በለቡ ቅድመ ግቢ ጉባዔ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፪ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነዳይንን በመመገብ ተዘክሮ ዋለ
******************** ******************** ********************
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪዎች በቅድመ ግቢ ጉባዔ መርሐግብራቸው የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን 35ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ነደያንን መግበዋል፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ቅድመ ግቢ ጉባዔ ኅዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በአምስት ጉዳዮች ላይ ማለትም በትምህርት፣በዝማሬ፣(በዝክርና ነዳይን ምገባ)፣(ዲያቆናትን አገልግሎት ምደባና የማስዋብና ጉዞ)፣ እንዲሁም የአባላትና ግንኙት ሥራዎችን የሚሠሩ ክፍሎችን አዋቅሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መንፈሳዊ ጉዞዎችን፣ዝክርና ነዳያንን መመገብ፣ከ70 በላይ አባላቱን የንሰሃ አባት በመስያዝና ትምህርተ ንስሃን በማሰጠት ለቅዱስ ሥጋው ለክቡር ደሙ አብቅቷል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ 18 ቅድመ ግቢ ጉባያት ጋር የአንድነት መርሐግብራትን ከማካሄዱም በላይ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን 35ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ ነዳያንን በመመገብ አስበው ውለዋል፡፡
የለቡ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ቅድመ ግቢ ጉባዔ ማክሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በለቡ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ 35ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐግብር የብፁዕነታቸውን አስተምህሮ፣ ሥራዎቻቸውንና ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ያበረከቷቸውን ዘመን ተሸጋሪ አሻራዎች በመዘከር እና ለብጹነታቸው መታሰቢያ የተዘጋጀውን ጸበል ጸዲቅ ለነዳያን በመዘከር አክብረውታል፡፡ ይህ ተግባር በሌሎች ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶችም ተግባራዊ መሆን እንዳለበት በመርሐግበሩ የተሳተፉ ታዳሚዎች እንዳነሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲጓዙ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ድካም በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው ማረፋቸው ይታወሳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

በድጋሜ ስለማሳወቅ
ክቡራን ባለአክሲዮኖች ከዚህ በፊት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የትምህርት፣ሙያና የስራ ልምድ መረጃ ለማደራጀት ይረዳ ዘንድ መረጃ እንድትልኩልን መጠየቃችን ይታወሳል፡፡
ስለሆነም እስካሁን ያላካችሁልን ባለአክሲዮኖች https://forms.gle/u3XzKRPVQ4x2ykzRA ማስፈንጠሪያውን በመጫን አስፈላጊውን መረጃ ሞልታችሁ እንዲልኩልን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃን፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ

Google Docs
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የባለአክሲዮኖች የትምህርት፣ ሙያና የስራ ልምድ መሰብሰቢያ ቅጽ
በባሕርዳር በ6ኛ እና8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ሲያስመዘግቡ መምህራን ሽልማት ተበረከተላቸው
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች አባይ ማዶ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ያስታወቀ ሲሆን በ2017 የትምህርት ዘመን የተሻለ ስራ አፈጻጸም ያሳዩ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ሁለት መምህራን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አባይ ማዶ ቅርንጫፍ ተማሪዎች በ6ኛ ክፍል ተማሪ አቤል እውነቱ 99.96 በመቶ ሲያስመዘግብ ከ8ኛ ክፍል ተማሪ ከነአን መልካሙ 99.97 በመቶ በማስመዝገብ ከባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ስር ካሉ ተማሪዎች መካከል ቀዳሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በቅርቡ ባዘጋጀው “የመምህራን ቀን” ዝግጅት ላይ በ2017 የትምህርት ዘመን የተሻለ ስራ አፈጻጸም ያሳዩ ትምህርት ቤቶች መካከል የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መምህራን የሥነ ዜጋ መምህሩ የሆኑት መምህር አስናቀው አንተነህ እና የሂሳብ መምህር የሆኑት መምህር ጌትነት አካላት የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል።
ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::