TIKVAH-ETHIO
702 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#ETHIOPIA

ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች አጥኚ እና ተመራማሪ ናቸው።

በተጨማሪ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፀጥታ ተቋማትን በፀጥታ አመራር ተጠያቂነት እና በብሄራዊ ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን የሰጡ ባለሞያ ናቸው።

በአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ሱማሊያ እና ኢትዮጵያ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የጥናት ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በዚህ ምክንያት ቀጠናውን በተለይ ውስብስቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመረዳት እድል የሰጣቸው ሰው ናቸው።

ከሰሞኑን ከቪኦኤ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ በተለይ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፕሮፌሰሯ ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና ለኢትዮጵያ ቀውስ በአብዛኛው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን በቃለምልልሳቸው ወቅት ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ ትርክትን ለመቆጣጠር የሚደረግ የመረጃ ጦርነት፣

- በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር፣

- የኢትዮጵያ አዲስ መንግስት ለሀገሪቱ የፖለቲካ መረጋጋት እና ለውጭ ግንኙነት ሊያመጣ ስለሚችለው ለውጥ፣

- በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እና በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በኩል ተፈፀመዋል ስላሉት የፖለቲካ ስሌት ስህተት፣

- አምና ጥቅምት ወር የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት (ሰሜን ዕዝ) ላይ ስለፈፀመው ጥቃትና ኢትዮጵያ መንግስት ስለወሰደው እርምጃ፣

- የሰሜኑ ጦርነት እና የማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃዎች ተፅእኖ ፣

- ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሁኔታ የክልል ልዩ ኃይሎች ያላቸው ድርሻ፣

- ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ እንድትወጣ ሊደረግ ስለሚገበው ጉዳይም ፕሮፌሰሯ አብራርተዋል።

ከሰሞኑን ቪኦኤ ከፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ በተጨማሪ የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺንን ቃለመጠይቅ ያደረገ ሲሆን እሳቸውም በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

መልካም ንባብ 👇
https://telegra.ph/VOA-10-21

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,292 የላብራቶሪ ምርመራ 620 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 512 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 14 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,762 የላብራቶሪ ምርመራ 441 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 528 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Ethiopia

የአሜሪካ ተ/ም/ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል።

ኮሚቴው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ሁከትና ሰብአዊ መብት ረገጣዎችን ያወገዘ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች ግጭት እንዲያቆሙ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ተደራሽነትን እንዲፈቅዱና ተዓማኒነት ያላቸው የግፍ እና ጭካኔ ድርጊቶች ክሶችን በተመለከተ ለገለልተኛ ምርመራዎች እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

የውሳኔ ሃሳቡ ከተላለፈ በኋላ ካረን ባስ ባወጡት መግለጫ፥ " እኔ ይህንን ውሳኔ የመራሁት በብሔር፣ በፖለቲካና በታሪክ የተወሳሰበ ለዚህ ሁለገብ ግጭት ሰላማዊ ፣ የድርድር መፍትሄ ማየት ስለምፈልግ ነው" ብለዋል።

ባስ እኤአ በጥቅምት 2020 የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ግጭቱ መጀመሩንና ግጭቱ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች መስፋቱን ገልፀዋል።

" H.Res 445 " የተሰኘው ይህ የውሳኔ ሃሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁከት እንዲቆም ፤ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በአስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ ይጠይቃል።

ከውሳኔ ሀሳቡ በተጨማሪ TPLF ህፃናትን ለውትድርና መጠቀም እንዲያቆም፤ ከአማራ ክልልም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ፤ ከOLA-ሸኔ ጋር ያለውን ጥምረት እንዲያቆም ተጠይቋል።

ባስ፥ የውሳኔ ሀሳቡ ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት እንዲኖር ሚጠይቅ በቀን ቢያንስ 100 የጭነት መኪናዎችን ወደትግራይ መላክ እንዳለበት የሚገልፅ ነው ብለዋል።

TPLF መራሾቹ ኃይሎች ጦርነት ለመቀጠል ሲሉ የጭነት መኪናዎችን ወይም የእርዳታ ዕቃዎችን ከመዝረፍ እንዲቆጠቡ እንደሚያሳስብም ተናግረዋል።

telegra.ph/US-HFAC-10-25

@ETHIO_TIKVHA
Pዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,815 የላብራቶሪ ምርመራ 472 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 510 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 16 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,578 የላብራቶሪ ምርመራ 386 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 486 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ “አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home Grown Economic Reform) ምሰሶዎች የሆኑትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሥራ ዕድል ፈጠራ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። 

በአዲስ አበባ ለ2 ቀናት በተካሄደው 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን መርሃግብር ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር አንዋር ሱሳ መሪነት በመገኘት የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል እድገት ለውጥ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው “ወደገበያ ለመግባት እየተዘጋጀንበት ባለበት በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገልን አበረታች ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ። በኢትይጵያ ድንቅ አቅም እንዳለ ተመልክተናል። ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎችን መስጠት እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲጂታል 2025 ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ስነምህዳር መገንባትን እንቀጥላለን” ብለዋል። 

ያንብቡ : https://telegra.ph/Safaricom-Ethiopia-10-28

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,753 የላብራቶሪ ምርመራ 478 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 435 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Ethiopia : የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ማብራሪያ መስጠታቸውን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማምሻውን ዘግቧል።

በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የከፈተውን ጦርነት እና ጦርነቱን እየመራበት ያለው ህዝባዊ አካሄድ አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፀው ቴሌቪዥን ጣቢያው ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ እንደነበር አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በቅስቀሳ የመጣውን የህዝብ ኃይል ለማስተናገድ በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት እንዳልነበር በዛሬው መድረክ የተናገሩ ሲሆን አሁን ላይ ከዛ ሁኔታ እርምት ተወስዶ ስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እየተሰራበት እንደሆነ መግለፃቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው ዘገባ ያስረዳል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,296 የላብራቶሪ ምርመራ 205 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 414 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,341 የላብራቶሪ ምርመራ 327 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 420 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ETHIOPIA

ማንኛውም የፀጥታ ችግር እንቅስቃሴ ሲመለከቱ ወይም ደግሞ ጥቆማ ለመስጠት ከፈለጉ ከላይ በተቀመጡት የስልክ መስመሮች ፈጥነው እንዲደውሉ የፌዴራል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#ሼር #Share

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA