Covenant Hub Law Firm LLP
197 subscribers
36 photos
4 videos
2 files
44 links
Make difference
Download Telegram
በኮንስትራክሽን ሕግ እና ወሎች ዙሪያ ከ40 ዓመት በላይ የማማከር ልምድ ካላቸው አቶዘውዱ ተፈራ ወርቄ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንት ውይይት ስናደርግ ነበር፡፡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሰፊ እና ውስብስብ ብዙ አካላት የሚሰታፉበት እንደ ሀገርም ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘርፍ ሕግ ያለው ወሳኝነት እና ሚና መነሻ በማድረግ ዝርዝር ጉዳዮችን እያነሳን እንገኛለን፡፡ ነገ  እሁድ ሐምሌ 12-2018 ዓ.ም በሚኖረው ወይይትም ሀሳብ ፣ ጥያቄ ካላችሁ በአጭር መልዕክት  ቁጥር 8545 / በስልክ ቁጥር 0115585431 እና 0115585432 በመደወል መሳተፍ ይቻላል፡፡
ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት ከአራዳ ኤፍኤም 95.1 ጋር በመተበባበር
በእስረኞች የሕክምና መብት እና በጸጥታ ስጋት መካከል ያለው ሚዛን
የሰ/መ/ቁ. 203051 | የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. | ቅፅ 25
በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ሕክምና የማግኘት መብት እና የመንግሥት የጸጥታ ስጋት መከራከሪያ በሚጋጩበት ጊዜ ፍርድ ቤቶች እንዴት ሊያመዛዝኑት ይገባል? የሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ መዝገብ የሰጠው ውሳኔ 3 ቁልፍ ነጥቦችን በግልጽ አስቀምጧል፦
የመታከም መብት እና የመንግሥት ኃላፊነት፡ ታካሚዎች እምነት በሚጥሉበትና በመረጡት ሐኪም እንዲሁም የሕክምና ተቋም የመታከም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው መሠረታዊ ሰብዓዊ መብት ነው። መንግሥት በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የሚያልፉ ተጠርጣሪዎች ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህ ግዴታ በማረሚያ ቤት በሚገኙበት፣ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት እና ወደ ሕክምና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜ ሁሉ በጥብቅ ሊተገበር ይገባል።
የመንግሥት አዎንታዊ ግዴታ፡ መንግሥት የጸጥታ ስጋት አለኝ በሚል ሰበብ የመታከም መብትን ከመገደብ ይልቅ አስፈላጊውን ጥበቃ በመመደብ ስጋቱን የመቆጣጠርና የማስወገድ አዎንታዊ ግዴታ አለበት።
ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ውሳኔዎች፡ የሕክምና መሣሪያዎችና ተቋማት ባህሪ ቋሚ በመሆናቸው ሆስፒታልን እንደ ተንቀሳቃሽ አካል ቆጥሮ ማረሚያ ቤት ድረስ ሄዶ እንዲያክም ማዘዝ በተግባር ሊፈጸም የማይችል ስህተት ነው።
የሰበር ችሎቱ የይግባኝ ሰሚውን ውሳኔ በመሻር መንግሥት ተገቢውን የደህንነት ጥበቃ በማድረግ አመልካቾች ቀድሞ በመረጡት ሆስፒታል ሕክምናቸውን እንዲያገኙ ወስኗል። ይህም የመንግሥት ቀዳሚ ሚና መብቶችን መገደብ ሳይሆን መብቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲከበሩ ማመቻቸትና ጥበቃ ማድረግ መሆኑን ያረጋገጠ ውሳኔ ነው፡፡
#CovenantHubLawFirmLLP
👍1