Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
12.1K subscribers
5.57K photos
42 videos
136 files
1.48K links
EPHI one of the oldest and known public health institutes in Africa. It is open 24/7 for public health emergency management through Emergency Operation Center.

For any information and help call 8335 or send us a message through ephieoc@gmail.com
Download Telegram
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ በይፋ ስራ ጀመረ
------------------
በወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ጊቢ የሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ዛሬ ሚያዝያ 29/2017 በይፋ ስራ ጀመረ።

ዶ/ር ሳሮ አብደላ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክትር በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ላቦራቶሪው ለክልሉ ሕብረተሰብ ጥራት ያለውና የላቀ የጤና ምርመራ አገልግሎት መስጠት የሚችል እና ከ30 በላይ የበሽታ አይነቶችን መመርመር የሚያስችል ማሽኖች በላቦራቶሪው እንደሚገኙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ጠቅሰው፣ የጨቅላ ህፃናት የኤች አይ ቪ፣ የጉበትና መሰል በሽታዎችን በጥራት መመርመር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክትርን መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዮቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማር ባርባ እንደገለፁት በዓለማችን ላይ በተለያዩ ለውጦች ምክንያት የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶች እየጨመሩ ይገኛሉ፡- ተላላፊና ዳግም እየተከሰቱ የሚገኙ በሽታዎች፣ የፀረ-መድሃኒት ብግርነት መጨመር፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች መበራከትና እየከፋ መምጣት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ቀድሞ መተንበይ፣ መከላከል፣ መቆጣጠርና ምላሽ መስጠት እንደ አመራር ከኛ የሚጠበቅ ግዴታ ስለሆነ ይህ ላብራቶሪ ይህንን ኃላፊነታችንን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችለን መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የጤናው ዘርፍ ልማት ኢንቨስትመንት ዕቅድን ለማሳካት የሕብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ማቋቋም፣ በቴክኖሎጂ በማዘመን ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ እስረድተዋል።

የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በበኩላቸው በክልሉ ከዚህ ቀደም የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ባለመኖሩ፣ የምርመራ አገልግሎት ከሌላ ስፍራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ክልላዊ ላቦራቶሪ መቋቋሙ ይህን መሰል ችግሮችን በመቅረፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አብራርተው፣ በክልሉ ለተቋቋመው የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ እውን መሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ከላቦራቶሪው ይፋ ማስጀመሪያ ስነ ስርዐት በፊት ዶ/ር ሳሮ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከክልሉ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የተለያዩ ሆስፒታሎችንና የጤና ተቋማትን ጎብኝተዋል።
www.ephi.gov.et/news
የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ምርምር ዘርፍ የበጀት ዓመቱን የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ገመገመ
------------------
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ምርምር ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፣ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና፣ በዘርፉ ስር ያሉ የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች፣ የኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ ግንቦት 1እና2/2017 ዓ.ም ተካሄደ።

መድረኩ ባለፉትዘጠኝ ወራት የምርምር ዕቅድ አፈፃፀም ወቅት የተከናወኑት የምርምር ስራዎች ለሕብረተሰብ ጤና ፓሊሲና ፕሮግራም ማጠናከሪያ በግብአትነት ለመጠቀም፣ በጠንካራ አፈፃፀም የተገኙ የምርምር ውጤቶች በህትመት ተለይተው የሚቀርቡበትና ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር የልምድ ልውውጥና የምርምርና ጥናት ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው:: የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በፕሮግራሙ ሲከፍቱ እንደገለፁት ኢንስቲትዩቱ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባራት በዝርዝር ጠቁመው ኢንስቲትዩታችን ከመንግሥት በተሰጠው ሃላፊነትና ተግባር ከተልዕኮ አንፃር በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል በማለት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጣም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ተመራማሪዎች በከፍተኛ ትጋት የሰራችኋቸዉ ስራዎች ዉጤታማ እንደሆኑ በሚደረጉ ክትትሎችና በቀረበው ሪፖርትም ማየት ችለናል ካሉ በኋላ ባጠቃላይ በጣም ጥሩ ስራዎች እንደተሰሩ ገልፀው ሊሻሻሉ የሚገቡ ስራዎች በሚገባ ተለይተው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰራባቸው እንደሚገባ ከገለጹ በኋላ አያይዘውም ኢንስቲትዩቱ ከአምስት በአፍሪካ ዉስጥ ካሉ ከተመረጡ ኢንስቲትዩቶች ተወዳድሮ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር የልዕቀት ማዕከል በመሆን መመረጡን፣ ኢንስቲትዩቱ ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር በኩል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን፣ ከአጋር አካላትም ከአጋር አካላትም ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝና ወደፊትም ከክልሎች ጋር በመሰራት ላይ እንዲሁም የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው በመናበብና በቅንጅት እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በበኩላቸው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ኢንስቲትዩታችን በ100 አመት ሂደት ዉስጥ እስከአሁን በአጠቃላይ ሲሰራ የነበረው የምርምር ስራዎች ዉስጥ የተሰጠውን ተልዕኮና የተለያዩ አደረጃጀቶች አልፎ ዛሬ የቆመበት እና አሁን ያለበትን በምርምር፣በሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከል፣በላብራቶሪ እና በዳታ ማኔጅመንት ላይ የፓሊሲ ግብአት የሚሆኑ መረጃ የማመንጨት ተግባራትን ሲያከናዉን የነበረ እንዲሁም በማከናወን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው በማለት ተናግረዋል።

የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሮችና የምርምር ዳይሬክተሮች በግምገማው ላይ በመገኘት በክልሎች እየተሰሩ ያሉ የምርምር ተሞክሮዎችን በማቅረብ የልምድ ልውውጥም ተደርጓል:: የዚህ አመት ዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ውይይት ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ ለፖሊስና ፕሮግራም ግብአት የሚሆኑ የምርምር ስራ ህትመቶችና ውጤቶች በአውደ ርዕይ ቀርበው በጥያቄና መልስ ተሞክሮዎች በቂ አስተያየት የተሰጠበት እንዲሁሞ ለቀጣይ ስራ የምርምር አጀንዳ የሚሆኑ ግብአቶች ትኩረት ያገኙበት የግምገማ መድረክ ነበር::
www.ephi.gov.et/news