ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመሰረታዊ ኮምፒዩተር ክህሎት ስልጠና መስጠት ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

ስልጠናውን ለመከታተል የአመልካቾች ምዝገባ እስከ ማክሰኞ ታህሳስ 18/ 2015 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን
ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ስልጠናውን ለመከታተል የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች ሲሆን የስልጠናው ክፍያ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር መሆኑ ተመላክቷል።

ስልጠናው በቀን፣ በማታ ወይም በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብሮች ይሰጣል።
👍1
ከአንድ ሺ ለሚበልጡ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በቴክኖሎጁ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ በስልጠናው ወቅት  እንደገለጹት የጊዜውን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አገሩን የሚገነባ ትውልድ መፍጠር ከመምህራን የሚጠበቅ ተግባር ነው።

በመሆኑም መምህራን የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማሳደግ በስርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጡ ዓላማዎችን ተማሪዎች በቀላሉና በተሻለ  እንዲረዱ  ማስቻል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ከፍተኛ የድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ አለሙ ተስፋዬ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ መምህራን ቴክኖሎጁን አማራጭ የትምህርት መረጃ መሳሪያ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ለማጠናከር ነው ብለዋል።

ስልጠናው መምህራን የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን በማሳደግ  አዳዲስ ዕውቀቶችን እንዳያብሩና በአንድ ጊዜ   ብዙ ተማሪዎችን ለመድረስ  እንደሚያስችላቸውም  አቶ አለሙ ተናግረዋል።

ከሁሉም ክልሎች ለተመለመሉ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በ11 የስልጠና ማዕከላት በተሰጠው በዚህ ስልጠና ከአንድ ሺ አንድ መቶ የሚበልጡ ተሳታፊዎች መገኘታቸውንም  ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ 3ሺ 12 የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ለማጎልበት  ልዩ የአንድ ዓመት የስራ ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ ገልጸዋል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስትር ነው
👍1
30ኛው የአካል ጉዳተኞች ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን ከ6ቱም ካምፓስ ከመጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጋር ታኅሣሥ 9/2015 ዓ/ም ተከብሯል፡፡

የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካፒታ ዋልጬ እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ሙሉ የምናደርገውና ውጤታማ ሥራ የምንሠራው አካል ጉዳተኞችን ማካተት ስንችል ነው፡፡ አካል ጉዳተኞች አቅማቸውን አውጥተው መጠቀም እንዲችሉ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ አለበት ያሉት ዳይሬክተሩ ቀኑን ስናከብር በዩኒቨርሲቲያችን ያሉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ለመስተናገድ ሲመጡ ፈጣን ምላሽ በመስጠት በመማር ማስተማርና ምርምር ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እንዳለብን በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

በዳይሬክቶሬቱ የልዩ ፍላጎት ባለሙያ ወ/ሮ ዳግማዊት አባይነህ የተባባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዛሬ 31 ዓመት ኅዳር 24 ቀን የአካል ጉዳተኞች ቀን ሆኖ እንዲከበር ሲወስን አካል ጉዳተኞች በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች መብታቸውን የሚጠይቁበት እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲያችን ለአካል ጉዳተኞች እንደየፍላጎታቸው ድጋፍ ለማድረግ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ አገልግሎት ሰጪዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተወካይ ተማሪ አገዘ አስናቀ የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ሥራ ክፍሎች አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በቀናነት ማስተናገድና መደገፍ እንደሚገባቸው አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በፕሮግራሙ የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካፒታ ዋልጬ፣ የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ፕሬዝደንት ተማሪ ደስያለው ቆለጭ፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንት ተማሪ አገዜ አስናቀ፣ የሰላም ፎረም ፕሬዝደንት ተማሪ መብራቱ ተስፋዬ፣ የተማሪ ኅብረት ፓርላማ አመራሮች፣ የሁሉም ካምፓሶች የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎችና አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
👍1
ጠ/ሚ ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ የወላይታ ሶዶ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ መረቁ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የወላይታ ሶዶ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካን ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን መርቀዋል፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ይህ ፋብሪካ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከሚሠሩ በርካታ ድኻ ተኮር ሥራዎች አንዱ ነው ብለዋል።

ሥራው ኢትዮጵያን ቀጣናዊ እና አህጉራዊ የዳቦ ቅርጫት ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል። በ9 ወር ጊዜ ውስጥ የተገነባው ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ በቀን 300ሺሕ ዳቦ ማምረት እንደሚችል ታውቋል፡፡
ዕድላቹን መክሩት!!!
Royal Thai Government Scholarships 2023 in Thailand (Fully Funded)

University: Asian Institute of Science and Technology
Degree level: Masters, PhD
Scholarship coverage: Fully Funded
Eligible nationality: International
Award country: Thailand
Last Date: 28 February 2023

👉 Apply link:- https://bit.ly/3hNHXPB
የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።

የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።
👍3
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ የዝርፊያ ሙከራ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተሰማ።

ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም ለሊት 8፡00 አካባቢ የተማሪዎች መኝታ ክፍል በመግባት ዝርፊያ ለመፈጸም ሲሞክሩ ሦሥት ተማሪዎችን በስለት በመውጋት ጉዳት ማድረሳቸውን ጥቆማቸወን ለቲክቫህ ያደረሱ ተማሪዎች ገልጸዋል።

ይበልጣል ወርቁ የተባለ የዩኒቨርሲቲው የ4ኛ ዓመት የሶሲዮሎጂ ተማሪ ህይወት ማለፉን ሰምተናል።

በጉዳዩ ዙሪያ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን ያነጋገርን ሲሆን "ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑንና ምርመራው ሲጠናቀቅ አስያየት እንደሚሰጥ" አሳውቆናል።

ምንጭ፡ ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ
ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

ጉዳዩ፡ የእንቅስቃሴ ገደብ የተከለከለባቸው ቦታዎችን ስለማሳወቅ

በሁለተኛ ዙር ከታህሳስ 15 እስከ ታህሳስ 23/2015 ዓ.ም  የሚሰጠውን የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስመልክቶ ለዩኒቨርሲቲው ሁሉም ማህበረሰብ የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለባቸው ቦታዎች ስላሉ ወደ ተከለከሉ ቦታዎች ከመሄድ ተማሪዎች እንዲታቀቡ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

በዚህም መሰረት  ወደ ካምፓስ ሁለት ወይም ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት አካባቢ ያለውን አደባባይ አልፎ መሄድ እንዲሁም በተማሪዎች መግቢያ በር ኮብል/በር አንድ መግባትም ይሁን መውጣት እንዲሁም የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ክልከላውን በመተላለፍ ለሚደርሱ ተጠያቂነቶች ዩኒቨርሲቲው የትኛውንም አይነት ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑንም ጨምሮ አሳውቋል።
#መቐለ #ራያ #አክሱም #ዓዲግራት

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡

በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC
ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ምልከታ ሊያደርግ ነው፡፡

በግጭቱ ምክንያት ሥራ ያቋረጡትን አክሱም፣ ራያ፣ አዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ አክሱም እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ዳግም ወደ አገልግሎት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ንግግር መጀመሩን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለፋና ተናግረዋል።

በቀጣይም ከመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነት እንደሚጀመር ኃላፊው አመላክተዋል፡፡

በአክሱም ከተማ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተከትሎ፤ ስድስት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ከሰኞ ጀምሮ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናውን ግቢ ጨምሮ አድዋ እና ሽረ ግቢዎችን በስፍራው በመገኘት ምልከታ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በቤተ ሙከራ፣ በኔትወርክ፣ በመኝታና መማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታል፣ በቤተ መጻሕፍት እና ሌሎች አገልግሎቶች ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለውን ሁኔታ ይመለከታል፡፡ #FBC
👍1
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ከጉጂ ዞኖች በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን ያልወሰዱ ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው ትላንት መቀበል ጀምሯል።

ተማሪዎቹ ነገ ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም ገለጻ የሚሰጣቸው ሲሆን ከታህሳስ 18 እስከ 21/ 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይታወቃል።

የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናም በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ የሚበልጡ የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን ዛሬ ተቀብሏል።

በተለያየ ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ 1 ሺህ 70 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።

ከተፈታኞቹ መካከል 752ቱ በተቋሙ ቴክኖሎጂ ግቢ የሚፈተኑ ሲሆን ቀሪዎቹ 318 ደግሞ በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ እንደሚፈተኑ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም ድረስ ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ ፈተናው ይሰጣል።
በተያዘው ዓመት መጨረሻ ራስ ገዝ የሚሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለራስ ገዝ አስተዳደር የሚያስፈልግ የአሰራር ማንዋል ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ራስ ገዝ አስተዳደር ሲኖራቸው ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የተሻለ ገቢ መሰብሰብ እንደሚያስችላቸው
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የራስ ገዝ አስተዳደሩ ምሁራን የአካዳሚ ነጻነት ኖሯቸው ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም በምርምር የተደገፈ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ያስችላልም ብለዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ አስተዳደር ነጻነት እንደሚሰጠው ከተገለጸ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ለራስ ገዝ አስተዳደር የሚመጥን የስነ-ልቦና እና የአሰራር ማኑዋል ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡
በመቐለ ከተማ የባንክ እና የስልክ አገልግሎት በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል
**********************

በትግራይ የነበረው ጦርነት በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌደራሉ መንግስት ከህወሓት ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት የተኩስ አቁሙን ተከትሎ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን የፌደራሉ መንግስት ማስጀመሩ የሚታወስ ነው።

በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም 27 የሚደርሱ የትግራ ከተሞች ላይ የስልክ አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም መቐለን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ትልልቅ ከተሞች የሀይል አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል።

ወደ መቐለ ያመራው የፌደራሉ መንግስት ልኡክ ለትግራይ ህዝብ እንዳረጋገጠው፥ በክልሉ ትልቅ ችግር የሆነው የባንክ አገልግሎት በቅርቡ ይፈታል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ባለሞያዎችን ወደ መቐለ እንዳሰማራ የጠቀሱት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፤ ባንኩ የሚስተካከሉ የሲስተምና የኦዲት ስራዎችን በዚህ ሳምንት አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በትግራይ የባንክ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ህብረተሰቡ ለከፋ ችግር እንደተዳረገ እንረዳለን ያሉት አቶ አቤ ሳኖ፤ ይህንን ችግር  በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከዛሬ ጀምሮ ባለሞያዎቻችን ወደ ስራ ገብተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የሰላም ጅምሩ እንዲፀና ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

በተመስገን ሽፈራው
👍1
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው።

ፈተናው ከዛሬ ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 21/2015 ዓ.ም በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

በተለያዩ ተቀባይነት ባገኙ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ በሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ለፈተና ይቀመጣሉ።

በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ትላንት የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ተሰጥቷቸዋል።
መቀሌ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘቷ ተገለጸ

በዛሬው እለት መቀሌ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ አስታወቁ።

የመጀመሪያው የስልክ ጥሪ በመቀሌ እንደተካሄደም ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።

ከሰላም ስምምነቱ ማግስት በተሰራ ስራ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል 27 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘት መቻሉንም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

የባንክ ብሎም የቴሌኮም ጥገና በማድረግ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንና 981 የኢትዮ ቴሌኮም ፋይበር ጥገና መደረጉን ተቋሙ አመልክቷል።

በክልሉ 61 ባንኮችም አገልግሎት መጀመሩን ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሊዮኔል ሜሲ ያረፈበት ክፍል ወደ ሙዚየምነት ሊቀየር መሆኑ ተነገረ
*********************

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሊዮኔል ሜሲ ያረፈበት ክፍል ወደ ሙዚየምነት ሊቀየር መሆኑ ተነገረ።

ታዲያ ድንቅ የዓለም ዋንጫን ማዘጋጀት የቻለችው ኳታር፣ በውድድሩ አስገራሚ ብቃትን ያሳየውን አርጀንቲናዊ ምትሃተኛ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ታሪክ ለማስታወስ የቆየበትን ክፍል ወደ ሙዚየምነት ልትቀይር መሆኗ ታውቋል።

ሜሲ አርጀንቲናን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ለክብር ሲያበቃ ያርፍበት የነበረው የመኝታ ክፍሉ ወደ አንስተኛ ሙዚየምነት መቀየሩ ሜሲ የዓለም ዋንጫን ለማንሳት የሄደበትን መንገድ ለአድናቂዎቹ ያሳያል ነው የተባለው ።

ሊዮኔል ሜሲ ሃገሩን በአምበልነት እየመራ ከ36 አመታት በኋላ ዋንጫውን እንዳነሳ እና እርሱም የውድድሩ ኮኮብ ተጫዋች መባሉ ይታወሳል።