ኢንስቲትዩቱ የቤት እድሳት ማስጀመሪያ ኘሮግራም አካሄደ
------------------------
የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የኢንቲትዩቱ የስራ አመራሮች እና የወረዳው አመራሮች በተገኙበት የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ።
በመርሀ ግብሩም ከዚህ ቀደም ኢንስቲትዩቱ በከተማ ደረጃ የተጀመረውን ሰው ተኮር ተግባር በማጠናከር በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን እና በዛሬው እለት የተጀመረውን የቤት እድሳት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክብ ተገልጿል።

የጤናዉ ዘርፍ ሪፎርም ትግበራ የደረሰበት የጤና ሚኒስቴር፣ ተጠሪ ተቋማት እና ፌደራል ሆስፒታሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሄደ።
አገር አቀፍ የወባ በሽታ አሁናዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሣምንታዊ ግምገማ ተካሄደ
ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኔስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት አገር አቀፍ የወባ በሽታ አሁናዊ ሁኔታን አስመልክቶ በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል ትላንት ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም በበይነ መረብ ሣምንታዊ ግምገማ ተካሄደ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝን በተመለከተ የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል፣ የክልል ጤና ቢሮዎች፣ ክላስተሮች ወረርሽኙን ከመከላከልና ከመቆጣጣር አንጻር አሁናዊ ሁኔታ በሪፖርት የገለጹ ሲሆን የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግብቦችን በመጠቀም ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ እየተፈጠረ መሆኑን፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ የተለያዩ ንቅናቄዎችን በመፍጠር እና በቅንጅት በርካታ የመከላከል ስራዎች እተሰሩ መሆናቸውን፣ በአጎበር፣ በኬሚካል ርጭት እና በአካባቢው የተፈጠሩ የኩሬ ውሃዎችን የማፋሰስ እና የማድረቅ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን እንዲሁም ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ በቀጣይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የመከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚሰሩ ከሪፖርታቸው መረዳት ተችሏል፡፡
ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር እንደገለጹት የመረጃ አያያዝና ጥራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራው ስራ በሽታውን በመከላከሉ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን እና የተለያዩ የመከላከያ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ትልቅ ትኩረት በመስጠት ድጋፍ የሚፈልጉ ቦታዎችን የመለየት፣ ያሉትን የመከላከያ መንገዶች ሁሉ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው፣ የተጀመሩት የንቅናቄ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ አንዲሁም እስከ ሚቀጥለው ሳምንት የተሻሉ ለውጦች ማስመዝገብ እንደሚገባ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኔስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የወባ ወረርሽኝን በመከላከሉ ረገድ ትኩረት ሊሰጣቸው ስለሚገባቸው ጉዳዮች እና ቅንጅታዊ ስራዎችን እሰመልክቶ መደረግ ስለሚገባቸው ተግባራት አንስተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የመንግስትና የጤናዉ ዘርፍ የ100 ቀናት አፈፃፀም ላይ ተወያየ
------------------
የኢትዮዽያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ዶ/ር ሳሮ አብደላ እና ዶ/ር መልካሙ አብቴ እንዲሁም የማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ አጠቃላይ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞቸ በተገኙበት የ2017 ዓ.ም የመንግስትና ጤናዉ ዘርፍ የ100 ቀን አፈጻጸም ላይ ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም ዉይይት ተካሄደ።
በመድረኩ እንደመንግስት የታቀዱ ስራዎች ያለፉት መቶ ቀናት አፈጻጸም እና የማክሮ ፋይናንስ ሪፎርም፣ እንዲሁም ሌሎች ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ በዋና ዳይሬክተሩ ሪፓርት የቀረበ ሲሆን፤ የኢንስቲትዩቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትም ከቀርበ በኋላ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶባቸዉ መድረኩ ተጠናቋል።

የኮቪድ-19 ፓክስሎቪድ (Paxlovid) ማከሚያ መድሐኒት ውጤታማነቱ ተገመገመ
የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ዲቪዥን ከጤና ሚኒስቴርና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ፓክስሎቪድ (Paxlovid) የተባለ የኮቪድ-19 በሽታን ለማከም የሚያስችል መድሃኒት በአራት ክልሎች በተመረጡ 17 የጤና ተቋማት ላይ እየተካሄደ የሚገኘውን የሙከራ አፈጻጸም እና የተመዘገቡ ውጤቶችን አስመልክቶ ጥቅምት 19 እና 20/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የግምገማ መድረክ አካሄደ፡፡
የግምገማ መድረኩ ዋና ዓላማ ለ11 ወራት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውን የኮቪድ-19 በሽታን ለማከም ተፈጻሚ የተደረገው መድሃኒት ምን ያህል ጥቅም ላይ ውሏል፣ ወጤታማነቱ ምን ይመስላል፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት፣ በተግባራዊነቱ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው እና በቀጣይ መቀመጥ ያለባቸው አቅጣጫዎች ምንድን ናቸው የሚሉትን ለመገምገምና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ነው፡፡
አቶ አዳነ ወልደአብ የኢንስቲትቱ የኮቪ-19 ዲቪዥን አስተባባሪ በንግግር የከፈቱ ሲሆን የኮቪድ-19 የማከሚያ መድሀኒት ትግበራን እና አሁናዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተካሄደው የግምገማ መድረክም የኮቪድ-19 የማከሚያ መድሃኒት በተመረጡት የጤና ተቋማት ተግባራዊ በመደረጉ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸው በቀላሉ እንዲያገግሙ ማስቻሉን፣ በዚህም ምክንያት የሞት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ማድረጉን በመድረኩ የተረጋገጠ ሲሆን በቀጣይም ለተመረጡት ጤና ተቋማት በቂ የሆነ መድሃኒት እና መመርመሪያ ኪት በቅርቡ የሚሰራጭ መሆኑን እና በተለዩ ክፍተቶች ላይ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣የሆስፒታልና የክልል የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች፣ የተመረጡ መንግስትና የግል ጤና ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የአጋር ድርጅት ተወካዮች በመድረኩ ተሳትፈዋል፡፡