በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ የዝርፊያ ሙከራ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተሰማ።

ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም ለሊት 8፡00 አካባቢ የተማሪዎች መኝታ ክፍል በመግባት ዝርፊያ ለመፈጸም ሲሞክሩ ሦሥት ተማሪዎችን በስለት በመውጋት ጉዳት ማድረሳቸውን ጥቆማቸወን ለቲክቫህ ያደረሱ ተማሪዎች ገልጸዋል።

ይበልጣል ወርቁ የተባለ የዩኒቨርሲቲው የ4ኛ ዓመት የሶሲዮሎጂ ተማሪ ህይወት ማለፉን ሰምተናል።

በጉዳዩ ዙሪያ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን ያነጋገርን ሲሆን "ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑንና ምርመራው ሲጠናቀቅ አስያየት እንደሚሰጥ" አሳውቆናል።

ምንጭ፡ ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ
ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

ጉዳዩ፡ የእንቅስቃሴ ገደብ የተከለከለባቸው ቦታዎችን ስለማሳወቅ

በሁለተኛ ዙር ከታህሳስ 15 እስከ ታህሳስ 23/2015 ዓ.ም  የሚሰጠውን የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስመልክቶ ለዩኒቨርሲቲው ሁሉም ማህበረሰብ የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለባቸው ቦታዎች ስላሉ ወደ ተከለከሉ ቦታዎች ከመሄድ ተማሪዎች እንዲታቀቡ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

በዚህም መሰረት  ወደ ካምፓስ ሁለት ወይም ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት አካባቢ ያለውን አደባባይ አልፎ መሄድ እንዲሁም በተማሪዎች መግቢያ በር ኮብል/በር አንድ መግባትም ይሁን መውጣት እንዲሁም የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ክልከላውን በመተላለፍ ለሚደርሱ ተጠያቂነቶች ዩኒቨርሲቲው የትኛውንም አይነት ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑንም ጨምሮ አሳውቋል።
#መቐለ #ራያ #አክሱም #ዓዲግራት

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡

በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC
ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡

በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC
👍1
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ከጉጂ ዞኖች በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን ያልወሰዱ ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው ትላንት መቀበል ጀምሯል።

ተማሪዎቹ ነገ ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም ገለጻ የሚሰጣቸው ሲሆን ከታህሳስ 18 እስከ 21/ 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይታወቃል።

የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናም በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ የሚበልጡ የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን ዛሬ ተቀብሏል።

በተለያየ ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ 1 ሺህ 70 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።

ከተፈታኞቹ መካከል 752ቱ በተቋሙ ቴክኖሎጂ ግቢ የሚፈተኑ ሲሆን ቀሪዎቹ 318 ደግሞ በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ እንደሚፈተኑ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም ድረስ ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ ፈተናው ይሰጣል።
በተያዘው ዓመት መጨረሻ ራስ ገዝ የሚሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለራስ ገዝ አስተዳደር የሚያስፈልግ የአሰራር ማንዋል ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ አስተዳደር ሲኖራቸው ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የተሻለ ገቢ መሰብሰብ እንደሚያስችላቸው
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የራስ ገዝ አስተዳደሩ ምሁራን የአካዳሚ ነጻነት ኖሯቸው ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም በምርምር የተደገፈ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ያስችላልም ብለዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ አስተዳደር ነጻነት እንደሚሰጠው ከተገለጸ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ለራስ ገዝ አስተዳደር የሚመጥን የስነ-ልቦና እና የአሰራር ማኑዋል ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡
በመቐለ ከተማ የባንክ እና የስልክ አገልግሎት በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል
**********************

በትግራይ የነበረው ጦርነት በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌደራሉ መንግስት ከህወሓት ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት የተኩስ አቁሙን ተከትሎ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን የፌደራሉ መንግስት ማስጀመሩ የሚታወስ ነው።

በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም 27 የሚደርሱ የትግራ ከተሞች ላይ የስልክ አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም መቐለን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ትልልቅ ከተሞች የሀይል አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል።

ወደ መቐለ ያመራው የፌደራሉ መንግስት ልኡክ ለትግራይ ህዝብ እንዳረጋገጠው፥ በክልሉ ትልቅ ችግር የሆነው የባንክ አገልግሎት በቅርቡ ይፈታል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ባለሞያዎችን ወደ መቐለ እንዳሰማራ የጠቀሱት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፤ ባንኩ የሚስተካከሉ የሲስተምና የኦዲት ስራዎችን በዚህ ሳምንት አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በትግራይ የባንክ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ህብረተሰቡ ለከፋ ችግር እንደተዳረገ እንረዳለን ያሉት አቶ አቤ ሳኖ፤ ይህንን ችግር  በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከዛሬ ጀምሮ ባለሞያዎቻችን ወደ ስራ ገብተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የሰላም ጅምሩ እንዲፀና ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

በተመስገን ሽፈራው
👍1
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው።

ፈተናው ከዛሬ ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 21/2015 ዓ.ም በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

በተለያዩ ተቀባይነት ባገኙ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ በሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ለፈተና ይቀመጣሉ።

በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ትላንት የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ተሰጥቷቸዋል።
መቀሌ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘቷ ተገለጸ

በዛሬው እለት መቀሌ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ አስታወቁ።

የመጀመሪያው የስልክ ጥሪ በመቀሌ እንደተካሄደም ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።

ከሰላም ስምምነቱ ማግስት በተሰራ ስራ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል 27 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘት መቻሉንም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

የባንክ ብሎም የቴሌኮም ጥገና በማድረግ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንና 981 የኢትዮ ቴሌኮም ፋይበር ጥገና መደረጉን ተቋሙ አመልክቷል።

በክልሉ 61 ባንኮችም አገልግሎት መጀመሩን ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሊዮኔል ሜሲ ያረፈበት ክፍል ወደ ሙዚየምነት ሊቀየር መሆኑ ተነገረ
*********************

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሊዮኔል ሜሲ ያረፈበት ክፍል ወደ ሙዚየምነት ሊቀየር መሆኑ ተነገረ።

ታዲያ ድንቅ የዓለም ዋንጫን ማዘጋጀት የቻለችው ኳታር፣ በውድድሩ አስገራሚ ብቃትን ያሳየውን አርጀንቲናዊ ምትሃተኛ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ታሪክ ለማስታወስ የቆየበትን ክፍል ወደ ሙዚየምነት ልትቀይር መሆኗ ታውቋል።

ሜሲ አርጀንቲናን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ለክብር ሲያበቃ ያርፍበት የነበረው የመኝታ ክፍሉ ወደ አንስተኛ ሙዚየምነት መቀየሩ ሜሲ የዓለም ዋንጫን ለማንሳት የሄደበትን መንገድ ለአድናቂዎቹ ያሳያል ነው የተባለው ።

ሊዮኔል ሜሲ ሃገሩን በአምበልነት እየመራ ከ36 አመታት በኋላ ዋንጫውን እንዳነሳ እና እርሱም የውድድሩ ኮኮብ ተጫዋች መባሉ ይታወሳል።
ኹለተኛውን ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የገባችው ተማሪ ሴት ልጅ መገላገልዋ ተገለጸ

በምዕራብ ወለጋ ዞን ማንዲ ከተማ የኦሎንኮሚ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነችው ላሊስቱ ሆርዶፋ ኹለተኛውን ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተገኘችበት ወቅት ሴት ልጅ መገላገልዋ ተገለጸ።

ተማሪዋ በዩኒቨርሲቲው ሪፈራል ሆስፒታል ልጇን መውለዷ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት እናትየውም ሆነ የተወለደችው ልጅ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ዩንቨርስቲው አስታውቋል።
በስልጤ ዞን በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሲያስተምሩ የነበሩ 26 መምህራን እርምጃ ተወሰደባቸው!!

በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ 26 መምህርን እና 1 ባለሙያ በድምሩ 27 ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መገኘቱን የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት አስታውቋል ።

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን መሀመድ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደተናገሩት በወረዳው በ2015 ዓም በተደረገው የትምህርት መረጃ የ100 መምህርና የ141 የወረዳው የመንግስት ሰራተኞች በድምሩ 241 የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ መደረጉን አስታውቀዋል።

በእዚህም የ26 መምህራንና የ1 ክሊኒካል ሰርቪስ ባለሙያ በድምሩ 27 ግለሰቦች የትምህርት ማስረጃዎች ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱን ገልፀዋል።ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በተገኘባቸው አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የተነገረ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ 9 መምህራን እና 1 ባለሙያ በድምሩ 10 ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ ተይዞ ወደ ወራቤ ማረሚያ ቤት መላካቸውን አንስተዋል።

ቀሪዎቹ መምህራን ደግሞ በህግ እየተፈለጉ መሆኑን ገልፀዋል።በወረዳው ሀሰተኛ የትምህርት ማሰረጃ የማጣራት ሥራ ከ 2012 ዓመት ጀምሮ ከ1489ኙ የ516 የተጣራ ሲሆን (34 በመቶ) በመከናወኑ አጠቃላይ ሥራው ሲጠናቀቅ መረጃው ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ አቶ ኡስማን መሀመድ ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል።

ፈተናው ላለፉት አራት ቀናት ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ እየተሰጠ ቆይቷል።

በተለያዩ ተቀባይነት ባገኙ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ የሁሉም ክልል ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ፈተናውን እየወሰዱ ነው።
#Update

" የፈተናውን ውጤት በአጭር ጊዜ እናሳውቃለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ ይህ የፈተና ሥራ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለተፈታኞች ደግሞ መልካም ውጤት ተመኝቷል።

" በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈተናውን ውጤት የምናሳውቅ ይሆናል " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፏል።
በትግራይ ክልል  ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እና ምልከታ ተካሄደ።
-----------------------------------------

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ  የባለሙያዎች ቡድን በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር  በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እና  ምልከታ አድርገዋል።

የባለሙያዎቹ ቡድን  ምልከታውን ያደረገው በማዕከላዊ ዞንና በሰሜን ምዕራብ ዞኖች ስር ባሉ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአክሱም ዩኒቨርስቲ ሽሬ እና አድዋ ካምፓስ ነው።

ቡድኑ በዞኖቹ  ትምህርት ለማስጀመር  ባሉ አስቻይ ሁኔታዎችና ትምህርት ቤቶቹ ባሉበት ቁመና ዙሪያ ከየዞኖቹ  የትምህርት ስራ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

ከሁለተኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን ፣ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ከ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት በተፈጠረው ሰላም ትምህርት ለመጀመር እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

በውይይቶቹም በትምህርት ቤቶች  እና ዩኒቨርስቲዎች የተፈጸሙ  ዘረፋዎችና  ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች ማረፊያዎች  መሆናቸውና ሌሎችም  ተግዳሮቶች  ቢኖሩም ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት እንዲጀመር   ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ ተመለክቷል።

በመሆኑም የተጓደሉ መሰረታዊ ግብአቶች ተሟልተው ባጭር  ጊዜ በዞኖቹ  የተቋረጠው ትምህርት ሊጀመር እንደሚገባ በምልከታው ወቅት መግባባት ላይ ተደርሷል።
👍1