ጳጒሜን ፭
በሦስቱ ወንጌላውያን በዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስ እና ዮሐንስ ዘመናት በ፭ ስትጨርስ በአንዱ በዘመነ ሉቃስ ደግሞ በ፮ ትጨርሳለች።
ታድያ ይኽች ጳጒሜን ፭ የምታርፍበት ዕለት የጌታም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው።
ለምሳሌ ጳጒሜን ፭ ኃሙስ ከዋለች በዓለ ልደትም ኃሙስ ላይ ነው የሚውለው። ይኽችም ዕለት ዕለተ ምርያ በመባል ትታወቃለች።
ለዚኽች ለተመረጠች መሸጋገርያ ዕለት ያደረሰን ፈጣሪ ይመስገን።

Telegram
ዕለታት
ጳጒሜን ፭/፮
ይኽች ቀን የተለያየ ምሥጢር አላት። አንዱ ምሥጢርም በሦስቱ ወንጌላውያን በዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስ እና ዮሐንስ ዘመናት በ፭ ስትጨርስ በአንዱ በዘመነ ሉቃስ ደግሞ በ፮ ትጨርሳለች።
ታድያ ይኽች ጳጒሜን ፭ የምታርፍበት ዕለት የጌታም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው።
ለምሳሌ ጳጒሜን ፭ ረቡዕ ከዋለች ልደትም ረቡዕ ላይ ነው የሚውለው።
ለዚኽች ለተመረጠች መሸጋገርያ ዕለት ያደረሰን ፈጣሪ…

❤2🙏1
የዘመን አቆጣጠራችን- በጥቂቱ
በሀገራችን ዘመን አቆጣጠር ዘመናት ለአራቱ ወንጌላውያን ተከፍለው ይቆጠራሉ። አራቱ ወንጌላውያን የተባሉ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስ ናቸው።
እኒኽ ወንጌላውያን ዓመታትን ብቻ ሳይኾን ዕለታትንም በሰዓታት ይከፋፈሏቸዋል፦
ከምሽት እስከ ሌሊት ማቴዎስ
ከሌሊት እስከ ንጋት ማርቆስ
ከጠዋት እስከ ቀትር ሉቃስ
ከቀትር እስከ ምሽት ዮሐንስ፤ አንድን ዕለት በዚኽ መንገድ ለስድስት ሰዓታት ይከፋፈሉታል።
በዚኽም መሠረት ማቴዎስ ማታ ሲጀምር፣ ማርቆስ ሌሊት፣ሉቃስ ጠዋት፤ ዮሐንስ ቀትር ላይ ይጀምራል ማለት ነው።
ስለዚኽ ዘመነ ሉቃስ ጠዋት ላይ ተራውን ይቀበላል ማለት ነው።
በዓመት ውስጥም አራት ወቅቶች አሉ፤ ጸደይ፣ ክረምት፣ መፀው እና ኃጋይ የተባሉ፤ እያንዳንዳቸውም ፺፩ (91) ዕለታት ከ ፲፭ ኬክሮስ ይካፈላሉ፤ ድምራቸው ፫፻፷፬ (364) ዕለታት ይኾናል።
ጳጉሜን ፭ ከብርሃን ትገኛለች ብለው ቀመር አውጥተውላታል፤
ጳጒሜን ፮ትንም የራሷን ቀመር ሰርተውላታል፤
ጳጒሜን ፯ በ፮መቶ ዓመት ትኾናለች ብለው ቀምረውላታል።
አባቶቻችን ዘመናትን የቀመሩልን የኢትዮጵያን ሰማይ የኢትዮጵያን ዕለትና ፀሐይ በረከቷንም አይተው ነው። መነሻቸውም ሥነ ፍጥረት ነው።
የኢትዮጵያ ፀሐይ የኢትዮጵያ ሰማይ ሲባል እኛ ፀሐይ ስናገኝ የሚዘንብባቸው፤ እኛ መፀው ስንል ጸደይ የሚሉ ሃገራት ስላሉ ነው።
ጎርጎሮሳውያን ደግሞ ዘመን አቆጣጠራቸውን ቅድሚያ በጌታ ጽንሰት መጋቢትን ይዘው ሞከሩ፤
ኋላም ስሕተት ቢያገኙበት ግብጻውያን ሊቅ አስተካክሎላቸው በግብጻውያን ፰ኛ ሊቀ ጳጳስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው በጌታ ልደት መነሻቸውን አድርገዋል ።
መስከረምንም የዓመታት መጀመርያ ወይም ርዕሰ ዐውደ ዓመት የምንላት መነሻዋ ኦሪት ዘሌዋውያን ነው።
ስለዚኽ በፀሐይ አቆጣጠር ፯ሺ፭፻፲፱ (7519) እያልን ነው።
የምንይዘው ዘመንም ዘመነ ሉቃስ ነው። የሚገባውም ከጠዋቱ ዐሥራ ኹለት ሰዓት ጀምሮ ነው።
አሮጌ ዘመን የሚባለው ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረው ፭ሺ፭፻(5500) ዘመን ነው።
ዐዲስ ዘመን የምንለው ፳፻፲፱ ዓ.ም. ሙሉውን ነው። በዚኽ ዘመን አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም የተወለደበት፤ በነፍስም የማናረጅበት ዘመን ነውና።

👍3❤1
ምትረተ ርእሱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ዮሐንስ ነፍስን ሥጋን የሚያረካ አስደሳች ማለት ነው። እናቱ ኤልሳቤጥ አባቱ ዘካርያስ ይባላሉ።
ዮሐንስ በእናቱ ማሕጸን በ፮ ወሩ ጌታም በተጸነሰ በ፩ ወሩ፤ ዮሐንስ በእናቱ ማሕጸን ኾኖ እየዘለለ ለጌታ ሰግዶ አምላክነቱን የገለጠ ነው።
ዮሐንስ አድጎ በዮርዳኖስ "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ ሐዲስ ትምህርት እግዚአብሔር ገልጦለት ማስተማር የጀመረ ነው።
ጥምቀቱም ከበሽታ የሚያነጻ ከአጋንንት የሚያላቅቅ ነበር። በዚኽም ብዙ ሕዝብ ይከተሉት ነበር። የአይሁድ ካህናትና ባለስልጣናትም "ክርስቶስ ነኽን" ብለው ላኩበት።
እርሱም "እኔ የነቢይን ትንቢት ለመፈጸም አስተምራለኹ አጠምቃለኹ፤ ኃጢአትን የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ግን በመኻከላችኹ አለ"፤
"እሺ ብትሉት በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቃችኹ፤ እምቢ ብትሉት በገሃነመ እሳት የሚኮንናችኹ በመካከላችኹ አለ" ብሎ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስክሯል።
ጳጒሜን ፩ ንጉሥ ሄሮድስ ሄሮድያዳ በተባለች ሴት ምክንያት ዮሐንስን አሰረው፤ "ሄሮድያዳን (የወንድምህን ሚስት) ማግባት አትችልም" ይለው ነበርና።
ጌታም የመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች እንዳይበተኑ ያስተምራቸው ነበር። በዮሐንስ ጥያቄ መሠረትም አምላክነቱን ገልጦላቸዋል።
መስከረም ፪ ቀን ሄሮድስ ልደቱን የሚያከብርበት ዕለት የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን ደስ ብታሰኘው "ምን ላድርግለሽ" አላት፤
ልጅም በእናት ምክር "የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አኹን በወጭት ስጠኝ" አለችው።
በእስር ቤትም ራሱን ቆረጡት።
ተማሪዎቹም ወስደው በድኑን ቀበሩት።ታድያ አንገቱ ክንፍ አውጥታ በሰማይ እየበረረች ለ ፲፭ (15) ዓመታት ወንጌልን አስተምራለች።
በ፲፭ ዓመቷ በአረብ ሃገር ወድቃ የአረብ ነጋዴዎች ለተማሪዎቹ ሰጥተው የዮሐንስ አስከሬን በነበረበት ቦታ ወስደው ቀበሩት። ይኽም አስክሬን በግብጽ ሃገር ተአምራት እየሰራ ይገኛል።
የመጥምቀ መለኮት ቃል ኪዳን እንደ መላእክት ቃል ኪዳን እንደ ክረምት ጎርፍ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋም ነው፤ ይኽ ነው ተብሎ አይለካም።

🙏4
Forwarded from በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
እስኪ ደግሞ "ሰትየ"ን እንግሠሠው።
ሰትየ=ጠጣ [Drink/Drank]
ይሰቲ=ይጠጣል [will drink]
ይስተይ=ይጠጣ ዘንድ [to drink]
ይስተይ=ይጠጣ [let him drink]
ሰትይ/ሰትዮት=መጠጣት [drinking]
ስቱይ/ሰታዪ=የጠጣ [drinker/Drunken]
ስቱያን/ሰታይያን=የጠጡ [drinkers]
ስትይት/ስቲት/ሰታዪት=የጠጣች
ስቱያት/ሰታይያት=የጠጡ [ሴ]
ሰትዮ=ጠጥቶ [having drunk]
መስትይ/መስተስትይ/መስተሳትይ [ባ.ቅ]
መስትያን/መስተስትያን/መስተሳትያን [በብዙ]
መስትይት/መስተስትይት/መስተሳትይት [ለሴት]
መስትያት/መስተስትያት/መስተሳትያት [ለብዙ]
ሰተይት=መድበል=የጠጡ
ስታይ=ዘመድ ዘር=መጠጥ
ስቴ=ጥሬ ዘር=መጠጥ
ምስታይ=ባዕድ ዘር=መጠጫ
ስቴት=ሳቢ ዘር=መጠጣት
መስቴ=ባዕድ ጥሬ ዘር=መጠጫ
ሠናይ በዓል ይኩንክሙ [ይኩን ለክሙ]። ግሡን አውርጄዋለሁ። በብርጭቆ ማወራረድ ነው የሚቀረኝ።
ቀጥሎ ነድየ ነው 😁
© በትረ ማርያም አበባው ካሣ
የዩቲይብ ቻናሌ ንሕነ ዘክርስቶስ We belong to Christ ወይም ሊንኩ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=GWc54SKTPg4RBlfN
የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw ወይም ሊንኩ https://www.facebook.com/betremariam.abebaw ነው።

😁2🤗1
ልደቱ ለዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
እናቱ ከነገደ አሮን ስትኾን ማርያም ባውፍልያ ትባላለች፤ አባቱ ከነገደ ይሁዳ ሲኾን ዘብዴዎስ ይባላል።
ይኽም በአሮን ከቤተ መቅደስ፤ በይሁዳ ከቤተ መንግሥት፤ የተወለደ አድርጎታልና፤ ወልደ ነጎድጓድ ይባላል።
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ተምሮ ኋላ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ኾኗል።
ቅዱስ ዮሐንስ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ከመስቀል ስር ኾኖ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ፤ ለእመቤታችንም በአደራ የተሰጠ ሐዋርያ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስን፦
ጌታ እጅግ ስለሚወደው፦
ፍቁረ እግዚእ
የዘብዴዎስ ልጅ ስለኾነ፤ በአባቱ፦
ወልደ ዘብዴዎስ
ነገረ መለኮትን በጥልቀት በማስተማሩ፦
ነባቤ መለኮት
ኃላፊውን መጪውን በራእይ በመግለጹ፦
አቡቀለምሲስ
የጌታን መከራ እያሰበ ሰባ ዓመት አዝኖ ፊቱ ተቋጥሮ በመኖሩ፦
ቁጹረ ገጽ ተብሏል።
መስከረም ፬ ልደቱ ነው።

❤7
አቡነ አሮን መንክራዊ
ትውልዳቸው ደንቢያ ላስታም የሚል አለ። አባታቸው ገብረ መስቀል እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ።
ዘመናቸውንም በጽኑዕ ምንኩስና ያሳለፉ ጻድቅ አባት ናቸው።
በቀን ሰባት ጊዜ ፻፶ውን መዝሙረ ዳዊት እና ውዳሴ ማርያም ያደርሱ ነበር። ዕንባን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፤ በሠንሰለት ጀርባቸውን ገርፉ፤ ከስግደታቸው ብዛትም ጉልበታቸው እስኪጎዳ ድረስ ነው።
አቡነ አሮን ካሳለፏቸው መከራ መኻከል፤ በዘመኑ የነበረ ንጉሥ በአንድ ሚስት አልወሰን ብሎ ንጉሡን "ቁርባን አናቀብልኽም" ስላሉት ንጉሡ፡
ከነማኅበራቸው እግራቸው እንዲታሰር፣ በጅራፍ እንዲገረፉ፣ ቢያደርግም አቡነ አሮንን ምድር ሰውራቸዋለች።
በሀገረ ሮሃ (ላሊበላ) አንድ ጻድቅ ዓይነ ሥውር መካነ ዕረፍታቸውን ነግሯቸው፤ ወደ መቄት አድባራት ኼደዋል።
ያንንም ቦታ አባታችን በትምህርት ቢያስፋፉት ሐሜተኛ ሰው ንጉሥ አያከብርም ብሎ ለዐጼ ሰይፈ አርእድ አማቸው።
ከዛ ፯ መቶ ከሚኾኑ ማኅበራቸው ጋር ወደ በረሃ ተሰደው ቢራቡ አቡነ አሮን በእንባ "አትተወን፤ ስለ ስምኽ ብለኽ ምራን መግበን…" ብለው ጸልየው ሦስቴ በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለው፤
ምድሪቷን ቢወጓት ውሃም ከምድሪቱ ወጣ። ንጉሡም በዚኽ ጊዜ አስኬማ ልብሳቸውን ይገፏቸው፤ ይገርፏቸው፤ ይረግጧቸውም ዘንድ አዘዘ።
የተራቡም አናብስት አቡነ አሮን ዘንድ ቢያመጡ እንኳን ሊበሏቸው እግራቸውን እየላሱ ከስራቸው ቁጭ ብለዋል።
የንጉሡ ሰራዊትም ከዚኽ ጻድቅ ጋር ክፉ ባንዳረስ ብለው ልቦሶቻቸውን ሰጥተዋቸዋል።
ዕረፍታቸውም በደረሰ ጊዜ በሰማያት አባቴ ተስፋ አለኝ እናንተም እስከ ሞት ደርስ አትነዋወጹ ብለው ማኅበሮቻቸውን አረጋግተው መስከረም ፭ ዐረፉ።
ደብራቸውም መቄት ወረዳ ይገኛል። ልዩ የሚያደርገው ጣራው ክፍት ኾኖ ከፀሐይ በቀር ዝናም አለማስገባቱ ነው።

❤4
ሰላም ለከርሥኪ ውስተ ከርሠ ሥርዓት ዘሕግ
ወለልደትኪ ፀሐይ ሰዳዴ ጽለመት ፀዋግ
ጽጌ በትረ አሮን ሐና ወዘወይነ ሙሴ ሐረግ
ይሰፍሑ አዕፁቅኪ በምድረ ሴዎን ወአግ
ወለሥረዊሆሙ ይሠቅዮ ዘኤዶም ፈለግ
መልክአ ሐና
መስከረም ሰባት ከአሮን ወገን የምትኾን የእናታችን ሐና ልደት ነው።
አባቷ ማጣት ይባላል። ሦስት ልጆችንም ወልዷል፤ ማርያም፣ ሶፍያ፣ እና ሐና የተባሉ።
ማርያም ሰሎሜን፤ ሶፍያ ኤልሳቤጥን፤ ሐናም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወልዳለች።
ስለዚኽ ሰሎሜ እና ኤልሳቤጥ ለእመቤታችን የእኅትማማቾች ልጆች ወይም የአክስት ልጆች ናቸው ማለት ነው።

❤3
ዜና ሞቱ ለሙሴ
ሙሴም እግዚአብሔርን "ነፍሴን የምትወስድባትን ቀን ንገረኝ" ብሎት፤ እግዚአብሔርም "ዕለተ ዐርብ" ቢለው ሙሴ ዕለተ ዐርብን ተዘጋጅቶ ይጠብቅ ነበር።
ከረዥም ጊዜ በኋላ ሙሴ ዕለተ ሞቱን በረሳበት ዕለት ወደ እግዚአብሔር ሊጸልይ ደብረ ሲና ወጥቶ ሳለ፤ መልአከ ሞት ወጣት እስራኤላዊ መስሎ ሰላምታ አቀረበለት።
ሙሴም ደንግጦ መናገር ተስኖት፤ እግሩም ተንቀጥቅጦ ሰግዶ ተነሳ። ቃሉ አስፈርቶት ነበርና፤ መልአኩም "እኔ ሱርያል መልአከ ሞት ነኝ" አለው።
ሙሴም "በላከኽ በእግዚአብሔር አምልሃለኹ ሚስት እና ልጆቼ ጋር ሳልኼድ አትውሰደኝ" አለው። ከደብረ ሲና ወርዶም ቅድሚያ ወደ እናቱ ኼደ፤ እናቱም ፊቱን አይታ ደንግጣ ብትጠይቀው፤
ዕለተ ሞቱ መድረሱን ነገራት፤ እርሷም "እግዚአብሔርን ገጽ በገጽ ቃል በቃል የተነጋገረ ይሞታልን?" ብትለው፤ "አዎን" አላት፤
"ወደ እግዚአብሔር መሪር ሞትን ያቀልልኝ ዘንድ ለምኝልኝ" ብሏት ኼደ፤ እናቱ ዮካብድም አለቀሰች።
ከዛም ወደ ሚስቱ ኼደ፤ "እንዴት ይኾናል" ብትለው፤ አብርሃምም ነቢያትም ሞተዋል ብሎ አስረዳት። ከልጆቹም ጋር ተላቀሱ።
እግዚአብሔር ሙሴን "ስለምን ታለቅሳለኽ" ቢለው "ልጆቼ እና ሚስቴን ለማን እተዋቸዋለኹ? ወንድሜ አሮን ሞቷል፤ የሚስቴ አባት ዮቶር ሞቷል፤ እሱ ነው የሚያስለቅሰኝ" አለው።
ጌታም "ስትወለድ የሸሸግኩኽ፤ የፈርዖንን ልጅ ያራራኹልኽ፤ ትናንሽ ነፍሳትን የማልረሳ ልጆችኽን የምረሳ ይመስልኻል? አኹን ጊዜኽ ደርሷልና ቶሎ ውጣ" አለው።
በመንገድም ሦስት ወጣቶች መቃብር ሲቆፍሩ አግኝቶ የእግዚአብሔር ሰላምታ ሰጥቷቸው "ይኽን መቃብር ለማን ትቆፍራላችኹ?" አላቸው፤ እነርሱም "ለእግዚአብሔር ወዳጅ" አሉት።
ላግዛችኹ ብሎ እያገዛቸው አዘጋጁት። ከዛም የሚቀበረውን አምጡት አላቸው፤ እነርሱም "መቃብሩ እንዳያጥር ፈራን፤ ሰውየው አንተን ያኽላልና እስቲ መቃብር ውስጥ ገብተኽ እንይኽ" ሲሉት ሙሴም ወደ መቃብሩ ገባ።
መልአከ ሞትም መቃብር ውስጥ አገኘው፤ ሙሴንም "ሰላም ላንተ ይኹን" አለው፤ ሙሴም ሰላምታውን ተቀበለው፤ ከዛም ሙሴ ሞተ፤ መላእክትም ቀበሩት።
ሦስት ወጣት የተባሉት መላእክት ናቸው፤ ሊቀ ነቢያት ሙሴም ዕረፍቱ መስከረም ፰ ነው። የዮሐንስ መጥምቅ አባት ካህኑ ዘካርያስም በመስዋዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው።

❤1
እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፤
እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
መስከረም ፲ የአባቶቻችንን በዐል ተቀጸል ጽጌ የእመቤታችንንም ስዕል ተአምር ጼዴንያ ማርያም ይከበራል።

ጼዴንያ ማርያም
ቅድስት ማርታ የምትባል ባሏ የሞተባት ልጅ የሌላት የሶርያ ተወላጅ ነበረች። እግዚአብሔርን በምን ላስደስት ብላ ታስብ ነበርና፤ እንግዳ መቀበል ጀመረች።
እንግዶቹ ሊቃናት መነኮሳት ሲኾኑ በርከክ ብላ ቃለ እግዚአብሔርን አስተምሩኝ ትል ነበር። ስለ እመቤታችንም ነግረዋት፤ እባካችኹ ስዕሏን አምጡልኝ ብላ አደራ አለቻቸው።
አባ ቴዎድሮስ የተባሉ መነኩሴም ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ ስዕሉን ረሱት፤ ከሰማይም ድምጽ መጣ፤ "የዛች መበለትን ስዕል መግዛት ለምን ረሳኽ" ሲል።
ተመልሶም ያችን የቅዱስ ሉቃስ ስዕል ሽጠውለት፤ በበረሃ አንበሳን አባራለት ከሽቶችም አድናው መጥቷል።
አባ ቴዎድሮስም ከስዕሏ ተአምር የተነሳ ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ ሊወስዳት አስቦ መርከብ ተሳፈረ። መርከቡን ግን ማዕበል ገፍቶት ወደ ጼዴንያ(ሶርያ ውስጥ) አደረሰው።
ከማርታ ቤትም ተስተናግዶ ሊወጣ ሲል በሩ ተሰወረበት፤ ማርታም አባቴ አሞኻል መሰለኝ ቤቴ የእንግዳ ነው፤ ለፈለክበት ጊዜ ኑርበት አለችው።
ኹለት ሦስት ቀን ሲቸገር አይታው፤ "ታመኽ ነውን ወይስ በጤናኽ" ብላ ጠየቀችው። መነኩሴውም ማንነቱን ነግሯት የገጠመውን አጫወታት።
ስዕሊቱንም ከሸሸገበት አውጥቶ የሸፈነበትን ሐር ሲገልጠው፤ ወዟ ይንጠፈጠፍ ነበር። ማርታም በእልልታ ጮኸች።
ማኖርያ አድርጋ ስዕሉን አስቀመጠፍችው፤ ካህናትም እንጥፍጣፊውን እየቀዱ ለድውያን ሰጥተው ይፈወሱበት ነበር።
ማርታም ፳፬ ሰዓት መብራት ታበራለት፤ ስዕሉንም አታስነካም ነበር። የምትተኛው ከስዕሉ ስር፤ ኋላም ቤቷ ገዳም ሲኾን እመምኔቶችም ከስዕሉ ስር ነበር የሚተኙት።
መስከረም ፲ ቀን ስዕሏ ጼዴንያ የገባችበት፤ እናታችን ማርታ ያረፈችበት ነው። ስዕሏንም በቦታው አለ ብለው የሚያስቡ ሙስሊም ክርስቲያኑ እየኼደ ይሰግዱላታል።
ዐጼ ዳዊት በ፲፬ ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ስዕሏን ከቅዱስ መስቀል እና ከቅዱሳን ዐጽም ጋር ወደ ኢትዮጵያ አምጥቷታል።
ቅድሚያ በሸዋ ኋላም እመቤታችን አመልክታው ጣና ሐይቅ ጽርሐ ጽዮን ደሴት ውስጥ አስቀምጧታል። ከዛም ግራኝ ተነስቶ ገዳሙን አጥፍቶታል።
ስዕሏ ግን አኹን ደብረ ወርቅ ወይም ደብረ ዘመዳ እንዳለች ይነገራል።
ተቀጸል ጽጌ፤ ዐጼ መስቀል
ከዐጼ ገብረ መስቀል(፮ኛው ክፍለ ዘመን) ጀምሮ መስከረም ፲ ቀን ቅዱስ መስቀሉን በአበባ አስጊጠው፤ መስቀሉን እያከበሩ እየዘመሩ ከንጉሡ ጋር ኾነው አባቶቻችን ያከብሩት የነበረ በዓል ነው።
ይኽ በዓል በዐጼ ዳዊት ዘመን ቅዱስ መስቀሉን አስመጥተዋልና፤ ዐጼ መስቀል ተብሏል።አኹንም በአንዳንድ አድባራት በዓሉ ይከበራል።

ቅዱሳን ስዕላት
ቅዱሳን ስዕላት መቀመጥ የሚገባቸው ንጹሕ ቦታ ውስጥ ነው፤ ያም ማለት ቤተ ክርስቲያን ወይም የጸሎት ቤት ውስጥ ነው።
ሃሳባችን፣ግብራችን እና አንደበታችን ከኃጢአት ሙሉ ለሙሉ አይለይምና፤ በቤት ስዕለ አድኅኖ አይቀመጥም፤ ያለ ጸሎት ክፍል በስተቀር።
ስዕላትን ለመስቀል መቅደድ አይገባም፤ ስዕለ አድኅኖ ራሱ የቅዱሳን አካል ነውና።
ኩርዓተ ርእሱ የተሰኘው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስዕለ አድኅኖ ጌታ ፊቱን በጨርቅ አብሶ መልኩ ጨርቁ ላይ የታተመ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የስነ ስቅለቱን ስዕል በቀራንዮ እንዳየው አድርጎ የሳለ ነው።
ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ የሳለውም እመቤታችንን በቤተ ልሔም የኹለት ዓመት ልጇን ታቅፋ ሰብአ ሰገል ሲሰግዱላት እየታየው ነው።
ሲጨርስም ስጋ የለበሰች መስላ ታይታዋለች። ሙቀት ሲኾን ከስዕሏ ወዝ ይንጠፈጠፋል፤ በስለት ሲነኳት ከስዕሏ ደም ይንጠባጠባል፤ መከራ ሲኾንም ስዕሏ ታለቅሳለች።
ቅዱሳን ስዕላት ስዕለ አድኅኖ ይባላሉ እንጂ፤ ምስል አይባሉም። ምስል ለጣኦት ነው። "ምስለ ፍቁር ወልዳ" ማለት ከተወደደ ልጇ ጋር ማለት ነው።
ቅዱሳን ስዕላት የሚያስፈልጉት የሰው ልጅ ደካማ ነውና፤ እስራኤላውያንም የሚታይ ነገር ፈልገው ጣዖት ቢያመልኩ፤
ጌታ እንዳይስቱ ማደርያውን ታቦት፤ ማደርያውን ስዕለ ኪሩብ ሰጣቸው። ይኽም ማለት ቅዱሳን ስዕላት የተጀመሩት በፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር ነው።
የስዕላት ማስፈለጋቸውም የማይታየውን አምላክ በሚታይ ነገር አድሮ ለመናገር ነው።
እኛም ስዕሉን አናመልክም፤ በስዕሉ ያደረውን እግዚአብሔር ነው የምናመልከው። ለነዚኽም ስዕላት እንሰግድላቸዋለን።