Covenant Hub Law Firm LLP
199 subscribers
36 photos
4 videos
2 files
44 links
Make difference
Download Telegram
Channel photo updated
Channel name was changed to «Covenant Hub Law Firm LLP»
ዲጂታል ነጋሪት የራዲዮ ፕሮግራም ታኅሳስ 05-2018 ዓ.ም የመጀመሪያውን ፕሮግራም አድርጓል። የፕሮግራሙን ቅጅ እንድታዳምጡት ተጋብዛችኋል።
3
Covenant Hub Law Firm LLP
Audio
ዲጂታል ነጋሪት የመጀመሪያ ፕሮግራም ታኅሳስ05-2018 ዓ.ም
በዛሬው ዲጂታል ነጋሪት የራዲዮ ፕሮግራም
በአራዳ ኤፍኤም 95.1 ከቀኑ 7፡00- 8፡00

ከፌደራል ጠበቆች ማኅበር ፕሬዝዳንት ጠበቃ ተስፋዬ ደረሰ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጠበቃ መሰረት አያሌው ጋር ቆይታ ይኖረናል።
በቀጥታ በራዲዮ እንዲሁም Arada FM 95.1 ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/1AwdiBy1qE/ በቀጥታ መከታተል ይችላሉ።

አዲሶቹን አመራሮች እንዲጠየቁላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄ በ8545 አጭር መልዕክት ፣ በ0115-585431/32 ሊያደርሱን ይችላሉ፡፡

#እሁድን ከእኛ ጋር!
#ዲጂታል ነጋሪት የራዲዮ ፕሮግራም
#ኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት
👍3
Ensuring Cybersecurity in Ethiopia's Digital Transformation Journey 🇪🇹 As we strive towards the goals of the Digital Ethiopia 2030 Strategy, addressing cybersecurity challenges is paramount for a resilient digital economy.
Join our weekly radio program, Digital Negarit, as we host Dr. Metasebia Kassa, Founder & Manager of ECHO Engineering and Leader of ECYBER Academy. With over 20 years of experience in the field, Dr. Metasebia will provide expert insights into:
🔹 The impact of the Digital 2030 Strategy on national growth. 🔹 Emerging cyber threats accompanying digital expansion. 🔹 Practical defense mechanisms for individuals and organizations.
📢 Tune in this Sunday: 🕒 1:00 PM – 2:00 PM (Local Time) 📻 Arada FM 95.1 Live Stream Arada FM 95.1 Facebook Page (https://web.facebook.com/aradafm)
Presented by Covenant Hub Law Firm
#DigitalEthiopia2030 #CyberSecurity #EthiopiaTech
👍3
በሳምንታዊ ዲጂታል ነጋሪት የራዲዮ ፕሮግራም በቀጣይ እሁድ በዘርፉ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱት ዶክተር መታሰቢያ ካሳ (የኤኮ ኢንጂነሪንግ መስራችና የኢ-ሳይበር አካዳሚ መሪ) 🚀 ዲጂታል 2030፡ የሳይበር ደህንነት እና የኢትዮጵያ ጉዞ በሚል ርዕስ ዙሪያ እንግዳችን ይሆናሉ።
በውይይታችን ምን ይዳሰሳል? የ"ዲጂታል 2030" ስትራቴጂ ፋይዳ፤ ከዲጂታል እድገት ጋር አብረው የሚመጡ የደህንነት ስጋቶች፤ በሀገራችን በብዛት የሚስተዋሉ የሳይበር ጥቃቶች፤ ራስንና ተቋምን ከሳይበር ጥቃት የመከላከያ መንገዶች።
📅 ቀን፦ እሁድ 🕐 ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡00 - 8፡00 📻 ሬዲዮ፦ አራዳ ኤፍኤም 95.1
አቅራቢ፦ የኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት

ያለፉትን የራዲዮ ፕሮግራሞች በየዩቲዩብ ቻናላችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
https://www.youtube.com/@CovenantHubLawFirm
👍3
ዲጂታል ነጋሪት 3ኛ ሳምንት የራዲዮ ፕሮግራም የሳይበር ደህንነት እና ዲጂታል 2030 ከዶክተር መታሰቢያ ካሳ ጋር የነበረን ቆይታ
🛑 የበዓል ገበያና የሸማቹ መብት፦ የሕግ ጥበቃ ወይስ የገበያ መርህ?
የበዓል ሰሞን ግብይት ሲደራ የሸማቾች ፈተናም አብሮ ይገዝፋል። ካልተገባ የዋጋ ንረት እስከ ጥራት ጉድለት፤ በአካል ከሚደረግ ግብይት እስከ ዲጂታል ክፍያና ርክክብ ድረስ ያሉ ተግዳሮቶችን እንዴት እንወጣቸዋለን?
እንደ ሸማች ያለን መብትና ግዴታስ ምንድን ነው? የአቅራቢዎችስ ኃላፊነት እስከምን ድረስ ይዘልቃል? በተለይ አሁን ግብይቱ እየዘመነ ባለበት ወቅት፦
🔹 ምርቱን በአካል ሳይገመግሙ በዲጂታል መንገድ የሚፈጸሙ ግብይቶች ዋስትናቸው ምንድነው?
🔹 በኦንላይን ክፍያ፣ በዕቃ ርክክብ እና በምርት ጉድለት መሃል ለሚፈጠሩ ፈተናዎች ተጠያቂው ማን ነው?
🔹 የሕግ ጥበቃ ወይስ የገበያ መርህ—ለእርስዎ የትኛው ይቆማል?
ሁላችንም ሸማቾች ነን! በእያንዳንዱ ግብይት ጀርባ ያለውን መብትና ግዴታዎን፣ እንዲሁም የአቅራቢዎችን ኃላፊነት ጠንቅቀው እንዲያውቁ ዲጂታል ነጋሪት ይጎሰማል።
📻 የፕሮግራም መረጃ
️ ዲጂታል ነጋሪት የራዲዮ ፕሮግራም (አራተኛ ሳምንት)
📅 ቀን፦ እሁድ ታኅሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
🕐 ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡00 - 8፡00
📻 ጣቢያ፦ አራዳ ኤፍኤም 95.1
🛑 በኮቨናንት ሀብ የጥብቅና ድርጅት ከአራዳ ኤፍኤም 95.1 ጋር በመተባበር የሚቀርብ
📢 ዲጂታል ነጋሪት፦ ለመብትዎ የሚቆም የሕግ ልሳን!

#ዲጂታልነጋሪት #የሸማቾችመብት #የበዓልገበያ #የሕግጥበቃ #ኮቨናንትሀብ #አራዳኤፍኤም #ኢትዮጵያ
2👍1