እትዮ መጽሐፍት መደብር
118 subscribers
39 photos
1 video
10 files
4 links
ማንኛውንም መጽሐፍት እዚህ ግሩፕ ላይ መለቀቅ ይቻላል ።
በእውቀት አዕምሮ ማዳበር ብልጠት ነው ።
ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋል ።
Download Telegram
​​✞ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ ✞

🥖 🥖 🥖 🥖 🥖 🥖🥖 🥖 🥖🥖 🥖 🥖

#ደብረ_ታቦር ✞

#ደብረ_ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው። ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው።

#ይሕስ_እንደ_ምን_ነው_ቢሉ:- አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር። በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም

ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር። በርግጥ ያንን ነደ እሳት ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም።

ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል። እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል። ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-
1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12)
2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)
3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
4.አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6.ተራራውን ለመቀደስ
7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው።

ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር። እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት።

ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ። የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው። (ማቴ. 16:13)

መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው። ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ። እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::

በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ: ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ። "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል። ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::

በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ። አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት።

ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም። መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል።

በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው። በዚህም 3 ዳስ እንሥራ። አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል።

ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል። ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው።

እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው። አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ።

ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር። (ማቴ. ማር. ሉቃ. )

በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::

ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል። ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.)

ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-

"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"

ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን። ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 t.me/EthiopianOrtodoxTewahido 💚
💛 t.me/EthiopianOrtodoxTewahido 💛
❤️ t.me/EthiopianOrtodoxTewahido ❤
ሰውነታችን ያቀፋቸው አስገራሚ ሀቆች

✔ አንድ ሰው በአማካኝ በአመት ውስጥ 6,205,000(ስድስት ሚሊዮን ሁለት መቶ አምስት ሺህ) ጊዜ አይኑን ገጥሞ ይከፍታል፡፡

✔ስንኮሳተር በአማካይ አርባ ሶስት የሚደርሱ ጡንቻዎችን ስንጠቀም፡ በፈገግታ ወቅት ደግሞ በአማካይ አስራ ሰባት ጡንቻዎችን እንጠቀማለን፡፡

✔ አንድ አማካይ ሰው በህይወት ዘመኑ አስር ሺህ ጋሎን ያክል ምራቅ ያመነጫል፡፡

✔ሰዎች እያንዳንዳችን የየራሳችን የሆነ የተለያየ የምላስ አሻራ አለን፡፡

✔አንድ አማካይ ሰው በህይወት ዘመኑ ልቡ 300,000,000(ሶስት ቢሊየን ጊዜ ይመታል)

✔አንድ አማካይ ሰው በህይወት ዘመኑ 48 ሚሊየን ጋሎን የሚደርስ ደም በሰውነት ውስጥ ይረጫል፡፡

✔ለአንድ ደቂቃ ያህል ያለማቋረጥ ስንሳሳም 26ኪሎ ካሎሪ ኢነርጂ እናቃጥላለን፡፡

✔ አንድ አማካይ ሰው ሰውነት ውስጥ የሚገኘው:-
       ❖የሰልፈር መጠን በአንድ ውሻ ላይ ሊኖር የሚችል ማናቸውንም አይነት ተባዮችን የማጥፋት ፡
       ❖የካርቦን ጥርቅም ዘጠኝ መቶ የሚደርሱ እርሳሶችን የመስራት፡
       ❖የፖታሲየም መጠን ከፍተኛ የሆነ ዕሳት የመፍጠር፡
       ❖የስብ ክምችት ሰባት ያህል ሳሙናዎችን የመስራት:
       ❖የፎስፈረስ መጠን ደግሞ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ የሚደርሱ የክብሪት ፍሬዎችን የመስራት አቅም አለው፡፡

#ከቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት የተወሰደ

አንብበዉ ሲጨርሱ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ ═══◉❖◉════
◉⇲ @EthioBooksStore ⇲◉
◉⇲ @EthioBooksStore ⇲◉
ማንበብ ሙሉ ሰው ያረጋል ፡፡🙏

ክፍል 1 ቀደምት ጥበብ
በርባኖስ (the Black hole) ምንድን ነዉ?
የአለማትን የሳይንሱን ዘረፍ የፈተነዉ ፍንጩ እንኳ ለመስጠት የሚያስቸግረዉ በርባኖስ ምንድን ነዉ?
ቀደምት ኢትዮጵያዉያን ስለ በርባኖስ ምን ብለዋል?
ብራናወቻችን አለም ተመራምሮ ስላልደረሰበት የሚስጥራት ሁሉ ሚስጥር ስለሆነዉ ስለ አለማት አፈጣጠርና አመሰራረት እንዲሁም በርባኖስ ምን ይላሉ?

መልካም ንባብ.......
ቀደምት ኢትዮጵያዉያን አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ጥበብና ሚስጥር ተመግበዉ በዘመኑ ለሳይንስ ለቴክኒዎሎጂ እንቆቅልሽ የሆነ ምስጥራዊ እዉቀቶችን ና ጥበቦችን ትተዉልን አልፈዋል፡፡
እንዲሁም መለስ ብለን ታሪክን ስንመረምር፤ የተፃፉ ዶሴወችን ስናገላብጥ፤ የብራና መፃሆፍቶቻችንን ስንመረምር፤ አሁን ድረስ አለም ያልፈታቸዉ በረቀቀና በመጠቀ መልኩ ተብራርተዉና ተቀምጠዉ የሚገኙ አያሌ እዉቀቶች አሉ፡፡
ከነዚህም መካከል በምላት ና በስፋት ተብራርቶ የምናገኛቸዉ የአለማት አፈጣጠር ሚስጥራትን ነዉ፡፡
በዚህም የተነሳ የሚስጥር ማህበረሰብ የሚባሉት የምዕራቡ አለም ነገስታት አለምን አንድአድርጎ ለመግዛት ካላቸዉ ጉጉት የተነሳ የአዳም ልጆች ከሰለጠኑባት ከ ኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ የሚገኙትን የአራቱን አለማት አፈጣጠር ሚስጥራትና ጥበባት ለመበዝበዝ ያላሰቡት ሀሳብ ያለፈነቀሉትም ድንጋይ አልነበረም፡፡

ከሰማያዊዉ ህብረት ሃይላት ህብረት መፍጠር የቻሉት ኢትዮጵያዉያን በየዘመኑ ከአራቱም አለማት ሚስጥራትና በመረዳታቸዉ በዘመናቸዉ ብርቱና ሀያል ሁነዉ ከማለፋቸዉ ባሻገር በመንፈሳዊ ፅናትና አቋማቸዉ ምክኒያት ወደ ሀገራቸወ ሲመጡ ለነበሩት ቅዱሳን ይህኔን ጥበባት አስተምረዋል፡፡
በምዕራባዉያን ሳይንስና ቴክንሎጂ የህዋ ምርምር ተቋማት ሚስጥራቸዉ አልፈታም ብለዉ ከተዘረዘሩት አንዱና ዋናዉ በርባኖስ ወይም ብላክ ሆል በመባል ይታወቃል፡፡
ስለዚህ ሚስጥራዊ ቦታ የተለያዩ ተመራማሪወች ሀሳባዊ መላምቶቻቸዉን አስቀምጠዋል ሁኖም ግን ከመላምታዊ ድምዳሜ የዘለለ አንዳችም ተጨባጭ ነገር ለመናገር አልቻሉም፡፡
ነገር ግን ቀደመት ኢትዮጵያዉያን ምሁራን በሚደንቅ እና በሚረቅ ትንታኔ አስቀምጠዉልን አልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ አለማት 20 ሲሆኑ 14ቱ የሳትና የምድር ሲሆኑ 6 ደግሞ የነፍስና የዉሃ ናቸዉ፡፡
የሳት ፣የምድር፣ የነፋስ፣ እንዲሁም የዉሃ አለማት በመባል የሚታወቁ ጠቅለል ሲሉ አራት አለማት በመባል ይታወቃሉ፡፡
የሳት አለማት የሚባሉት 9 ሲሆኑ የምድር አለማት ደግሞ 5 ናቸዉ ፡፡
በ14 አለማት ዉስጥ የሚገኙት ፍጥረታት አንዳቸዉ ከአንዳቸዉ ግንኙነት የሚፈጠርባቸዉ ህቡዕ መንገዶች የሀይላቸዉ ማረፊያና ማደሪያ የሆኑ 12 የተለያዩ ቦታወች አሉ፡፡
እነዚህ የአለም ሀገራት black hool ብለዉ የሚጠሯቸዉ ከእነዚህ የተለያዩ ቦታወች 6ቱን ነዉ፡፡
የሳት አለማት የሚባሉት እጂግ በሚያንፀባርቅና በነበልባል በተከበበ ከፍተኛ በሆነ የሃይል መጠን የሚገኙባቸዉ አለማት ናቸዉ፡፡
እኒህ 20 አለማት በዝርዝር እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል፡፡
ዘጠኝ የእሳት: አምስት የመሬት: አራት የውሃና ሁለት የንፋስ ዓለማት ናቸው።

ሀ. የእሳት ዓለም ( በቁጥር 9 ዘጠኝ ናቸው ) ከላይ
ወደ ታች ሲቆጠሩ :-
1 ጽርሐ አርያም ( የእግዚአብሔር የምስጋናው አዳራሽ )
2 መንበረ መንግሥት/ስብሐት ( የጌታ ዙፋን ያለባት )
3 ሰማይ ውዱድ( በአራቱ እንስሳዎች ክንፎች ላይ የተዘረጋ ሰማይ )
4 ኢየሩሳሌም ሰማያዊት/ ዛዶር ( በመጀመሪያ
ሳጥናኤል የተፈጠረባት በኋላም ከእሱ ተነጥቃ ለአዳም ልጆች የተሰጠች )
5 ኢዮር ( የአርባው ነገድ የመላእክት ከተማ )
6 ራማ ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ )
7 ኤረር ( የሠላሳው ነገድ የመላእክት ከተማ )
8 ምጽናተ ሰማይ ( ባህረ እሳት )
9 ገሀነመ እሳት ናቸው።
አዳም አባታችን በዚች እኛ በምንኖርባት ምድር ከመሰልጠኑ አስቀድሞ ምድር ለሰባት ተቆርሳ ወይንም ተከፍላ ነበር። ይህ ማለት እንግዲህ ከምድራችን ጋር ተመሳሳይ የሀይል የጊዜና የግዝፈት መጠን ያላቸው ነገር ግን የማናውቃቸው ስድስት የመሬት ክፍሎች አሉ። እነዚህ በስድስት የተከፈሉ ሰባት የምድር ክፍሎች
የሚከተሉት ናቸው:፡
1,መሬት(እኛ አሁን የምንገኝበት)
2, ብሔሞት
3, አራዊት ብቻ የሚገኙበት
4, እሳት ብቻ የሚገኝበት
5, በረድ ብቻ የሚገኝበት
6, ሌዋታን
7, በርባኖስ (ጨለማ ስፍራና እስርቤት)
የስነፍጥረት አንድምታ መፅሐፍ እንደሚያስረዳው ኢዮር ራማና ኤረር አሰራራቸዉ አራት ማዕዘን ሲሆን ሰባት የሳት ቅፅርና ሰባት የሳት መጋረጃ የጋረዳቸዉ የሳት አለማት ናቸዉ፡፡ እኒህ አለማት ከሰዉ በተሰወረና ከመላእክት እንኳ በረቀቀ መልኩ ይገናኛሉ፡፡
አራት ማአዘን ቅርፅ ይዛ የተፈጠረችው ምድር ለሰባት ከተከፈለች በኃላ
ውሃ መላት። አንዳቸውን ከአንዳቸው እንዲሁ ውሃ ለያቸው።
በዚህ የተነሳ መሬትን እኛ የምንገኝባትን ውሃ ከበባት በዚህ
የተነሳ መሬት ክብ ናት የሚል ግንዛቤ ኖረን።
ከአራቱ አለማት አንዱ የሆነው መሬት አምስት ሰማያትን
ጠቅልሎ ይዟል እነርሱም ሲዖል ፣ መሬት፣ ብሔረ ብፁአን፣
ብሔረ ሕያዋን፣ ገነት ናቸው።
ከነዚህ መካከል መሬት ከላይ
እንዳየነው የሰው ልጅ በቅጡ ያልተረዳቸው ስድስት ክፍሎችን
ይዛለች።
ይቀጥላል ...

አንብበዉ ሲጨርሱ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ ═══◉❖◉════
◉⇲ @EthioBooksStore ⇲◉
◉⇲ @EthioBooksStore ⇲◉
በመጀመሪያ ከሁሉ አስቀድሜ አባቶቼ እናቶቼ ወንድሞቼ እህቶቼ ጓደኞቼ
ሁላችሁም በልዑል ሃያል በእግዚአብሔር ስም ሁላችሁንም የበደልኳችሁ የበደላችሁኝ ያስቀየምኳችሁ ያስቀየማችሁኝ በሙሉ ይቅርታ አርጉልኝ እኔ ይቅርታ አርጌላችኋልሁ

ዝም ማለት አይቻልም
አሜን በሉ

🌼🌼ፈጣሪ በአዲሱ አመት🌼🌼
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ታሞ ከመማቀቅ፣
በብድር ከመሳቀቅ፣
ተፈትኖ ከመዉደቅ፣
የምንወዳትን ቺክ ከመነጠቅ፣
ይሰዉረን !✨
🌼
ከሰዉነት አንሶ እንስሳ ከማከል፣
የራስ እያረረ የሰዉ ከማማሰል፣
ለዘር ለጎጠኝነት ዱላ ከማቀበል፣
በቸልተኝነት ጉዞ ሚስኪኑን ከመበደል፣
ይሰዉረን !! ✨✨
🌼
ፈገግ ብለዉ ከሚገሉን፣
ጀነን ብለዉ ከሚያዋርዱን፣
ደንዘዘዉ ከሚያደነቁሩን፣
እሱ ይሰዉረን! 🙏
🌼
ሀብታም ሆኖ ሰገጤ፣
ድሃ ሆኖ አራዳ፣
አዕምሮ ይዞ ዘረኛ፣
ሀብት ይዞ ጎጠኛ፣
ከመሆን ይሰዉረን!! 🙏
🌼
ከባለሃብት ቋጣሪ፣
ከእነቅልፋም ታታሪ፣
ከወንድ ፈሪ፣
ከሴት አስነዋሪ፣
ይሰዉረን! 🙏
🌼
ከመሪ ሸረኛ፣
ከሴት ነገረኛ፣
ከወንድ ጉረኛ፣
ከማህፀን በረኛ፣
ይሰዉረን! 🙏

#መልካም_አዲስ_አመት
*
ዝና በሉ እሰቲ

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ

ጥቅሶቹን ተጋበዙልኝ

• ሁሉም ሰው ጠላቴ ነው ብለህ ስታስብ በዙርያ ያለው ሰው ሁሉ ጠላትህ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡

• የቱንም ያህል ጎበዝ ብትሆንም እንዴት ከሰው ጋር መስራት እንዳለብህ ካላወክ ተሸናፊ ነህ፡፡

• ምርጥ ሰዎችን ሳይሆን ትክክለኛ ሰዎችን ፈልግ፡፡

• ዛሬ ከባድ ነው፡፡ነገ እንዲሁም ይከፋል፡፡ተነገ ወዲያ ግን ፀሐይ ትወጣለች፡፡መቼም ተስፋ አትቁረጥ፡፡

• ሊኖሩን ከሚገቡ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች መካከል ትዕግስት ዋነኛው ነው፡፡

• ከተፎካካሪህ መማር እንጂ መኮረጅ የለብህም፡፡ኮርጅ.... በኋላ ግን ትሞታለህ፡፡ ”

• ገንዘብ አላጣንም፡፡ያጣነው ህልመኛ ሰዎችን ነው፡፡ብርቅ የሆኑት ለህልማቸው የሚሞቱ ሰዎች ናቸው፡፡

• መስፈርቱን የሚያሟሉትን አትቅጠር፡፡እብድ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ቅጠር፡፡

• በህይወት የሆነ ነገር ስትሞክር፣ የሆነ ነገር ላይ ጠንክረህ ስትሰራና የሆነ ነገር ስትለወጥ መጥፎ ነገር መከሰት ያቆማል፡፡

• ሰው ምንም ያድርግ ምንም፣ ተሳካለት አልተሳካለት ከስራው የሚያገኘው ልምድ በራሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡

• ተስፋ ካልቆረጥክ አሁንም እድል አለህ፡፡

ለሌሎች ሼር ያድርጉ

@EthioBooksStore

መልካም ጊዜ
ተፈትተሽ ኑሪ

መምህር ኤፍሬም ተስፋ

የሁለቱ ቆነጃጅት ወጎች

መምህር ኤፍሬም ተስፋ

ቄስ ማጋባት አልሻም የቆሎ ተማሪ

ያንን ድሀ መሳይ ያንን ጦም አዳሪ

ለነምሳው ድጓ ለነራቱ ቅኔ

ከነሱ ላንዳቼው ሚስት አልሆነም እኔ።

እያለች ስትቦርቅ ስትስቅ ስታሽካካ

የተማሪው ጮኛ ትሰማለች ለካ።

ተማሪ ተማሪ ሲሉሽ

ከአውሮፓ የመጣ ዶራል መሰለሽ?

መቋሚያው ወርቅ ነው መጠምጠሚያው ሻሽ።

የተማሪው ከንፈር ማሪቱ ማሪቱ

ውዳሴ ማርያምን የደገመባቱ

አወ ካንች አታርፍም አትወድቅም በከንቱ።

በሰማይ በምድር ደሞዝ የሚበላ

እስኪ ሰው ጥሪልኝ ከየኔታ ሌላ።

በየሔደበቱ ስሙ የሚጠራ

ተናግሮ ሚወደድ ተቆጥቶ ሚፈራ

መምህሬ አይደለም ሆይ የሕዝባችን አውራ።

ይህንን ስትመልስ የተማሪው ጮኛ

የዜማው አድናቂ የቅኔው ምርኮኛ።

ኮረዳዋ ደግሞ አጭር ሱሪ ለብሳ

ኧረ ባክሽ ዝምበይ አካበድሽውሳ።

ጭፈራቤት አይወስድ ምሽት አያዝናና

አይዘፍን አይደንስ አይስም በጎዳና

ሁሌ መቅደስ መቅደስ ቅዳሴ ቅዳሴ

እሱን ተከትዬ ልሆን ነው መነኩሴ?

የተሜ ፍቅረኛም ፈገግ አለችና

ምን አልሽኝ ውድዬ አይስም በጎዳና?

ከቶ ለመሆኑ ዳንስና ጭፈራ

ለማን ትዳር ሆነ የማነን ቤት መራ

ደግሞ የምሽቱ የዘፈኑ ነገር

አንች ምትፈልጊው ትዳር ወይስ አዳር?

የኔስ እርካታየ ያእምሮየ ደስታ

የፍቅሬ ማርከሻ የልቤ ትዝታ

የሐይቁ ገዳም ነው የውሀውላይ ካርታ

የቅኔው ቀመር ነው የእጣኑ ሽታ

የድጓ ቅኚቱ የመጽሐፉ አንድማታ

መላ ሰውነቴን መጥቶ እየወረረኝ

እሱ ነው በፍቅሩ ነብሴን የሠወረኝ።

ባለአጭር ሱሪዋ ጠይሟ ኮረዳ

በተሜ ፍቅረኛ በመልሷ ተናዳ

የምትለው አጥታ የምትናገረው

ከንፈሯ ተጋጭቶ ሜካፕ እስኪነስረው

እየተበሳጬች ኃይለቃል አውጥታ

እንኳንም አልኖረኝ ቄስ ያገባ ዘመድ

መንቀሳቀስ የለ ከወደዱት መሔድ

መታሠር ነውኮ በረቀቀ ገመድ።

አግብቶ ማይፈታ ፈቶ ማያገባ

ለሱ ብቻ ትርገፍ የውበቴ አበባ?

የተሜው ፍቅረኛም ይበቃሻል ውዴ

እኔ እድለኛ ነኝ እሱን በመውደዴ።

የቀናትን ቀመር ቀሞሮ ሚገፋ

ሰማይን በመሥጢር ቀዶ የሚሰፋ

የእውቀት ሠረገላ የጥበብ ፈላስፋ

ተሜን በማፍቀሬ እኔ እንዴት ልከፋ?

ያልተቀነሰ ፍቅር ያልተቸረቼረ

ከልቡ ወጥቶ ለኔ እየተቼረ

ያልተበረዘ ውድ ሰጥቶኝ ስለኖረ

መቼ ከፋኝና ምኔ ተቸገረ

ማሕሌት ቆመ እንጅ ፈጥኖ እየበረረ

ጭፈራ ቤት ሒዶ ጥሎኝ አላደረ

አፍሽ እንዳመጣ እንደተናገርሽው።

ውበት አበባሽን ለብዙ ካቀድሽው

አበባ እርሻ ቦታ ሓጂና ነስንሽው።

ቄስ አግብቶ መኖር በፍቅር በተስፋ

መታሠር ነው ካልሽኝ ልብሽ ከተከፋ

የሚፈታ ይስጥሽ ወልዶ የሚጠፋ

በፍቅር መታሠር ከሆነሽ ገሀነም

ተፈትተሽ ኑሪ እስከዘለዓለም።
" እኔ አንቺን ስወድሽ "

እኔ አንቺን ስወድሽ ምክንያት አበጅቼ
ፍቅርሽን ስቀበል በገንዘብ ገዝቼ

አይደለም አለሜ ......

እኔ አንቺን ስወድሽ ከአፍ የዘለቀ
ከሰማይ እርቆ እጅግ በመጠቀ
ከጨረቃም ውበት ከፀሐይ ነፀብራቅ
ከአለም ብልጭልጭ በጣሙን በሚልቅ
በመልክሽ ፀአዳ በከንፈርሽ ውበት
በሽንጥና ዳሌ በቁመትሽ ልኬት
በምላስ ቅላፄ በአነጋገር ለዛ
አይደለም እወቂው በሚሆነው ጤዛ።
እኔ አንቺን ምወድሽ በአስተሳሰብ ልቀት
በውስጥሽ ማንነት ለኔ ባለሽ ስሜት
በሰጠሽኝ ፍቅር ፣
ለሰው ባለሽ ክብር ፣
በንፁህ ማንነት በተቸረሽ ፀጋ
እኔ አንቺን ስወድሽ የሰጠሁሽ ዋጋ

በዚ ነው አለሜ ......

በተዋበ ፍቅር ከልቤ ከተማ
ሳዘልቅሽ ሳስገባ ምንም ሳላቅማማ
ሳነግስሽም ውዴ አድርጌ ንግስቴ
ላልተውሽ ምዬ ነው እስከለተ ሞቴ።

በዳኒዘር
ተፃፈ በ13/07/13 ዓ.ም
#ለሰርጌ_ብቅ_በል 👰🥀😋
እኔ ፍቅር ስክብ አንተ ደግሞ ስትንድ
ብዙ እድሜዬ ሂዷል እንዲሁ ስትቀልድ
ለመውደዴም ብዬ ሰርክ ስንገላታ
ቆጥረኸዋል አንተ ልክ እንደ ጨዋታ
ታዲያ ዛሬ እኔም ቀልድህ ተጋብቶብኝ
ድርሻዬን ልጫወት እንደተኛህ ሄድኩኝ
🤷‍♀
🤷‍♀
መቻል ተሸክሜ የትግስት ቀንበር
ዕልፍ ብታክትም አንተን ለመቀየር
አልለወጥ ስላልክ ፀንተህ በማፌዙ
ወሰንኩኝ ልለቅህ አድክሞኝ መያዙ 😏
🏃‍♀
🏃‍♀
እናም ከተመቼህ ለመጪው ታህሳስ
ለሰርጌ ጎራበል ከመሞሸሪያው ዳስ 😜
#ይቅናህ_በመንገድህ 🤷‍♀👫👉❌
የኔና አንተ ነገር •••••• እንደዚህ ከሆነ
❣
በተቃርኖ ቀለም እህልውሀው ተፅፎ፣
ካንድነቱ ይልቅ ልዩነቱ ገዝፎ፣
ለዛ ያጣ ኩርፊያ ቤታችን ከዋለ፣
ከፍቅራችን ይልቅ ጠባችን ካየለ
እኔን ሆድ ካረገኝ አንተን ደሞ ጀርባ፣
ዃላናፊት አይነት ፍፁም ያልተግባባ፣
አንዱ ብቻ አስቦ
ባንድ እጅ አጨብጭቦ
አይገፋም እና ያብሮነት አቀበት
ይበቃናል ዛሬ መኖሩ የውሼት
ይቅናህ በመንገድህ ይቅናኝ በመንገዴ
ጠብም መፍትሄ ነው በሂዎት አንዳንዴ
ምን ይሉታል ይኸን-

ወደድኩሽ እያሉ ሰወችን መከመር
በማስመሰል ሀሳብ ህሊናን ማሳወር
ለሰው ይምሰል ብቻ ያልሆነውን ማፍቀር
ምን ይሉታል ይኸን ከማስመሰል በቀር

ለራስ ጥቅም ብሎ ሌሎችን መጉዳቱ
ደስታቸውን ነጥቆ ደስታውን ማብዛቱ
እራስ ወዳድ ሁኖ ሀገሩን መክዳቱ
ምን ይሉታል ይኸን የማይረባ ከንቱ

ብለው ቢጠይቁኝ መልስ ብፈልግም
አለም እኩል ሁና ሰው ቢለያይም
ያስመሰለ ሰው ግን ሂወቱ አያምርም
ብየ ነገርኳቸው ቢከብደኝ ምላሹም

ከዚያም ቀጠሉና
ለሰው ክብር ኑሮት አላማውን ያጣ
ሌሎቹን አንግሶ እራሱን የቀጣ
የሱን መኖር ትቶ ሌሎቹን ያኖረ
ከጥላቻው ይልቅ ፍቅሩ የጨመረ
ምን ይሉታል ይኸን ለሰወች የኖረ

ብለው ሲጠይቁኝ ምላሽ ስሰጣቸው
አምላክ አይጥለውም ብየ ነገርኳቸው

ግጥም ወዳጇ
✍አንቺና ቁንጅናሽ✍
እኔም ለኔ ስልሽ
ሌላም ሠው ሲመኝሽ
ተወዳደርኩ እኔም
የግሌ ላደርግሽ
ግና ምን ያደርጋል
መስፈርትሽ ይከብዳል
እንኳን እኔ ቀርቶ
እብዱም ደግሞ ያብዳል፡፡

✍✍.............
#እርሜን_ዛሬ_ብስቅ 😢
የ ልቤን እረመጥ በእንባ ሳጠፋ
ብሶት ሀዘኔ ጋር እንደዛ ስጋፋ
ቀን እስኪወጣልኝ ሁሉን ቻል አድርጌ
ብቻዬን ስከርም ከሰው ተሸሽጌ
ጎኔ ያልነበሩ እንዴትነህ ያላሉኝ
ከነ መፈጠሬም ከቶውን የረሱኝ
😢
እርሜን ዛሬ ብስቅ ጥርሶቼ ተገልጠው
ሊጠይቁኝ መጡ ምን አገኘ ብለው
#አቤቱ!!
መጣሁ ብለህ ቆየህ...
(ይኸው ካንተ ወዲህ)
ባህር ገማሽ ነቢ' አሻጋሪም ጠፋ፣
የጫንክብን ቀንበር....
ወገብ አስጎብጦን መንገዱ እየከፋ፣
አታጉረምርም!!! አልከኝ....
ሰይፍህን ፈርቼ ከንፈሬን ብነክሰው፣
ኩርኩም አንሶኝ ነው ወይ??....
የበደሌ ቅጣት ከዚህ የደረሰው?!!!
This is not fair
🙊🙊🙊🙊
​🍃ምነው_ሄደሽ_ቀርሽ 🍃


አምና ከዚህ ቀደም ባሳለፍነው ጊዜ
ቃል የገባሽልኝ የእምነት ንዛዜ
ስጠብቀው አለሁ ሆኖኛል ምርኩዜ
ፈፅሞ አልጠፍም የፍቅርሽ አባዜ

🍃እኔ ምልሽ ፍቅሬ🍃

ካንደበትሽ ወጥቶ የተገባልኝ ቃል
ፀንቶ ሳይሰበር ሲጠብቅሽ ኖራል
አንችን በመናፍቅ አመታት ጠብቃል
በቃልኪዳን ታስሮ ጨለማን ተሻግራል

🍃ታድያ ምን ገጠመሽ🍃

ለጠበቀሽ ነብሴ ምላሹን ነሳሽው
በደስታ አስውበሽ ሀሴትን ሞልተሽው
ከሄድሽበት ቆየሽ ፍቅሬን ከየት ጣልሺው
እንደወጣሽ ቀረሽ ጨለማን ሞላሺው።