Ethio 360 Media
14.2K subscribers
773 photos
87 videos
3 files
4.8K links
ይህ የኢትዮ 360 ቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
አዲስ አበባ ተወጥራ ዋለች

(ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 14/2017)የአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በሰው በላው ቡድን ሃይል ተወጥራ መዋሏን የኢትዮ 360 የአይን እማኝ ምንጮች ገለጹ።

በተለይ ከብሔራዊ ቲያትር ሥታዲየምን ይዞ አራት ኪሎ የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ ነው የሚባለው ሃይል በብዛት በተጠንቀቅ ቆሞ መመልከታቸውንም ይናገራሉ።

ከተማዋ በዚሁ ሃይል በተወረረችበት ሁኔታ ውስጥ በየመንገዱ የሚገኙ ወጣቶች ደግሞ በገፍ ሲታፈኑ ማየታቸውንም የኢትዮ 360 ምንጮች ይናገራሉ።

ብሔራዊ ቲያትር ቤትና ሥታዲዮም አካባቢ ወጣቶች በገፍ እየተያዙ በሚኒ ባሥ ተሽከርካሪ ሲጫኑ እንደነበርም ተናግረዋል።

ከእሥጢፋኖሥ ቤተክርሥቲያን ፊት ለፊት ወደ አራት ኪሎ፣ ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወሥደው ጎዳና ላይ ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል በገፍ የገባው የኦህዴዱ የፖሊስ ሃይል እግረኞችን እያስቆመ ሲፈትሽ መመልከታቸውን አስታውቀዋል።

ሁሌም በፍርሃት ውስጥ እየራደ ያለው የሰው በላ ስብስብ ምን አዲስ ነገር እንደሰማና እንደተፈጠረበት ባይታወቅም ከወትሮው በተለየ መልኩ ከተማዋን አስወርሯት ውሏል ሲሉ የኢትዮ 360 የአይን እማኝ ምንጮች ተናግረዋል።
68 ያህል ቦታዎች ተለይተዋል
(ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 14/2017)የሰው በላ ቡድን በአማራ ክልል ተጨማሪ የድሮን ጥቃቶችን ለመፈጸም 68 ያህል ቦታዎችን መለየቱን የኢትዮ 360 ምንጮች አጋለጡ።
በርካታ ቦታዎችን ሲያጠና የቆየው ይሄው ገዳይ ቡድን 68 የሚደርሱ ቦታዎች ተለይተው ለኦህዴዱ አየር ኃይል ሪፖርት መደረጋቸውንም አስታውቀዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያልቸው ቁጥር ያላቸው የመረጃና የስለላ ሰዎች መሰማራታቸውንም ምንጮቹ ይናገራሉ።

በፋኖ ውስጥም አስቀድሞ ተመሳስለው እንዲገቡ የተደረጉና ለመረጃ እና ለስለላ ሥራ ተመልምለው የተቀመጡ ሆድ አደሮች መኖራቸውን አጋልጠዋል።
የሰው በላው ቡድን አየር ኃይል በቀን እና በሌሊት ጥቃት ለመፈጸም መሬት ላይ ከተሰማሩ የመረጃ ሰዎች ጋር በየሰዓቱ መረጃ ልውውጥ እያደረገ መሆኑንም ነው ምንጮቹ የጠቆሙት።
ሕዝብ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን ከድሮን እና ከአየር ጥቃት እንዲጠብቅ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚያሳስቡት ምንጮቹ የፋኖ ሃይሎችም በውስጣቸው ሆኖ ጥቆማ ለመስጠት የተዘጋጀውን የባንዳ ቡድን አስቀድመው ሊደርሱበት ይገባል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አስቀድሞ የፋኖ ሃይል አመራሮች ያሉበትን አጥንቼ ጨርሻለሁ ያለው የሰው በላ ቡድን በተደጋጋሚ በፈጸመው የድሮን ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ንጹሃን የአማራ ተወላጆችን መፍጀቱንም ምንጮቹ አስታውሰዋል።
በጎጃም ባንዳዎች ተያዙ
(ኢትዮ 360 -ሚያዚያ 14/2017)በጎጃም ሰሞኑን ለተፈጸመው የድሮን ጥቃት አቅጣጫ ጠቋሚ የነበሩ ባንዳዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፋኖ ሃይል አመራሮቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ይህንን ጥቆማ የሰጡት በቁጥር አራት ባንዳዎች ሲሆኑ አሁን በቁጥጥር ስር የዋለው አንዱ ብቻ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
የራሱን ወገን ለማስጨፍጨፍ ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን የተቀበለውን ይህንን ባንዳ በቁጥጥር ስር ያዋለው የፋኖ ሃይል ምርመራ እያደረገበት መሆኑንም አመራሮቹ ጨምረው ገልጸዋል።
የድሮን አቅጣጫ ጠቋሚ ባንዳን በቁጥጥር ስር ያዋለው የፋኖ ሃይል በቢቸና ዋና የአማራው ጠላት ነው የሚባለውን ኮማደር ማናየን በቁጥጥር ውሏል ብለዋል።
ይሄኛው ባንዳ በቁጥጥር ስር የዋለው በስምተኛ ክፍለ ጦር ፋኖዎች መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ዛሬ ደሞ ባንዳው እቃና ውሃ ያመላልስበት የነበውን ግመል የአማራ ፋኖ በጎጃም ስደስተኛ ክፍለ ጦር በረህኛው ጅበላ ጎተራ ብርጌድ ፋኖዎች በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል።
የጎንደር እዝ ፋኖ የሰው በላውን ቡድን እርስ በርሱ አጫረሰው

(ኢትዮ 360 - ሚያዚያ 18/2017)የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖን ከበባ ውስጥ አስገባለሁ ብሎ በሶስት አቅጣጫ የመጣውን የሰው በላ ቡድን ጥቂት ፋኖዎች በተጠና መልኩ መሃሉ በመግባት እርስ በርሱ እንዲጫረስ ማድረጋቸውን የእዙ ዋና አዛዥ ራስ አርበኛ ደርጄ በላይ ለኢትዮ 360 ገለጸ።

ከፍተኛ ሃይሉ ከነከባድና ቀላል መሳሪያው በተደመሰሰበት በዚህ ዘመቻ ካራማራ ክፍለ ጦርን ጨምሮ የእዙ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች በጋራ መሰለፋቸውንም አስታውቋል።

በስተምስራቅ በኩል ዛሬ ከመንዶካ ተነስቶ ወደ መርትራድ ፣ በስተምዕራብ በኩል ከቱመት ተነስቶ የቁጥር አንድ መገልበጫ መንገዱን በመያዝ ወደ መርትራድ ፣ እንዲሁም ከቱመት ቀጥታ መሐል መንገዱን በመያዝ በሶስት አቅጣጫ አዳሩን ሲጓዝ አድሮ የፋኖ ሃይልን ከበባ ውስጥ ለማስገባት ሞክሮ ነበር ይላል።

ግዙፉ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ግን የተጠናና ስልታዊ የውጊያ ስትራቴጅ በመንደፍ ጠላትን ስበው ወጥመዳቸው ውስጥ ማስገባታቸውን ይናገራል።

አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድም አብዛኛውን የደመሰሱት ሲሆን የቀረውም ቁስለኛ ሆኗል፣ከነሱ ጥይት ያመለጠውም እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጧል ብሏል።

የጠላት ሀይል አካሄድን በማጥናትና እንቅስቃሴውን በመቆጣጠር ጥቂት ልጆችን በግራና ቀኝ ባለው ጠላት መካከል በማስገባትና ተንኩሰውት እንዲወጡ በማድረግ እርስ በእርሱ እንዲጨራረስ ተደርጓልም ብሏል።

የራሳቸው ሞርተር ተኳሽ የወገኑንና የጠላትን ቦታ መለየት ተስኖት የራሱን ሰራዊት ሲጨፈጭፍ ውሏል ይላል።

ገዳዩ ቡድን በአሁኑ ሰአት የሞተውን ቁስለኛ ማንሳት አቅቶት አብዛኛውን ቁስለኛ ጥሎት ፈርጥጧል ሲል የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ ራስ አርበኛ ደረጀ በላይ ለኢትዮ 360 ገልጹዋል።