠት ነው ።
ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋል ።
Download Telegram
❤️የህልም ጏደኛ!!!

የእግዚአብሔርን ተአምር ላካፍላችሁ::
በትእግስት አንብቡት:-

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆኜ ማገልገል ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በርካታ አጋጣሚዎችን አሳልፌያለሁ:: ፈታኝ የሚባሉ እንዲሁም እጅግ መንፈስን የሚያረኩ ኩነቶ ጭምር::
ታዲያ ሁሉም የህፃናቱን ህይወት ለመታደግ ስለሆነ ወጀቡን በድል እንድሻገር ብርታት ሆኖኛል::

ደከመን ሰለቸን ከማይሉ የህክምና ባለሙያዎች; የህዝብ ግንኙነት ስራን በትጋት ከሚከውኑ እህት ወንድሞች እንዲሁም ቅን ከሆኑ ኢትዮጵያን ጋር ማገልገል መባረክ ነው::

ነገሩ እንዲህ ነው:- አንድ የስጦታ መርሀግብር የተከናወነበት እለት ጠዋት ላይ ጨርሼ ልወጣ ስል አንዲት ሴት ተከትላኝ ትወጣና በመርበትበት "እባክሽ የእህቴ ልጅ ከተወለደች ገና ሰባት ወሯ ነው የልብ ታማሚ ናት እናም ሀኪሞች የሷ ህመም እዚህ ሀገር መታከም ስለማይችል ባስቸኳይ ወደ ውጪ ሀገር ሄዳ መታከም ይኖርባታል ካልሆነ ህይወቷ አደጋ ላይ ነው ብለውናል እኛ ደግሞ አቅሙም የለን ስለጉዞው ሂደትም አናውቅም እርጂን" አለችኝ:: ግራ ገባኝ "የኔ አገልግሎት ማስተባበር ጉዳዩ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ማድረግ ነው ስለሂደቱ ባለሙያዎቹ ናቸው የሚያውቁት" አልኳት:: "እባክሽ ገብተሽ ህፃኗን እያትና መፍትሄ አፈላልጊ" አለችኝ:: ወደ ውስጥ ስገባ እናትዬዋ አግዳሚ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ህፃኗን እያጠባቻት ነበር ደም እምባ ታለቅሳለች ቃላት ከአፏ መውጣት አልቻለም ህፃኗም በስቃይ ታቃስታለች:: እጅግ ልብ ይሰብራል 💔 እህቷን የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ይዣት ገባሁ እና የጉዳዩን አንገብጋቢነት አስረዳቻቸው:: በሚከታተላት ሀኪም በኩል መፍትሄ እንደሚያፈላልጉ ነግረውን ወጣን::

የቤተሰቡ ሁኔታ ያስጨንቃል::
የህፃኗ አይን ይንከራተታል አንጀት ትበላለች! ግራ ተጋባሁ! በርከክ ብዬ እራሷን እየዳበስኩ በአርምሞ ፀሎት ወደአምላኬ አድርሼ አይዟችሁ የሚቻለውን ነገር ሁሉ እሞክራለሁ ብያቸው ወጣሁ:: ግን በደመነፍስ ነበር የተራመድኩት:: ወረፋ የሚጠብቁ ህፃናት ሁሉ እንዲሁም የእናቶቻቸው ለቅሶ ሁሌም ቢረብሸኝም እንደዚህ ደግሞ ጉዳያቸው አንገብጋቢ እና ባስቸኳይ መፍትሄ የሚሹ ህፃናት ጉዳይ እረፍት ይነሳኛል::

መንፈሴ ስለተረበሸ የዛን ቀን የነበረኝን ኝሮግራም ሰርዤ ወደቤት ገባሁና እመቤቴ ስእል ፊት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ:: ፀሎት ብቻ ሳይሆን አምላኬን ሞገትኩት! ለምን? እነዚህ ለምን እንኳን ወደዚች ምድር እንደመጡ የማያውቁ ህፃናትን ለስቃይ ትፈጥራለህ ብዬ የማይሳሳተውን አምላክ ሞገትኩ:: ከዛን በኃላ ለቀናት እንቅልፍ መተኛት አልቻልኩም ነበር:: እነዛ እየተቁለጨለጩ መዳን እፈልጋለሁ እርጂኝ የሚሉ የሚመስሉ የህፃኗ ንፁህ አይኖች በውስጤ ታትመው ቀርተዋል::

ከቀናት በኃላ በኢንስታግራም አካውንቴ መልእክት አገኘሁ ተዋናይት አዚዛ አህመድ ነበረች:: "መሲዬ እዚህ አሜሪካን ሀገር የምትኖር አንዲት ጏደኛዬ ለአንድ ጉዳይ ልታዋራሽ ትፈልጋለች ስልክሽን ሰጥቻታለሁ እባክሽ አንሺላት" የሚል ነበር እሺ ትደውልልኝ የሚለው ምላሼን አስቀመጥኩላት::
የዛን ቀን ማታ ከሜኔሶታ ሄለን የምትባል ልጅ ደወለችልኝ:: ድምፄን ስትሰማ በስንት መከራ አፈላልጌ አገኘሁሽ ብላ በደስታ ነበር ያዋራችኝ::
ለምን እና እንዴት ለሚሉ ጥያቄዎቼ ስትመልስልኝ:-

" ይገርምሻል መሲዬ በፊልሞችሽና በምትሰሪያቸው ስራዎች እንጂ በአካል አግኝቼሽ አላውቅም::
ትዲያ አንድ ቀን ሌሊት በህልሜ መጥተሽ አንዲት ህፃን ታቅፈሽ "ሄለን ይቺ ህፃን ልቧን ታማለች የምታድኛት ደግሞ አንቺ ነሽ" ትይኛለሽ: "እንዴ? እኔ እንዴት ነው የማድናት እኔ ፋርማሲስት እንጂ የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪም አይደለሁም" ስልሽ "በጭራሽ ካንቺ ውጪ ይቺን ልጅ የሚያድናት የለም" ብለሽ ልጅቷን ታሳቅፊኛለሽ::
ተቀብዬሽ ሀኪም ጋ ወሰድኳት ሀኪሙ ቀዶ ጥገናውን ካአደረገላት በኃላ ህፃኗ ተነስታ አልጋ ላይ ቁጭ አለች::
አንቺም "አየሽ ልጅቷን አዳንሻት" አልሽኝ
"አይ እኔ ሳልሆን ሀኪሙ ነው ያዳናት" አልኩ
"አንቺ ባትኖሪ ኖሮ ልጅቷ በህይወት አትኖርም ነበር" አልሽኝ:: ከዛም ልጅቷን በፍቅር አንስቼ ሳቅፋት ነቃሁ::
ብዙም ህልም ስለማላይ ከነቃሁ በኃላ ይሄ ነገር የሆነ መልእክት አለው መሲን ማፈላለግ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ እናም አገኘሁሽ አለችኝ::"

ይሄን ስታወራኝ እያለቀስኩ ነበር::
የእግዚአብሔር ምላሽ አስደምሞኝ!
"ሄለን የሚገርምሽ ሰሞኑን አንዲት የልብ ታማሚ ህፃን ጉዳይ እረፍት ነስቶኝ አምላኬን እየሞገትኩት ነበር እናም ባንቺ በኩል መልስ ሊሰጠኝ ነው ማለት ነው" ብዬ የህፃኗን ጉዳይ ወደውጪ ሀገር ሄዳ ካልታከመች ህይወቷ አደጋ ላይ እንደሆነም ያለውን ነገር አብራራሁላት::

አጋጣሚው ደነቃት:: "ሁሌም ሰዎችን ማገዝ እፈልግ ነበር ሁኔታዎች አላመች ብለውኝ እንጂ::
የልጆች እናት ነኝ ይቺን ህፃን ማገዝ ባለብኝ ሁሉ አግዛታለሁ ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉና የእናቷን ስልክ ላኪልኝ" አለችኝ:: ፈነደቅኩ! ተምበርክኬ አምላኬን አመሰገንኩት! ጊዜ አላጠፋሁም በሌሊት እህቷ ጋ ደውዬ የሆነውን ነገርኳት ተደሰተች::
በዛው ሌሊት የህፃኗን ፎቶና የእናቷን አድራሻ ላኩላት::

ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ የተጋቡት ቤተሰቦች በሰዎች አማካኝነት ጎፈንድሚ አካንት ከፍተው 3500 ዶላር አካባቢ ቢሰበስቡም ተጨማሪ 6500 ዶላር ለህክምናዋ ማግኘት አለባቸው:: ለሄለን ነገርኳት ሁሉንም ገንዘብ እኔ እችላለሁ አለችኝ አላመንኩም:: እናቷ ይሄን ስትሰማ ሲቃ ያዛት:: በሉ በፍጥነት ፕሮሰሱን ጀምሩ ሄለን እዛ ያለውን ነገር ትጨርሳለች አልኳቸው የቪዛው ሂደት ትንሽ ዘግይቶ ስጋት ቢይዘንም ቆይቶ ተሳካ::

ሄለን ህንድ ሀገር ህፃኗ የምትታከምበት ሆስፒታል አድራሻ; የሚያክማትን ሀኪም ጭምር አግኝታ ስላለው ሁኔታ በዝርዝር አውርተዋል:: በሙያዋ ፋርማሲስት ስለሆነች በቀላሉ በሙያዊ ቋንቋ ተግባብተዋል:: ህፃኗ(ክርስቲያን) ነው ስሟ::
ከልብ ህመም በተጨማሪ (Down syndrome) አለባት:: ( it’s a genetic disorder) ህክምናው ይሳካ ይሆን? የሚለው ስጋት ነበር:: በመጨረሻም ጉዞ ወደ ህንድ ሀገር ሆነ:: እናቷ ደውላ መሲዬ ፀልይልን ዛሬ ነው ጉዟችን አለችኝ " እግዚአብሔር ይቅደማችሁ" አልኳት::

ከቀናቶች ክትትል በኃላ የክርስቲያን ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ:: ሄለን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ትከታተል ስለነበር እየፈነደቀች ደወለችልኝ:: ሰው በዚህ ደረጃ አንድም ቀን እንኳን አይቶት ባማያውቀው ሰው ይደሰታል? ምን አይነት የተባረከች ሴት ናት!!!
ከቀዶ ህክምናው በኃላ ለተወሰኑ ቀናት (ICU) ክፍል ነበረችና ስትነቃ ሌላ ደስታ ሆነ::

ሄለን የነበረውን ሂደት በሙሉ ለሀኪሞቹ ስትነግራቸው ተገረሙ:: በዚህ ታሪክ የተመሰጠው Dr. Rick Hodes “A baby, a heart and a dream” በሚል ርእስ ታሪኩን በመሉ ፅፎ ፎቷችንን አስደግፎ ዌብ ሳይቱ ላይ ለጥፎቷል:: ሊንኩ ከስር አለ እዩት👇

https://rickhodes.org/a-baby-a-heart-and-a-dream

ባጠቃላይ ከወር ቆይታ በኃላ ክርስቲያንና እናቷ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ተመልሰዋል:: እንደገባች ነበር የደውለችው:: ምርቃት; ደስታ;ምስጋና......
ሁሉን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን🙏
በህልም አመካኝቶ ይቺን ህፃን እንድትታደጊያት ያደረገሽ ውድ ሄለን ዘመንሽ ሁሉ የተባረከ ይሁን! የክርስቲያንን ሳቅ እንደመለሽ በኑሮሽ ሁሉ ሳቅ
ይሁን!!!
ክርስቲያን አድጋ ይሄን ታሪክ እንደምትሰማ አምናለሁ:: የድንግል ልጅ በብዙ ሞገስ እና ፀጋ ያሳድግሽ!

አሁን ሄለን ቤተሰቤ የሆነች ያክል ነው የሚሰማኝ:: "በህይወቴ አግኝቼ የማላውቀውን ደስታ እንዳገኝ ምክንያት ሆንሽኝ" ትላለች::
እውነተኛ ደስታ በመስጠት እንጂ በመቀል ስላልሆነ!
በደወለች ቁጥር "የህልሜ ጏደኛ" ትለኛለች::
እንዳንቺ አይነት ቅን ሴት በእውኑ አለምም ያብዛልኝ::

ወዳጆቼ የእግዚአብሔር ስራ አይገርምም?
ሁሌም ድንቅ ነው! አጉረምርመን ሳንጨርስ ጉንጫችንን በሳቅ ይሞላል::
ሌሎች ምስኪን ህፃናትንም በምህረቱ ይታደጋቸው::

የልጆችን ተስፋ ከማስቀጠል በላይ ምን ደስታ አለ?
እናንተም ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ተረባረቡና ብዙ ደስታና በረከት ሰብስቡ::
በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገራትም የምትኖሩ ወገኖቼ ብዙ ሺህ ህፃናት ወረፋ ይዘው መዳናቸውን በጉጉት እየጠበቁ ነውና በምትችሉት ሁሉ አግዟቸው::

#ህልማችሁ ልቦች ይጠገኑበት 🙌
መሰረት መብራቴ

#Cardiac_Center_Ethiopia❤️
#6710 A/B/C/D

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ——-1000001839806
አዋሽ ባንክ————--------01308236167000
ዳሽን ባንክ-————-------0041600483011
አባይ ባንክ............................1021817336052015
አቢሲኒያ ባንክ.......................60263547
😂😂😂
🙊🙊🙊🙊
የዛሬው ጤና መረጃ ትኩረቱ እዚህ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡

የ እናት ጡት ወተት በምን ምክንያት ይቀንሳል?

• ልጅሽ እንደተወለደ ወዲያው ጡት ካልጠባ
• ልጅሽ በትክክለኛ ባልሆነ አያያዝ እና አጠባብ ጡት የምትሰጭው ከሆነ
• ልጅሽን ቶሎ ቶሎ በሰዓቱ ካላጠባሺው
• የአዕምሮ ዉጥረጥ መጨናነቅ እና አለመረጋጋት ካለ
• በቂ እረፍት ካልወሰድሽ
• በቂ ምግብ እና ፈሳሽ ካልወሰድሽ
• ልጅሽ ከእናት ጡት ወተት ዉጭ ሌላ ወተት የሚወስድ ከሆነ
• ማንኛዉም ሱስ ካለብሽ
• መድሃኒቶች የምትጠቀሚ ከሆነ በተለይ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች
• ደም ግፊት እና ከመጠን ያለፈ ዉፍረት
• ከፍተኛ የካፌን ንጥረ ነገሮች ያላቸዉን ምግቦች እና መጠጦችን(ቡና ሻይ ለስላሳ መጠቶች) የምታዘወትሪ ከሆነ

የጡትሽ ወተት በቂ ከሆነ ልጅሽ ላይ የሚከተሉትን ምልክቶች ይታያሉ፡፡

✍ ልጅሽ ጠብቶ በቀን ቢያንስ 5 ወይም 6 ጊዜ ሽንት ይሸናል፣
✍ 2 ወይም 3 ጊዜ ይጸዳዳል፡፡
✍ ኪሎው እየጨመረ ይሄዳል(በቀን 30 ግራም)
✍ በደንብ ይተኛል (ቢያንስ 2 ሰዓት)

✍ በደንብ ሲጠባ እና ሲውጥ ላንቺም ይታወቅሻል

የጡት ወተትሽ በቂ እንዲሆን ማድረግ ያለብሽ ነገሮች፡፡

1. ከላይ የተዘረዘሩትን የ ጡት ወተት የሚቀንሱ ነገሮችን አስወግጂ:
2. ጡትሽ ቶሎ ቶሎ ማለብ ወይም ማጥባት
3. ልጅሽን ደረትሽ ላይ ዳይፐር ብቻ አርገሽ አስተኝው
4. ለብ ባለ ዉሃ የተነከሩ 2 ፎጣዎች ከጡትሽ ከላይ እና ከታች ይዘሽ ቀስ ብለሽ ከላይ ወደ ታች ማሳጅ ማድረግ በቂ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ በቂ ፈሳሽ መውሰድ በተለይ ከአትክልት እና ፍራፍሬ ፓፓያ, ብርቱካን, ሃባብ ማንጎ መውሰድ
5. በተቻልሽው መጠን በቂ እንቂልፍ እና እረፍት ማድረግ
6. አለመጨነቅ

እነዚህን ሁሉ አርገሽ ምንም ለውጥ ከሌለ ወይም ልጅሽ ትኩሳት እና በጣም መነጫነጭ ካመጣ እንደራበው ጡትሽን ቀድመሽ ትሰጪና ቀጥሎ በንፅህና የተዘጋጀ የጣሳ ወተት መስጠት ትቺያለሽ፡፡ ይህ ግን የ መጨረሻ አማራጭ ብታደርጊው መልካም ነው::

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)
የናፍቆት ረሃብ ልቤን ከሚያነደው
ዐይንና ከንፈሯን ሰርቄ ልውሰደው?! 😳
እዩልኝ የውሻን ፍቅር 😍 ልብን የሚነካ ምስሎች 😯 😥
"ምረጪኝ"
ፍቅሬን ተቀብለሽ ምርጫሽ ብታረጊኝ
የልብሽን በር ቁልፉን ብትሰጪኝ
በረሃውን ለምለም
ሀገራችንን ሰላም
አየሩን ነፋሻማ
ማሣውን ፍሬማ
ስትጠሪኝ አቤት
ስትልኪኝ ወዴት
የምልሽ ነኝ እኔ ሙች ስልሽ እመኚኝ
አደርግልሻለው ብቻ እኔን ምረጪኝ
ምልክቴም ይሄው ያዢው ተቀበዪኝ
ለብሽ ውስጥ ልግባ ልቤን ተቀበዪኝ
#ለካስ_ትዝታ_ነው 🤔👫💓
ከመለየት ገዝፎ ፣ ከመጣላት በልጦ
እቅምን እየነሳ ፣ ጉልበትን አሟጦ
ውስጥን የሚጎዳው ፣ ልብን አቆሳስሎ
ከሄደው ወዳጅ ጋር ፣የማይሄድ ኮብልሎ
ለካስ ትዝታ ነው ክፉኛው በሽታ
ቀስበቀስ አዝሎ ሰውን የሚረታ
#እስከመች_ነው_ፍቅርህ 🤔🌹🌷
አፈቅርሻለሁ ላልከኝ •••••• 🚶‍♂
ከማለትህ በፊት ወደድኩሽ ሞትኩልሽ
ከራስህ ጋር አውራ ስሜትህን ፈትሽ
ተይቅ አንተነትክን ከውስጥህ ተማከር
አስተውልና አድምጥ የልብህን ነገር
ላፍታ ብቅ ብለው ሳይቆዩ ሚተኑ
አሉና ስሜቶች ጤዛ አይነት የሆኑ
እስከ መች ነው ፍቅርህ ??
መልስ አለህ ወይ ለዚህ ??
እንደው እንበልና ባምንህ ያልከውን ቃል
ይህ ያሁን ስሜትህ እስከመች ይዘልቃል ?
በላ ንገረኛ ••••• 😉
በወጉ ተረድተህ የአፍቃሪን ትርጉም
ከጎኔ ሳትርቅ በክፉም በደጉም
መኖር ሲያነቅፈኝ እጆቼን በመያዝ
የሂዎት መንገዴን አብረኸኝ ልትጓዝ
የቱን ያህልስ አስበሀል ?
ከራስህ ጋር አውርተሀል ?
ለሳቅ ለደስታዬ እየሆንክ ሰበብ
ከሁሉ አስቀድመህ ስለኔ በማሰብ
አጥፍቼ ስታየኝ ሳሮጥ ለወቀሳ
አሳልፈህ ለሰው ስሜን ሳታነሳ
ቁጭ አርገህ እጎንህ
ደባብሰህ በጆችህ
ከፍቅረኛም አልፈህ ሁነህ መምህርም
ልትመክረኝ በጥበብ ስተቴን እንዳርም
ምን ያህል ብርቱ ነህ ?
ወደደድኩሽ ያልከውን ለማሳየት ሁነህ
ከጠብ በላይ ለይቅርታ ፣
ከውሼት ይልቅ ለእውነታ
ቅድሚያ ሰጥተህ ፍፁም ታምነህ
ለምኞቴ ለእቅዴ አጋዥ ሁነህ
ጎደሎየን ልትሞላ ልታደርገኝ ሙሉ እመቤት ኮርተህብኝ ልትመርጠኝ ለጎጆህ ሴት
የቱን ያህል አስበሀል ?
ከራስህ ጋር አውርተሀል?
🤷‍♂••••• መልስ ይኖርህ ይሆን •••••🤷‍♂
ስማኝ እየውልህ
አቋሜን ልንገርህ
ማሬ ውዴ በሚል የውሻሸት ተረት
መግፋት አልፈልግም ፍቅርን በወረት
ለግዚያዊም ስሜት በጭፍን ተጉዤ
የሴትነት ክብሬን ፈቅጄ ሰርዤ
ከሂዎት ለማርፈድ በድሜዬ አልቀልድም
አልፈልግም አዎ ፀፀትን አልወልድም
እናም እልሀለሁ ••••••
ወደድኩሽ ሞትኩልሽ ከማለትህ በፊት
ስሜትክን አበጥር ይዘህ የሀቅ ወንፊት
ልቤ የት ድረስ ነው
መውደድ የወጠነው
ፍቅሬስ እስከ መች ነው ያለመው አብሮነት
በልና እራስህን 🤔
ጠይቀው አፋጠው ሞግተው የእውነት
ቸር የምንሰማበት
ላንቺ ደስታ ኩራት
በተለይ ከዚህ ቤት
ይቀኙታል በእውነት

አንቺየ የኔ አለም
መሃፀነ ለምለም
መሰረት የሁሉም
ኑሪልን ዘላለም

ከማንም በላይ ነሽ
በእምነትሽ የገዘፍሽ
በጀግኖች የታጠርሽ
በውበት የደመቅሽ

አለን አለን አለን
አንቺን እየጠበቅን
በጉያችን ይዘን
ትንሳኤሽን ልናፈጥን
ካንቺው ደጅ ቆመን

🙏 💚💛❤ 🙏
ከዛ ከከተሜ እዬታዩ ደምቀው
በወረት ፍቅር ልቤን ከሚያደቀው
ይውሰደኝ ባላገር ፍቅሩ የማያልቀው// 😋
የሚኒስትሪ ተፈታኙ ኦቦ ሃሮ ቡሉልታ
#FastMereja
የ70 አመቱ ኦቦ ሃሮ በጉጂ ዞን ጎሮ ዶላ ወረዳ ነዋሪ ናቸው። አረጀው ብለው ትምህርትን አልተውም ተመዝግበው ተምረው እነሆ ዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈትነዋል። መልካም እድል ብለናል ለአባታችን 🙏