Elon Academy plc ኤሎን አካዳሚ
5.74K subscribers
3.12K photos
231 videos
1.58K files
165 links
EVERY STUDENT,EVERY CHANGE,EVERY DAY AT ELON!!!
For more information

ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች
https://t.me/Elonschool7/4669
Download Telegram
Check out this TikTok I posted! #sounds ▶️Watch the full video now! https://vt.tiktok.com/ZSxM4QNXw/
2
🤔 ምን አዲስ ?!!🤔

በ2019 የትምህርት ዘመን ይዘናቸዉ ለመምጣት ት/ቤታችን እየተዘጋጀባቸዉ ካሉት ጉዳዮች መሀል አንዱ የተየማሪዋችን የደንብ ልብስ ይመለከታል።

በተደጋጋሚ ከወላጆች ከሚሰጡን አስተያየቶች መሀል አንዱ ተማሪዋች በሳምንቱ መሀል የሚቀይሩት የደንብ ልብስ ቢኖራቸዉ የሚለዉ ይገኝበታል።

ይህንኑ የወላጆች ተደጋጋሚ ጥያቄና የተማሪዋቻችንንም ፍላጎት ግምት ዉስጥ ከቶ ትምህርት ቤታችን ለአዲሱ አመት ለተማሪዋቻችን በሳምንቱ መሀል ቅያሪ የሚሆን ፣በሰዉነት ማጎልመሻ ክፍለግዜም ሊለብሱት የሚችሉት ደረጃዉን የጠበቀና የት/ቤቱ አርማና ስም ያለበት የደንብ ልብስ ለማዘጋጀት እስቧል። ምን ይላሉ?
35👍29
🎯ጥቅል መረጃ ስለመስጠት🎯

የቴሌግራም ገፃችን የተለያዮ መረጃዋችን በማቀበል እንዲሁም ከዉድ የኤሎን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየት በመቀበል ላለፋት 6 አመታት ሲያገለግለን ቆይቷል። በዚህም ደስተኞች ነን። የገፁን የአጠቃቀም መመሪያ አክብረዉ
(https://t.me/Elonschool7/5837) የሚንቀሳቀሱ ቤተሰቦች ስላሉንም አመስጋኞች ነን።

ትምህርት ቤታችን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳሳወቀዉ ወላጆች የሚኖራቸዉን የትኛዉንም አስተያየት ለመቀበል በሩ ክፍት ነዉ ። ለዚህም ሲባል የschoolx፣ የኮሚኔኬሽን መፅሀፍንና የተለያዩ ስልክ ቁጥሮችን
(https://t.me/Elonschool7/5871) ለዚሁ አላማ እየተጠቀመ ይገኛል።

ሆኖም ጥቂት ግለሰቦች በግል የሚሰማቸዉን ቅሬታ ብሎም በማስረጃ ያልተደገፋ አሉባልታዋችን የቴሌግራም ገፁን በመጠቀም አለን ለሚሉት አቤቱታም ሆነ ቅሬታ ምላሽ ሊያስገኝ በማያስችል መንገድ ስም የማጥፋት ተግባር ላይ ተሰማርተዉ እንዳሉ አስተዉለናል ። አሉባልታዉን በመንዛት የተጠመዱት ወገኖች ማንነታቸዉንና አድራሻቸዉን ሰዉረዉ የሚንቀሳቀሱ መሆኑንም ልብ ይሏል።

ጉዳዩን በቸልታ ለማለፍ የሞከርን ቢሆንም አሉባልዋቹና ክሶቹ የአንዳንድ ወገኖችን ስሜት እንደረበሹ አስተዉለናል ።

በመሆኑም:-

📍በተቋማችን ላይ ምንም አይነት ቅሬታ ያላችሁ ወገኖች ማስረጃዋቻችሁን ይዛችሁ ልጆቻችሁ በሚማሩበት ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት አሊያም በስልክ ቁጥሮቻችን በነፃነት ማቅረብ እንደምትችሉ በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

📍 የቴሌግራም ገፁን ላልተገባ አላማ የሚጠቀሙትን ከዚህ በኃላ የማንታገስ መሆኑንም መግልፅ እንወዳለን።

📍በስራ ሂደት የሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደሚኖሩ የምንቀበል ሲሆን ፣ሆኖም ከቸልተኝነት፣ከቅንነት መጉደልና ሆን ተብሎ የሚደረግ ነገር እንዳልሆነም በትህትና ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ተባብረን በመስራት ለዉጥ አምጥተናል።

የትምህርት አጋርዋ!!!
10👍3
Elon Academy plc ኤሎን አካዳሚ pinned «🎯ጥቅል መረጃ ስለመስጠት🎯 የቴሌግራም ገፃችን የተለያዮ መረጃዋችን በማቀበል እንዲሁም ከዉድ የኤሎን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየት በመቀበል ላለፋት 6 አመታት ሲያገለግለን ቆይቷል። በዚህም ደስተኞች ነን። የገፁን የአጠቃቀም መመሪያ አክብረዉ (https://t.me/Elonschool7/5837) የሚንቀሳቀሱ ቤተሰቦች ስላሉንም አመስጋኞች ነን። ትምህርት ቤታችን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳሳወቀዉ ወላጆች የሚኖራቸዉን…»
12
#AddisAbaba

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተናዎች የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

በአዲስ አበባ የ2018 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡
 
በዚህ መሰረት የ6ኛ ክፍልፈተና ሰኔ 8 ፣ 9 እና 10/2018 ዓ.ም እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
 
በ6ኛ ከፍል 84,882 ተማሪዎች በ199 የመፈተኛ ጣቢያዎች እንዲሁም በ8ኛ ከፍል 86,808 ተማሪዎች በ201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናዉን ለመውሰድ ተመዝግበዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia
7
🔖ከ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ጋር በተያያዘ 🔖

ከ2019 የትምህርት ዘመን ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ እንድትሉ እንጠይቃለን።

🎖የመደበኛ ተማሪዋቻችን እህትና ወንድሞች ቅድመ ምዝገባ እስከ ሰኔ 1 በሁሉም ቅርንጫፎቻችን።

🎖 የቅርንጫፍ ለዉጥ ጠያቂ ወላጆችም ባለዉ ክፍት ቦታ መስተናገድ እንዲችሉ ከታች ከተዘረዘሩት ቅርንጫፎች በየትኛዉ ልጅዋ እንዲማር እንደሚፈልጉ ለይተዉ እንዲያሳዉቁ እሰከ ሰኔ 1,2018 ድረስ እናሳስባለን።

🎯 ዊንጌት አፀደ ሕፃናት፣

🎯 ዲዝኒ አፀደ ሕፃናት

🎯 22 አፀደ ሕፃናት

🎯 ራስ ደስታ አፀደ ሕፃናት

🎯 ኢምፔሪያል አፀደ ሕፃናት

🎒ፓላስ አንደኛ ደረጃ

🎒ኢስት ዊንግ አንደኛ ደረጃ

🎒 ኢምፔሪያል አንደኛ ደረጃ

🎖ለምዝገባዉ ምንም አይነት ክፍያም ሆነ ሰነድ አያስፈልግም።

🎖 ከተጠቀሰዉ ግዜ ዉጭ ምንም አይነት መሰል ጥያቄ አናስተናግድም ።

🎖ጥያቄዉን ለማቅረብ በአካል በየቅርንጫፎቻችሁ መገኘት ይኖርባችኃል።

የትምህርት አጋርዋ።
35
Elon Academy plc ኤሎን አካዳሚ pinned «🔖ከ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ጋር በተያያዘ 🔖 ከ2019 የትምህርት ዘመን ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ እንድትሉ እንጠይቃለን። 🎖የመደበኛ ተማሪዋቻችን እህትና ወንድሞች ቅድመ ምዝገባ እስከ ሰኔ 1 በሁሉም ቅርንጫፎቻችን። 🎖 የቅርንጫፍ ለዉጥ ጠያቂ ወላጆችም ባለዉ ክፍት ቦታ መስተናገድ እንዲችሉ ከታች ከተዘረዘሩት ቅርንጫፎች በየትኛዉ ልጅዋ እንዲማር እንደሚፈልጉ ለይተዉ እንዲያሳዉቁ…»
Check out this TikTok I posted! #ሁሉም_ይቻላል ▶️Watch the full video now! https://vt.tiktok.com/ZSxUTEpdS/
👍21
Check out this TikTok I posted! #ለጤናችን ▶️Watch the full video now! https://vt.tiktok.com/ZSxx32gYP/
1
🌙 ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ የኤሎን ቤተሰቦች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሳችሁ! 🌙
1👍1