የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝነት"

ራስ ገዝ ሆነው የሚደራጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም አቀፍ ውድድር አዲስ ፕሬዝዳንቶችን እንደሚመርጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህ አሰራር በአገር ውስጥ ውድድር ተወስኖ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ቅጥር ሂደት በማስፋት የውጭ ዜጎችም ጭምር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪነት እንዲወዳደሩ ዕድል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ ዕቅድ ይዟል። በዚህ እቅድ ከተካተቱት ውስጥ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው በጀት ዓመት የራስ ገዝ አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ይጠበቃል።

መንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶቻቸውን ከሀገር ውስጥ ካሉ ምሁራን አወዳድረው ሲቀጥሩ ቢቆዩም፤ በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች (በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በመቐለ ዩኒቨርሲቲዎች) ለተወሰኑ ዓመታት የውጪ ዜጎችም በፕሬዚዳንትነት ተመርጠው አገልግለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆናቸው የአስተዳደር፣ የአካዳሚ፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

በተለያዩ አገራት በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ እና በአመራርነት የሚሰሩ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን ቢመሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል። 

ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ሊኖራቸው የሚጠበቀው የትምህርት ደረጃ “ዶክትሬት ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የሚወክል ትምህርት እና ልምድ” መሆን እንዳለበት በመመሪያው ሰፍሯል። ሆኖም የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች “በልዩ ሁኔታ” ሊመረጡ እንደሚችሉ በመመሪያው ተቀምጧል። 

እስካሁን በነበረው አሰራር በትምህርት ሚኒስቴር ሹመት የሚያገኙ ፕሬዝዳንቶች የሥራ ዘመናቸው ስድስት ዓመት ሲሆን ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ ሊመረጡ ይችላሉ። ምክትል ፕሬዝዳንቶች በአንጻሩ ሹመታቸው የሚጸድቀው በዩኒቨርስቲዎች ቦርድ ሲሆን አራት ዓመት የስራ ዘመን ይኖራቸዋል።

ራስ ገዝ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ዩኒቨርስቲዎች፤ ፕሬዝዳንቶቻቸውን የሚመርጡበትን መስፈርት፣ የአገልግሎት ዘመን እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚወስኑ ዝርዝር ድንጋጌዎች እንደሚኖራቸው ዋና ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ያለ ትምህርት ሚኒስቴር ጣልቃ ገብነት ፕሬዝዳንቶቻቸውን በቦርድ ማጽደቅ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ኢትዮጵያኢንሳይደር
የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመሩ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መሰቀልና መዝሙር መዘመር ጋር በተገናኘ፣ በት/ት ቤቶች ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመሩ መመሪያ መሰጠቱ ተሰማ፡፡

ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲመሩ ትዕዛዝ ያስተላለፈው የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሲሆን፤ በጥብቅ ይፈጸም የተባለው አሰራር በተማሪዎች እና በመምህራን ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ያዛል ተብሏል፡፡

#አዲስ_ማለዳ በትምህርት ቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ተፈርሞ፣ ለኹሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች የተላለፈውን ደብዳቤ መመልከቷን ዘግባለች፡፡

በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው፤ ትምህርት ቤቶች አንድ ቀን ላረፈደ ተማሪና አንድ ቀን ለቀረ ተማሪ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡ ታዘዋል፡፡

እንዲሁም ኹለት ቀን ያረፈደና የቀረ ተማሪ በወላጅ ፊት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ዘላለም በፈረሙበት ደብዳቤ ላይ ሰፍሯል፡፡ ከኹለት ቀን በላይ ያረፈደና የቀረ ተማሪ በመመሪያው መሰረት ተፈጻሚ የሚሆን እርምጃ  እንደሚወሰድበትም ተመላክቷል፡፡

በትምህርት ቤቶች በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ እንዲደርግ የሚያዘው ደብባቤው፣ ተማሪዎች ስልክ፣ ርችትና ፊኛ የመሳሰሉ ቁሶችን ወደ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይሄዱ ገደብ ጥሏል፡፡ ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ መገልገያዎችን፣ ይዞ የተገኘ ተማሪ የድስፕሊን እርምጃ እንዲወስዱ ትምህርት ቤቶች መታዘዛቸውም ተነግሯል፡፡

የትምህርት አመራር፣ መምህራንና ሰራተኞች በሙሉ የሥራ ሰዓታቸውን አክብረው፣ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ጥብቅ ትዕዛዝ የተሰጣቸውም ሲሆን፤ በዚህም ማርፈድ፣ መቅረትና የሥራ ሰዓት ሳያልቅ ከትምህርት ቤት ግቢ መውጣት የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡

የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ትዕዛዝ ባስተላለፉበት ደብዳቤ፣ ያስተላለፉትን ትዕዛዝ የማያስፈጽም በየደረጃው የተቀመጠ የትምህርት ቤት አመራርም ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ኃላፊው ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች፣ ባስተላለፉት ትዕዛዝ “ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ቦታ ናቸው” ያሉ ሲሆን፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያደናቅፍ ተግባራ የሚፈጽም ማንኛውም አመራር፣ መምህር፣ ሰራተኛና ተማሪ ላይ ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድና ሪፖርት እንዲደረግም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ አዲስ ማለዳ
በአዲስ አበባ በትምህርት ቤቶች ላይ  ከሰንደቅ  አላማ ጋር  በተያያዘ  የተፈጠረው ችግር አሳዝኖኛል ሲል ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ ገለጸ፡፡

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርትቤቶች ላይ  ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር  ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ  እንዴት ያይዋል ሲል አሀዱ ጠይቋል
በቀላሉ መጨረስ የሚቻለውን ጉዳይ  በዚህ ልክ ችግር  እስኪፈጠር ድረስ ተግባራዊ መደረጉ አሳዝኖናል ሲሉ የኮምሽኑ  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  ኮምሽነር ዶክተር ዬናስ አዳዬ ተናግረዋል፡፡

በንግግር መጨረስ የሚቻለውን  ነገር  ልዩነትን ወደ የሚፈጥር ፤ወደ ግጭቶች እንዲቀየር እና በህይወት  እስኪጠፋ ድረስ  መድረግ አልነበረበትም ነው ያሉት፡፡
ብዝሀነት  የሚደገፍ ቢሆንም ህዝቡን  በሚለያይ መልኩ ሳይሆን ባማከለ መልኩ መደረግ አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ ኮምሽኑ ለመስራት ያቀዳቸው ስራዎች እንዳልተሳካ የተናገሩት ኮሚሽነሩ እናዚህ ጉዳይዎች በምክክር እና በውይይት እንደሚፈቱ ኮምሽኑ ያምናል ብለዋል፡፡

ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣት እንደሚያስፍልግል ኮምሽኑ የችግሮች መሰረታዊ ምክንያቶች ምንድናቸው የሚለውን ከህዝቡ የመጡ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚቻልም አንስተዋል፡፡ከህዝቡ የሚመጡ የመዋቅራዊ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማድረግ መንግስት እንዲህ ማድረግ  አለበት በሚልም ምክረ ሃሰቦች እንደሚሰጡ አንስተው፤ እንዲህ አይነት ተግባራት የኮምሽኑን  አካሄዶች ሊያደናቅፉ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡

©Ahadu
ሰባት ተማሪዎችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ሰባት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው በማፈናቀል በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል ።

ተማሪዎችን ከትውልድ አካባቢያቸው በእግር እና በባጃጁ ተሽከርካሪ በማራቅ በወግዲ ወረዳ ለሚ ታዳጊ ከተማ በአውቶቡስ ጭነው  ለማዘዋወር ሲሞክሩ እንደተያዙ ተገልጿል ።   በአውቶቡስ ውሰጥ ተሳፍረው የነበሩ የፀጥታ ሀይሎች የተማሪዎችን ሁኔታ በመጠራጠር ባደረጉት ማጣራት አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወግዲ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽ/ት ቤት ኃላፊ አ/ቶ ደሳለው ጌትነት  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ተማሪዎች የቀበሌ መታወቂያ ይዘው የተገኙ ሲሆን እድሜያቸው መታወቂያ ለማግኘት ያልደረሰ እንደሆነ ተገልጿል ። ልጆችን ከትምህርት ገበታቸው በመነጠል በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ አካላት እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ የጠፉ ልጆቻቸውን በማፈላለግ ላይ የሚገኙ ወላጆች መናገራቸውን አ/ቶ ደሳለው ገልፀዋል ።


     #ዳጉ_ጆርናል
በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በኅብረተሰብ ጤና፣ በነርሲንግ እና በሚድዋይፈሪ ትምህርት ክፍሎች በመምህርነት ለመቀጠር የተመዘገባችሁ አመልካቾች የፈተናው ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ጣሊያን አገር ከሚገኘው ሳኒኖ (SANNIO) ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው ነው።
ስምምነቱን እጬ ዶ/ር ካሳሁን ሙላቱ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ፈርመዋል።
ዶ/ር አብዮት አስረስ የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የዩኒቨርስቲው አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር መምህር ወጋየሁ እንቢያለ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል ።
Mizan-Tepi University
Light of the green Valley!
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ‼️

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 18 ኢትዮጵያውያን ወደ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሰሞነኛው ‘ጉንፋን’ መሰል ወረርሽኝ
************************

ሰሞኑን በርካታ ሰዎች ' ጉንፋን'  መሰል  በሆነ በሽታ በስፋት ተይዘው ለህመም መጋለጣቸው ተስተውሏል።

በህብረተሰቡ ዘንድ በብዛት እየታየ ያለውን ሰሞነኛ ‘ጉንፏን’ መሰል ወረርሽኝ ጉዳይን አስመልክቶ ኢቢሲ ሳይበር የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን አናግሯል።

እየታየ ያለው ‘ጉንፋን’ መሰል ወረርሽኝ በአብዛኛው የኮቪድ 19 ምልክት እያሳየ መሆኑን ከተወሰዱ የቤተ ሙከራ ምርመራዎች ግንዛቤ መወሰዱን የኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ሻምበል ሀቤቤ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልጸዋል።

ወረርሽኙ ኮቪድ 19ን ጨምሮ የብዙ መተንፈሻ አካላት በሽታዎች ምልክት ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰው ኮቪድ የመሆን እድሉ ከፍተኛ መሆኑን አስተባባሪው አብራርተዋል።

የሰሞኑ ጉንፋን ከሚያስከትላቸው  ሕመሞች ዋና ዋናዎቹ ፡-
• ብርድ ብርድ ማለት
• ከፍተኛ ትኩሳት
• ሳል
• ኃይለኛ ራስ ምታት
• የመገጣጠሚያ ህመም
• ቁርጥማት 
• የምግብ ፍላጎት እና የማጣጣም ስሜትን መቀነስ ተጠቃሾች ናቸው።
ይህንን ጉንፋን መሰል በሽታ ለመከላከል ያስችላሉ የተባሉ መንገዶችንን ታማሚዎች እንዲተገብሯቸው የህክምና  ባለሙያዎች ይመክራሉ።
1
የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምልከታ አደረጉ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴምክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት ከታኅሣሥ 9-11/2015 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምልከታ አድርገዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ኃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላት በሰጡት የምልከታ ግብረ-መልስ እንዳመላከቱት ቋሚ ኮሚቴው በዩኒቨርሲቲው በነበረው ቆይታ ተቋሙ በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት በኩል ያሉ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ከቁልፍ የተግባር አመላካቾች አንፃር መመልከቱን ጠቁመዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በቆይታው ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት፣ ከግዥ፣ ከፋይናንስና ኦዲት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው መምህራን ጋር ውይይት በማድረግ መረጃ መሰብሰባቸውንም አመላክተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከምሥረታው አንስቶ በተለይ በውሃው ዘርፍ ብቃት ያላቸው ምሁራንን ማፍራት ማስቀጠሉ፣ የምርምር ዩኒቨርሲቲን የሚመጥን አደረጃጀት ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት፣ ካለው ተጨባጭ ሀገራዊ ሁኔታ አንጻር ሠላማዊ መማር ማስተማርን ማስቀጠል መቻሉ፣ በእንሰት ዙሪያ የሚደረጉ ምርምሮችና የፈጠራ ሥራዎች፣ በታዳሽ ኃይል አቅርቦት አንፃር የተሠሩ ሥራዎችና ለሴት ተማሪዎች የሚደረጉ ድጋፎች፣ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎችና ሠርቶ ማሳያዎች ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ የተመለከታቸው ተግባራት መሆናቸውን ም/ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡ በዋናነት በሳውላ ካምፓስ የሚስተዋለው የመማሪያ ክፍል፣ የቤተ-ሙከራ፣ የግብዓት ዕጥረትና ግዥዎች በወቅቱ አለመፈጸም፣ የመምህራን ክፍያዎች መዘግየትና በኦዲት ግኝቶች ላይ የተሟሉ የማስተካከያ እርምጃዎች አለመወሰድ ቋሚ ኮሚቴው ማስተካከያ እንዲደረግባቸው የለያቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ዶ/ር ከይረዲን ጠቁመዋል፡፡

ተጀምረው የቆሙ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ሥራ ማስጀመርና ማጠናቀቅ፣ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችን ማሟላት፣ የውስጥ ገቢን ማሳደግ፣ የውስጥ ኦዲትን በሰው ኃይልና በአሠራር ማጠናከር፣ በዩኒቨርሲቲው አቅም በሚመለሱ የመምህራን ጥያቄዎች ላይ ወቅታዊ ምላሽ መስጠት፣ ራስ አገዝ መሆንን ለማረጋገጥ አሠራሮችን ማሻሻልና ዕቅዶችን መከለስ፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚደረጉ የትብብር ሥራዎችን ማጠናከርና ሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ዶ/ር ከይረዲን አሳስበዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በቋሚ ኮሜቴው አባላት የተሰጡ አስተያየቶችና ጥቆማዎች ለዩኒቨርሲቲው ቀጣይ የትኩረት ሥራዎች አጋዥ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ዩኒቨርሲቲው በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ አስተያየቶችን በመጠቀም ለማስተካከል ዕቅድ ይዞ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡ ከሳውላ ካምፓስ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን መቅረፍን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ባለው አቅም ሁሉ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም እንደ ሀገር ለመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ግንባታዎችን ማካሄድ ባላመፈቀዱ በካምፓሱ ከግንባታ ጋር የተያያዙ ችግሮችን መቅረፍ አለመቻሉን ዶ/ር ዳምጠው ተናግረዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
👍1
ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ ሙዚቃና ትምህርት ቡድን ጋር በመተባበር የሙዚቃና የኪነ ጥበብ ሥራዎች ሊያቀርቡ ነው።

"ሃገር እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው መርሃ ግብሩ፤ ቅዳሜ ታህሳስ 15/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይከናወናል።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ተጋባዦች በዝግጅቱ እንደሚገኙ ይጠበቃል።
👍1
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመሰረታዊ ኮምፒዩተር ክህሎት ስልጠና መስጠት ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

ስልጠናውን ለመከታተል የአመልካቾች ምዝገባ እስከ ማክሰኞ ታህሳስ 18/ 2015 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን
ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ስልጠናውን ለመከታተል የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች ሲሆን የስልጠናው ክፍያ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር መሆኑ ተመላክቷል።

ስልጠናው በቀን፣ በማታ ወይም በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብሮች ይሰጣል።
👍1
ከአንድ ሺ ለሚበልጡ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በቴክኖሎጁ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ በስልጠናው ወቅት  እንደገለጹት የጊዜውን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አገሩን የሚገነባ ትውልድ መፍጠር ከመምህራን የሚጠበቅ ተግባር ነው።

በመሆኑም መምህራን የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማሳደግ በስርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጡ ዓላማዎችን ተማሪዎች በቀላሉና በተሻለ  እንዲረዱ  ማስቻል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ከፍተኛ የድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ አለሙ ተስፋዬ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ መምህራን ቴክኖሎጁን አማራጭ የትምህርት መረጃ መሳሪያ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ለማጠናከር ነው ብለዋል።

ስልጠናው መምህራን የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን በማሳደግ  አዳዲስ ዕውቀቶችን እንዳያብሩና በአንድ ጊዜ   ብዙ ተማሪዎችን ለመድረስ  እንደሚያስችላቸውም  አቶ አለሙ ተናግረዋል።

ከሁሉም ክልሎች ለተመለመሉ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በ11 የስልጠና ማዕከላት በተሰጠው በዚህ ስልጠና ከአንድ ሺ አንድ መቶ የሚበልጡ ተሳታፊዎች መገኘታቸውንም  ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ 3ሺ 12 የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ለማጎልበት  ልዩ የአንድ ዓመት የስራ ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ ገልጸዋል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስትር ነው
👍1
30ኛው የአካል ጉዳተኞች ቀን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን ከ6ቱም ካምፓስ ከመጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጋር ታኅሣሥ 9/2015 ዓ/ም ተከብሯል፡፡

የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካፒታ ዋልጬ እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ሙሉ የምናደርገውና ውጤታማ ሥራ የምንሠራው አካል ጉዳተኞችን ማካተት ስንችል ነው፡፡ አካል ጉዳተኞች አቅማቸውን አውጥተው መጠቀም እንዲችሉ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ አለበት ያሉት ዳይሬክተሩ ቀኑን ስናከብር በዩኒቨርሲቲያችን ያሉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ለመስተናገድ ሲመጡ ፈጣን ምላሽ በመስጠት በመማር ማስተማርና ምርምር ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እንዳለብን በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

በዳይሬክቶሬቱ የልዩ ፍላጎት ባለሙያ ወ/ሮ ዳግማዊት አባይነህ የተባባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዛሬ 31 ዓመት ኅዳር 24 ቀን የአካል ጉዳተኞች ቀን ሆኖ እንዲከበር ሲወስን አካል ጉዳተኞች በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች መብታቸውን የሚጠይቁበት እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲያችን ለአካል ጉዳተኞች እንደየፍላጎታቸው ድጋፍ ለማድረግ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ አገልግሎት ሰጪዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተወካይ ተማሪ አገዘ አስናቀ የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ሥራ ክፍሎች አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በቀናነት ማስተናገድና መደገፍ እንደሚገባቸው አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በፕሮግራሙ የተማሪዎች አገልግሎት ማእከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካፒታ ዋልጬ፣ የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ፕሬዝደንት ተማሪ ደስያለው ቆለጭ፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንት ተማሪ አገዜ አስናቀ፣ የሰላም ፎረም ፕሬዝደንት ተማሪ መብራቱ ተስፋዬ፣ የተማሪ ኅብረት ፓርላማ አመራሮች፣ የሁሉም ካምፓሶች የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎችና አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
👍1
ጠ/ሚ ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ የወላይታ ሶዶ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ መረቁ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የወላይታ ሶዶ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካን ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን መርቀዋል፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ይህ ፋብሪካ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከሚሠሩ በርካታ ድኻ ተኮር ሥራዎች አንዱ ነው ብለዋል።

ሥራው ኢትዮጵያን ቀጣናዊ እና አህጉራዊ የዳቦ ቅርጫት ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል። በ9 ወር ጊዜ ውስጥ የተገነባው ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ በቀን 300ሺሕ ዳቦ ማምረት እንደሚችል ታውቋል፡፡
ዕድላቹን መክሩት!!!
Royal Thai Government Scholarships 2023 in Thailand (Fully Funded)

University: Asian Institute of Science and Technology
Degree level: Masters, PhD
Scholarship coverage: Fully Funded
Eligible nationality: International
Award country: Thailand
Last Date: 28 February 2023

👉 Apply link:- https://bit.ly/3hNHXPB
የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።

የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።
👍3
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ የዝርፊያ ሙከራ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተሰማ።

ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም ለሊት 8፡00 አካባቢ የተማሪዎች መኝታ ክፍል በመግባት ዝርፊያ ለመፈጸም ሲሞክሩ ሦሥት ተማሪዎችን በስለት በመውጋት ጉዳት ማድረሳቸውን ጥቆማቸወን ለቲክቫህ ያደረሱ ተማሪዎች ገልጸዋል።

ይበልጣል ወርቁ የተባለ የዩኒቨርሲቲው የ4ኛ ዓመት የሶሲዮሎጂ ተማሪ ህይወት ማለፉን ሰምተናል።

በጉዳዩ ዙሪያ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን ያነጋገርን ሲሆን "ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑንና ምርመራው ሲጠናቀቅ አስያየት እንደሚሰጥ" አሳውቆናል።

ምንጭ፡ ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ
ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

ጉዳዩ፡ የእንቅስቃሴ ገደብ የተከለከለባቸው ቦታዎችን ስለማሳወቅ

በሁለተኛ ዙር ከታህሳስ 15 እስከ ታህሳስ 23/2015 ዓ.ም  የሚሰጠውን የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስመልክቶ ለዩኒቨርሲቲው ሁሉም ማህበረሰብ የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለባቸው ቦታዎች ስላሉ ወደ ተከለከሉ ቦታዎች ከመሄድ ተማሪዎች እንዲታቀቡ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

በዚህም መሰረት  ወደ ካምፓስ ሁለት ወይም ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት አካባቢ ያለውን አደባባይ አልፎ መሄድ እንዲሁም በተማሪዎች መግቢያ በር ኮብል/በር አንድ መግባትም ይሁን መውጣት እንዲሁም የትኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ክልከላውን በመተላለፍ ለሚደርሱ ተጠያቂነቶች ዩኒቨርሲቲው የትኛውንም አይነት ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑንም ጨምሮ አሳውቋል።