TIKVAH-ETHIO
709 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️ትግራይ ክልል የመጀመርያውን የኮሮና ሞት አስመዘገበ!

Tigray region reported it’s first #coronavirus death. A 29-years-old woman succumbed to #Covid19 in Humera after being taken to the hospital experiencing difficulty to breath, BBC News Tigrinya reported

#Ethiopia #Tigray

ኣብ ክልል ትግራይ፡ ሓንቲ ጓል-ኣንስተይቲ ብሕማም ኮሮናቫይረስ ዓሪፉ
---------------------------------
ኣብ ክልል ትግራይ፡ ሓንቲ ጓል 29 ዓመት፡ ብሕማም ኮሮናቫይረስ ተለኺፋ ከምዝዓረፈት ቢሮ ሓለዋ ጥዕና ትግራይ ሓቢሩ።

እታ ጓል: ሕጽረት ትንፋስ ኣጋጢምዋ ናብ ሑመራ ሆስፒታል ካሕሳይ ኣበራ ከምዝኸደትን፡ ምስ ተመርመረት ድማ በቲ ቫይረስ ተለኺፋ ከምዝጸንሐት እቲ ቢሮ ጥዕና ወሲኹ ገሊጹ።

ኣብ ክልል ትግራይ፡ ዛጊት 46 ሰባት በቲ ቫይረስ ተለኺፎም ኣለው።
#Tigray

• የኮሪያ ሪፐብሊክ ምስራቅ ሱዳን ውስጥ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች የ300 ሺ ዶላር ድጋፍ ማድረጓን የሱዳን ዜና አገልግሎት በድረገፁ አስነብቧል።

የኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት የሱዳን ህዝብ እና የሱደን መንግስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ተቀብሎ ስላስተናገደ ምስጋናውን አቅርቧል።

• የስዊድን መንግስት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።

ድጋፉ በIOM ፣ WFP፣ ICRC አማካኝነት ለተጎጂዎች እንደሚደርስ እንደሆነ የስዊድን ኤምባሲ ገልጿል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ቅየራ ድጋሚ ተጀምሯል፡፡

የብር ቅየራው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ አስታውቋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

"...የዕለት ደራሽ እርዳታው በተገቢው መንገድ እየደረሰን አይደለም" - በመቐለ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች

ባለፉት 2 ወራት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች ከሌላው አካባቢ በተለየ ሁኔታ ወደሌላው የትግራይ አካባቢ እና ወደ ሱዳን ተፈናቅለዋል።

ተፈናቃይ ወገኖች በጦርነቱ ምክንያት ለከባድ ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተዳርገዋል።

የተለያዩ ቤተሰቦቻቸው ወደ ተለያየ ቦታ በመበታተናቸው ህልውናቸውን ለማረጋገጥ እና ወደ ቤታቸው ለመመለስ የተመቻቸ ነገር እንደሌለ በመቐለ የተጠሉሉ ዜጎች ለትግራይ ቲቪ ተናግረዋል።

ከተፈናቃዮች መካከል አንደኛው ከወላጅ እናቱ እና ከእህቱ ጋር ይኖር እንደነበር እና ሁሉም ህይወቱን ለማትረፍ ወደ ተለያየ ቦታ እንደሸሸ ገልፆ በዚህም ምክንያት እናትና እህቱ የት እንደገቡ ፤ ይኑሩ ይሙቱ እንደማያውቅ እነሱም ስለሱ የሚያወቁት ነገር እንደሌለ ተናግሯል።

ሌላኛው ከሁመራ የተፈናቀለ ግለሰብ፥ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይሁን ሌላ አካል ያደረገው ነገርና ስለመመለሳቸውም የተሰጣቸው መረጃ እንደሌለ ገልጿል።

ተፈናቃዩ ፥ ቤቶቻቸውን ሌሎች ሰዎች እንደገቡባቸውና ብዙ ንብረት ትተው በመፈናቀላቸው ከባድ ችግር ውስጥ እንዳሉ ገልጿል።

አንድ እድሜያቸው ገፋ ያለ እናት ደግሞ : "የራሴ ቤት እና እርሻ ነበረኝ፥ ልጄ እዛው ነው በስልክ እንደነገረኝ ከሆነ ንብረታችን በሙሉ እየተወሰደ ነው። ለኔ ግን እንኳን ልጄ አልሞተ እንጂ ንብረት ቀረብኝ አልልም ሰርቼ መልሰዋለሁ።" ብለዋል።

የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የዕለት ደራሽ እርዳታ እየሰጠ ቢሆንም ተፈናቃዮች ተገቢውን እና በቂ ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

ዛሬ ጥር 11/2013 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ለሚዲያዎች ባሰራጨው መግለጫ : በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እየቀረበ ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና የሕክም አቅርቦቶችን የያዘ የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ደርሷል ብሏል።

አክሎም በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።

* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

የሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ከመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ጥሩዬ አሰፌ ጋር ትላንት ጥር 22 ቀን 2013 ምክክር ማድረጋቸው ተሰምቷል።

በወቅቱ በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ "ፆታዊ ጥቃቶች" ተፈፅሟል በሚል የተነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት እንዳደረጉ ነው የተገለፀው።

ጉዳዮን ለማጠራት የተቋቋመውን ግብረ ሀይል አስመልክቶ ውይይት የተደረገ ሲሆን ግብረ ሀይሉ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን እና መከላከያ ሰራዊትን ያካተተ መሆኑ ነው የተሰማው።

ግብረ ሀይሉም እውነተኛው ነገር ለማወቅ ምርመራ እና የማረጋገጥ ስራ እንደሚያከናውን ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ገልፀዋል።

መረጃው የሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኣርኣያ ይርጋ የተገኘ መረጃ ፦

- ከጦርነቱ በፊት በትግራይ 264 የሚጠጉ የጤና ተቋማት ነበሩ (24 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ 14 አጠቃላይ ሆስፒታል፣ 2 ሪፈራል ሆስፒታል እና 224 ጤና ጣቢያዎች) የክልሉ ጤና ቢሮ ሊደርድባቸው የቻለው 19 ሆስፒታሎች ሲሆን 16ቱ ሙሉ በሙሉ ስራ እየሰሩ ነው። 4ቱ ምንም አይነት አገልግሎት የሚሰጡበት ሁኔታ ላይ አይደሉም፤ ሆስፒታሎቹ ጉዳት የደረሰባቸው ወይም የፀጥታ ስጋት ያለበት አካባቢ ያሉ ናቸው (ፍረወይኒ ሆስፒታል፣ ሃውዜን ሆስፒታል፣ እንጥጮ ሆስፒታል፣ ኣብይ ኣዲ ሆስፒታል)

- በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸው ሆስፒታሎች አሉ። የወደሙ ሆስፒታሎች እንደአዲስ ተሰርተው አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሰራ ነው።

- ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች መካከል ውቅሮ ሆስፒታል ፣ ኣብይ ኣዲ ሆስፒታል ፣ ኣድዋ ሆስፒታል ፣ ሰለክለካ ሆስፒታል (ሽረ አካባቢ) ይገኙበታል። እነዚህ ሆስፒታሎች በፍጥነት (በአንድ ሳምንት) ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ጥረት እየተደረገ ነው።

- በክልል ትግራይ 20 ሺህ የጤና ባለሞያዎች ከጦርነቱ በፊት ስራ ላይ ነበሩ፤ በጦርነቱ ምክንያት 1,024 ተፈናቅለው ቀያቸውን ለቀዋል፣ 3,066 ስራ ላይ ናቸው፤ የተቀሩት ሪፖርት ያላደረጉ (ወደ ሱዳን የተሰደዱ፣ ወደ መሀል ሀገር፣ አ/አ የሄዱ) ባለሞያዎች ናቸው።

- መቐለ ውስጥ ኣይደር እና መቐለ አጠቃላይ ሆስፒታል 24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ ነው። ከመቐለ ውጭ ዓዲግራት ፣ መሆኒ ፣ ማይጨው እና ኣዲጉደም ፣ ሽረ ሆስፒታሎች 24 ሰዓት ለ7 ቀን አገልግሎት እየሰጡ ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

መጀመሪያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከዛም በጦርነቱ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት ካቋረጡ /ከትምህርት ከራቁ አመት ሊሆናቸው ነው።

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ትምህር ቤቶች ወድመዋል።

የልጆች/ተማሪዎች ስነልቦና በእጅጉ ተጎድቷል።

በጦርነቱ ወቅት ባዩት ነገር ተረብሸዋል።

መምህራርን ተገናቅለዋል፤ አካባቢያቸውን ጥለው ሰላም ፍለጋ ተሰደዋል።

አሁን ላይ ሁሉም የክልሉ አካባቢ አስተማማኝ ሰላም ሳይረጋገጥ ፣ ዝርፊያ እና ሌብነት በበዛበት፣ ፆታዊ ጥቃት እንደሚፈፀም ሪፖርት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት በምን አይነት መልኩ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ታስቧል ?

ምንም እንኳን አሁን ትግራይ ያለችበት ሁኔታ ፈታኝ ቢሆንም የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ተማሪዎች ከዚህ በላይ ተጎድተው እንዳይቆዩ ትምህርት ለመጀመር እያሰበ ነው።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ተስፋይ ሰለሞን እንዴት ትምህርት ለመጀመር እንደታሰበ አብራርተዋል።

በዚህ ማብራሪያቸው ትምህርት ቤት በወደሙባቸው እና የፀጥታች ችግር ባሉባቸው አካባቢዎች ያሉ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ወደ አመቺ ማእከል አጓጉዞ ፣ የምግብ ወጪ ሸፍኖ፣ ቲቶሪያል ሰጥቶ፣ መዝገባ አከናውኖ ለማስፈተን እንደተዘጋጀ ገልጿል።

ሰፋ ያለ መረጃ በ Instant View ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/Tigray-Region-Education-Bureau-02-10

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

ትላንት ምሽት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ በትግራይ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተጨማሪ የ52 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቀዋል።

አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ከተፈጠረ አንስቶ ያደረገችው ድጋፍ 153 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።

ሚኒስትሩ አሁንም ቢሆን አሜሪካ በትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያሳስባት ገልፀዋል።

በስቴት ዲፐርትመንት በኩልን በወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ ተደራሽነት በማሳደግ የሰራቸውን ስራዎች አሜሪካ እውቅና እንደምትሰጥ ገልፃለች።

በመግለጫው ላይ ያለ ፖለቲካዊ መፍትሄ በትግራይ የሰብዓዊ ሁኔታው እየተባባሰ ሊቀጥል እንደሚችል ይገልፃል ፤ ግጭት ቆሞ በአስቸኳይ የኤርትራ ወታደሮች እና የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ያሰፈራቸውን የአማራ ክልል ኃይሎች እንዲነሱ ማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብሏል።

ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ግፎች በኢትዮጵያ መከላከያ ውስጥም ሆነ በህወሓት፣ በኤርትራ ኃይል ወይም በአማራ ክልል ኃይል ተጠያቂ አካል መኖር አለበት ይላል የስቴት ዲፓርትመት መግለጫ።

www.state.gov

ብሊንከን ከዚህ ቀደምም ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የአማራ ኃይል ይውጣ ሲሉ ማናገራቸው እና ፥ የአማራ ክልል መንግስትም ትግራይ ውስጥ እንደሌለ እና የአማራ ኃይል አሁን ያለበት ቦታ "በታሪክም የትግራይ እንዳልሆነ" ፤ የአማራ ኃይል ትግራይ ውስጥ አለ እየተባለ የሚገለፀውም ስህተት እንደሆነ የሚገልፅ ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በዚህ ጉዳይ ሉአላዊነትን የሚጋፋ ፣ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልጋ የመግባትና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል መግለጫ እንደሰጠበት ይታወሳል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

"... ወደ ትግራይ ክልል መድኃኒት ለማድረስ የሔዱ አሽከርካሪዎች እስካሁን አልተመለሱም ፤ ያሉበትንም ሁኔታ እናዉቅም" - ቤተሰቦቻቸዉ

ወደ ትግራይ መድሃኒት ለማድረድ የሄዱ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ አሽከርካሪዎች እስካሁን እንዳልተመለሱ እና ያሉበትን ሁኔታም እንደማያዉቁ ቤተሰቦቻቸዉ ለአሐዱ ሬድዮ ጣቢያ ገለፁ።

አሽከርካሪዎቹ ሰኔ 16/2013 መድኃኒት ጭነው ከአዲስ አበባ የተነሱ ሲሆን እሁድ ቀን አፋር ሰመራ ደርሰዉ እንደደወሉላቸዉ እና ሰኞ መቀሌ በሰላም መግባታቸዉን ተናግረዉ ከዛ በኋላ ግንኙነታቸዉ እንደተቋረጠ ቤተሰቦቻቸዉ ገልፀዋል።

አሽከርካሪዎቹ አራት ሲሆኑ የአራቱም ቤተሰቦች እስካሁን ድረስ ድምፃቸዉን ባለመስማታቸው በእጅጉ እንደተጨነቁ ተናግረው የሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሄደው ቢጠይቁም በቂ ምላሽ እንዳልተሰጣቸዉ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የስምሪት አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደምሴ ካሳ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ፥ አሽከርካሪዎችን ለመመለስ ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር እና ለሰላም ሚንስቴር ደብደቤ ፅፈዉ ምላሽ እየጠበቁ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አሐዱ ሬድዮ ጣቢያ

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Tigray

የትግራይ ክልል የተጠቃለለ ሪፖርት ፦

(ሰኔ 25 ቀን 2013 ዓ/ም)

• በትግራይ በግንኙነት መቋረጥ በቂ መረጃ ለመሰብሰብ አሁንም አሰቸጋሪ ቢሆንም የሳተላይት ስልክ የሚጠቀሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ዛሬም ለተከታታይ 5ኛ ቀን በመላ ትግራይ ፦

- ኔትዎርክ የለም /ማንኛውም የስልክ ግንኙነት አለም/
- የባንክ አገልግሎት የለም።
- የኤሌክትሪክ ኃይል የለም።
- ወደክልሉ የሚገባ ነዳጅም ሆነ የምግብ ግብዓት የለም።
- ገንዘብ እጥረት አጋጥሟል።

• UK የመንግስት በFCDO በኩል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ያወጀውም የተናጠል የሰብዓዊ ተኩስ አቁም በደስታ ተቀብሎ ሁሉም ወገኖች ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲያሳልፉ ብሏል።

• (UNHCR)/ፊሊፖ ግራንዲ የመቐለ እንዲሁም የሽረ አየር ማረፊያዎች ክፍት እንዲሆኑ መጠየቃቸው፤ የEU ጆሴፕ ቦሬል በተኩስ አቁሙ ላይ የሰጡት አስተያየት።

• የOCHA እና የWFP ሪፖርት.

• በፌዴራል መንግስት ህወሓት አውድሞታል ላለው የተከዜ ድልድይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለማቅረብ እና ለድልድዩ ጥበቃ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ማሳወቁ።

(ለቲክቫህ አባላት ከተቋማት፣ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ መገናኛ ብዙሃን ተሰብስቦ የቀረበ ዕለታዊ ሪፖርት)

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA