TIKVAH-ETHIO
702 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#US #EU #USEmbassyAA

አሜሪካ በድጋሚ ተኩስ እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር ጠየቀች (ይህን ስትል በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛዋ ነው)

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት አሜሪካን እጅግ እንዳሳሰባት አሳውቀዋል።

ብሊንከን ጦርነቱ በስፋት መዛመቱ ሰብዓዊ ቀውሱን እንደሚያከፋው ጠቁመዋል።

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉም በመግለጫቸው ላይ አሳስበዋል።

ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነር ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ሁሉም ወገኖች ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን እንዲያቀላጥፉ እና የጥላቻ ንግግሮችን እንዲያቆሙም አሳስበዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ህብረቱ እምነቱን ገልጿል።

በሌላ መረጃ ፦

አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰሜን ኢትዬጵያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአማራ ክልል፤ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ግጭት ተባብሷል ብሏል። በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ካሉም ለመጠለል መዘጋጀት እንዳለባቸውና እነዚህን አካባቢዎች መልቀቅ ሊያስቡበት እንደሚገባ አብቆ አሳስቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA