የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ትራምፕ ድርድሩን "እንደ ሪል ስቴት ንግድ" ነበር የያዙት አሉ::
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አግራቺ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በለጠፉት ጽሑፍ፤ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “በክፋት ተነሳስተው የድርድር ጠረጴዛውን በቦምብ ደብድበዋል” ሲሉ ከሰሱ።
“ውስብስብ የሆኑ የኒውክሌር ድርድሮች እንደ ሪል እስቴት ንግድ ሲያዙ፣ እና ትላልቅ ውሸቶች እውነታን በሚጋርዱበት ጊዜ መሬት የማይወርዱ ነገሮች በፍጹም ሊሳኩ አይችሉም” ብለዋል።
“ውጤቱስ? በክፋት ተነሳስተው የድርድር ጠረጴዛውን በቦምብ ደብድበዋል” በማለት ጽፈዋል።
ጦርነቱ ከመጀመሩ ቀናት አስቀድሞ ጄኔቫ ውስጥ ሲደረግ በነበረው ድርድር ቴህራንን ከወከሉ ተደራዳሪዎች ዋነኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አግራቺ ናቸው።
በዚህ የኒውክሌር ድርድር “ጥሩ መሻሻሎች” እንደተመዘገቡ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ከቀናት በኋላ አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጥቃት በመፈጸም ጠቅላይ መሪውን ጨምሮ በርካታ አመራሮችን ገድለዋል።
ሐሙስ ዕለት ስዊትዘርላንድ ጄኔቭ ላይ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ድርድር ከተካሄደ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ነበር አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የከፈቱት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ጨምረውም "ትራምፕ በዲፕሎማሲ ላይ እና በመረጣቸው የአሜሪካ ሕዝብ ላይ ክህደት ፈጽመዋል" በማለት ጽፈዋል።

👍1
በጅቡቲ በተፈጸመ 'የድሮን ጥቃት' አራት ሕፃናት መገደላቸው ተገለጸ
በደቡባዊ ጅቡቲ በደረሰ ፍንዳታ አራት ሕፃናት መገደላቸውን ባለሥልጣናት ማክሰኞ ዕለት ያስታወቁ ሲሆን፣ አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ደግሞ ጥቃቱ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የተፈጸመ መሆኑን ገልጿል።
የጅቡቲው ዓቃቤ ሕግ ሐሰን መሐመድ ሐሰን ባወጡት መግለጫ፣ ሕፃናቱ የሞቱት በአፋር ክልል በሚገኘው የዲኺል (Dhikil) ዞን በደረሰ ፍንዳታ መሆኑን ጠቅሰው ድርጊቱን "አሳዛኝ ክስተት" ሲሉ ገልጸውታል።
ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ አገሪቱን በጠንካራ ቁጥጥር እየመሩ ያሉት የፕሬዝዳንት ኢስማኢል ዑመር ጌሌ መንግሥት፣ በአብዛኛው የኢሳ ማኅበረሰብ አባላትን ያቀፈ በመሆኑ የአፋር ማኅበረሰብ "ተገለናል" የሚል ቅሬታ በተደጋጋሚ እንደሚያነሳ ይታወቃል።
የጅቡቲ የሰብአዊ መብቶች ሊግ (LDDH) በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፣ ዕድሜያቸው ስድስት እና ሰባት ዓመት የሆኑ ሁለት ሕፃናት በቦታው ሲገደሉ፣ ሌሎች ሁለት ሕፃናት ደግሞ በፍጥነት ወደ ሕክምና ባለመወሰዳቸው ምክንያት ማክሰኞ ዕለት ሕይወታቸው ማለፉን ጠቁሟል።
ጥቃቱ የደረሰው ሕፃናቱ ከብት እየጠበቁ በነበረበት ወቅት ሲሆን፣ ከሟቾቹ በተጨማሪ ሌሎች ስድስት ሰዎች ለከባድ እና ለቀላል መቁሰል ተዳርገዋል ተብሏል።
ድርጅቱ አክሎም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በዚሁ አካባቢ በሚገኙ ዘላን ማኅበረሰቦች ላይ የተፈጸመ "ስድስተኛው የድሮን ጥቃት" መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶበታል።
የፍንዳታውን መንስኤ ለማጣራት የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ዓቃቤ ሕጉ ገልጸዋል።

ኢራን ቱርክ ላይ የቃጣችውን ሚሳዔል መትቶ መጣሉን ኔቶ አሳወቀ።
የቱርክ ብሔራዊ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ኔቶ የአባል ሀገራቱን አየር ክልል ሲቆጣጠር አክሽፏል ብሏል።
ኔቶ፣ ሚሳዔሉን መትቶ ከመጣሉ በፊት የኢራቅ እና ሶርያ አየር ክልልን አቋርጦ እንዳለፈ ተገልጿል።
ኢራን በቱርክ ላይ ጥቃት ስትፈጽም ከጦርነቱ በኋላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
ኢራን ተፈጽሟል ስለተባለው የሚሳዔል ጥቃት የሰጠችው ማብራሪያ የለም ሲል ኖቪኔት ዘግቧል።
ኔቶ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት "ገለልተኛ" መሆኑን ትናንት አሳውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ኢራን የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክን ኢላማ ማድረጓን ተከትሎ የተቃጣውን ጥቃት ማክሸፉን ኔቶ አሳውቋል።
ኔቶ በየትኛውም አባሉ ላይ የተቃጣ ጥቃት የመከላከል ስልጣን አለው።

በትግራይ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ መቋረጡ ተገለጸ።
የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር በክልሉ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የሚከፈል የደሞዝ ጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው በይፋ አስታወቀ።
ትናንት የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ/ም ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ወጥቶ ለሁሉም የመንግስት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ እንደተመላከተው፣ የካቲት ወርን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ጊዜያት የሚሆን የደሞዝ ክፍያ የሚውል በቂ ጥሬ ገንዘብ በክልሉ ካዝና ውስጥ እንደሌለ ተረጋግጧል።
📌 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የችግሩ መንስኤ፦ ከፌዴራል መንግስት የሚላከው የበጀት ድጋፍ በመዘግየቱ እና ክልሉ በቂ የገንዘብ ዝውውር (Liquidity) ባለመኖሩ እንደሆነ ተጠቅሷል።
የተጎዱ ወገኖች፦ በክልሉ ስር የሚገኙ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች እና የሥራ ማስኬጃ ክፍያዎች ላይ ተፅዕኖ አርፏል።
የጊዜ ገደብ፦ ክፍያው እስከ መቼ ሊቋረጥ እንደሚችል በደብዳቤው ላይ በግልጽ ያልተቀመጠ ሲሆን፣ "ላልተወሰነ ጊዜ" የሚል ይዘት አለው።
ይህ ውሳኔ በተለይ የኑሮ ውድነት በበረታበት በዚህ ወቅት በሺዎች በሚቆጠሩ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።

❤1👍1
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ በዜጎች ላይ በደረሰው የሕይወት መጥፋትና መፈናቀል የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል።
በዚህ አሰቃቂ አደጋ የ52 ወገኖች ሕይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለጋሞ ዞን እና ለመላው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ልባዊ መጽናናትን ተመኝቷል።
በአሁኑ ወቅት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በአደጋው ስፍራ በመገኘት የተጎዱ ወገኖችን የማጽናናትና የድጋፍ ስራዎችን በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን በአደጋው ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ቁሳቁሶችና የምግብ አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲደርስ ክልሉ ከፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ሰፊ የርብርብ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ።
መንግሥት ጊዜያዊ ድጋፍ በማድረግ ብቻ ሳይወሰን፣ ተጎጂዎችን ወደ ቀደመ ኑሯቸው ለመመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን ተጨማሪ የህይወትና የንብረት ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከልም የስጋት ቀጠና ተብለው በተለዩ ስፍራዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የማንሳትና ወደ አስተማማኝ አካባቢዎች የማዘዋወር ሥራ በቅንጅትና በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት ያለው ዝናባማ የአየር ሁኔታ መሰል አደጋዎችን ሊያስከትል ስለሚችል፣ በተለይም በደጋማና ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ከመንግሥት የሚሰጡ የጥንቃቄ መልዕክቶችንና መመሪያዎችን በአንክሮ በመተግበር አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል ።
የኢፌዴሪ መንግሥት በአደጋው ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ከክልሉ መንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ለሟች ወገኖቻችን ሰላማዊ እረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ይመኛል ።

የጸና ወዳጅነት፣ በመተማመን ላይ የተመሠረተ ትብብር! በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በነበረኝ የስራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተገናኝቼ ተወያይተናል።
ውይይታችን በኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ለተደረገልኝ አቀባበል እና በሀገሮቻችን መካከል የፀና ወዳጅነታችንን የበለጠ ለማጠናከር ለተጋራነው የፀና አቋም ምስጋናዬ የላቀ ነው።

እስራኤል በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈተች።
እየተካሄደ ባለው ጦርነት እስራኤል በምዕራባዊ ኢራን መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቷ ተሰምቷል፡፡
የእስራኤል ጦር እንዳስታወቀው፤ ዘመቻው በምዕራባዊ ኢራን የሚገኙ የአብዮታዊ ዘቡ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረገ ነው።
በተመሳሳይ ኢራን በርካታ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል እንዲሁም በኢራቅ እና በኩዌት ወደሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች በማስወንጨፍ ጥቃት ፈፅማለች መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኢራን ከትናንት ጀምሮ የአሜሪካ እና እስራኤል አጋር ባለቻቸው ሀገራት ላይ ጥቃት እየፈፀመች ሲሆን፤ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ጨምሮ በአምስት የቀጣናው ሀገራት ላይ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶች ሰንዝራለች፡፡
ኢራን ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏን ያረጋገጠው የእስራኤል መከላከያ ሀይል፤ በጥቃቱ ሁለት ሰዎች ተጎድተዋል ብሏል።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን መደራደር ትፈልጋለች ነገር ግን የሚያስማማ የድርድር ሃሳብ የላትም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት የባሕር ሀይላቸውን ወደ አካባቢው በማስጠጋት የአሜሪካን ዘመቻ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

🔴 ሰበር ሰበር‼️
እስራኤል የኢራን ቁልፍ የደኅንነት ባለሥልጣን የሆኑት አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ተናገረች።
የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ አስታወቁ።
ሌሊቱን በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው የተነገረው ላሪጃኒ በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ከነበራቸው መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።
የባለሥልጣኑ በእስራኤል ዒላማ መሆን እየተነገረ በነበረበት ጊዜ ቢያንስ ሁለት የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ ይሰጣሉ ብለው ነበር።
አንድ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣን አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል መከላከያ ዒላማ መደረጋቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
አሊ ላሪጃኒ በኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት የሟቹ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ተወካይ እና ዋና ፀሐፊ ሆነው የተሾሙት ባለፈው ዓመት ነሐሴ በፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ነበር።
ለ12 ዓመታት የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ የነበሩት ላሪጃኒ “ለዘብተኛ ወግ አጥባቂ” እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፤ በተጨማሪም በኢራን መገናኛ ብዙኃን የጠቅላይ መሪው አማካሪ እንደሆኑ ይጠቀሱ ነበር።
እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸው የተነገረው ታዋቂው ኢራናዊ ፖለቲከኛ የፓርላማው አፈ ጉባዔ ከመሆናቸው በፊት ኢራንን ከምዕራባውያን ጋር እያወዛገበ በሚገኘው የኒውክሌር ድርድር ላይ አገራቸውን ወክለው ተደራዳሪ ነበሩ።
በኢራን ፖለቲካ ውስጥ አሊ ላሪጃኒ ብቻ ሳይሆኑ ወንድማቸውም ከፍተኛ ተሰሚነት አላቸው። ወንድማቸው ሴዴጌ ላሪጃኒ በኢራን ሁለት ኃያል ምክር ቤቶች የበላይ አካል የሆነው ጉባዔ ሊቀ መንበር ናቸው።
#war #Trump #Israel #Iran #iranisraelwar

🔴 ሰበር ዜና‼️
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ተገደሉ::
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ እና ምክትል ሕዝብ ግንኙነት አሊ ሞሃመድ ናኢኒ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አስታውቋል።
አሊ ሞሐመድ ናኢኒ የአብዮታዊ ዘቡን ለአራት አስርታት ያገለገሉ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ቃል አቀባይ በመሆን ሰርተዋል ሲል ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 2018 ዓ.ም. ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱበት ዕለት አንስቶ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በርካታ አመራሮች ተገድለዋል።
የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጦርነቱ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተገደሉ ሲሆን ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ አመራሮችም የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት ዒላማ ሆነዋል።

🔴 ሰበር ዜና ‼️
በዋሽንግተን የጋዜጠኞች የራት ግብዣ ላይ የተኩስ ጥቃት ተፈጸመ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአስቸኳይ ከስፍራው እንዲወጡ ተደረገ::
ትላንት ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው ዓመታዊ የዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች የራት ግብዣ (White House Correspondents’ Dinner) ላይ በተከሰተ የተኩስ ድምፅ ምክንያት ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል።
በዝግጅቱ የጸጥታ መፈተሻ ኬላ አቅራቢያ የተኩስ ድምፅ መሰማቱን ተከትሎ፣ የዩኤስ ሚስጥራዊ አገልግሎት (Secret Service) አባላት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ከአዳራሹ በአስቸኳይ አስወጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከስፍራው ሲወጡ በነበረው ከፍተኛ ግርግር ወቅት በመሰናከል ሲወላከፉ የታዩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን በሰላም እና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
የጸጥታ አካላት በሰጡት መግለጫ፣ አንድ ተጠርጣሪ በዝግጅቱ የጥበቃ ክልል አቅራቢያ ተኩስ የከፈተ ሲሆን፣ ወዲያውኑ በህግ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር ውሏል።

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ በመክፈት ከፍተኛ ግርግር የፈጠረው ተጠርጣሪ ማንነት ይፋ ሆኗል። የ31 ዓመቱ የካሊፎርኒያ ቶራንስ ነዋሪ የሆነው ኮል ቶማስ አለን፣ ዓመታዊው የእራት ግብዣ በሚካሄድበት ዋሺንግተን ሂልተን ሆቴል አዳራሽ ውጭ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ መሆኑን የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበዋል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በልዩ ጥበቃ በፍጥነት ከስፍራው ሲሸሹ፣ ታዳሚዎች፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ሰዎች መሬት ላይ ለመደፋት ተገደው ነበር።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ የተጠርጣሪውን ፎቶ እና ቪዲዮ በማጋራት፣ ጥቃት አድራሹን "በጠና የታመመ ሰው" እና "ወንበዴ " ሲሉ ጠርተውታል።
የአሜሪካ አቃቤ ሕግ ጂኒን ፒሮ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደገለጹት፣ በአለን ላይ የጦር መሣሪያ መጠቀምን እና በአደገኛ መሣሪያ የፖሊስ ኦፊሰርን ማጥቃትን ጨምሮ ሁለት ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ ክሶችም በቅርቡ ሊከተሉ ይችላሉ። ከተኩሱ በኋላ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ባለሥልጣናት ተጠርጣሪው በሂልተን ሆቴል ክፍል ተከራይቶ አዳሪ እንደነበር እና "ሾትጋን (shotgun)፣ ሽጉጥ (handgun) እና በርካታ ቢላዋዎችን" ታጥቆ እንደነበር አረጋግጠዋል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ አለን እ.ኤ.አ. በ2017 ከካልቴክ ዩኒቨርሲቲ በሚካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ደግሞ በኮምፒውተር ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን አጠናቋል።
በሊንክድኢን ገጹ ላይ ራሱን "በዲግሪ ሚካኒካል ኢንጂነር እና የኮምፒውተር ሳይንቲስት፣ በልምድ ራሱን የቻለ የጌም አበልጻጊ፣ እንዲሁም በተፈጥሮ ደግሞ መምህር" በማለት ይገልጻል። በአሁኑ ቀጣሪው "ሲቱ ኤጁኬሽን" ውስጥ "የወሩ ምርጥ መምህር" ተብሎ ተሸልሞ እንደነበርም በገጹ ላይ አስፍሯል።
እስካሁን ባለው መረጃ፣ አለን ይህንን ጥቃት ብቻውን እንዳቀደ እና እንደፈጸመ ይታመናል። በአሁኑ ወቅት ለፖሊስ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠት የተቆጠበ ቢሆንም፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ኢላማ ማድረጉን የሚጠቁም ንግግር አድርጎ እንደነበር (ምንም እንኳን የተወሰነ ሰው ስም ባይጠቅስም) የምርመራ ባለሥልጣናት ለኤቢሲ ኒውስ አረጋግጠዋል።