ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
115K subscribers
5.87K photos
105 videos
6 files
941 links
Journalist-at-large
Download Telegram
"የህፃን ሄቨንን ጉዳይ በተመለከተ ሙሉ የፍርድ ቤት ውሳኔውን ልላክልህ እየው፣ በጣም ደካማ ውሳኔ ነው። እኔ ከህግ ባለሙያ አንፃር ነው የማየው እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላይ ይግባኙ ላይ ሁላችንም ትኩረት ካላደረግን ይህን ውሳኔ እንዳይሽሩት እሰጋለው"--- አንድ የህግ ባለሙያ ያጋራኝ መልዕክት

ይህ እንዲሆን ፈፅሞ ልንፈቅድ አይገባል፣ የሚድያ ክትትል በማድረግ እኛም እንሳተፋለን።

@EliasMeseret
ዛሬ ምሽት 1 ሰአት ላይ በመሠረት ሚድያ የሚደረገውን ውይይት ይካፈሉ

Join ማድረጊያ ሊንክ:

https://t.me/meseretmedia
ጳጉሜ የኢትዮጵያውን መዝናኛና ባህል ማዕከል በ6ኛው ዙር የሽልማት መርሀ-ግብሩ በጋዜጠኝነት ዘርፍ ተሸላሚ አድርጎ መርጦኛል

ጳጉሜ 2/2016 ዓ/ም ሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርንያ ተገኝተን ሽልማት እንቀበላለን።

ከፍ ያለ ምስጋና ለእውቅናው እና ለሽልማቱ 🙏🏽

@EliasMeseret
የሚያስመሰግን ስራ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀቸው ሕጻን ሄቨን እናት የመኖሪያ ቤት አበረከተ 🙏🏽

@EliasMeseret
#ትኩረት ከወደ ደቡብ ኦሞ የሚሰማው የዜጎች ስቃይ እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ልብ ይሰብራል። ከአንድ ቤተሰብ በርካታ ሰው በወባ እየሞተ ነው፣ ሰሞኑን በተከሰተ የውሀ ሙላት ደግሞ መድረሻ ያጣው ብዙ ነው... ኦሞራቴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ሊውጥ የሚችል የውሀ ስጋት ተደቅኗል

ሙሉ መረጃው ከመሠረት ሚድያ ⤵️

"እኛ የሚጮህልን ሚድያም ሆነ አክቲቪስት የለንም፣ ብዙ ህዝብ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነው ያለው። ከብቶቼም አልቀዋል፣ ንብረቴም ወድሟል፣ የእኔ መኖር ምን ዋጋ አለው የሚለው ብዙ ነው"- የደቡብ ኦሞ ነዋሪዎች ለመሠረት ሚድያ

ሊንክ: https://www.facebook.com/61562533862014/posts/pfbid02cNNr2ytX9HaeSiASdNgGJo2QFJvnNzbPYQm3QvgVPZD7vHK6sHg8Wfqo54J5z9mql/

@EliasMeseret
ለሰላም ወዳዱ፣ ታታሪው እና ደጉ የሰላሌ ህዝብ ይሄ አይገባውም ነበር

ዛሬ "ሰው ሀጥያተኛ ነዉ፣ በሬ ምንም አያውቅም" ብሎ በሬዉንና ልጁን ጠምዶ ሰላም አውርዱልን ብሎ አደባባይ ወጥቷል። 

ሙሉ መረጃው: https://youtu.be/vjt7pqEQWSs?feature=shared
ለህሊናው፣ በህሊናው የኖረ ምሁር!

ነፍስህ በሰላም ትረፍ ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ!

@EliasMeseret
እንደ ሀገር የሚያዙ እቅዶች ...

አንዳንዴ ግርም ይለኛል!

@EliasMeseret
ለሞት የሚከፈል የሶስተኛ ወገን ከዘንባባ መግጨት እንዴት ያንሳል ተብሎ ከሰሞኑ ሲጮህ አዲስ ክፍያ ዛሬ ተግባራዊ ሆኗል። ውጤቱስ?

- ለሞት የሚከፈል ጣርያ ከ40,000 ብር ወደ 250,000 ብር ከፍ ብሏል

- የሚያሳዝነው ግን የሶስተኛ ኢንሹራንስ ፕሪሚየም ህዝቡ ላይ እስከ 500 ፐርሰት ጨምሯል። ድሮ 500 ብር የሚከፍል ከዛሬ ጀምሮ 3,000 ብር እና ከዛ በላይ!

ሙሉ ዜናው መሠረት ሚድያ ላይ ⤵️

https://www.facebook.com/61562533862014/posts/pfbid02iUse45Q4UCRt3TiZStU9PBzMzAQgs5DPtzouyDcQKTatSGgKCi6C1VoD2uj2LoSXl/

Via @MeseretMedia
የመሠረት ሚድያ ሎጎን እንዲሁም ብራንዲንግ በበጎ ፈቃደኝነት የሰራውን የበህር ማርኬቲንግን በጣም አመሰግናለሁ!

የበህር ማርኬቲንግ ለአዲስ አመት 50% ቅናሽ ይዞ መጥቷል። ምርትና አገልግሎትዎን በማህበራዊ ሚድያ፣ በቪድዮ እንዲሁም ጥራት ባላቸው ደንበኛን ቀልብ በሚስቡ ፎቶዎች እና ግራፊክስ ዲዛይን ያስተዋውቁ!

ስልክ 0938438262 ወይም 0930109760
ቴሌግራም: @yebehir2
ድረ-ገፅ: www.yebehir.com
የአፋልጉን ጥሪ!

ስሙ ምትኩ በላይ ይባላል፣ የ3 ልጆች አባት ነው። ትላንት የፈረስ ትራንፖርት አገልግሎት እየሰራ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ስልኩ አይሰራም። አዳራችንን ስንፈልገ አደርን ምንም ፍንጭ የለም፣ እርዱን እባካችሁ ። የመኪናው አይነት ቪትዝ AA B 45852 ሲልቨር ከለር።

ፈልግን ፈለግን አጣነው እባካችሁ እርዱን፣ አቅም አጣን

ስልክ 0973067336; 0951108861; 0989397787
"እቀርፅሀለው"... "ላይቭ እያስተላለፍኩት ነው"

ስለ አቪዬሽን አሰራር በቅርበት ስለምከታተል አንዳንድ ነገሮች ይገቡኛል ብዬ አስባለሁ፣ እናም በአንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ስለተከሰተ ድርጊት የሚሰራጨውን ቪድዮ አይቼ ይህን ማለት ወደድኩ።

በወቅቱ ተሳፋሪዎች ላይ ዛቻ፣ ድብደባ፣ ማዋከብ እና ማስፈራራት ከነበረ ስህተት ነው።

ከዛ ውጪ ግን የካቢን ክሪው ለመብረር አደጋ አለው ብሎ ካመነ በረራውን የማቆየት እና የመሰረዝ ሀላፊነት አለበት። ተጓዦች ብዙ ሰዓት አውሮፕላን ውስጥም ሆነ ተርሚናል ውስጥ ቆይተው ተጉላልተው ይሆናል፣ ግን በተለይ ከትናንት ጀምሮ እንደሰማነው አይነት ጭጋግ ከተከሰተ አየር መንገዱ ቅድሚያ የሚሰጠው ለደህንነት ነው። 

"እቀርፅሀለው"... "ላይቭ እያስተላለፍኩት ነው" በማለት ለማስፈራራት መሞከሩ ዋጋ የለውም፣ እንደውም ያልተለመደ የበረራ ደህንነት ሴክዩሪቲዎች ትዕግስት ገርሞኛል።

በአንድ ወቅር ከፍራንክፈርት ወደ ለንደን በነበረኝ በረራ ላይ አብራሪዎችን መነሻ ሰዓት አዘገያችሁ ብሎ ግርግር የፈጠረ አንድ ተጓዥ እንዴት አንጠልጥለው እንዳስወጡት አስታውሳለሁ።

አየር መንገዱም ሆነ ኤርፖርት ውስጥ የሚፈፀሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ደጋግሜ አንስቻለሁ፣ አንዳንዶቹ ላይም ማስተካከያ ተደርጓል። ግን እንዲህ አይነት አምቧጓሮም ተገቢነት የለውም።

ለተሳፋሪ ደህንነት ሲባል በረራ አይደረግም ከተባለ በቃ፣ እዛ ጋር አበቃ። የትም አለም ላይ ያለ አሰራር ነው።

@EliasMeseret
'ማሻሻያ' ወይም 'improvement' የአንድን ነገር መሻሻል ወይም በጎ መሆን ይገልፃል

በእኛ ሀገር ግን ባንኮች፣ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ አምራቾች ወዘተ 'ማሻሻያ አርገናል' ካሉ በተቃራኒው ተጠቃሚው ላይ 'ዋጋ ጨምረናል' ማለታቸው ነው።

'ማሻሻያ' in my opinion is one of the most abused words in Ethiopia these days.

@EliasMeseret
ድምፅ በመስጠት እንሳተፍ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው 'World Travel Awards' ሽልማት ላይ በስድስት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ ቀርቧል። እርስዎም ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ድምፅዎን የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት ለሆነው አየር መንገድዎ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል።

https://www.worldtravelawards.com/vote-r3

የሌሎች ሀገራት አየር መንገዶች በብዛት በሶሻል ሚድያ አማካኝነት ድምፅ እያገኙ ነው፣ እኛም ድምፃችንን በመስጠት እንሳተፍ። ድምፅ መስጠት ጷጉሜ 3 ስለሚያበቃ አሁኑኑ ድምፅ ይስጡ።

@EliasMeseret
በነዚህ ልጆች ድርጊት አፍሬ እና ስራቸውን አውግዤ ከአራት ቀን በፊት አስተያየት አቅርቤ ነበር። አሁን ይህን ክስ በተመለከተ እነዚህን ነጥቦች ላንሳ:

1ኛ: ማንም ሰው ከህግ በላይ አይደለም የሚለው መርህ በሀገራችን ይሰራል እንበል እና ጉዳዩን ወደ ሽብር ክስ መውሰዱ ለምን እንዳስፈለገ በሂደት እናየዋለን። ልጆቹ እንዲሁም ህብረተሰቡ ሊማርበት የሚችል ክስ አቅርቦ ማስኬድ እየተቻለ ከኢህአዴግ ግዜ ጀምሮ እንደለመድነው 'ከውጭ ሀይሎች ጋር ተባብረው' የሚል ታግ መለጠፍ ተመርጧል። 'ሽብር' የሚለውን ክስ ነገ ከነገ ወዲያ እንደሚተዉት መገመት ይቻላል፣ አካሄዱ ግን ምን ያህል ከድሮው እሳቤ እንዳልወጣን ማሳያ ነው። 'አየር መንገዱ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ' የሚል ነገር ክስ ውስጥ ገብቷል፣ እውነት ያየነው ይህን ነበር? በቲክቶክ እውቅና የከነፉ እና ልጅነት ብዙም ያልለቀቃቸው ወጣቶች ድርጊት እንጂ እኔ ሌላ ለእኔ አልታየኝም።

2ኛ: አንዳንድ ሰው በሽብር ህግ መከሰሳቸውን ደግፎ አይቻለው፣ መብት ነው። ይህን በማድረግ ግን ወደፊት ረብሸሀል፣ ያልተፈቀደ ነገር አርገሀል ተብሎ ህዝቤ በሽብር ቢከሰስ ሊከፋው አይገባም። ምንም ያህል ልጆቹ የፈፀሙትን ድርጊት ብንጠላ አሁን ላይ 'ለምን በሽብር ህግ?' ብለን ካልጠየቅን ነገም እኔ ላይ ይፈፀምብኝ ብሎ ፈቃድ እንደመስጠት ነው።

3ኛ: ይህ አካሄድ በትክክል እንግልት የሚደርስባቸውን ዜጎች እና ካለ አግባብ ለሚንገላቱ ሰዎችን ድምፅ እንዳያፍን ያሰጋል። አየር መንገዱ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ ሁሌ ተገልጋዮች ቅሬታ ወይም ነቀፋ ሊሰነዝሩ ይችላሉ፣ ግን የሽብር ህጉን ከህግ ፍሬው በተለየ መምዘዙ እነዚህን ድምፆች ዝም ለማስባል ከሆነ ይበልጥ ችግር ፈጣሪ እንጂ መፍትሄ አይሆንም።

መልካም ምሽት።

@EliasMeseret
ይህ የፍትህ ስርዐቱን እና የፍትህ አስፈፃሚ አካላትን አፈፃፀም ሌላኛ መልክ በወፍ በረር ያሳየ መረጃ ነው!

በሌላ በኩል ደግሞ ቶሎ ካልታሰሩ መረጃ ያወጣሉ ተብለው እስር ቤት የሚማቅቁት ጋዜጠኞች ታወሱኝ።

@EliasMeseret
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማምሻውን ያወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ በቀጠናው እየተከሰተ ያለውን ውጥረት የሚመጥን ነው

ትናንት የግብፅ ጦር ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሞቃዲሾ ጭነት ማጓጓዛቸውን ተከትሎ እንዲህ አይነት መግለጫ ቢኖር ብዬ ተመኝቼ ነበር፣ ከምኞት በዘለለ ግን ቃሉን ወደ ተግባር የሚቀይር በቂ ዝግጅት እና በቅርብ ጊዜያት የተፈፀሙ ዲፕሎማሲያዊ መንገጫገጮችን ላለመድገም ጥረት ሊደረግ ይገባል።

#Ethiopia

@EliasMeseret
የመሠረት ሚድያን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቅለዋል?

በርካታ ወቅታዊ መረጃዎች በአማራጭነት እየተጋሩበት ነው ⤵️

https://t.me/meseretmedia
በአሜሪካ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑ የተመረጡት ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጡ

ለሙሉ ዘገባው ከመሠረት ሚድያ ⤵️

https://t.me/meseretmedia/229