የጎንደር እዝ ፋኖ የሰው በላውን ቡድን እርስ በርሱ አጫረሰው
(ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 18/2017)የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖን ከበባ ውስጥ አስገባለሁ ብሎ በሶስት አቅጣጫ የመጣውን የሰው በላ ቡድን ጥቂት ፋኖዎች በተጠና መልኩ መሃሉ በመግባት እርስ በርሱ እንዲጫረስ ማድረጋቸውን የእዙ ዋና አዛዥ ራስ አርበኛ ደርጄ በላይ ለኢትዮ 360 ገለጸ።
ከፍተኛ ሃይሉ ከነከባድና ቀላል መሳሪያው በተደመሰሰበት በዚህ ዘመቻ ካራማራ ክፍለ ጦርን ጨምሮ የእዙ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች በጋራ መሰለፋቸውንም አስታውቋል።
በስተምስራቅ በኩል ዛሬ ከመንዶካ ተነስቶ ወደ መርትራድ ፣ በስተምዕራብ በኩል ከቱመት ተነስቶ የቁጥር አንድ መገልበጫ መንገዱን በመያዝ ወደ መርትራድ ፣ እንዲሁም ከቱመት ቀጥታ መሐል መንገዱን በመያዝ በሶስት አቅጣጫ አዳሩን ሲጓዝ አድሮ የፋኖ ሃይልን ከበባ ውስጥ ለማስገባት ሞክሮ ነበር ይላል።
ግዙፉ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ግን የተጠናና ስልታዊ የውጊያ ስትራቴጅ በመንደፍ ጠላትን ስበው ወጥመዳቸው ውስጥ ማስገባታቸውን ይናገራል።
አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድም አብዛኛውን የደመሰሱት ሲሆን የቀረውም ቁስለኛ ሆኗል፣ከነሱ ጥይት ያመለጠውም እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጧል ብሏል።
የጠላት ሀይል አካሄድን በማጥናትና እንቅስቃሴውን በመቆጣጠር ጥቂት ልጆችን በግራና ቀኝ ባለው ጠላት መካከል በማስገባትና ተንኩሰውት እንዲወጡ በማድረግ እርስ በእርሱ እንዲጨራረስ ተደርጓልም ብሏል።
የራሳቸው ሞርተር ተኳሽ የወገኑንና የጠላትን ቦታ መለየት ተስኖት የራሱን ሰራዊት ሲጨፈጭፍ ውሏል ይላል።
ገዳዩ ቡድን በአሁኑ ሰአት የሞተውን ቁስለኛ ማንሳት አቅቶት አብዛኛውን ቁስለኛ ጥሎት ፈርጥጧል ሲል የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ ራስ አርበኛ ደረጀ በላይ ለኢትዮ 360 ገልጹዋል።

በሳማ ቀበሌ ለ84ኛ ክፍለ ጦር ድጋፍ ሊይደርግ የገባው የሰው በላ ቡድን ተራገፈ።
(ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 19/2017)የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር የነበልባል ብርጌድ በተሰው ሰማዕታት ስም ባወጀው በዘመቻ በዞ በአውራ ጎዳና 84ኛ ክፍለ ጦርን ለማገዝ ወደ ሳማ ቀበሌ የገባውን ገዳይ ቡድን በሳማ ጅሉ አገር አካባቢ የጠበቀው የፋኖ ሃይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎ መመለሱን የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ኢንጂነር ታደሰ ወንድሙ ለኢትዮ 360 ገለጸ።
ስው በላው ቡድን በተለያዩ ግንባሮች ሀይል በመጨመር በአውራጎዳና ቀበሌ 21ኛ ክ/ጦርን በእግር በማስገባት በሞጆ መስመር ለወራት በነበልባሎቹ በትር ሲበታተን ለነበረው 84ኛ ክ/ጦር ጭማሪ ሀይል ወደ ሳማ ቀበሌ መላኩን ይናገራል።
ይሄ ወደ አካባቢው እንዲገባ የተደረገው ሃይል በሳማ ጅሉ አገር አካባቢ ሲደርስም በፋኖ ሃይል በተሰነዘረበት ድንገተኛ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ መሆኑን አስታውቋል።
ነገር ግን በአካባቢው የነበሩት የነበልባሉ ፋኖዎች በሰነዘሩበት ጥቃት ሙትና ቁስለኛውን በአንቡላንሶች ጭኖ ወደ አረርቲ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል ብሏል።
ከአረርቲ ወደ ጨሌ መስመር ያመራው ሰው በላይ ሃይል በአጉጭ አገር እና ስብሌን ጋራ በነበልባል ፋኖዎች በተሰነዘረበት መብረቃዊ ጥቃት በየማሳው ተራግፉዋል፣አስከሬንና ቁስለኛውንም ወደ አረርቲ ሲያግዝ ውሏል ብሏል።
በሌላኛው ግንባር ወደ ድሬ ቀበሌ ለመግባት ሲቅበዘበዝ የነበረውን ይህንኑ ገዳይ ቡድን ኮርማ ሀገር ቀበሌ ህብስት ላይ ሲጠብቀው በነበረው የፋኖ ሃይል መራገፉን አስታውቋል።
ለአረርቲ ከተማ ቅርብ ወደ ሆነው ካምፕ አራዳ በር በመግባት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ በከፈቱት መብረቃዊ ጥቃት ከፍተኛ ሃይሉን አስከሬንና ቁስለኛ አድርገውት ተመልሰዋል ይላል።
በአውራ ጎዳና ወደ መልካጅሎም የገባው አረመኔው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ምሽት አካባቢ በነበልባሉ ፋኖዎች መራገፉን ይናገራል።
በጠዋቱ ከመልካጅሎ ወደ አረርቲ ሲያቀና ከላዲ አፋፍ ደፈጣ የዘረጉት ፋኖዎች በርካታ ሀይሉን ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል አገዛዙም በርካታ አስከሬኑን ወደ ሞጆ እየጫነ በጅምላ መቃብር ሲቀብር ውሏል ሲል ለኢትዮ 360 አስታውቋል።

በጎንደር የሰው በላው ቡድን ሕጻናትና አረጋውያንን ሲገል ስድስት ቤቶችንም አወደመ
( ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 19/2017)የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ የአጼዎቹ ክፍለ ጦር ደጃች አስናቀ ብርጌድ ፋኖዎች ብቻ በጎንደር ዙሪያ ለምባ አካባቢ የሰነዘሩበትን ጥቃት መመለስ ያልቻለው ገዳይ ቡድን ከአራት በላይ ህጻናትና አረጋውያንን ሲገድል ስድስት ቤቶችን ባስወነጨፋቸው ሞርተሮች ማውደሙን የክፍለ ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ የሺዋስ ቢተው ለኢትዮ 360 ገለጸ።
የሰው በላው ቡድን ከሞርተሩ ሌላውም የድሮን ጥቃት መሰንዘሩንና በዚህ ግን ኢላማውን በመሳቱ ምንም ጉዳት ሳያደርስ መክሸፉን ተናግሩዋል።
የአጼዎቹ ክፍለ ጦር ደጃች አስናቀ ብርጌድ ብቻውን ዛሬ በጎንደር ዙሪያ ይህንን የሰው በላ ቡድን ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ከአካባቢው እንዲፈረጥጥ አድርጎታል ብሏል።
አብዛኛው ሃይሉ ሙትና ቁስለኛ የሆነበት ይሄ የሰው በላ ቡድን በንዴት ተከታታይ የሞርተር ጥቃቶችን ወደ ንጹሃን መሰንዘሩን አስታውቋል።
በዚህም ጥቃት እስካሁን ከአራት በላይ ህጻናትና አረጋውያን የተገደሉ ሲሆን ስድስት የንጹሃን ቤቶችም መውደማቸውን አስታውቋል።
የቤቶቹ ፍርስራሾች ሲነሳሱ ምናልባትም የሌሎች ንጹሃን አስከሬን ሊገኝ ይችላል ሲልም ቃል አቀባዩ ፋኖ የሺዋስ ቢተው ለኢትዮ 360 አስታውቋል።