የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
Status update on #COVID19Ethiopia
https://t.me/EthPHIEPHIET
https://www.facebook.com/EPHIET
https://twitter.com/EPHIEthiopia?s=09
Status update on #COVID19Ethiopia
https://t.me/EthPHIEPHIET
https://www.facebook.com/EPHIET
https://twitter.com/EPHIEthiopia?s=09
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
Status update on #COVID19Ethiopia
https://t.me/EthPHIEPHIET
https://www.facebook.com/EPHIET
https://twitter.com/EPHIEthiopia?s=09
Status update on #COVID19Ethiopia
https://t.me/EthPHIEPHIET
https://www.facebook.com/EPHIET
https://twitter.com/EPHIEthiopia?s=09
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የነጭ ሪቫን ቀንን ምክንያት በማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ሴቶችና ወጣቶች ፎረም ጋር በጋራ በመሆን ልደታ አካባቢ በሚገኘው ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት መጠለያ ማእከል ተገኝቶ በመጎብኘት ለማእከሉ ተጠቃሚዎች ተላላፊ በሆኑ በሽታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ለመጠለያው አገልግሎት የሚውል የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ግብአት ድጋፍ ተደርገጓል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በተጨማሪም ለመድሀኒአለም የሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት ለስርአተ ጾታ ክበብ የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ በማድረግ በአሉን አክብሯል፡፡
ባለፉት 30 አመታት በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ጤና ላይ የተካሄደዉ ጥናትና ምርምር ዉጤት ይፋ ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ካዉንት ዳዉን 2030 የጥናት ምርምር ቡድን ጋር በመተባበር የእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት የጤና ክብካቤ ሽፋን፣ የሞት መጠን ቅነሳን አስመልክቶ አገር አቀፍ መረጃዎችን በመተንተን ከ1990-2019 የተመዘገቡ ዉጤቶችን በመፈተሸ ያካሄደዉን የጥናት ውጤት ታህሳስ 13/4/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ለባለድርሻ አካላት ባካሄደው አውደ ጥናት ይፋ አደረገ፡፡
የእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅነሳ እ.ኤ.አ ከ1990 እስከ 2019 እንዲሁም ከ2016 አስከ 2020 የጤና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም ግምገማዊ ጥናት የተካሄዱ የጥናትና ምርምር ግኝቶችን በአዉደ ጥናቱ ላይ ይፋ ተደርገዋል፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር በአዉደ ጥናቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት የካውንት ዳውን 2030 ኢትዮጵያ በትብብር የተሰሩ ጥናቶች ባለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በሀገሪቱ የእናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ሞትን ለመቀነስ የጤና ስርዓቱን ስኬቶችና ተግዳሮቶችና መንስዔዎች፣ የጤና ፖሊሲውን፣ ስትራቴጂውን፣ ፕሮግራሞች እና ዕቅዶች መረጃዎችን በመገምገም እና በመተንተን ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገ እምነታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸዉ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው ጥናቶቹ የወላድ እናቶችንና ጨቅላ ህጻናት ሞትን ለመቀነስ፣ አጠቃላይ የጤና ሽፋንን በማሻሻል በኩል እና የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ ትግበራ ለማሳለጥ ባለፉት አስርተ ዓመታት ውስጥ ተምሳሌታዊ ሆኖ ሊጠቀስ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተካሄደው ጥናት እንዳመለከተው ኢትዮጵያ የተለያዩ የስነ-ተዋልዶ፤ጨቅላ ሕፃናት እና ልጆች ጤና (RMNCH) ላይ ያተኮሩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመተግበሯ በ2000-2019 የእናቶች እና ጨቅላ ሕፃናት ሞት በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ መቻሉን፣ የእናቶች ሞት ምጣኔ በተመለከተ እ.ኤ.አ በ2000፣ በ100,000 በህይወት ከወለዱ እናቶች ከነበረዉ 1030 የሞት ምጣኔ በ2017 ወደ 401 የደረሰ መሆኑን፣ ይህም በ61 በመቶ መቀነስ መቻሉን በተለይም በቅርብ 10 ዓመታት ዉስጥ ከ2005 እስከ 2017 በግማሽ መቀነሱን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡
በተያያዘም በኢትዮጵያ የጨቅላ ህፃናት ሞት በ2000 ከነበረዉ 140,000 የሞት መጠን በ2019 ወደ 100,000 መቀነሱን፣ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ላሉ ህፃናት በ1990 ላይ የሞት መጠን 31 በመቶ ከነበረበት በ2010፣ 47 በመቶ የነበረ መሆኑን እንዲሁም በ2019 ከግማሽ በላይ (56 በመቶ) መድረሱን እና አጠቃላይ ጥናቱ የእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅነሳ ላይ ሲካሄዱ የነበሩት የተለያዩ ስራዎች የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻላቸውን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
በቀረቡት ጥናቶች ላይ ዉይይት ከመካሄዱም በላይ በኢንስቲትዩቱ፣ በጤና ሚኒስቴር እና በካዉንት ዳዉን የምርምር ቡድን በቀጣይ 2023 አስከ 2025 እ.ኢ.አ በጋራ በሚሰሩ የምርምር ስራዎች ላይ ዉይይት በማካሄድ የጋራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ ዳይሬክቶሬት ኃላፊዎች የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ የተለያዩ የምርምር ስራ ክፍል ኃላፊዎች፣ የክልል ጤና ቢሮዎችና ኢንስቲትዩቶች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችና አጋር ድርጅቶች በአውደ ጥናቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡