ት/ሚኒስቴር ለምን ፀጥ አለ???
👉 የመጫወቻ ካርዶቹን ፍቆ ስላልጨረሰ ማለትም
#1 የመጀመሪያው ካርድ- አድማውን አስተባብረዋል ያላቸውን ስራ አስፈፃሚዎች በማሳሰርና በማዋከብ መምህራን ክላስ እንዲገቡ የማድረግ  ሙከራ - የከሽፈ
#ካርድ 2 - ጥያቄዎቻችንን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖራቸው ከዘር፡ ሀይማኖትና ሌሎች ነገሮች ጋር በማያያዝ አንድ እንዳንሆን በማድረግ የተወሰኑ መምህራን ክላስ እንዲገቡና ሌሎችም እንዲከተሉ የማድረግ ሙከራ- አደገኛ ግን አንድ በመሆናችን የከሸፈ ካርድ
#ካርድ 3- ተስፋ አስቆራጭ ማስታወቂያዎችን(ት/ሚኒስቴር ምንም መግለጫ አይሰጥም የሚል- ጎንደር ዩ/ቲ) መለጠፍ , ማሰጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤዎችና ኢ-ሜሎችን ለት/ት ክፍል ሃላፊዎች በመላክ በመካከላችን ልዩነት እንዲፈጠር በማድረግ የተወሰነ መምህር ክላስ እንዲገባ መሞከር- እየከሸፈ ያለ
#ካርድ 4- ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ አዘል መግለጫ በት/ሚኒስቴር - ያልተፍቀ ካርድ ግን የሚከሽፍ ሙከራ
# 5- ሳይወዱ በግድ ለጥያቄዎቻችን የመፍትሄ ሃሳብ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
ፖሊስ በመዲናዋ በትምህርት ቤቶች ረብሻ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩና ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስአበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ፖሊስ "በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በአንድ በኩል የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብትና ማንነታቸውንና ባህላቸውን መግለፅን እንደ ጫናና በሃይል በሌሎች ላይ እንደተጫነ አድርጎ የመቀስቀስ በሌላ በኩል ደግሞ፤ የኦሮሞ ህዝብ እየሞተ ነው የህዝብ ባህልና ማንነት ተዋረደ የሚሉ እርስ በእርሱ የሚቃረን የግጭት ማቀጣጠያ  አጀንዳ በመፍጠር እንዲሁም፤ የወልቃይትና የአዲስ አበባ ጉዳይ አንድ ነው የሚል መፈክር ይዘው ከመውጣት ባሻገር  የሐገሪቱን ሰንደቅ ዓላማና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና ከሰንደቁ ላይ በማውረድና መሬት ለመሬት በመጎተት ከፍተኛ ድፍረት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።" ብሏል፡፡

ሰሞኑን በተወሰኑ አንደኛና ጥቂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጥፋት አጀንዳቸውን ከተቀበሉ አንዳንድ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን በማደናገርና በማወናበድ ምንም የማያውቁ አብዛኛው ተማሪዎችን ከፊት በማሰለፍ ባስነሱት ረብሻ  በትምህርት ቤቶቹ ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን መረጋገጡንም የአዲስአበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
“ኢትዮጵያ ትፈተናለች  እንጂ አትሸነፍም” ጠቅላይ  ሚኒስትር ዐቢይ  አህመድ
***********************

ኢትዮጵያ ትፈተናለች  እንጂ አትሸነፍም ሲሉ ጠቅላይ  ሚኒስትር ዐቢይ  አህመድ ተናገሩ።

በሀዋሳ ከተማ በተከበረው 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ክብረ በዓል ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ የሁላችን ቅርስ ፣እሴት የሚታይበት እና በኢትዮጵያ ጥላስር ሆነን የምንሰባሰብበት ቀን ለሆነው ለኢትዮጵያዊነት ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

የተለያየ ባህልና  እሴት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ሰበዝ ሁነው  ሲደምሩ  ታላቋን ኢትዮጵያ እንደሚፈጥሩ በማጤን በአብሮነት  የጋራ ቤታችንን ለመስራት ትኩረት መስጠት አለብን ብለዋል።

የጋራ ቤትን በጋራ መገንባት ላይ ትኩረት  በመስጠት  ከውጭ የሚመጡ አጀንዳዎችን ማክሸፍ እንደሚገባ  ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የእንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ችግር የሚፈታው የኢትዮጵያ ችግር  ሲፈታ በመሆኑ ለዚሁ በጋራ መስራት ላይ ትኩረት እንዲደረግም ጠይቀዋል።
ሙስና 'ሀራም' መሆኑን በተመለከተ ህዝበ ሙስሊሙን ለማንቃት ከነገ ጀምሮ በመስጂድ ኢማሞች ሁጥባዎች ይቀርባሉ ‼️

🗣የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት


ኢስላማዊ እና ሃይማኖታዊ አስተምህሮን መሰረት በማድረግ ሙስና "ሐራም' (ውጉዝ) መሆኑን በተመለከተ ህዝበ ሙስሊሙን ለማንቃት ከነገ ዓርብ ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ በሚገኙ ከ290 በላይ መስጂዶች በኢማሞች አማካይነት ሁጥባ (ምክር) እንደሚቀርብ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ ገልፀዋል።

በኢስላም አስተምህሮ ሙስና በፍፁም የማይደገፍና ፀያፍ ተግባር በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ሊያወግዘው እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የእምነት ሀገር መሆኗን በማውሳት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ እኩይ ተግባር እንዲታቀቡ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ደግሞ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር ናቸው።

ሙስናን ለመከላከል በዘመቻ መልክ እንዲሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮሚቴ አቅርበው ማሰየማቸው ይታወሳል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት በከፊል መቋረጡ ተሰማ‼️

ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም.  የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዋነኛነት "ሞት ይቁም" የሚል መፈክር ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ብዙም ሳይቆይ ሰልፉ በአድማ በታኞች እንዲበተን ተደርጎ እንደነበር የግቢው ተማሪዎች ነግረውናል።ሰልፉ ከተደረገ በኋላ እስከዛሬ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡንም ተማሪዎቹ ጨምረው ነግረውናል።

ዩኒቨርሰቲው በትናንትናው እለት ባወጣው ማስታወቂያ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ ትምህርት የማይመለሱ ተማሪዎች በገዛ ፍቃዳቸው ትምህርታቸውን እንዳቆሙ እንደሚቆጠር አሳስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ተማሪዎች ሙሉ ሙሉ ወደ መደበኛ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸው ታውቋል።

ስለጉዳዩ ለማጣራት #አዲስ_ዘይቤ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርስቲው የስራ ኃላፊ ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ትምህርታቸው አለመመለሳቸውን አረጋግጠውልናል።
ከኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን #አዲስ_ማለዳ በወቅቱ በቦታው ከነበሩ ተማሪዎች ሰምታለች፡፡

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎቸ መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱም ተሰምቷል።

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች እና የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪዎች ጭምር ከሁለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡ በሰንደቅ አላማው ይሰቀላል አይሰቀልም ውዝግብ በተነሳው ግጭት ጉዳት ያስተናገዱ ተማሪችን ወደ ህክምና ተቋም ለመውስድ ሁለት አንቡላንሶች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡

ምንጭ፡ አዲስ ማለዳ
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ካውንስል ውይይት በማካሄድ መማር ማስተማሩ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ስለሆነም ሥራ ያቋረጣችሁ መምህራን ከነገ ህዳር 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ የማስተማር ሥራ እንድትመለሱ እያሳወቅን ይህን ባላደረጉ መምህራን ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አሳውቋል።
#DTU

ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ለነገ 8:00 ላይ ከመምህራን ጋር ለመወያየት ጥሪ አቅርቧል።


በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች አስተማሪዎች ስራ የማቆም አድማ አድርጓል።
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከትላንት ጀምሮ የአባልነት ምዝገባ ጀምሯል፡፡

አባል በመሆንዎ የሚያገኟቸው ጥቅሞች፦

• መጻሕፍት በነጻ መዋስ፣

• ጆርናሎችና የመመረቂያ ጽሑፎችን ኦንላይን ያገኛሉ።

• ነጻ የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኛሉ። (ቤተ-መጻሕፍቱ በዓመት ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ለ12 አባላቱ ነጻ የትምህርት ዕድል ይሰጣል።)

• አባላት ወደ ቤተመጻሕፍቱ ሲመጡ የቶሞካ ትኩስ መጠጦች 35 በመቶ ቅናሽ ያገኛሉ።

ለአባልነት ምዝገባው የትምህርት ቤት እና ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ያስፈልጋል።
የዩንቨርስቲ መምህራን ጥያቄ
ከሰኞ ህዳር 26 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ዓርብ ኅዳር 30 ቀን ድረስ የሥራ ማቆም አድማ መተዉ የነበሩት መምህራን የፊታችን ሰኞ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ገለፁ።

ከሰኞ ኅዳር 26 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ዓርብ  ኅዳር 30 ቀን ድረስ  የሥራ ማቆም አድማ አድገው የነበሩት የዩንቨርስቲ መምህራን የፊታችን ሰኞ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ገለፁ። ዶቼ ቬሌ ያነጋገራቸው ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የዩንቨርስቲ መምህር እንደተናገሩት፤ አድማዉን በተለያዩ ዩንቨርስቲ የሚያስተምሩ በርካታ መምህራን ትግላችንን ተቀላቅለው ነበር ብለዋል። «አድማው ዛሬ  አምስተኛ ቀኑ ነው ዛሬ የመጨረሻም ቀኑ ነው » ብለዋል ከ36 ዩንቨርስቲች በላይ የሚገኙ መምህራን በተለያዩ መልኩ አድማውን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል ።

መምህራኑ አድማቸዉን ያቋረጡት፤ ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ ይሆን ብለን ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ  ሲመልሱ « እንኳን ጥያቄውን ለመመለስ ቀርቶ የሚመለከታቸው አከሎች መምህራንን   አላወያዩም በመግለጫም ይሁን በምንም መልክ መግለጫ አልሰጡም ባልሰማ ዝም ብለው ነው ያሉት » ብለዋል መምህራን ለተማሪው ለአገርም ስለምናስብ ወደስራ እንገባለን ነገር ግን ለ5 ቀን ያደረግነውን አድማ መንግሥት እንደማስጠንቀዊያ ወስዶት በሦስት ሳምንት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ የማይሰጥ ከሆነ ግን ከሦስት ሳምንት በኋላ ከዚህ ከፍ ባለ ትግል ስልት መርጠን ደግመን እንደምንጀምር ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠን ነው ያጠናቀቅነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ፤ ኅዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም የሥራ ማቆም አድማ የጠራው  የመምህራን ቡድን ኢንፎርማል ወይም እውቅና የሌለው ቡድን ነው ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረው ነበር ። ዶክተር በፈቃዱ ለሚመለከተው  አካል ጥያቄያችንን አስገብተናል ሲሉ ተናግረዉም ነበር። ማህበሩ ላቀረበው ጥያቄ ምን ምላሽ አገኛችሁ ለማለት ለኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ለዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር ኅዳር አጋማሽ ላይ ለትምህርት ሚኒስቴር ያስገባው 14 የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች፤ መካከል የደመወዝ ጭማሪ፣ የደረጃ ዕድገት፣ የቤት አበል  ክፍያ ፣በተጨማሪ ሥራዎች የሚገኝ ገቢ ላይ የግብር ቅነሳ የሚሉ ጥያቄዎችን ያካተተ ነው። አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ፤ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፤ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፤ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፤ እንዲሁም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ትላንትና እና ዛሬ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ባሰራጩት መልዕክት ከዛሬ ኅዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም መምህራን ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲገቡ አሳስበዋል ።

የመምህራኑን አድማና ጥቃቄን ይዘን ወደ ሚመለከተው የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ለማካተት ወደ ለሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ስልክ ደውለን ስብሰባ ላይ እንደሆኑ እና ማናገር እንደማይችሉ በመግለጻቸው ሃሳባቸውን ልናካትት አልቻልንም።
መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል :- ትምህርት ሚኒስቴር
**************************

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ  ዙሪያ በተዘጋጀ አውደ ጥናት ላይ  እንደገለጹት፣  መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ  ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ  የመውጫ ፈተና  ከ6 ወራት  በኋላ  እንደሚሰጥም  ዶክተር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት  ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው፣ ፈተናውን   ለ200,000  የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
👍1
በመውጫው ፈተና ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የሁሉንም የጋራ ጥረት እንደሚሻ ተገለጸ።(ሚቴዩ ታህሳስ 5/2015)
********
ይህ የተገለጸው ከሰኔ ወር 2015 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው ሦስቱም ግቢዎች የሚገኙ የኮሌጅ ዲኖችና የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች በዛሬው እለት በዋናው ግቢ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
በውይይቱ መጀመሪያ በዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እጩ ዶ/ር ካሳሁን ሙላቱ ለፈተናው ዝግጅት የተሰሩ ስራዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስመልክተው በዝርዝር መግለጫ ያቀረቡ ሲሆን በእስካሁን በተለያዩ ኮሌጆች በተለይ ስለ መውጫ ፈተናውና ከተማሪዎች በሚጠበቁ መሠረታዊ ጉዳዮች የግንዛቤ መስጨበጫ ውይይት ስለመደረጉም ገልጸዋል።
የትምህርት ስርዓታችን ብቁና በገበያ ተወዳዳሪ የሰው ሀይል የሚያፈራ መሆን እንዳለበት የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቱ የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥና በአገር አቀፍ ደረጃ ብቁ ምሩቅ በጥራት ለማፍራት እንደሚያስችል የታመነበት የመውጫ ፈተና በሚፈለገው ልክ በዩኒቨርሲቲያቸው የተሳካ እንዲሆን ከሁሉም አካላት ከፈጻሚ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ጉዳዮችን እና በየኮሌጁ ስላሉ ነባራዊ ሁኔታ አቅርበዋል። መሟላት የሚገባቸውንም ግብዓቶች አሳይተዋል።
በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ዙር ከ3000 በላይ ተማሪዎች መውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ እጬ ዶ/ር ካሳሁን ሙላቱ ገልጸው እነዚህን ተማሪዎች የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ለውጤት ማብቃት እንደ አገርም ለዩኒቨርሲ ቲው ከፍ ያለ እውቅና የሚያሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ ከኮሌጅ ዲኖችና ትምህርት ክፍል ሀላፊዎች ጋር የነበረውን ውይይት የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሱለይማን አብዱልቃድርን ጨምሮ በጋራ ውይይቱን የመሩ ሲሆን በቅድሚያ የኮሌጅና ትምህርት ክፍል ሀላፊዎች በየኮሌጆቻቸውና ትምህርት ክፍሎቻቸው ለመውጫ ፈተናው ቅድሚ ተሰጥቷቸው ሊሟሉ የሚገባቸውን መሠረታዊ ግብዓቶች በየዘርፋቸው በዝርዝር እንዲያነሱ ተደርጓል ።
ፕሬዝዳንቱ በማጠቃለያው ላይ በውይይቱ ላይ በየደረጃው የሚገኘው አመራር የመውጫውን ፈተና በስኬት ለማጠናቀቅ እስከፍተኛው አመራር ድረስ ያለንን ጥቂት ሀብት በአግባቡ በመጠቀም መሟላት የሚገባቸው እስኪሟሉ መስራት ይገባዋል ብለው በዝርዝር የቀረቡት የግብዓት ጥያቄዎችም ተገቢነታቸውን ገልጸው በአጭር ጊዜ እንዲሟሉ በአስተዳደር ዘርፍ የተገኙ የግዥ፣ፋይናንስና ፕላን ፕሮግራም በጀት ዳይሬክተሮች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል ። በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው እስከዛሬ በመጣባቸው ጊዜያት ትምህርት በጥራት በመስጠት መልካም ስም እንዳለው በተለይ በጤናው እና በህግ ትምህርት መስኮች በሚገኙ ተማሪዎች ለተከታታይ አመታት በመውጫ ፈተናዎች ሲመዘገብ እንደነበረው ከፍተኛ ውጤት ዛሬም መድገም እንደሚገባ አጽንኦት በመስጠት ስራው የአካዳሚኩ ክፍል ብቻ ሳይሆን የጋራ ጥረት የሚጠይቅ ስለመሆኑም በድጋሚ አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል።
Mizan-Tepi University
Light of the green Valley!
በትግራይ ክልል የመማር ማስተማር ሂደትን በቀጣዮቹ አምስት ወራት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በትግራይ ክልል ላለፉት ሁለት ዓመታት ትምህርት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል።

በክልሉ የትምህርት ሥራን ለማስጀመር የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን እቅዶች መያዛቸውንና ዝግጅት መጀመሩን በሚኒስቴሩ የትምህርት መሰረተ ልማትና አገልግሎቶች ዴስክ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ለኢፕድ ተናግረዋል።

በክልሉ የሰው ሀብት የማደራጀት፣ የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን የመጠገንና ግብዓት የማሟላት እንዲሁም የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ እንደሚደረግ ኃላፊው አመልክተዋል።

በትግራይ ክልል የመማር ማስተማር ሥራው ሲጀመር ከሌሎች ክልሎች በተለየ መልኩ እንደሚሆነ የጠቆሙት ኃላፊው፤ በትግራይ ክልል የተማሪዎች ምገባ ለማስጀመር አጋር አካላት እና ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
👍1
2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከታኅሣሥ 18 እስከ 21 ቀን በዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፦ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት
*******

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከታኅሣሥ 18 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
ኢትዮቴሌኮም ቴሌድራይቭ የተሰኘ አዲስ አገልግሎት ይፋ አደረገ‼️

አገልግሎቱ የፋይል ማስቀመጫ ቋት ሲሆን በሶስት አማራጮች ነው ያቀረበው፣ 25GB በ30 ብር ወርሃዊ ክፍያ፣ 100GB በ65 ብር ወርሃዊ ክፍያ እና Unlimited በ300 ብር ወርሃዊ ክፍያ ነው።

አዲሱ የፋይል ማስቀመጫ አገልግሎት ስልኮች በፎቶ፣ ቪዲዮና ሌሎች ፋይሎች ሳይጨናነቁ፤ ሚሞሪ ካርድም ሳያስፈልግ ማስቀመጥ ያስችላ የተባለ ሲሆን ስልካችን እንደ አጋጣሚ ቢጠፋ/ቢበላሽ እንኳ በውስጡ ያሉት ፋይሎች በፍፁም እንደማይጠፉ ኢትዮቴሌኮም አስታውቋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች አድማ በመምታት ትምህርት ማቋረጣቸውን ሰምተናል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዓመት ተማሪዎች ያለ አግባብ የምንመረቅበት ጊዜ በተለይም የ2013 ባች ተማሪዎች  እስከ ሁለት ሴሚስተር ያህል ማለትም ከመመረቂያ ጊዜያችን አንድ ዓመት ዘግይተን እንድንመረቅ ዩንቨርሲቲው ወስኗል በሚል ምክንያት ተቃውሟቸውን ክፍል ባለመግባት እየገለፁ እንደሆነ ከተማሪዎቹ ያግኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጉዳዩ ላይ ግልፅ ውይይት ለማድረግ ኮሚቴ አዋቅረን ጥረት ብናደርግም ዩንቨርሲቲው የኛን ጥያቄ ከመስማት ይልቅ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አካላትን በማሰማራት ማስፈራሪያ እያደረሰብን ነው ሲሉ ከሰዋል።

ቤተሰቦቻችን ከኛ ብዙ ነገር ይጠብቃሉ የሚሉት ተማሪዎቹ በሌሎች ዩንቨርሲቲዎች ከሚገኙ ጓደኞቻችን እኩል መመረቅ ባለብን ካላንደር መሰረት ተመርቀን ተወዳዳሪ እንሁን ማለታችን እንደ ስህተት ተወስዶ አግባብነት ያለው ጥያቄያችን በጉልበት ሊታፈን አይገባም ብለዋል።
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝነት"

ራስ ገዝ ሆነው የሚደራጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም አቀፍ ውድድር አዲስ ፕሬዝዳንቶችን እንደሚመርጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህ አሰራር በአገር ውስጥ ውድድር ተወስኖ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ቅጥር ሂደት በማስፋት የውጭ ዜጎችም ጭምር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪነት እንዲወዳደሩ ዕድል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ ዕቅድ ይዟል። በዚህ እቅድ ከተካተቱት ውስጥ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው በጀት ዓመት የራስ ገዝ አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ይጠበቃል።

መንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶቻቸውን ከሀገር ውስጥ ካሉ ምሁራን አወዳድረው ሲቀጥሩ ቢቆዩም፤ በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች (በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በመቐለ ዩኒቨርሲቲዎች) ለተወሰኑ ዓመታት የውጪ ዜጎችም በፕሬዚዳንትነት ተመርጠው አገልግለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆናቸው የአስተዳደር፣ የአካዳሚ፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

በተለያዩ አገራት በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ እና በአመራርነት የሚሰሩ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን ቢመሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል። 

ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ሊኖራቸው የሚጠበቀው የትምህርት ደረጃ “ዶክትሬት ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የሚወክል ትምህርት እና ልምድ” መሆን እንዳለበት በመመሪያው ሰፍሯል። ሆኖም የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች “በልዩ ሁኔታ” ሊመረጡ እንደሚችሉ በመመሪያው ተቀምጧል። 

እስካሁን በነበረው አሰራር በትምህርት ሚኒስቴር ሹመት የሚያገኙ ፕሬዝዳንቶች የሥራ ዘመናቸው ስድስት ዓመት ሲሆን ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ ሊመረጡ ይችላሉ። ምክትል ፕሬዝዳንቶች በአንጻሩ ሹመታቸው የሚጸድቀው በዩኒቨርስቲዎች ቦርድ ሲሆን አራት ዓመት የስራ ዘመን ይኖራቸዋል።

ራስ ገዝ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ዩኒቨርስቲዎች፤ ፕሬዝዳንቶቻቸውን የሚመርጡበትን መስፈርት፣ የአገልግሎት ዘመን እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚወስኑ ዝርዝር ድንጋጌዎች እንደሚኖራቸው ዋና ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ያለ ትምህርት ሚኒስቴር ጣልቃ ገብነት ፕሬዝዳንቶቻቸውን በቦርድ ማጽደቅ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ኢትዮጵያኢንሳይደር
የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመሩ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መሰቀልና መዝሙር መዘመር ጋር በተገናኘ፣ በት/ት ቤቶች ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመሩ መመሪያ መሰጠቱ ተሰማ፡፡

ትምህርት ቤቶች በጥብቅ ዲስፕሊን እንዲመሩ ትዕዛዝ ያስተላለፈው የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሲሆን፤ በጥብቅ ይፈጸም የተባለው አሰራር በተማሪዎች እና በመምህራን ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ያዛል ተብሏል፡፡

#አዲስ_ማለዳ በትምህርት ቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ተፈርሞ፣ ለኹሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች የተላለፈውን ደብዳቤ መመልከቷን ዘግባለች፡፡

በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው፤ ትምህርት ቤቶች አንድ ቀን ላረፈደ ተማሪና አንድ ቀን ለቀረ ተማሪ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡ ታዘዋል፡፡

እንዲሁም ኹለት ቀን ያረፈደና የቀረ ተማሪ በወላጅ ፊት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ዘላለም በፈረሙበት ደብዳቤ ላይ ሰፍሯል፡፡ ከኹለት ቀን በላይ ያረፈደና የቀረ ተማሪ በመመሪያው መሰረት ተፈጻሚ የሚሆን እርምጃ  እንደሚወሰድበትም ተመላክቷል፡፡

በትምህርት ቤቶች በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ እንዲደርግ የሚያዘው ደብባቤው፣ ተማሪዎች ስልክ፣ ርችትና ፊኛ የመሳሰሉ ቁሶችን ወደ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይሄዱ ገደብ ጥሏል፡፡ ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ መገልገያዎችን፣ ይዞ የተገኘ ተማሪ የድስፕሊን እርምጃ እንዲወስዱ ትምህርት ቤቶች መታዘዛቸውም ተነግሯል፡፡

የትምህርት አመራር፣ መምህራንና ሰራተኞች በሙሉ የሥራ ሰዓታቸውን አክብረው፣ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ጥብቅ ትዕዛዝ የተሰጣቸውም ሲሆን፤ በዚህም ማርፈድ፣ መቅረትና የሥራ ሰዓት ሳያልቅ ከትምህርት ቤት ግቢ መውጣት የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡

የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ትዕዛዝ ባስተላለፉበት ደብዳቤ፣ ያስተላለፉትን ትዕዛዝ የማያስፈጽም በየደረጃው የተቀመጠ የትምህርት ቤት አመራርም ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ኃላፊው ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች፣ ባስተላለፉት ትዕዛዝ “ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ቦታ ናቸው” ያሉ ሲሆን፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያደናቅፍ ተግባራ የሚፈጽም ማንኛውም አመራር፣ መምህር፣ ሰራተኛና ተማሪ ላይ ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድና ሪፖርት እንዲደረግም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ አዲስ ማለዳ
በአዲስ አበባ በትምህርት ቤቶች ላይ  ከሰንደቅ  አላማ ጋር  በተያያዘ  የተፈጠረው ችግር አሳዝኖኛል ሲል ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ ገለጸ፡፡

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርትቤቶች ላይ  ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር  ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ  እንዴት ያይዋል ሲል አሀዱ ጠይቋል
በቀላሉ መጨረስ የሚቻለውን ጉዳይ  በዚህ ልክ ችግር  እስኪፈጠር ድረስ ተግባራዊ መደረጉ አሳዝኖናል ሲሉ የኮምሽኑ  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  ኮምሽነር ዶክተር ዬናስ አዳዬ ተናግረዋል፡፡

በንግግር መጨረስ የሚቻለውን  ነገር  ልዩነትን ወደ የሚፈጥር ፤ወደ ግጭቶች እንዲቀየር እና በህይወት  እስኪጠፋ ድረስ  መድረግ አልነበረበትም ነው ያሉት፡፡
ብዝሀነት  የሚደገፍ ቢሆንም ህዝቡን  በሚለያይ መልኩ ሳይሆን ባማከለ መልኩ መደረግ አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ ኮምሽኑ ለመስራት ያቀዳቸው ስራዎች እንዳልተሳካ የተናገሩት ኮሚሽነሩ እናዚህ ጉዳይዎች በምክክር እና በውይይት እንደሚፈቱ ኮምሽኑ ያምናል ብለዋል፡፡

ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣት እንደሚያስፍልግል ኮምሽኑ የችግሮች መሰረታዊ ምክንያቶች ምንድናቸው የሚለውን ከህዝቡ የመጡ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚቻልም አንስተዋል፡፡ከህዝቡ የሚመጡ የመዋቅራዊ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማድረግ መንግስት እንዲህ ማድረግ  አለበት በሚልም ምክረ ሃሰቦች እንደሚሰጡ አንስተው፤ እንዲህ አይነት ተግባራት የኮምሽኑን  አካሄዶች ሊያደናቅፉ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡

©Ahadu
ሰባት ተማሪዎችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ሰባት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው በማፈናቀል በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል ።

ተማሪዎችን ከትውልድ አካባቢያቸው በእግር እና በባጃጁ ተሽከርካሪ በማራቅ በወግዲ ወረዳ ለሚ ታዳጊ ከተማ በአውቶቡስ ጭነው  ለማዘዋወር ሲሞክሩ እንደተያዙ ተገልጿል ።   በአውቶቡስ ውሰጥ ተሳፍረው የነበሩ የፀጥታ ሀይሎች የተማሪዎችን ሁኔታ በመጠራጠር ባደረጉት ማጣራት አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወግዲ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽ/ት ቤት ኃላፊ አ/ቶ ደሳለው ጌትነት  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ተማሪዎች የቀበሌ መታወቂያ ይዘው የተገኙ ሲሆን እድሜያቸው መታወቂያ ለማግኘት ያልደረሰ እንደሆነ ተገልጿል ። ልጆችን ከትምህርት ገበታቸው በመነጠል በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ አካላት እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ የጠፉ ልጆቻቸውን በማፈላለግ ላይ የሚገኙ ወላጆች መናገራቸውን አ/ቶ ደሳለው ገልፀዋል ።


     #ዳጉ_ጆርናል