TIKVAH-ETHIO
708 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#BulenWoreda

ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ታኅሣሥ 13 በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን ገልጿል።

የሟቾችን ማንነት የማጣራቱ ስራ በመታወቂያ እና ከጥቃቱ በተረፉ ሰዎች ምስክርነት አማካኝነት መጀመሩ ታውቋል።

በዚህም መሰረት፣ በጥቃቱ ሕይወታቸው ካለፉ አዋቂዎች መካከል 133ቱ ወንዶች ሲሆኑ 35ቱ ሴቶች ናቸው።

አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ በጥቃቱ አስራ ሰባት ሕጻናት ተገድለዋል። ቀሪ ሃያዎቹ አዛውንቶች መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከሟቾች መካከል ሁለቱ በቡለን ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እያለ ታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የሞቱ መሆናቸውን፣ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በቡለን ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች (ጭላንቆ ፣ በኩጂ ፣ ዲሽባኮ እና ባር) የተፈናቀሉና ቁጥራቸው ከ500 የሚበልጡ ሰዎች በጋሌሳ ቀበሌ በሚገኝ የአውቶቡስ መናኃሪያ እንዲሁም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀበሌውን ጥለው ከ40 ኪ.ሜ. በላይ በእግራቸው በመጓዝ ወደ ቡለን ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

የቡለን ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተፈናቃዮችን እየመገቡ ነው።

ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እስከሚመለሱ ድረስ የሚቆይ አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ኢሰመኮ ያስታወቀ ሲሆን ተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች በሰብአዊ እርዳታ እጥረት ምክንያት ለተጨማሪ አደጋ እንዳይጋለጡ ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA