(ሚቴዩ ህዳር 27/2015) የጸረ-ሙስና ትግል ግንዛቤ ትምህርት ህጻናትን ከቤተሰብ ጀምሮ በመልካም ስነ-ምግባር ቀርጾ ከማሳደግ ሊጀምር ይገባል ።
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ እንዲሁም በአገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአለም ጸረ-ሙስና ቀን "ሙስናን መታገል በተግባር "በሚል መሪ ቃል በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ በፓናል ውይይት ተከብሯል ።
በዓሉን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ ናቸው ። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የጸረ-ሙስና ትግሉ የሁሉንም ማህበረሰብ የጋራ ጥረት ይፈልጋል ብለው በተለይ ከህጻናት ጀምሮ በመልካም ስነ-ምግባር አንጾ በማሳደግ ረገድም የቤተሰብ ሀላፊነት ትልቁን ድርሻ እንደሚሰጠው ገልጸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርስቲው ስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈለገውን ግንዛቤ መፍጠር ይገባልም ብለዋል ።
የዩኒቨርስቲው ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት የስነ-ምግባር ዘርፍ ባለሙያ አቶ አሳየ ገሮ በእለቱ ለውይይት የቀረበውን የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል። በሰነዱም ዝርዝር መረጃዎች በተለይ ከበዓሉ መሪቃል ማለትም"ሙስናን መታገል በተግባር" ከሚለው ሀሳብ ጋር በተጣጣመ መልኩ ለውይይት እንዲመች ሆነው ቀርበዋል ። ውይይቱንም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት የእለቱን የውይይት ሰነድ ካቀረቡት ባለሙያ ጋር በመሆን መርተዋል።
ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሀሳቦችም ሰፊ ውይይት ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል ።

Mizan-Tepi University
Light of the green Valley!
#Update

ፖሊስ ሰኞ ዕለት ያሰራቸውን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማኅበር ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ጨምሮ ያሰራቸውን አራት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ዛሬ እንደለቀቀ ከምንጮቹ መስማቱን #አዲስ_ስታንዳርድ ዘግቧል። በዩኒቨርስቲው ከትናንት ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደት መቋረጡንና መምህራኑ መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ፀጥታ ቢሮ እና የዞን አመራሮች የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ  የትምህርት ክፍል ኃላፊወችን ሰብስበው በማንገራገር አድማውን ለማሰናከል ሞክረው ነበር። ነገር ግን መምህራን ጉዳዩን በሚገባ ካስረዷቸው  በሗላ አመራሮቹ ስለ ጉዳዩ በቂ መረጃ እንዳልነበራቸው በመግለፅ ይቅርታ ጠይቀው ስብሰባው ተጠናቋል። ይህ የሆነው ሰኞ ህዳር 26 ነበር።
በበነጋታው ማክሰኞ ህዳር 27 ደግሞ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝደንቶች የት/ት ክፍል ሓላፊወችን በመሰብሰብ ትምህርት እንዲጀምሩ ጫና ለመፍጠር ሞክረው ነበር።
ይሁን እንጂ መምህራኑ የዞን የፀጥታ አካላትን ለምን አስገባችሁ በሚል ምክትል ፕሬዝደንቶቹን አፋጠዋቸዋል። ምክትሎቹም የዞን ፀጥታ አካላት ከነሱ እውቅና ውጭ ባይገቡም ያለ ፍላጎታቸው እንደገቡ ገልፀውላቸዋል።
የመምህራን ትግል ያሸንፋል!
#የዩኒቨርስቲ_መምህራን ለምን እንቃወማለን ? በደሉ ላልገባችሁ ብቻ
===================================
ሀገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው (ከነ ችግሮቹም ቢሆን) ምሁራን መካከል ከ90 ፐርሰንት በላዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ለአመታት ምርምሮችን ሲሰራ እና ሲያሰተምር የከረመ የዩኒቨርሰቲ መምህር አሁን “እጅጉን” አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል፡፡ በዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ እየሆኑ ያሉ አንድ አንድ ነገሮች በጣም ያሳዝናሉ፡፡

ለምሳሌ፤
©እንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ1970ዎቹ ወይም 80ዎቹ ሲያስተምር የነበረ ዶክተር (ፒ ኤች ዲ) ደሞዝ በዚህ አመት ከተመረቀ ዶክተር (ፒ ኤች ዲ) ጋር እኩል ነው (ወደ 11 ሺ ብር ገደማ)፡፡

© ዩኒቨርስቲ መምህራን የፈለጉትን ያህል አመት ቢሰሩ የደሞዝ እድገት የሚባል ነገር የላቸውም፡፡ በ2008 ሲከፈል የነበረ አሁንም ከ8 አመታት በኋላ ያው ነው፡፡

© ለማነጻጸር አንድ የዛሬ 8 አመት ከዩኒቨርስቲ የተመረቀ ተማሪ ደምወዝ ቢያንስ አምስት ጊዜ ያድጋል (በመንግስት ተቋማት ውስጥ፡፡
  • እድሜውን በሙሉ ምርምር በመስራት እና በማስተማር ወገቡ የጎበጠ የአንድ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ደምወዝ በአንድ አንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከድግሪ ምሩቅ ደሞዝ ያንሳል፡፡

   • መንግስት መምህሩ ከሚያገኛቸው ከእያንዳንዷ ገቢ ከ30-35 ፐርሰንት ይቀንሳል (የተጨማሪ ሰዓት ክፍያን ጨምሮ)፡፡
  • አንድ መምህር ምርምር ሰርቶ ጽሁፍ አዘጋጅቶ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ለማቅረብ ሲሄድ የሚሰጠው ክፍያ 3 ሺ ብር ነው (ልብ አድርጉ ከዚህም 35 ፐርሰንት ይቆረጣል)፡፡

  • ለዩኒቨርስቲ መመህራን ለቤት ክራይ ተብሎ የሚሰጠው ብር 800 ሲሆን ከዚህም ታክስ ይቆረጣል (እውነት ይህ ብር የወር ቤት ክራይ ይከፍላል?)፡፡ ለማነጻጸር የጀግኖቹ የአዲስ አበባ መመህራን የቤት ክራይ 3000 ብር ነው፡፡ እነርሱም ቢሆን ያንሳቸዋል፡፡

   • ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት ለመማር የሚላክ መምህር የኪስ ገንዘብ 1800 ብር ነው፡፡ (አዲስ አበባ ውስጥ 1800 ለታክሲ፣ ለፕሪንት እና ሌሎችም ወጪዎች፡፡ መቼም ግሩም ነው፡፡)

   • አንድ PH.D. ተማሪ መመረቂያ ጽሁፉን እንዲሰራ ለማህበራዊ ሳይንስ 45 ሺ ለተፈጥሮ ሳይንስ 60 ሺ ይሰጠዋል (ይህ እንግዲህ ከ3-5 አመት የሚፈጅ የምርምር ፕሮጀክት ነው) ምን አይነት ምርምር ነው ግን ቢዘህ የሚሰራው?፡፡ MA/MSC ተማሪ እንደውም 25 ሺ ነው የሚሰጠው፡፡

   • ብዙዎች እንደዚህ ከሆነ ለምን መምህራኑ ለቀው ወጥተው ሌላ ስራ አይሰሩም ይላሉ፡፡ ወዳጄ… ዩኒቨርስቲዎች እንደ አራጣ አበዳሪ መምህሩን በአራጣ ይዘውታል፡፡ ሁለት አመት MA/MSC ከዩኒቨርስቲ ተልኮ የተማረ መምህር አራት አመት ወይም ከ200 ሺ ብር በላይ እንዲሁም PH.D. የተማረ 8 አመት ወይም ከ680 ሺ ብር በላይ ካልከፈለ የትም ንቅንቅ አይልም ምክንያቱም ምንም የትምህርት ማስረጃ በእጁ ስለሌለ፡፡

   • የመምህሩን ሮሮ ላለመስማት መንግስት “ችግር ላይ ነኝ፣ ሀገርም ችግር ላይ ነች” ይላል ፡፡ እውነት ነው ይህንን ለመረዳት መመህሩ የሚከብደው አይመስልም፡፡ ግን በየአመቱ ጭማሬ የሚደረግላቸው እንደ ንግድ ባንክ፣ ገቢዎች፣ ኢዜአ፣ ኢቲቪ… ያሉ ተቋማት የመንግስት አይደሉምን?:: ( እነዚህን ተቋማት በቅርብ ስለማውቃቸው እንጂ በየአመቱ የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ የሚደረግላቸው የመንግስት ተቋማትም አሉ)፡፡
ትምህርት ሚኒስትር ከላከዉ አቴንዳንስ እና ለዩኒቨርሲቲዎች ካስተላለፈዉ አድማዉን በራሳቸዉ እንዲፈቱት ካስቀመጠዉ አቅጣጫ በግልፅ እንደምንረዳዉ ምንመ አይነት ምላሽ ከቀን 26-30 እንደማይኖር እና በተለያዩ ዘዴዎች ማለትም በየዩኒቨርሲቲዉ ባሉት ተላላኪዎቹ ዉዥንብር በመፍጠር ፤ ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት ምንም አይነት ፖብሊክ ሚድያ እንዳይዘግበዉ ignorance በማካሄድ አድማዉን አለማሳካት ነዉ።  ይሄም በቁርጠኝነት እየተካሄደ ይገኛል። የተላከዉ ልዩ መቆጣጠሪያ ከቀን 26-30 ብቻ የሚል መሆኑ ለዚህ እንደ ማሳያ ሊቀመጥ ይችላል። በመሆኑም መምህሩ ትግሉ እንዳይኮላሽበት እና ግቡን እንዲመታ ከፍርሃት ቆፈን ወጥተዉ በአንድነት መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። እኔ በአንድ ዩኒቨርሲቲ በሃላፊነት ደረጃ ያለዉ ሲሆን በእኛ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሬዝደንቱ ጭምር በየካምፖሱ እና በየኮሌጁ የሃሰት ሪፖርት ጭምር በፐርሰንት እየተቀመጠ መምህሩ ልዩነት ያለዉ እንዲመስለዉ በማድረግ እና በአንድ አንድ ትምህርት ክፍሎች ከአቅም በታች በጎሳ ኮታ የገቡ ደካማ መምህራን ፤ ካድሬዎችን ብቻ በመጠቀም 90% ገብቷል በማስባል ዉዥንብር ለመፍጠር እየተሞከረ ነዉ። በመሆኑም ትምህርት ሚኒስትር እስከ 30/03/2015 ዓ/ም ያሰበዉ ሴራ ካልተሳካ እና አንድነቱ ካልተሸረሸረ ወደቀልቡ መመለሱ ግድ ነዉ።  ይሄ ትግል ወደ ቀጣይ ሳምንት ከዘለቀ ያለጥርጥር ፐብሊኩን ያገኛል እያገኘም ነዉ።
           አንድነት ሃይል ነዉ!
      ይሄ መልዕክት ለሁሉም ይድረስ
👍2
ሌላኛው ነገ ብትቀሩ ዋ የሚሉ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ ላይ ናቸው ።

ሁለቱም ልጥፍ  ርባና ቢስ ነው ።

ዩንቨርስቲዎች የሚመልሱት አንድም ጥያቄ የለም ። ሁሉም ከአቅማቸው በላይ ነው ። እንዲያውም የእነርሱም ጥያቄ ነው ።

መፍትሄው

1. ትምህርት ሚኒስትሩ ወይም መንግስት ነኝ ያለው በፅሁፍ ለደረሱት ጥያቄዎች ምላሹን በሚዲያ መስጠት ፣ በጣም ቀላል !

2. የመምህራን ተወካዮችን ሠብስቦ መነጋገር ፣ ማሰር ማሳደዱ it makes us more tuner !

3. በአንድ ቀን የሚፈቱ እና የማይፈቱ የሚባሉትን ለይቶ መግባባት ላይ ለመድረስ መስራት ፣

   ካልሆነ ምንም ጠብ የሚል ነገር የለም ።  በዓለም ላይ ረዢሙ የስራ ማቆም አድማ ተደርጎ የሚመዘገበው አድማ በኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲ መምህራን ይደረጋል !

እንዳልነው መምህር ስራ ያልገባበት ቀን ተቆጥሮ ቢቀጣ የሚቀርበት 270 ብር ነው
👍1
ወደ ት/ቤት በመሄድ ላይ የነበረችን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡

ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በአንበሳሜ ከተማ ህዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ  ተማሪ አበባይቱ አራጋው ወደ አንበሳሜ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር በመሄድ ላይ እያለች ተፈራ ማሬ ካሳ የተባለ ግለሰብ አስፈራርቶ በመያዝ አስገድዶ ሲደፍራት በአካባቢው የጸጥታ ሀይል ይያዛል።

በዚህም ወንጀለኛው ላይ ምርመራው በማድረግ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶበት የወረዳው ፍ/ቤትም መዝገቡን መርምሮ ጥፋተኛ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ8 አመት ፅኑ እስራት የተቀጣ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መረጃው፦ የደራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው
በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች
ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር መወሰኑ ተሠማ።

ይህ የተገለጸው የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ባለድርሻ አካላትን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰኞ ኅዳር 26/2015 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው የፐብሊክ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ ዘሪሁን አስፋው እንደተናገሩት፥ የመንግሥትን ሀብት በመመዝበር በተለዩ ስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ጭብጦችን የመለየት ሥራ በመከናወን ላይ ነው።

የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድባቸው የተለዩት ዩኒቨርሲቲዎችም ቡሌ ሆራ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልድያ፣ ሀዋሳ፣ መቱ፣ ደብረ ታቦር፣ ዲላ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ በሙስና የተመዘበረ ገንዘብ ወደ መንግሥት ካዝና ማስመለሱን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ
*********

በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ እና ከ24 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ በሙስና የተመዘበረ የከተማ ቦታ ማስመለሱን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የሙስና ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በፍትሕ ተቋማት መካከል ከአጥፊዎች የተሻለ ቅድመ ዝግጅት እና የምርመራ ብቃት እንደሚያስፈልግም  በአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኅላፊ ዝጋለ ገበየሁ  አስታውቀዋል፡፡
17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች  እና ህዝቦች ቀን በሐዋሳ እየተከበረ ነው
*********************

17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል በሐዋሳ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዓሉ ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ብሔር ብሔረሰቦች፣ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ፎቶ:- በናትናኤል ፀጋዬ እና በመሐመድ ፊጣሞ
መልዕክት ከእንጅባራ ዩንቨርሲቲ                         ----------------------------------------------------- እኛ  ዩንቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች የምናደርገውን ትግል ጠልፈው ለመጣት የሚታትሩ የትምህርት ክፍል ኃላፊወችንና ሌሎች ግለሰቦችን ደረሰንባቸዋል።ስለሆነም ከዚህ ትግል መጨረሻ በኋላ የመጀመሪያው ስራችን የሚሆነው እነዚህን ሰዎች ከኋላፈነታቸው አስወግደን ፤ከምንም አይነት የአካዳሚክም ሆነ ማህበራዊ ህይወት መስተጋብር የምናገላቸው መሆኑን እየገለፅን፤ የስምና፣የስልክ፣የኢሜል አድራሻቸውን እያደራጀን ስለሆነ በፍጥነት እራሳቸውን እንዲያርሙ እናሳስባለን።
ት/ሚኒስቴር ለምን ፀጥ አለ???
👉 የመጫወቻ ካርዶቹን ፍቆ ስላልጨረሰ ማለትም
#1 የመጀመሪያው ካርድ- አድማውን አስተባብረዋል ያላቸውን ስራ አስፈፃሚዎች በማሳሰርና በማዋከብ መምህራን ክላስ እንዲገቡ የማድረግ  ሙከራ - የከሽፈ
#ካርድ 2 - ጥያቄዎቻችንን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖራቸው ከዘር፡ ሀይማኖትና ሌሎች ነገሮች ጋር በማያያዝ አንድ እንዳንሆን በማድረግ የተወሰኑ መምህራን ክላስ እንዲገቡና ሌሎችም እንዲከተሉ የማድረግ ሙከራ- አደገኛ ግን አንድ በመሆናችን የከሸፈ ካርድ
#ካርድ 3- ተስፋ አስቆራጭ ማስታወቂያዎችን(ት/ሚኒስቴር ምንም መግለጫ አይሰጥም የሚል- ጎንደር ዩ/ቲ) መለጠፍ , ማሰጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤዎችና ኢ-ሜሎችን ለት/ት ክፍል ሃላፊዎች በመላክ በመካከላችን ልዩነት እንዲፈጠር በማድረግ የተወሰነ መምህር ክላስ እንዲገባ መሞከር- እየከሸፈ ያለ
#ካርድ 4- ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ አዘል መግለጫ በት/ሚኒስቴር - ያልተፍቀ ካርድ ግን የሚከሽፍ ሙከራ
# 5- ሳይወዱ በግድ ለጥያቄዎቻችን የመፍትሄ ሃሳብ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
ፖሊስ በመዲናዋ በትምህርት ቤቶች ረብሻ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩና ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስአበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ፖሊስ "በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በአንድ በኩል የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብትና ማንነታቸውንና ባህላቸውን መግለፅን እንደ ጫናና በሃይል በሌሎች ላይ እንደተጫነ አድርጎ የመቀስቀስ በሌላ በኩል ደግሞ፤ የኦሮሞ ህዝብ እየሞተ ነው የህዝብ ባህልና ማንነት ተዋረደ የሚሉ እርስ በእርሱ የሚቃረን የግጭት ማቀጣጠያ  አጀንዳ በመፍጠር እንዲሁም፤ የወልቃይትና የአዲስ አበባ ጉዳይ አንድ ነው የሚል መፈክር ይዘው ከመውጣት ባሻገር  የሐገሪቱን ሰንደቅ ዓላማና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና ከሰንደቁ ላይ በማውረድና መሬት ለመሬት በመጎተት ከፍተኛ ድፍረት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።" ብሏል፡፡

ሰሞኑን በተወሰኑ አንደኛና ጥቂት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጥፋት አጀንዳቸውን ከተቀበሉ አንዳንድ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በመሆን በማደናገርና በማወናበድ ምንም የማያውቁ አብዛኛው ተማሪዎችን ከፊት በማሰለፍ ባስነሱት ረብሻ  በትምህርት ቤቶቹ ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን መረጋገጡንም የአዲስአበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
“ኢትዮጵያ ትፈተናለች  እንጂ አትሸነፍም” ጠቅላይ  ሚኒስትር ዐቢይ  አህመድ
***********************

ኢትዮጵያ ትፈተናለች  እንጂ አትሸነፍም ሲሉ ጠቅላይ  ሚኒስትር ዐቢይ  አህመድ ተናገሩ።

በሀዋሳ ከተማ በተከበረው 17ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ክብረ በዓል ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ የሁላችን ቅርስ ፣እሴት የሚታይበት እና በኢትዮጵያ ጥላስር ሆነን የምንሰባሰብበት ቀን ለሆነው ለኢትዮጵያዊነት ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

የተለያየ ባህልና  እሴት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ሰበዝ ሁነው  ሲደምሩ  ታላቋን ኢትዮጵያ እንደሚፈጥሩ በማጤን በአብሮነት  የጋራ ቤታችንን ለመስራት ትኩረት መስጠት አለብን ብለዋል።

የጋራ ቤትን በጋራ መገንባት ላይ ትኩረት  በመስጠት  ከውጭ የሚመጡ አጀንዳዎችን ማክሸፍ እንደሚገባ  ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የእንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ችግር የሚፈታው የኢትዮጵያ ችግር  ሲፈታ በመሆኑ ለዚሁ በጋራ መስራት ላይ ትኩረት እንዲደረግም ጠይቀዋል።
ሙስና 'ሀራም' መሆኑን በተመለከተ ህዝበ ሙስሊሙን ለማንቃት ከነገ ጀምሮ በመስጂድ ኢማሞች ሁጥባዎች ይቀርባሉ ‼️

🗣የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት


ኢስላማዊ እና ሃይማኖታዊ አስተምህሮን መሰረት በማድረግ ሙስና "ሐራም' (ውጉዝ) መሆኑን በተመለከተ ህዝበ ሙስሊሙን ለማንቃት ከነገ ዓርብ ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ በሚገኙ ከ290 በላይ መስጂዶች በኢማሞች አማካይነት ሁጥባ (ምክር) እንደሚቀርብ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባ ገልፀዋል።

በኢስላም አስተምህሮ ሙስና በፍፁም የማይደገፍና ፀያፍ ተግባር በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ሊያወግዘው እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የእምነት ሀገር መሆኗን በማውሳት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ እኩይ ተግባር እንዲታቀቡ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ደግሞ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር ናቸው።

ሙስናን ለመከላከል በዘመቻ መልክ እንዲሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮሚቴ አቅርበው ማሰየማቸው ይታወሳል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት በከፊል መቋረጡ ተሰማ‼️

ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም.  የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዋነኛነት "ሞት ይቁም" የሚል መፈክር ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ብዙም ሳይቆይ ሰልፉ በአድማ በታኞች እንዲበተን ተደርጎ እንደነበር የግቢው ተማሪዎች ነግረውናል።ሰልፉ ከተደረገ በኋላ እስከዛሬ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡንም ተማሪዎቹ ጨምረው ነግረውናል።

ዩኒቨርሰቲው በትናንትናው እለት ባወጣው ማስታወቂያ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ ትምህርት የማይመለሱ ተማሪዎች በገዛ ፍቃዳቸው ትምህርታቸውን እንዳቆሙ እንደሚቆጠር አሳስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ተማሪዎች ሙሉ ሙሉ ወደ መደበኛ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸው ታውቋል።

ስለጉዳዩ ለማጣራት #አዲስ_ዘይቤ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርስቲው የስራ ኃላፊ ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ትምህርታቸው አለመመለሳቸውን አረጋግጠውልናል።
ከኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን #አዲስ_ማለዳ በወቅቱ በቦታው ከነበሩ ተማሪዎች ሰምታለች፡፡

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎቸ መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱም ተሰምቷል።

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች እና የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪዎች ጭምር ከሁለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡ በሰንደቅ አላማው ይሰቀላል አይሰቀልም ውዝግብ በተነሳው ግጭት ጉዳት ያስተናገዱ ተማሪችን ወደ ህክምና ተቋም ለመውስድ ሁለት አንቡላንሶች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡

ምንጭ፡ አዲስ ማለዳ
ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ካውንስል ውይይት በማካሄድ መማር ማስተማሩ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ስለሆነም ሥራ ያቋረጣችሁ መምህራን ከነገ ህዳር 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መደበኛ የማስተማር ሥራ እንድትመለሱ እያሳወቅን ይህን ባላደረጉ መምህራን ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አሳውቋል።