TIKVAH-ETHIO
708 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#Mekelle

ሌተናል ጀነራል አበባው ታደሰ ከትላንት በስቲያ (ሰኞ) በመቐለ ከተማ ከጦር አዛዦቻቸው ጋር መምከራቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

ምክክሩም በህግ እየተፈለጉ የሚገኙት "የህወሓት ቡድን አባላትን" ለመያዝ የሚያስችል ሀሳብ ላይ እንደነበረ ተገልጿል።

#FDREDefenseForce

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Mekelle

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ለቢቢሲ ገልጿል።

የአይደር ሆስፒታል መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉት የነበሩት አቅርቦቶች በከፍተኛ ደረጃ በመሟጠጣቸው ህክምና ለሚፈልጉ ሰዎች አገልግሎቱን ለመስጠት አዳጋች ደረጃ ላይ መድረሱ አሳውቋል።

እስከ ትናንት ባለው መረጃ አይደር ሆስፒታል ድንገተኛ እና ህይወት አድን የሚባሉ ለምሳሌ ቀዶ ጥገናና የፅኑ ህሙማን ህክምና ለማቋረጥ መገደዱን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል የምሥራቅና የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ቃለ አቀባይ ክሪስታል ዌልስ ተናግረዋል።

ቃለ አቀባይዋ ለዚህ እንደ ምክንያትነትም ያስቀመጡት መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችና ነዳጅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በማለቃቸው ነው ብለዋል።

የተፈጠረውንም ችግር ለመቅረፍም ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር እየተወያዩ መሆኑንም አስረድተዋል።

"የህክምና ግብአቶችን ጨምሮ አስፈላጊ የሚባሉ ቁሳቁሶችን አዲስ አበባ ካለው ክምችታችን ወደ መቐለ እንዲሄድ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ ነን። ይህንም በቅርቡ እንደሚፈፀም ተስፋ አለን" በማለት ለBBC ተናግረዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የህወሓት አመራሮች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ?

ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ቃላቸውን እየሰጡ እንደሆነ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትላንት ለውጭ ሚዲያዎች ተናግረዋል።

በቅርብ ጊዜ ስለነበሩበት ሁኔታ ህዝቡ መረጃ እንዲያገኝ እንደሚደረገ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፥ "የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ምን እንደተፈፀመ ተጨማሪ መረጃ እናውቃለን ብለን እንገምታለን" ብለዋል።

በቁጥጥር ስር ስለሚገኙት የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፖሊስ እንዲሁም አቃቤ ህግ በቅርቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKCHA
#Mekelle

በትግራይ ኢንተርኔት እና ስልክ ባለመኖሩ ከአንድ ወር ጊዜ በላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ ከቤተሰቦቹ ጋር መገናኘት አልቻለም።

ከመቐለ ከተማ ወደ አ/አ የገባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ባለፉት ቀናት በመቐለ ስላለው ሁኔታ አሳውቆናል።

መቐለ ከተማ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፦

- ግጭቱ ከተነሳ ጀምሮ የመቐለ ከተማ ነዋሪ በእጅጉ እየተቸገረ ነው።

- በከተማው የነዳጅ፣ ፣ የውሃ፣ የኔትዎርክ፣ የመብራት አለመኖር በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አሳድሯል።

- በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በአንዳንድ መድሃኒቶች ላይ እጥረት በመኖሩ ሰዎች እየተቸገሩ ነው።

- ከፍተኛ የሆነ የምግብ ግብአት አቅርቦት ችግርም አለ ፤ የንግድ ተቋማት መዘጋታቸው ነዋሪውን ክፉኛ ለችግር አጋልጦታል።

- ዝርፊ በእጅጉ አለ፤ በቀን ሳይቀር ዝርፊያ ይፈፀማል ፤ በከተማው መደበኛው የፀጥታ መዋቅር ባለመኖሩን የደህንነት ችግር እንዳለ ተናግሯል።

- የመቐለ ነዋሪዎች በከተማው ውስጥ በሚፈፀመው የለየለት ዝርፊያ እጅግ አዝነዋል ፤ በአንዳንድ ቦታዎች ወጣቶች አካባቢያቸውን እንዲሁም የመንግስት ንብረት ለመጠበቅ እየሞከሩ ነው።

- በከተማው ውስጥ የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ለተቋማት ጥበቃ እያደረጉ ነው። በተለያዩ ቦታዎችም በምሽት ቅኝት ማድረግ ጀምረዋል።

- ከመቐለ ወደ አ/አ ያደረገው ጉዞ ሰላማዊ እንደነበር ገልጿል።

የቤተሰባችን አባል ያለው ችግር እንዲፈታ ፣ መንግስት የፀጥታ ሁኔታውን እንዲጠናከር ፣ የምግብ አቅርቦት በአፋጣኝ እንዲቀርብ ፣ የአንዳንድ መድሃኒት እጥረትም በቶሎ እንዲፈታ ፣ የግንኙነት መስመር ፣ የመብራት አገልግሎት እንዲመለስ ጠይቋል።

* ሌሎችም የትግራይ ክልል ቲክቫህ አባላት ባገኙት አጋጣሚ ስለነበረው ሁኔታ ሲያሳውቁን እናደርሳለን።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Shire

18,200 ኩንታል የምግብ አቅርቦት የጫኑ 44 ከባድ የጭነት መኪኖች በትላንትናው ዕለት ሽረ እንደገቡ የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ክፍፍሉ በሽረ እና በአቅራቢያው ባሉ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#FDREDefenseForce

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል መሰለ መሰረት እጅ የሰጡ እና የተያዙ የህወሓት አባላት እንዳሉ ለመከላከያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

እነማን እጅ እንደሰጡ እንዲሁም እንደተያዙ ይፋ አላደረጉም።

ሜጄር ጄነራል መሰለ መሰረት፥ "የቀሩ የህወሓት አባላት የትም አያመልጡም የገቡበት ገብተን እንይዛቸዋለን ፤ በሰላማዊ መንገድ እጅ ከሰጡ ጥሩ ፤ እጅ ካልሰጡ ግን መያዝ የሚገባቸው ይያዛሉ ፤ እስከመጨረሻው ድረስ እዋጋለው የሚለው ላይ እርምጃ እንወስዳለን" ብልዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ወይዘሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰመሓል መለስ በመቐለ ከተማ መታሰሯን ተናገሩ !

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰመሐል መለስ ትግራይ መቐለ ውስጥ ተይዛ እንደታሰረች እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወ/ሮ አዜብ ልጃቸው ሰመሐል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናገረው ፣ ወደ መቐለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንደሆነ ገልጸዋል።

አዲስ አበባ የሚገኙት ወይዘሮ አዜብ ጨምረውም ሰመሐል ወደ መቀለ ያቀናችው በአባቷ የህይወት ታሪክ ላይ የተጻፈ መጽሐፍን ተንተርሶ የተዘጋጀን ቲያትር ለማስመረቅ በርካታ ሰዎች ካሉበት ቡድን ጋር መሆኑን አመልክተዋል።

ሰመሐል "የፖለቲካ አቋም ሊኖራት ይችላል። ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አመራርም፣ አባልም፣ ደጋፊም አልነበረችም" ያሉት እናቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የእስሯ ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ወ/ሮ አዜብ፥ ሰመሐል በየትኛው አካል እንደተያዘችና ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከአንዳንድ አካላት ለማወቅ ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ ነገር ግን ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል።

ከሰመሐል በተጨማሪ የጀነራል ኃየሎም አርአያ ልጅ የሆነው ብርሐነመስቀል ኃየሎም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አወል ሱልጣን እና የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጄይላን አብዲን ስለጉዳዩ ቢጠየቁም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

MORE : https://telegra.ph/BBC-12-21-3

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
Channel photo updated
#UPDATE

ሳዑዲ አረቢያ በፍጥነት እየተዛመት ነው የተባለውን አዲሱን የኮቪድ ዝርያ በመፍራት ሁሉንም አለም አቀፍ በረራዎች ለጊዜው አግዳለች።

እገዳው ለአንድ (1) ሳምንት ሲሆን ከዚህም ሊራዘም እንደሚችል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የካርጎ በረራዎች ይቀጥላሉ።

ይህ እገዳ ስለአዲሱ የኮቪድ ዝርያ ግልፅ የሆነ የህክምና መረጃ እስኪገኝ ሊቀጥል እንደሚችልም ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ የመሬት እና ባህር ወደቦችም ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ ተብሏል።

የሳዑዲ መንግሥት ባለፉት ሶስት ወራት ከአውሮፓ ሀገራት የመጣ ወይም በአውሮፓ ሀገራት በኩል ጉዞ ያደረገ ማንኛውም ሰው በአስቸኳይ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርግ አዟል።

በተመሳሳይ ፦

ኩዌት በረራዎችን አግዳለች ፤ የመሬት እና የባህር ድንበሮቿን ከዛሬ ጀምሮ እስከ Jan 1 (ታህሳስ 23) ዘግታለች።

የካርጎ በረራ ይቀጥላል።

እንዲሁም ኦማን የባህር ፣ አየር፣ የመሬት ድንበሮቿን ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ለአንድ (1) ሳምንት ትዘጋለች።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ከፍተኛ ስጋትን የደቀነው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ !

በርካታ የአውሮፓ አገራት ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ በብሪታኒያ አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው።

አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል።

እስከ አሁን ጀርመን ፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም ሁሉም ወደ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል።

ዛሬ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው።

አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል።

ለፈረንጆች ገና እና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል።

የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ይበልጥ ገዳይ ስለመሆኑ ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም።

ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮና ቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል ? እንዲባል አድርጓል።

የብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል ፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩኬ (UK) ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ሰመሓል መለስ ከእስር ተለቀቀች።

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰምሃል ከእሁድ ጀምሮ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ ለ36 ሰዓታት ተይዛ መቆየቷን ገልጸው ፤ ትናንት ምሽት እራሷ ደውላ መለቀቋን እንደገለጸችላቸው ዛሬ [ማክሰኞ] ጠዋት ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባይደን የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ።

ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ትላንት ምሽት የኮቪድ-19 ክትባት ተከትበዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ክትባቱን ሲወስዱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለህዝብ ተላልፏል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በተመሳሳይ የኮቪድ - 19 ክትባት መከተባቸው የሚታወስ ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

አዲሱ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው።

ከ40 በላይ አገራት ከUK ወደ አገራቸው የሚደረጉ በረራዎችን አግደዋል።

የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በዚህ ዙሪያ የጋራ ፖሊሲ ለማውጣት እየተወያዩ ነው።

ዴንማርክ ውስጥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመታየቱ ስዊድን ወደ ዴንማርክ የሚደረግ ጉዞ አግዳለች።

ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ ነው። በከፍተኛ ደረጃ ጎጂ ስለመሆኑ ግን እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም።

የዓለም ጤና ድርጅቱ ማይክ ራየን ፥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ ሂደት የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

የUK የጤና ሚንስትር ጸሐፊ ማት ሀንኮክ አዲሱ ዝርያ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ቢሉም ማይክ ራይን አዲሱ ዝርያ "ከቁጥጥር አልወጣም" ብለዋል።

UK ከተገኘው የቫይረስ ዝርያ የተለየ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል። የደቡብ አፍሪካ ተጓዦች ላይ እገዳ እየተጣለም ነው።

እስካሁን የአዲሱ ቫይረስ ዝርያ በዴንማርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን እና ኔዘርላንድስም ተገኝቷል።

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ፤ የቫይረሱ ዝርያ ከተገኘባቸው ቦታዎች ውጪ ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል።

UK የዘረ መል ቅንጣት ላይ ጥናት በማድረጓ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ እንደደረሰችበት አስረድተዋል።

በቤልጄም የሚሠሩት የቫይረስ አጥኚ ማርክ ቫን፤ "በቀጣይ ቀናት አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ በብዙ አገሮች ይገኛል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል። (BBC)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Ethiopia

ዛሬ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አምጥቃለች።

' ET-SMART-RSS ' በስኬት መምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በይፋዊ ፌስቡክ ጉፁ ላይ አስታውቋል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#የኢትዮጵያ_ማሳሰቢያ

በካርቱም ሲካሄድ የነበረው 2ተኛው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት መጠናቀቁን ፋና ዘግቧል።

ሁለቱም ወገኖች በጋራ የድንበር አካባቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ "በጋራ ድንበር" አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለውጦችና እንቅስቃሴዎች የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ መሆናቸው ተነስቷል፡፡

ከዚህ ባለፍ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚለውጥ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆሙ እና ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ ኢትዮጵያ አሳስባለች፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BenishangulGumuz

የኢትዮጵያ መንግሥት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ያለውን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ጥዋት አሳወቁ።

በክልሉ መተከል ዞን ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በተፈጸመው ኢሰብአዊ የሆነ ተግባርም በእጅጉ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ጠ/ሚሩ ችግሩን በተለያዩ መንገዶች ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም ብለዋል። መንግስት አሁን ላይ የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ ማድረጉን በፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ሀገር መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ 42 ታጣቂዎች ተደመሰሱ !

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ #ጥቃት ያደረሱ የታጠቁ ኃይሎች ላይ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ መደምሰሳቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት አሰውቋል።

የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ ታጣቂዎቹ ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እና ቀስቶችን በቁጥጥር ስር አዉሏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA