Ethio 360 Media
14.2K subscribers
779 photos
87 videos
3 files
4.8K links
ይህ የኢትዮ 360 ቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
ከጥቂት ደቂቃዋች በኋላ በልዩ መረጃ ይጠብቁን



👇
ኢትዮ 360 Channel 225 የዛሬ መግብያ ነው።
👇
https://youtube.com/@legendary1m-p6i?si=gjGuKc-BQsm-bhVc


በየግሩፑ ሼር አድርጉት በውስጥ ተላላኩ
የኢትዮ 360 አድማጭ ተመልካቾች !
----------
ዛሬ እለተ ማክሰኞ በቴክኒክ ምክንያት መደበኛ ፕሮግራም በሰአቱ ለመጀመር የተቸገርን መሆኑን እያሳወቅን። ችግሩን ፈትተን ለቀጥታ ስርጭት ዝግጁ ከሆንን ቀደም ብለን የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን !
እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ታግተው የነበሩ በርካታ አሽከርካሪዎችን ከነንብረታቸው ነጻ አወጣ
(ኢትዮ 360 _ጥር 20/2017)የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር በአርኖ ጋርኖ ከጎንደር ባህርዳር በሰራው ዘመቻ ታግተው የነበሩ በርካታን አሽከርካሪዎች ከነተሽከርካሪዎቻቸው ማስለቀቃቸውን የክፍለ ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለኢትዮ 360 ገለጸ።
የአንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ጉዛራ ሻለቃን ስምሪት በመስጠትም ተሽከርካሪዎች እንዳይታገቱ ማድረጋቸውንም አስታውቋል።
የክፍለ ጦሩ የፋንይናንስ ሃላፊን ስምሪት በመስጠትም በቀጠናው ህጋዊ ኬላ እንዲኖር በማድረግ በኩልም ውጤታማ ስራ መሰራቱን ነው የሚናገረው።
ትላንትናና ዛሬ ከጎንደር ባህርዳር የተለያዩ ኦፕሬሽኖችን የሰራው ክፍለ ጦሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይታገቱና የጎንደር የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑት የቅባት እህሎችን በመጠበቅ በኩል እየተሰራ መሆኑንም ነው ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለኢትዮ 360 የገለጸው።
ድምጽ
በጎጃም የሰው በላው ቡድን በንጹሃን ላይ የሚፈጽመው አፈና እየከፋ መቷል
(ኢትዮ 360 _ጥር 20/2017)የአማራ ፋኖ በጎጃም ራስ መንገሻ አቲከም ወይንም አምስተኛ ክፍለ ጦር በሚመራቸው ቀጠናዎች ውስጥ የሰው በላው ቡድን በተቆጣጠራቸው ከተሞች ውስጥ የሚፈጸመው አፈናና ግፍ እየከፋ መቷል ሲሉ አመራሮቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ከ14 አመት ጀምሮ ያሉ ህጻናትና ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እያጋዘ ያለው ይሄው ቡድን ነፍሰጡር እናቶችን ጭምር የምትወልዱት ልጅ ነገ እኛን የሚወጋ ነው በሚል ስቃዩን አብዝተውባቸዋል ይላሉ።
ሁዲት ቀጠና ላይ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖት ከሃይማኖት ለማጋጨት የሚሰራው የባንዳ ቡድንም ቀጠናውን እየበጠበጠው ነው ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ይሄው የሰው በላው ቡድን ያሰማራቸውና በፋኖ ስም የሚነግዱ ስብስቦችም የሚሰሩት ስራ ሲነቃባቸው ጠቅልለው ወደ ገዳዩ ቡድን መግባታቸውንም ነው ያስታወቁት።
ድምጽ
በዘንዘልማ ጎንባት ቀበሌ ለመንቀሳቀሰ የሞከረው የሰው በላው ቡድን ሙትና ቁስለኛ ተደረገ።
(ኢትዮ 360-ጥር 20/2017)የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለ ጦር ባህርዳር ብርጌድ በዘንዘልማ ጎንባት ቀበሌ ለመንቀሳቀሰ በሞከረው የሰው በላው ቡድን ላይ በፈጸሙት ድንገተና ጥቃት ሰባቱን ላይመለስ ሲሸኙት 5 ደግሞ ማቁሰላቸውን አመራሮቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ባህርዳር ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው የተለያዩ ቀጠናዎች አንዱ በሆነው በዘንዘልማ ወይንም ልዩ ቦታው ጎንባት ቀበሌ ላይ የገዳዩ ቡድን ሃይል ዛሬ ለሊቱን ለመጓዝ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይናገራሉ።
በሌሊት ጉዞ በማድረግ እቅዱን ለማሳካት የተንቀሳቀሰውን ይሄ ሃይል ብዙም ሳይጓዝ የደረሰበት የፋኖ ሃይል 7ቱን ወደ አስከሬንነት ቀይሮና አምስቱን አቁስሎ ከመንገዱ አስቀርቶ ቁስለኛና አስክሬኑን ይዞ እንዲሄድ አድርጎታል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በአካባቢው ለጠላት መረጃዎችን በማቀበል፣በየመጠጥ ቤቶች እየዞረ መረጃዎችን በመሰብሰብና የወንዳጣ ኢየሱስ እናአባራጅ ጊዮርጊስ ልዩ ቦታው ጭቃ መደብ ጎጥ የ31 አርሶአደር የግል ትጥቃቸውን ከጠላት ጋር በመሆን ቤትለቤት እየዞረ ያስወሰደው ባንዳን ላይመለስ አድርገው እንደሸኙትም ነው ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ ያሰፈሩት።
የባህርዳር ከተማ ባለሀብቶችን ከሰው በላው ቡድን ጋር በመሆን፣ በመጠቆም እና በማገት የፋኖን ስም ሲያጠለሽ እና በህዝብ ዘንድ ፋኖ እንዲጠላ ሲያደርግ የነበረ ዋነኛ ተባባሪ ባንዳ ቻሌ ድልነሳ ልዩ ቦታው አባራጅ ላይ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል ብለዋል።
በምዕራብ ሸዋ ኖኖ ወረዳ የተወሰደባችሁን ርስት አስመልሱ በሚል የአማራው መሬት እየተነጠቀ ነው።
(ኢትዮ 360 -ጥር 20/2017)በምዕራብ ሸዋ ኖኖ ወረዳ የተወሰደባችሁን ርስት አስመልሱ በሚል በአካባቢው ህገወጥ ቡድን ያሰማራው የሰው በላ ስብስብ የአማራውን መሬት እያስነጠቀ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በሃሰት ክስ እንዲመሰርቱ የተደረጉት እነዚህ ህገወጥ ቡድኖች መሬት እስከመውሰድ መድረሱንም ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሰርግ ላይ የአማርኛ ዘፈን ከፈታችሁ በሚል ሙሽሮቹን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መደብደባቸውን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ይህንን የፈጸሙት ደግሞ ከቀበሌው ሊቀመንበር ጀምሮ በአካባቢው አመራር ናቸው የሚባሉ የባንዳ ስብስቦች መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
ድምጽ
ቀን ሰብስክራይብ ስታደርጉት የነበረውን የኛን ሳንገባበት ዘግተውታል ለነገ መግብያ ነው ሰብስክራይብ አድርጉ ፡፡
ኢትዮ 360 Channel 226 የነገ መግብያ ነው።
👇
https://www.youtube.com/@DcStudio-k2s
አድርጋችሁ ስትመለሱ Done ፈጣን ምላሽ
በየግሩፑ ሼር አድርጉት በውስጥ ተላላኩ
በየቀኑ ሲዘጉ በየቀኑ እንከፍታለን የያዝነው ትግል ነው ለ206 ኛ ጊዜ ከዩቱዩብ ወርደናል ::

ትግላችን እስከቀራኒዮ ነው ዩቱዩብ ቻናል በመዝጋት የሚቆም ትግል የለም

...ገጥመናል ገጥመናል 💪

ገጥመን መስሎኝ በፍጥነት 1000 SUBSCRIBE .‼️

አዲስ ድምፅ Channel 206 የዛሬ መግብያ ነው።
👇
https://www.youtube.com/@AddisDimts206
አድርጋችሁ ስትመለሱ Done ፈጣን ምላሽ
በየግሩፑ ሼር አድርጉት በውስጥ ተላላኩ