Covenant Hub Law Firm LLP
197 subscribers
36 photos
4 videos
2 files
44 links
Make difference
Download Telegram
📌 ሕግና ሕንጻ፡ የኮንስትራክሽን ውሎች ስንክሳርና የ«ፎርሙላው» ሚስጥር!
ክፍል ፡ ፪
በቢሊዮን የሚቆጠሩ የሃገራችን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በሕግ ክርክርና በመዘግየት የሚታመሱት ለምንድን ነው? ውስብስብ የሆኑ የኮንስትራክሽን ውሎችን በቀላሉ የምንፈታበት «ቀመር» ይኖረው ይሆን?
በዚህ ሳምንት በ«ዲጂታል ነጋሪት» የሬዲዮ ፕሮግራማችን በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሆኑትን እውቅ የሕግ ባለሙያና መምህር አቶ ዘውዱ ተፈራን ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጀርመን ማርቲን ሉተር ዩኒቨርሲቲ የዘለቀው የሙያ ጉዟቸው፣ በፓሪስ ፍርድ ቤቶች የነበራቸው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት (Arbitration) ተሞክሮ እና ለዘርፉ ያበረከቱት ልዩ የሕግ «ፎርሙላ» ምን እንደሆነ በሰፊው ያጋሩናል።
💡 በውይይታችን ከሚዳሰሱ ነጥቦች፡-
• በኮንስትራክሽን ውሎች ላይ በብዛት የሚሰሩ ገዳይ ስህተቶች
• የዋጋ ንረት እና የሥራ ለውጦች (Variation) በሕግ አግባብ እንዴት ይስተናገዳሉ?
• አለመግባባቶችን በፍርድ ቤት ፈንታ በአማራጭ ሙግት መፍቻ (ADR) መፍታት ያለው ጥቅም!
የኮንስትራክሽን ባለሀብቶች፣ ተቋራጮች፣ አማካሪ መሐንዲሶችና የሕግ ባለሙያዎች መረጃ እና እውቀት የምታገኙትበት ውይይት ይዘን ቀርበናል!
📅 እሁድ፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
🕖 ከቀኑ 7፡00 – 8፡00 ሰዓት
📻 በአራዳ ኤፍኤም 95.1
ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት ከአራዳ ኤፍኤም 95.1 ጋር በመተባበር ያቀርባል።
📢 ዲጂታል ነጋሪትን ይከታተሉ፤ እውቀትዎን ያዳብሩ!
❤1👎1
📌 ሕግና ሕንጻ፡ የኮንስትራክሽን ውሎች ስንክሳርና የ«ፎርሙላው» ሚስጥር!
ክፍል ፡ ፫
በቢሊዮን የሚቆጠሩ የሃገራችን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በሕግ ክርክርና በመዘግየት የሚታመሱት ለምንድን ነው? ውስብስብ የሆኑ የኮንስትራክሽን ውሎችን በቀላሉ የምንፈታበት «ቀመር» ይኖረው ይሆን?
በዚህ ሳምንት በ«ዲጂታል ነጋሪት» የሬዲዮ ፕሮግራማችን በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሆኑትን እውቅ የሕግ ባለሙያና መምህር አቶ ዘውዱ ተፈራን ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስከ ጀርመን ማርቲን ሉተር ዩኒቨርሲቲ የዘለቀው የሙያ ጉዟቸው፣ በፓሪስ ፍርድ ቤቶች የነበራቸው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት (Arbitration) ተሞክሮ እና ለዘርፉ ያበረከቱት ልዩ የሕግ «ፎርሙላ» ምን እንደሆነ በሰፊው ያጋሩናል።
💡 በውይይታችን ከሚዳሰሱ ነጥቦች፡-
• በኮንስትራክሽን ውሎች ላይ በብዛት የሚሰሩ ገዳይ ስህተቶች
• የዋጋ ንረት እና የሥራ ለውጦች (Variation) በሕግ አግባብ እንዴት ይስተናገዳሉ?
• አለመግባባቶችን በፍርድ ቤት ፈንታ በአማራጭ ሙግት መፍቻ (ADR) መፍታት ያለው ጥቅም!
የኮንስትራክሽን ባለሀብቶች፣ ተቋራጮች፣ አማካሪ መሐንዲሶችና የሕግ ባለሙያዎች መረጃ እና እውቀት የምታገኙትበት ውይይት ይዘን ቀርበናል!
📅 እሁድ፣ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
🕖 ከቀኑ 7፡00 – 8፡00 ሰዓት
📻 በአራዳ ኤፍኤም 95.1
ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት ከአራዳ ኤፍኤም 95.1 ጋር በመተባበር ያቀርባል።
📢 ዲጂታል ነጋሪትን ይከታተሉ፤ እውቀትዎን ያዳብሩ!
👍5
በኮንስትራክሽን ሕግ እና ወሎች ዙሪያ ከ40 ዓመት በላይ የማማከር ልምድ ካላቸው አቶዘውዱ ተፈራ ወርቄ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንት ውይይት ስናደርግ ነበር፡፡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሰፊ እና ውስብስብ ብዙ አካላት የሚሰታፉበት እንደ ሀገርም ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘርፍ ሕግ ያለው ወሳኝነት እና ሚና መነሻ በማድረግ ዝርዝር ጉዳዮችን እያነሳን እንገኛለን፡፡ ነገ እሁድ ሐምሌ 5-2018 ዓ.ም በሚኖረው ወይይትም ሀሳብ ፣ ጥያቄ ካላችሁ በአጭር መልዕክት ቁጥር 8545 / በስልክ ቁጥር 0115585431 እና 0115585432 በመደወል መሳተፍ ይቻላል፡፡
ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት ከአራዳ ኤፍኤም 95.1 ጋር በመተበባበር
👍5
❤1👍1👏1
በኮንስትራክሽን ሕግ እና ወሎች ዙሪያ ከ40 ዓመት በላይ የማማከር ልምድ ካላቸው አቶዘውዱ ተፈራ ወርቄ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንት ውይይት ስናደርግ ነበር፡፡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሰፊ እና ውስብስብ ብዙ አካላት የሚሰታፉበት እንደ ሀገርም ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘርፍ ሕግ ያለው ወሳኝነት እና ሚና መነሻ በማድረግ ዝርዝር ጉዳዮችን እያነሳን እንገኛለን፡፡ ነገ  እሁድ ሐምሌ 12-2018 ዓ.ም በሚኖረው ወይይትም ሀሳብ ፣ ጥያቄ ካላችሁ በአጭር መልዕክት  ቁጥር 8545 / በስልክ ቁጥር 0115585431 እና 0115585432 በመደወል መሳተፍ ይቻላል፡፡
ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት ከአራዳ ኤፍኤም 95.1 ጋር በመተበባበር
በእስረኞች የሕክምና መብት እና በጸጥታ ስጋት መካከል ያለው ሚዛን
የሰ/መ/ቁ. 203051 | የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. | ቅፅ 25
በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ሕክምና የማግኘት መብት እና የመንግሥት የጸጥታ ስጋት መከራከሪያ በሚጋጩበት ጊዜ ፍርድ ቤቶች እንዴት ሊያመዛዝኑት ይገባል? የሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ መዝገብ የሰጠው ውሳኔ 3 ቁልፍ ነጥቦችን በግልጽ አስቀምጧል፦
የመታከም መብት እና የመንግሥት ኃላፊነት፡ ታካሚዎች እምነት በሚጥሉበትና በመረጡት ሐኪም እንዲሁም የሕክምና ተቋም የመታከም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው መሠረታዊ ሰብዓዊ መብት ነው። መንግሥት በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የሚያልፉ ተጠርጣሪዎች ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህ ግዴታ በማረሚያ ቤት በሚገኙበት፣ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት እና ወደ ሕክምና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜ ሁሉ በጥብቅ ሊተገበር ይገባል።
የመንግሥት አዎንታዊ ግዴታ፡ መንግሥት የጸጥታ ስጋት አለኝ በሚል ሰበብ የመታከም መብትን ከመገደብ ይልቅ አስፈላጊውን ጥበቃ በመመደብ ስጋቱን የመቆጣጠርና የማስወገድ አዎንታዊ ግዴታ አለበት።
ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ውሳኔዎች፡ የሕክምና መሣሪያዎችና ተቋማት ባህሪ ቋሚ በመሆናቸው ሆስፒታልን እንደ ተንቀሳቃሽ አካል ቆጥሮ ማረሚያ ቤት ድረስ ሄዶ እንዲያክም ማዘዝ በተግባር ሊፈጸም የማይችል ስህተት ነው።
የሰበር ችሎቱ የይግባኝ ሰሚውን ውሳኔ በመሻር መንግሥት ተገቢውን የደህንነት ጥበቃ በማድረግ አመልካቾች ቀድሞ በመረጡት ሆስፒታል ሕክምናቸውን እንዲያገኙ ወስኗል። ይህም የመንግሥት ቀዳሚ ሚና መብቶችን መገደብ ሳይሆን መብቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲከበሩ ማመቻቸትና ጥበቃ ማድረግ መሆኑን ያረጋገጠ ውሳኔ ነው፡፡
#CovenantHubLawFirmLLP
👍1