TIKVAH-ETHIO
708 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ጥዋት አዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ተገልጿል።

ሰራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቐለ እያመራ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Ethiopia

በህግ የሚፈለጉት የህወሓት አባላት በሰላማዊ ሁኔታ እጃቸውን እንዲሰጡ የተሰጠው የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል።

ይህንን ተከትሎም ዓለም አቀፍ የመብት ቡድኖች እና ተቋማት የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጠው እየተማፀኑ ነው።

ሁለቱም ኃይሎች ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠይቋል።

ወታደራዊ ባልሆኑ መሰረተ ልማቶች እና በሰላማዊ ሰዎች እና ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚቻለውን ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

ሰላማዊ ህዝብ ከሚበዛባቸው ሰፈሮች የወታደራዊ ቁሳቁሶችን ክምችት እንዲያስወግዱ እንዲሁም የወታደሮች እንቅስቃሴ በሰላማዊ ነዋሪዎች መኖሪያ አካባቢ እንዳይሆን ጠይቋል።

በተጨማሪ ተዋጊዎች ሰላማዊ ዜጎችን ጋሻ ከማድረግ እንዲቆጠቡ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች አስፈላጊው ከለላ እና ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለምክክር በZoom ተቀምጦ ነበር። ነገር ግን ስብሰባውን የአፍሪካ አገራት ባለመደገፋቸው #ያለመፍትሄ ተጥናቅቋል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ የፈረንሳይ ፣ እንግሊዝ ፣ ቤልጂየም ፣ ጀርመን እና የኢስቶንያ ዲፕሎማቶች አሜሪካንን በመደገፍ ውይይቱ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን SBS ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አገራት በሌሎች አገራት 'የውስጥ ጉዳይ' ጣልቃ ላለመግባት መርህ እንዲገዙ ዛሬ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
መንግስት የሰጠው የ72 ሰዓታት ጊዜ ወደ መጠናቀቁ እየተቃረበ ይገኛል።

የህወሓት አባላት ግን ይህንን ጥሪ አልተቀበሉትም ፤ ይልቁንም መንግስት ሽንፈት ስለደረሰበት ለመሸፋፈን የተጠቀመው ነው ብለውታል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ትላንት በሰጠው መግለጫ ለመጨረሻው ምዕራፍ ትዕዛዝ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል።

መቐለ ከተማን የከበበው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ ለ3ኛውና ለመጨረሻው ምዕራፍ በተጠንቀቅ ቆሞ ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ተገልጿል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት መቐለ ከተማን በ50 ኪሎ ሜትር ውስጥ መክበቡ ተገልጿል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ትላንት ለሮይተርስ በፅሁፍ እንዳሉት "መቐለ ተከቧል የሚባለው እስካሁን እንዲህ ያለ ነገር የለም" ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በመቐለ ከተማ ይኖራል በተባለው ኦፕሬሽን ንፁሃን እንዳይጎዱ ወታደራዊ ያልሆኑ መሰረት ልማቶች እንዳይጠቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የተለያዩ ተቋማት እየተማፀኑ ነው።

ተመድ መንግስት ያስቀመጠው የ72 ሰዓት ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በመቐለ ሊከሰት የሚችለው ሁኔታ ከወዲሁ እንዳሳሰበው አሳውቋል ፤ ድርጅቱ "የጦር ወንጅል" እንዳይፈፀምም ስጋት እንዳለው ገልጿል።

ዶ/ር አብይ ከሁለት ቀን በፊት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ "በመቐለ የሚኖረው የህግ ማስከበር እርምጃችን ጉዳትን እጅግ በቀነሰ መልኩ መከናወን እንዳለበት እናምናለን፣ ስለዚህም መቐለ ከተማን ከከፋ ጉዳት ታድገን ዘመቻውን በድል የምናከናውንበትን መንገድ እንደምንከተል ለመግለፅ እወዳለሁ" ብለዋል።

ጠ/ሚሩ የመቐለ ነዋሪዎች ከሰራዊቱ ጎን በመቆም በህግ የሚፈለጉትን አካላት ለፍርድ በማቅረብ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል ፤ ለጥቂት ሰዎች ሲባል አንድም ሰው መሞት ፣ ንብረትም መውደም የለበትም ብለዋል።

(ቲክቫህ)
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የዲያጎ ማራዶና ህልፈት !

ታሪክ አይሽሬው የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና " ወርቃማው ልጅ " በ60 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

• ከሳምንታት በፊት የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እንደተደረገለት ሲታወስ ህይወቱ ለማለፉ እንደ ምክንያትነት የተቀመጠው የልብ ህመም መሆኑ ተነግሯል።

• ማራዶና በልብ ህመሙ ምክንያት በመኖሪያ ቤቱ ህይወቱ እንዳለፈች ተገልጿል።

"አንድ ቀን ይከሰታል ፣ ይህ ክስተት ዛሬ ላይ ሆኗል ፣ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ህይወቱ አልፏል" ዜናውን ለዓለም ህዝብ በቀዳሚነት ያደረሰው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን በፊት ገፁ ያስነበበው።
#Mekelle

"...በህዝብ ላይ ምንም የሚመጣ ነገር አይኖርም" - ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ

የመከላከያ የህብረት ሎጅስቲክስ ዋና ማምሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮ/ል ሹማ ኦብሳ በሚካሄደው ወታደራዊ እርምጃ ሲቪል ዜጎችን ከታጣቂዎች የመለየት ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ዛሬ ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳውቀዋል።

ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ ፥ "ሁሉም ነገር በወታደራዊ ጥበብ ነው የሚሰራው፤ ዝም ተብሎ ከተማ ውስጥ እየተሮጠ ሆቴል መምታ አይደለም ፤ ቁልፍ ቦታዎች ይታወቃሉ እነዛ ቦታዎች ላይ ሰዎቹን መቆጣጠር ነው" ብለዋል።

ኮ/ል ሹማ በህግ የሚፈለጉትን ሰዎች ለመያዝ በጥንቃቄ ነው የሚሰራው ብለዋል።

አሁን ገብተዋል የሚባለው ቤተክርስቲያን ፣ መስጊድ አካባቢ ነው፣ መሳሪያም እዛ አስቀምጠዋል ይባላል ይህ ደግሞ ይታወቃል ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም በዚህ አካባቢዎች ላይ እነሱም ሲጨነቁ ሊወጡ ይችላሉ ፤ አሁን አልደረሱብንም ብለው ስላልተጨነቁ ነው ፤ ሲደረስባቸው ግን ህዝቡ እራሱ አውጥቶ ይሰጣቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

እንኳን ሀገር ውስጥ ውጭ ሀገር በርካታ ስምሪት እናደርጋለን ፤ ህዝብን ከጠላት ነጥለን ነው የምንሰራው ፤ ከዚህ በፊትም የውጊያ አካሄዳችን የሚታወቅ ነው ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም በህዝብ ላይ ምንም የሚመጣ ነገር አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል።

ኮ/ሌ ሹማ ፥ "የታጠቀ ኃይል ነው የምንፈልገው፤ የታጠቀው ኃይል በሰላማዊ መንገድ እጅ ስጥ እየተባለ ነው ፤ ይህ ኃይል የወጣው ከህዝቡ ነው ስለዚህ ለህዝቡ ማሰብ አለበት" ብለዋል።

መከላከያ በአሁን ሰዓት አብዛኛው የትግራይ ክልል ከተሞች በቁጥጥሩ ስር እንደሚገኝ አሳውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
አጫጭር መረጃዎች ፦

1. የመከላከያ ሰራዊት የመቐለ ኤርፖርት ፣ የክልሉን አስተዳደር ጽህፈት ቤት እንዲሁም ቁልፍ የሆኑ ህዝባዊ እና ሌሎች ተቋማትን በዋናነት መቆጣጠሩን ዶክተር አብይ አህመድ ገልፀዋል።

2. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ለሮይተርስ ጦራቸው ከመቐለ አካባቢ መልቀቁን ጠቁመዋል ፤ በፍልሚያው ግን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ዶክተር ደብረፅዮን "የእራስን እድል የመወሰን መብታችንን ለመከላከል ወራሪዎችን እስከ መጨረሻው እንታገላቸዋለን" ነው ያሉት።

3. ትላንት ምሽት ኤርትራ አስመራ ከተማ 6 የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱን በኤርትራ የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጿል። ኤርትራን በሚመለከት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት 'ህወሓት' ወደ ኤርትራ ለሶስተኛ ጊዜ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን ገልፀዋል።

4. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጡ አሳውቋል።

5. በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የተጠናቀቀውን የህግ ማስከበር ዘመቻን አስመልክቶና በቀጣይ ሁኔታ ላይ ከጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በመቐለ ከተማ መግለጫ እንደሚሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ገልፀዋል።

3ኛው ምዕራፍ የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል ተጠናቆ አሁን ላይ ወደ መልሶ ማደራጀት መገባቱን ሌ/ጄኔራሉ እንደገለፁት አብመድ ዘግቧል።

6. የUNHCR ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልፀዋል። "ሆኖም ግን በቀን ከ5 መቶ እስከ 6 መቶ የተፈናቃዮች ቁጥር ትንሽ የሚባል አይደለም" ብለዋል።

በሌላ በኩል በሱዳን የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመርዳት የሱዳን መንግሥት $147 ሚሊየን እንዲያስፈልገው መግለፃቸውን SBS አስነብቧል።

ህዳር 20/2013 ዓ/ም

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ICRC

በመቐለ የሚገኙ ሆስፒታሎች ቁስለኞችን ለማከም የህክምና ግብአት እጥረት እንደገጠማቸው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) አስታውቋል።

ICRC በመቐለ የሚገኘው ሆስፒታል የአስክሬን ማስቀመጫ ከረጢት እንደሌለውና የእጅ ጓንትን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች እያለቁ ነው ብሏል።

በዛሬው ዕለት መቐለ ከተማ ፀጥታ ብላ እንደዋለች #ICRC አሳውቋል።

https://www.icrc.org/en/document/ethiopia-hospitals-mekelle-struggling-care-wounded-medical-supplies-run-out-red-cross?utm_source=facebook&utm_medium=social&linkId=100000022072623

VIDEO : ICRC Africa (Tigray , Mekelle)
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ "ተመራቂ ተማሪዎች" ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት እንደሚጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ሪፖርት ያላደረጉ ተመራቂ ተማሪዎች ህዳር 24 እና ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ/ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
አጫጭር መረጃዎች ፦

1. ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በህግ የሚፈለጉት የህወሓት አባላት ከመቐለ ሸሽተው "ሀገረ ሰላም" (ከመቐለ 52 KM) አካባቢ እየተሰባሰቡ ነው ሲሉ ተናገሩ።

ትላንት ምሽት የነበሩበትን ሁኔታ በቀጥታ ስንከታተል ነበር፤ ጥቃት ግን አልፈፀምንም ለዚህ ምክንያቱ በሽሽት ውስጥ ሚስቶቻቸውን ፣ ልጆቻቸውን ፣ የታፈኑ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዘው ሄደዋል፤ ሀገር ሰላም እና አብይ ዓዲ አካባቢም መተረማመስ ስለነበር ነው ብለዋል። ይህ ሁኔታ ግን እንደማይቀጥል አሳስበዋል።

2. ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል "ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል" መባሉን "ሐሰት ነው" ሲሉ ለሮይተርስ መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል፤ "አሁንም በመቐለ ከተማ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተዋጋን ነው" ብለዋል።

የጠ/ሚር ፅ/ቤት ፕሬስ ሰክሬቴሪያት ቢለኔ ስዩም "የፌዴራል መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በማረጋጋት ስራ ላይ ተጠምዷል ፤ ተበታትኖ ላለ ወንጀለኛ ንግግር መልስ መስጠት ጉዳያችን አይደለም" ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን "በመቐለ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውግያ ቀጥለናል" ብለው መናገራቸውን አጣጥለዋል።

3. የወልቃይት እና ሑመራ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው 'የስልክ አገልግሎት' ዳግም መጀመሩን የአካባቢውን ነዋሪዎች ማረጋገጣቸውን አል ዓይን ዘግቧል።

4. ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር በምትገኘው ከሰላ ግዛት አከባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ መያዟን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ ፀጥታ ኃይሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዝ የቻሉት ከኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በኩል ወደ ሱዳን በሚያገናኘው ድንበር አከባቢ ሰሞኑን በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን የሱዳኑ ዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል።

ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ/ም

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#UPDATE

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ለውጭ ሚዲያዎች መገለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በመግለጫቸው ፦

- የቀድሞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

- የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የነበሩት ኬሪያ ኢብራሂምም በቅርቡ እጅ መስጠታቸውን አስታውሰዋል።

- ሌሎችም በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

- በመንግሥት ኃይል እየተፈለጉ የሚገኙት የቀሩት የህወሓት አመራሮች በጥቂት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ተናግረዋል።

- የተመድ የሰብአዊ ድርጅት ሰራተኞች ያልተፈቀዱ 2 ኬላዎችን አልፈው ሲሄዱ የተወሰኑት ተተኩሶባቸው እና ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። በቁጥጥር ስር የዋሉት አሁን ላይ ተለቀዋል።

- የተባበሩት መንግስታት (UN) የሰብአዊ ድርጅቶች በትግራይ ክልል የሚያከናውኑትን ስራ ከመንግሥት ጋር ተናበው የመስራት ግዴታ እንዳለባቸው በተደረሰው ስምምነት መሰረት መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን (AlAin)
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKCHA
#UPDATE

የሀዋሳ ሞያሌ የ500 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ እና የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክቶች በነገው እለት ይመረቃሉ።

የሀዋሳ ሞያሌ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የፈጀ ሲሆን ፣ የግንባታው ወጪ የተሸፈነው ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ብድር ነው።

በተመሳሳይ በኬንያ በኩል ደግሞ ከኢሲኦሎ እስከ ሞያሌ የሚወስደው የ503 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታም በመጠናቀቁ ነገ ይመረቃል ተብሏል።

መንገዶቹ ግንባታ የትራንስ አፍሪካ አውራ ጎዳ አንዱ አካል ናቸው። ግንባታዎቹ መጠናቀቃቸው ኢትዮጵያ እና ኬንያ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቸ ላይ ያላቸውን የትብብር ግንኙነት ለማሳለጥ ያግዛል ተብሏል።

መንገዶቹ ናይሮቢ ሞምባሳ እስከ አዲስ አበባ ያሉትን መንገዶች የሚያገናኘው የአፍሪካ አህጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል እንደሆኑ ኢዜአ ገልጿል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Mekelle

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ለመቐለ ነዋሪዎች የመጠጥ ውኃ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

እስካሁን ድረስ 2 ሺ የተጠፋፉ ቤተሰቦችንም በቀይ መስቀል የሰላማት መልዕክት ማገናኘቱን ማህበሩ አስታውቋል፡፡

ICRC ለሺዎች የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ ፣ የአንቡላንስ አገልግሎት፤ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሣቁሶችን በአላማጣ ፣ በሁመራ ፤ በሽረ ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Mekelle

ሌተናል ጀነራል አበባው ታደሰ ከትላንት በስቲያ (ሰኞ) በመቐለ ከተማ ከጦር አዛዦቻቸው ጋር መምከራቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

ምክክሩም በህግ እየተፈለጉ የሚገኙት "የህወሓት ቡድን አባላትን" ለመያዝ የሚያስችል ሀሳብ ላይ እንደነበረ ተገልጿል።

#FDREDefenseForce

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Mekelle

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ለቢቢሲ ገልጿል።

የአይደር ሆስፒታል መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉት የነበሩት አቅርቦቶች በከፍተኛ ደረጃ በመሟጠጣቸው ህክምና ለሚፈልጉ ሰዎች አገልግሎቱን ለመስጠት አዳጋች ደረጃ ላይ መድረሱ አሳውቋል።

እስከ ትናንት ባለው መረጃ አይደር ሆስፒታል ድንገተኛ እና ህይወት አድን የሚባሉ ለምሳሌ ቀዶ ጥገናና የፅኑ ህሙማን ህክምና ለማቋረጥ መገደዱን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል የምሥራቅና የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ቃለ አቀባይ ክሪስታል ዌልስ ተናግረዋል።

ቃለ አቀባይዋ ለዚህ እንደ ምክንያትነትም ያስቀመጡት መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችና ነዳጅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በማለቃቸው ነው ብለዋል።

የተፈጠረውንም ችግር ለመቅረፍም ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር እየተወያዩ መሆኑንም አስረድተዋል።

"የህክምና ግብአቶችን ጨምሮ አስፈላጊ የሚባሉ ቁሳቁሶችን አዲስ አበባ ካለው ክምችታችን ወደ መቐለ እንዲሄድ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ ነን። ይህንም በቅርቡ እንደሚፈፀም ተስፋ አለን" በማለት ለBBC ተናግረዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የህወሓት አመራሮች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ?

ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ቃላቸውን እየሰጡ እንደሆነ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትላንት ለውጭ ሚዲያዎች ተናግረዋል።

በቅርብ ጊዜ ስለነበሩበት ሁኔታ ህዝቡ መረጃ እንዲያገኝ እንደሚደረገ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፥ "የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ምን እንደተፈፀመ ተጨማሪ መረጃ እናውቃለን ብለን እንገምታለን" ብለዋል።

በቁጥጥር ስር ስለሚገኙት የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፖሊስ እንዲሁም አቃቤ ህግ በቅርቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKCHA
#Mekelle

በትግራይ ኢንተርኔት እና ስልክ ባለመኖሩ ከአንድ ወር ጊዜ በላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ ከቤተሰቦቹ ጋር መገናኘት አልቻለም።

ከመቐለ ከተማ ወደ አ/አ የገባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ባለፉት ቀናት በመቐለ ስላለው ሁኔታ አሳውቆናል።

መቐለ ከተማ በቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፦

- ግጭቱ ከተነሳ ጀምሮ የመቐለ ከተማ ነዋሪ በእጅጉ እየተቸገረ ነው።

- በከተማው የነዳጅ፣ ፣ የውሃ፣ የኔትዎርክ፣ የመብራት አለመኖር በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አሳድሯል።

- በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በአንዳንድ መድሃኒቶች ላይ እጥረት በመኖሩ ሰዎች እየተቸገሩ ነው።

- ከፍተኛ የሆነ የምግብ ግብአት አቅርቦት ችግርም አለ ፤ የንግድ ተቋማት መዘጋታቸው ነዋሪውን ክፉኛ ለችግር አጋልጦታል።

- ዝርፊ በእጅጉ አለ፤ በቀን ሳይቀር ዝርፊያ ይፈፀማል ፤ በከተማው መደበኛው የፀጥታ መዋቅር ባለመኖሩን የደህንነት ችግር እንዳለ ተናግሯል።

- የመቐለ ነዋሪዎች በከተማው ውስጥ በሚፈፀመው የለየለት ዝርፊያ እጅግ አዝነዋል ፤ በአንዳንድ ቦታዎች ወጣቶች አካባቢያቸውን እንዲሁም የመንግስት ንብረት ለመጠበቅ እየሞከሩ ነው።

- በከተማው ውስጥ የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ለተቋማት ጥበቃ እያደረጉ ነው። በተለያዩ ቦታዎችም በምሽት ቅኝት ማድረግ ጀምረዋል።

- ከመቐለ ወደ አ/አ ያደረገው ጉዞ ሰላማዊ እንደነበር ገልጿል።

የቤተሰባችን አባል ያለው ችግር እንዲፈታ ፣ መንግስት የፀጥታ ሁኔታውን እንዲጠናከር ፣ የምግብ አቅርቦት በአፋጣኝ እንዲቀርብ ፣ የአንዳንድ መድሃኒት እጥረትም በቶሎ እንዲፈታ ፣ የግንኙነት መስመር ፣ የመብራት አገልግሎት እንዲመለስ ጠይቋል።

* ሌሎችም የትግራይ ክልል ቲክቫህ አባላት ባገኙት አጋጣሚ ስለነበረው ሁኔታ ሲያሳውቁን እናደርሳለን።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Shire

18,200 ኩንታል የምግብ አቅርቦት የጫኑ 44 ከባድ የጭነት መኪኖች በትላንትናው ዕለት ሽረ እንደገቡ የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ክፍፍሉ በሽረ እና በአቅራቢያው ባሉ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#FDREDefenseForce

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል መሰለ መሰረት እጅ የሰጡ እና የተያዙ የህወሓት አባላት እንዳሉ ለመከላከያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

እነማን እጅ እንደሰጡ እንዲሁም እንደተያዙ ይፋ አላደረጉም።

ሜጄር ጄነራል መሰለ መሰረት፥ "የቀሩ የህወሓት አባላት የትም አያመልጡም የገቡበት ገብተን እንይዛቸዋለን ፤ በሰላማዊ መንገድ እጅ ከሰጡ ጥሩ ፤ እጅ ካልሰጡ ግን መያዝ የሚገባቸው ይያዛሉ ፤ እስከመጨረሻው ድረስ እዋጋለው የሚለው ላይ እርምጃ እንወስዳለን" ብልዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ወይዘሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰመሓል መለስ በመቐለ ከተማ መታሰሯን ተናገሩ !

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰመሐል መለስ ትግራይ መቐለ ውስጥ ተይዛ እንደታሰረች እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወ/ሮ አዜብ ልጃቸው ሰመሐል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናገረው ፣ ወደ መቐለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንደሆነ ገልጸዋል።

አዲስ አበባ የሚገኙት ወይዘሮ አዜብ ጨምረውም ሰመሐል ወደ መቀለ ያቀናችው በአባቷ የህይወት ታሪክ ላይ የተጻፈ መጽሐፍን ተንተርሶ የተዘጋጀን ቲያትር ለማስመረቅ በርካታ ሰዎች ካሉበት ቡድን ጋር መሆኑን አመልክተዋል።

ሰመሐል "የፖለቲካ አቋም ሊኖራት ይችላል። ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አመራርም፣ አባልም፣ ደጋፊም አልነበረችም" ያሉት እናቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የእስሯ ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ወ/ሮ አዜብ፥ ሰመሐል በየትኛው አካል እንደተያዘችና ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከአንዳንድ አካላት ለማወቅ ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ ነገር ግን ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል።

ከሰመሐል በተጨማሪ የጀነራል ኃየሎም አርአያ ልጅ የሆነው ብርሐነመስቀል ኃየሎም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አወል ሱልጣን እና የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጄይላን አብዲን ስለጉዳዩ ቢጠየቁም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

MORE : https://telegra.ph/BBC-12-21-3

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA