2_4_4 premiere league ⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
931 subscribers
79 photos
1 video
4 links
I top up
Download Telegram
Forwarded from MADO NEWS
ማንኛውም ሰው የኢንሹራንስ ኩባንያ ባለቤት ወይም መሪ መሆን አይችልም— አዲሱ የብሔራዊ ባንክ መስፈርት

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያላቸውን ግለሰቦች (ባለአክሲዮኖችና አመራሮች) ብቃት ለመመዘን አዲስ መመሪያ (SIB/63/2026) አውጥቷል።

መመሪያው በዘርፉ "ተጽዕኖ ፈጣሪ" ለመባል የሚከተሉትን መስፈርቶች በዋናነት ያስቀምጣል፦

👉​የገንዘብ አቅም እና ታማኝነት፦ ግለሰቦች በገንዘብ ራሳቸውን የቻሉና በሕግ ፊት ንጹህ መሆን ይኖርባቸዋል።

👉​የሙያ ብቃት ፦ ተቋማቱን የመምራትና የማስተዳደር ክህሎት መኖር።

👉​የመልካም ስነ-ምግባር መለኪያ ፦ ለቦርድ አባላትና ለሥራ አስፈጻሚዎች ጥብቅ የምዘና መለኪያዎችን ይደነግጋል።

መመሪያው የኢንሹራንስ ዘርፉ በባለሙያዎች ብቻ እንዲመራና የደንበኞች እምነት እንዲጠበቅ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
የኢራን ምድር አንቀጥቅጥ የምድር ጦር

ኢራን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተዋጊዎችን ለጦርነት አሰለፈች

​በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ወታደራዊ ውጥረት ወደ ከፋ ደረጃ መሸጋገሩን ተከትሎ፣ ኢራን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተዋጊዎችን በተጠንቀቅ ማሰለፏን አስታወቀች። ሀገሪቱ ይህን ግዙፍ ሰራዊት ያሰለፈችው ከአሜሪካ ሊሰነዘርባት ይችላል ላለችው የምድር ወረራ ምላሽ ለመስጠት መሆኑ ተገልጿል።

​ይህ ስምሪት መደበኛ የጦር ኃይልን፣ ተጠባባቂዎችንና ያልተማከሉ ታጣቂዎችን ያካተተ ሲሆን፤ ኢራን ከአነስተኛ ግጭቶች ወጥታ ወደ ሙሉ የጦርነት ዝግጅት መሸጋገሯን ያሳያል። የቴህራን "የተደራራቢ መከላከያ" ስልት የአሜሪካን የቴክኖሎጂ የበላይነት በግዙፍ የሰው ኃይልና በመልክዓ-ምድራዊ ጠቀሜታ ለመመከት ያለመ ነው።

​ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ የምድር ላይ ጦርነት ከተጀመረ ቀውሱ ከመካከለኛው ምስራቅ አልፎ በመላው ዓለም ላይ ከፍተኛ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መናጋት ሊያስከትል እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
🚨 ትራምፕ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለ10 ቀናት እንዳቆሙ አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሉት፣ ከኢራን መንግሥት የቀረበላቸውን "ጥያቄ" መነሻ በማድረግ፣ በሀገሪቱ የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት እስከ መጋቢት 28 ድረስ ለተከታታይ 10 ቀናት እንዲቆም ወስነዋል።

💬 "የኢነርጂ ተቋማት የማውደም እርምጃን ለ10 ቀናት አግጃለሁ… ውይይቶች እየተካሄዱ ነው… ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡" ሲሉ በትሩዝ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

ከዚህ ቀደም፣ የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር ድርድር እያደረገ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
MADO NEWS
Photo
📰አጫጭር መረጃዎች

🇮🇷🇦🇪🇰🇼🇸🇦 በአቡ ዳቢ በተጠለፈ የኢራን ሚሳኤል ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሶስት ሰዎች ቆስለዋል፡፡ በርካታ ተሸከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ኩዌት የአየር መከላከያ ስርአታቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጥለፍ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

🇺🇸🇮🇷  የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን መሪዎች ከአሜሪካ ጋር እየተደራደርን ነው ለማለት ፈርተዋል ሲሉ ተናገሩ፡፡

🇴🇲  የኦማን ብሔራዊ አየር መንገድ በአየር ክልል መዘጋት ምክንያት ወደ ዱባይ፣ ዶሃ፣ ባህሬን እና ኩዌት የሚደረገው በረራ እስከ ሚያዚያ 15 ድረስ እንደሚቋረጥ አስታዉቋል፡፡ ነገር ግን ወደ ዮርዳኖስ አማን እና ወደ ሳዑዲ አረቢያ ደማም የሚደረጉ በረራዎች በሚያዝያ 1 ይቀጥላሉ ብሏል።

🇮🇷🇮🇱  በኢራን የሚሳኤል ጥቃት በማዕከላዊ እስራኤል ክፋር ቃሲም አምስት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ከሊባኖስ የተተኮሰ የሮኬቶች ማዕበል ምስል በክትትል ካሜራዎች የተቀረፀ በማዕከላዊ እስራኤል ሰማይ ላይ የሮኬት መጥለፍ ትዕይንቶችን አጋርተዋል፡፡

🇱🇧🇮🇱  ሄዝቦላህ በደቡብ ሊባኖስ 7 የእስራኤል ታንኮች ላይ ኢላማ አድርጌያለሁ ሲል ያስታወቀ ሲሆን የእስራኤል ጦር በበኩሉ በሊባኖስ ውስጥ የተጠናከረ የምድር ላይ ዘመቻን እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ሰራዊቱ ሂዝቦላህን ትጥቅ ለማስፈታት እና ከደቡብ ሊባኖስ የተወሰኑ ክፍሎች ለማስወጣት የገባውን ቃል ባለማሟላቱ ትችት ተሰንዝሮበታል፡፡የእስራኤል ጦር እስካሁን ከ2ሺ የሚበልጡ የሂዝቦላህ ኢላማዎችን በመምታት 700 ያህል ተዋጊዎችን ገድሏል፡፡

🇷🇺🇮🇷 ሩሲያ ከጦርነት በፊት ለኢራን መረጃ ትሰጥ ነበር ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የመከላከያ ዋና ጸሀፊ ጆን ሄሊ ተናግረዋል፡፡ሩሲያ የስለላ መረጃን እየተጋራች እና ለኢራን ስልጠና ትሰጥ ነበር።አክለውም “የፑቲን ስውር እጅ” በኢራን ውስጥ አለ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

🛢 የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡን የቀጠለ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ በበርሚል እስከ 104 ዶላር እየተሸጠ ይገኘኛል፡፡ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነዳጅ ዋጋ ከ40 በመቶ በላይ ጨምሯል፣ይህም በዋናነት በሆርሙዝ ባህር ዳርቻ መዘጋት የተነሳ የመርከብ እንቅስቃሴ በመታገዱ ነዉ፡፡

🇱🇧🇮🇱  በደቡባዊ ሊባኖስ በተደረገ ውጊያ አንድ የእስራኤል ወታደር መገደሉን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።ጦር ሰራዊቱ በቴሌግራም በሰጠው መግለጫ የጎላኒ ብርጌድ ወታደር የሆነ የ21 አመቱ ኦሪ ግሪንበርግ ተገድሏል ሲል ይፋ አድርጓል።

🇷🇺🇺🇸🇮🇱🇮🇷የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ቡሽህር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት መፈጸማቸዉን ተከትሎ ሆን ብለው የኒውክሌር አደጋ ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው ሲል ከሷል።ሞስኮ ጥቃቱን ተከትሎ በኢራን-ሩሲያ ከተገነባው ቦታ ተጨማሪ ሰራተኞችን ለማስወጣት ተገዳለች፡፡

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
ራፐሩ የኔፓል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ

​በኔፓል የቀድሞው ታዋቂ ራፐር እና የካትማንዱ ከንቲባ የነበሩት ባሌንድራ ሻህ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሃላ ፈጸሙ።

የ35 ዓመቱ ወጣት ኢንጂነርና ድምፃዊ፣ በሹመት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጥቁር ልብስና ጥቁር መነጽር አድርጎ በመቅረብ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

​የእሱ "ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ" ባለፈው መጋቢት ወር በተካሄደው ምርጫ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።

ይህ ድል የመጣው እ.ኤ.አ. በ2025 በወጣቶች በተመራውና "የጄነሬሽን ዜድ አብዮት" በተባለው ተቃውሞ የቀድሞው መንግሥት ከወደቀ በኋላ ነው።

ባሌንድራ ሻህ በበዓሉ ላይ ሕገ-መንግሥቱን ለማክበርና ግዴታውን በታማኝነት ለመወጣት ቃል ገብቷል።

ይህ ክስተት በኔፓል ፖለቲካ ውስጥ የወጣቶች የበላይነት የመጣበት አዲስ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
ሆርሙዝ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ‼️

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ሰርጥ ክፍት ነው የሚል የተሳሳተ መረጃ መስጠቱን ተከትሎ 3 የኮንቴይነር መርከቦች በሆርሙዝ ለማለፍ ሲሞክሩ እንዲመለሱ መደረጋቸውን የኢራን ሪፐብሊክ መከላከያ አስታወቀ።  የሆርሙዝ ባህር ዳርቻ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል፣ በሆርሙዝ ለማለፍ የሚሞክር ማንኛውም መርከብ ከባድ አደጋ ይገጥመዋል"ስትል ኢራን አስጠንቅቃለች።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ በከባድ የማታለል ወንጀል ተከሰሰ

​በአዲስ አበባ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዳንኤል ዮሐንስ፣ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

ዐቃቤ ሕግ እንደገለጸው፣ ተከሳሹ "ሄሎ ታክሲ" እና "ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" የተባሉ ድርጅቶችን በመጠቀም፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በዱቤ እናስረክባለን የሚል አሳሳች ማስታወቂያ በታዋቂ ግለሰቦች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች አስነግረዋል።

​ተከሳሹ ከ5 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎችን ለቅድመ ክፍያ እና ለምዝገባ በሚል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ካደረጉ በኋላ፣ መኪኖቹን ሳያስረክቡ ድርጅቱን ዘግተው መሰወራቸው በክሱ ተመልክቷል።

ድርጊቱ የ1996 ዓ.ም የወንጀል ሕግን እና የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን የጣሰ መሆኑ ተገልጿል።

​በተጨማሪም፣ ተከሳሹ ቀደም ሲል በኢንተርፖል ከተያዘ ግብረ-አበር ጋር በመሆን፣ የውሸት ርክክብ ቪዲዮዎችን በማሳየት እና "መኪናዎች በመጓጓዝ ላይ ናቸው" የሚል ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት 19 ተደራራቢ ወንጀሎችን መፈጸማቸው ተጠቅሷል።

ጉዳዩን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት እየተመለከተው ይገኛል።FMC

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
ጦርነቱ አድማሱን እያሰፋ ነው‼️

እስራኤል ከደቂቃዎች በፊት የኢራንን የውሃ ማመንጫ ተቋምን እና የኑክሌር ማመንጫ ሀይልን መታለች።
ኢራን በውሃ እጥረት የምትሰቃይ ሀገር መሆኗ ይታወቃል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢራን የብረታ ብረት ፋብሪካ በአሜሪካ እና እስራኤል በዛሬው ዕለት ወድሟል።
ኢራን ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ የጦር ቤዝ ያለባቸው የሁሉንም ሀገራትን የብረታ ብረት ፋብሪካ ላይ ጥቃት እንደምትፈፅም ዝታለች።
የአሜሪካ እና እስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው የቀጠናው ፋብሪካዎች ሰራተኞቻቸውን በአስቸኳይ እንዲያስወጡ ኢራን ትዕዛዝ አስተላልፋለች።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
አሜሪካ የFBI ዳይሬክተር 'ኢሜል' የሰበረውን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አቀረበች

​የኢራን ደጋፊ ነው የሚባለው "ሓንዳላ" የሃከሮች ቡድን የFBI ዳይሬክተር ካሽ ፓቴልን የግል የጂሜል አካውንት በመስበር የግል ፎቶዎቻቸውንና ከ300 በላይ ኢሜሎችን ይፋ አድርጓል።

​ጥቃቱን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ሃከሮቹ መረጃ ለሚሰጥ እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

FBI የተሰረቁት መረጃዎች የቆዩ መሆናቸውንና የመንግስት ምስጢር እንዳልተጋለጠ ቢገልጽም፣ ድርጊቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሳይበር ጦርነት አባብሶታል።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ በኩልም ከባድ ሰላማዊ ሰልፍ

በእስራኤል ከኢራን ጋር ያለውን ጦርነት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ


​በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት፣ በእስራኤል ዋና ዋና ከተሞች ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቁ መጠነ-ሰፊ ተቃውሞዎች ትናንት ተካሄዱ።

በቴል አቪቭ፣ በሃይፋ እና በኢየሩሳሌም በተደረጉ ሰልፎች ላይ ፖሊስ በወሰደው የኃይል እርምጃ ቢያንስ 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

​ሰልፈኞቹ “ሚሊዮን ህፃናት በቦምብ መጠለያ ውስጥ እያደጉ ነው” የሚሉ መፈክሮችን ያነገቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ግን ስብሰባዎቹ ከ50 ሰው በላይ በመሆናቸው “ህገ-ወጥ ናቸው” በሚል በትኗቸዋል።

በሃይፋ የፓርላማ አባል አይማን ኦዴህ ላይ የሃይል እርምጃ ተወስዷል። ቀደም ሲል በግራ ዘመም አክቲቪስቶች ብቻ ይደረግ የነበረው ተቃውሞ አሁን ላይ ሰፊው የህብረተሰብ ክፍል እየተቀላቀለው መሆኑ ተገልጿል።

​ [ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
10 ቀን ብቻ ቀረው‼️

የባንክ ሒሳብዎን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የማጣመሪያ ጊዜ መጋቢት 30 ፣ 2018 ይጠናቀቃል። ባሉበት ሆነው ከስር የተቀመጠውን ሊንክ ብቻ በመጠቀም አካውንታችሁን ማጣመር ትችላላችሁ።
የሁሉንም ባንኮች ማጣመሪያ ሊንክ ከስር አስቀምጠናል።

👉https://id.et/connect

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
ግብፅ በኢራን ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ የሚፈልጉ ፕሮጀክቶችን ለሁለት ወራት ያህል ልታቆም ነው

🇮🇷🛢 መንግሥስት በኢራን ጦርነት ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የኃይል ወጪ ተከትሎ ፍጆታን ለማመጣጠን ከፍተኛ ነዳጅ የሚጠይቁ ፕሮጀክቶችን ለሁለት ወራት ለማቆም አቅዷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞስጣፋ ማድቦው አስታውቀዋል።

👉 እንደ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ኩቾክ ገለጻ፤ የዕዳ ክፍያ ወጪ በሚቀጥለው የበጀት ዓመት በ5% እንደሚጨምር ተገምቷል።

[ @MadoNews ]
Forwarded from MADO NEWS
የተሳፈሩበት ዶልፊን ተሽከርካሪ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት ሴኖትራክ ላይ የተሳፈሩ 8 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በቄለም ወለጋ ዞን ሰዮ ደንታ ወረዳ አሸዋ የጫነ ገልባጭ ሴኖ ትራክ ላይ የተሳፈሩ ተጓዦች በደረሰባቸው የተሽከርካሪ መገልበጥ አደጋ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታወቋል።

የዞኑ ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሞቲ ጉዲሳ እንደተናገሩት መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓም 3:30   ከ20 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች ከደንቢ ዶሎ ከተማ ወደ አሺ ሙጌ ወረዳ በአንድ የሕዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲጓዙ ተሽከርካሪዎ መንገድ ላይ ነዳጅ በመጨረሱ የተነሳ ተሳፋሪዎቹ  አሸዋ የጫነ ሴኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ለመሳፈር ተገደዋል።

የተሳፈሩበት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-35460 ኢቲ የሆነው አሸዋ የጫነ ሴኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ፣ ነዳጅ ጨርሶ ከቆመው የሕዝብ ማመላለሻው ዶልፊን የወረዱትን ከሃያ በላይ ተጓዦች በጫነው አሸዋው ላይ አሳፍሮ ወደ ሙጊ ከተማ ሲጓዝ ደንታ ቀበሌ፣ አባ ጃራ  ቀረብቾ፣ የተባለ ስፍራ ሲደርስ በመገልበጡ ወዲያውኑ የስምንት ሰዎች ህይወት አልፋል።

በአደጋው  6 ወንዶች እና 2 ሴቶች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ ሁለቱ ሕፃናት ናቸው።በ 12 ሰዎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰ ሲሆን ከዚያ ውስጥ 7ወንዶች እና 5 ሴቶች እንደሆኑ ምክትል ኢንስፔክተር ሞቲ ጉዲሳ ጨምረው ተናግረዋል።

አደጋውን ያደረሰው የሴኖ ትራኩ የጭነት አሽከርካሪ ለግዜው ከህግ ቢሰወርም ክትትል እየተደረገበት ይገኛል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ደንቢ ዶሎ ከተማ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

[ @MadoNews ]