Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ
6.25K subscribers
5.06K photos
69 videos
30 files
2.38K links
ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡
በዚህ ገጽ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡
- የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡
ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMeslene
Download Telegram
🌻ከአባቶች አንደበት🌻
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
💧💧💧የዕለቱ "መልካም ዘር"

፩. ‹‹ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ፣ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከሆነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል ህይወትም የለውም››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፪. ‹‹ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል››
ማር ይስሐቅ

፫. ‹‹ጸሎት አእምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው ››
ማር ይስሐቅ

፬. ‹‹ጸሎት ጸጋን ይጠብቃል፣ቁጣንም ያሸንፋል ትዕቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል››
ከአባቶች

፭. ‹‹የመንፈስ ፍሬዎችን ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፮. ‹‹ጸሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግበት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፯. ‹‹በጸሎት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርክ አይደለምን??እንዴት ያለ መብት ነው!!!››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፰. ‹‹ጸሎትን ለማድረግ አታቅማማ፣ሥጋ ከመብል(ከምግብ) በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች››
አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ

#ሼር
@EMislene
@EMislene
@EMislene
🌿👉እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አለን!👈🍀
#የጌታችንና_የመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የልደት_በዓል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
++++++=====🌻🌼🍀🌻=====++++++
የአምላካችን የዐማኑኤል ዐመታዊ ክብረ በዓል ሲከበር እንዲሁም በደብራችን ሊከናወን የታቀደው ዘመናዊ ሁለገብ ሕንጻ የመሠረት ድንጋይም ማስቀመጥ በብጹዕ አባታችን በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡
#ዐማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር_ምስሌነ ማለት ነው፡፡ ትርጓሜውም #እግዚአብሔር_ከእኛ_ጋር_ሆነ ማለት ነው፡፡ ማቴ 1፡ 23
የዕለቱን ድባብ በምስል፡ -
ምስል ቀረጻ፡ በጳውሎስ ገብሩ
https://youtu.be/KfIi1EmPCAM
ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ.....
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››

@EMislene
📌
ጥር ፪
ዕለተ ሰንበት
ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ
🔖በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
📌

#እንዳይቀሩ! #ለሌሎችም ይጋብዙ
#ሼር
@EMislene
@EMislene
Audio
🔹 እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ🔹🌻 “ንሴብሖ” ዓምዳችን 🌻

💥የምስራች ደስ ይበለን

የምስራች ደስ ይበለን /2/
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን ምስራች ደስ ይበለን
የምስራች ደስ ይበለን /2/ ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን/2/
ንጉሥ ሔሮድስ ይህንሲሰማ/2/
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ/2/
ሰባ ሰገል እንደታዘዙት/2/
በኮከብ ተመርተው ህፃኑን አገኙት/2/
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው/2/
ወርቅና ዕጣኑን ከርቤውንም ሰተው/2/

====🔅===🍁===🔅===🍁====
#ሼር በማድረግ ብዙ ነፍሳት የእግዚአብሔርን ቃል
ይመገቡና ያመሰግኑ ዘንድ ይፍቀዱ!
#Share
#Share
👉 https://t.me/EMislene
👉 https://youtu.be/ARj1QE-ik38
====🔅===🍁===🔅===🍁====
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እርሷንም አውርዷት💥
ረቂቋ ቤተክርስቲያን!
በ Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.facebook.com/EMislene
"ኑ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ"
💥ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ
ኑ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ፤ ኑ በፀሎት ወደአምላክ ቅረቡ ፤ በፀሎት ማለት እንዴት ነው? ይህስ የልባችሁን ምስጢር ሁሉ ሳትደብቁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልጋችሁ መናገር ማለት ነው ፤ እንዲህም በሉ ፦ “ጌታ ሆይ ወደ አንተ መምጣት እፈልጋለሁ ፡ ጌታ ሆይ ካንተ ተለይቼ እኔ ምንም ነኝ ፡ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴን አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ደስታየን ሁሉ አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ትርጉም አልባ ሆነ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ጣእም አልባ ሆነ” በሉ ፤ ዳግምም ከእግዚአብሄር እግር ስር ተደፍታችሁ እንዲህ በሉት፦ “ አምላኬ ሆይ ፦ ወደ አንተ መመለስ እፈልጋለሁ ፤ ነገር ግን ጠላቶቼ ከእኔ በእጅጉ የሚበልጡ ናቸው ፤ ነፍሴንም አምላክሽ አያድኑሽም የሚሏት ብዙ ናቸው” ፡፡ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ፤ “ ጌታ ሆይ ታደገኝ ወደ አንተ የምመለስበትን መንገድ ምራኝ” በሉት ፤ ለአምላካችሁ ንገሩት ፦ “ካንተ ከተለየሁ ወዲህ አቅሜ ሁሉ ተዳክሟልና ጌታ ሆይ ልዩ ኃይልህን ላክልኝ ፡ ወዳንተ የምመለስበትን ልዩ ርዳታህን ስጠኝ ፤” በማለት፡፡ ብዙ ሰዎች በመደጋገም “ወደ እግዚአብሔር የምመለሰው እንዴት ነው ?” ይላሉ፡፡ ከእግዚአብሔር እግር በታች ራሳችሁን ጣሉ ፡ እንዲህም በሉት ፦ “ ጌታ ሆይ ሳትባርከኝ አልለቅህም ፡ ወዳንተ አቅርበኝ ፡ ከልጆችህ እንደአንዱ አድርገኝ ፡ ኃጢአቴን ብቻ ይቅር እንድትልልኝ አልሻም ፡ ይልቁንም ከኃጢአት ፍቅር ትለየኝ ዘንድ ጭምር እንጂ ፡”በሉት ፦ ዳግምም “ ጌታ ሆይ የኃጢአት ፍቅር ልቤን ተቆጣጥሮታልና ይህን ካላስወገድኩ ወዳንተ መቅረብ አይቻለኝም ፡ ጌታ ሆይ የኃጢአትን ፍቅር ከልቤ ላይ ንቀል ፡” በሉት ዳግምም እንዲህ በሉት ፦ ”ጌታ ሆይ ከኃጢአቴ ነፅቼ ወዳንተ መምጣት እንደምን ይቻለኛል? ይልቁንስ መጀመሪያ አንተ ናልኝ ኃጢአቴንም ደምስስ እንጂ “ እንዲህም በሉት ፦ “ በራሴማ ኃጢአትን ማስወገድ ብችል ወዳንተ መቼ መመለስ ያቅተኝ ነበር? እኔ ግን አንተ ኃሃጢአቴ እንድታርቀኝ እወዳለሁ ፡ ጌታ ሆይ ፦ ሃይልህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” በሉት፡፡
እመኑኝ የምወዳችሁ ልጆቼ ፦ ትክክለኛዋን ፀሎት ያወቃት እርሱ ትክክለኛዋንም ንስሃን የሚያውቅ እርሱ ነው ፤ ማር ይስሃቅ እንደተናገረው ፦ “ንስሃ ከፀሎት ውጭ እንደሚገኝ የሚያስብ ሰው እርሱ በዲያቢሎስ የተታለለ ነው” ምክንያቱም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱበትን ኃይልን ታገኛላችሁና፡፡ ስለሆነም ከየትኛውም ስራ ይልቅ ራሳችሁን ለፀሎት አስገድዱ ፤ ምክንያቱም በፀሎት አማካኝነት በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ግድግዳ አስወግዳችሁ እንደገና ወደእርሱ ትመለሱ ዘንድ ይቻላችሗልና ፤ በጣም ብዙ ሰወች ከፀሎት ይልቅ ለአገልግሎት መትጋታቸው የሚገርም ነው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በንባብ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በተመስጦ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በመንፈሳዊ ስብሰባዎች ለመታደም የሚተጉትም እንደዚያው ፤ ለዚህ እኮ ነው ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኙነት የማይሳካላቸው ፤ ይፀልያሉ ያነባሉ ደግሞም ስብሰባዎችን ይታደማሉ በዚህ ሁሉ ሰአት ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም ።
ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ፤ ወደእግዚአብሔር ተመለሱና ከእርሱ ውሰዱ ፤ አንዳንድ ሰዎች በመፀለይ ለእግዚአብሔር የሚሰጡት እንዳለ ያስባሉ ፡ ለእግዚአብሔር ቃላትን ይሰጡታል ፡ ጊዜን ፡ ምናልባትም ስሜታቸውን ፤ ነገር ግን ጥልቅ የሆነ ፀሎት ከእግዚአብሔር የመውሰድ ጉዳይ ነው ፤ እርሱ ሰጭ እንጂ ተቀባይ አይደለምና ፤ በፀሎቱ ስኬታማ ውጤትን የሚያመጣ ሰው እርሱ ከእግዚአብሔር ስለሚወስደው የፀለየና እንደዚያም የሚያምን ነው ፤ እርሱ ነው በፀሎቱ የተሳካለት፡፡ በምትፀልዩበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ኃይልን እንደተቀበላችሁ ከተሰማችሁ ፡ ያን ጊዜ ውጤታማ ፀሎት ፀለያችሁ ፤ አንድ ሰው ፀልዮ ከእግዚአብሔር በረከት ከተቀበለ፡ እንግዲህ ይህ ሰው ነው ውጤታማ ፀሎት ያቀረበው ፤ ማንም በፀሎት በፀፀትና በንስሃ ወደእግዚአብሄር ቢቀርብ እርሱ ውጤታማ ፀሎትን አቀረበ ፤ አንድ ሰው ቢፀልይና ለቅድስና ቢታገል ፡ ይህ ሰው ፀሎቱ ውጤታማ ሆነ ፤ አንድ ሰው ቢፀልይና ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ቢያጠናክር ይሄኔ ውጤታማ ፀሎትን አቀረበ፡፡
እግዚአብሔር እንድትመጡ ይናገራችሗል ፡ በፀሎት ኑና የሚያስፈልጋችሁን ልስጣችሁ እያለ ፤ ነገር ግን እናንተ ለሁለት ደቂቃ ብቻ ትፅልዩና ወዲያው ትሰለቻላችሁ ፡ ከእግዚአብሔርም አንዳች ሳትቀበሉ ትኄዳላችሁ ፤ እግዚአብሔር ወደእናንተ ያይና እንዲህ ይላል ፦ “ስለምን ከእኔ ሳትቀበሉ ተመለሳችሁ? የሚያስፈልጋችሁን ልሰጣችሁ ወድጄ ነበርና ፤ ስለምን ቶሎ ተመለሳችሁ ያዘጋጀሁላችሁን ሳትወስዱ?” እያለ ፤ ነገር ግን እናንተ ቶሎ ሰለቻችሁና ለመሄድ ወሰናችሁ ፤ እሺ ሂዱ ፡ ከዚያ ግን እግዚአብሔርን መፈለግ ትጀምራላችሁ አታገኙትም ፤ ጥላችሁ ስትሄዱ ያጣችሁት ምንም ሳትይዙ መሄዳችሁን ብቻ እንዳይመስላችሁ በልባችሁ ለእግዚአብሔር ጊዜ እንደሰጣችሁት ማሰባችሁም ጭምር እንጂ ፤ ወዲያውም ከመንፈሳዊ የስኬት ድርጊቶች ውስጥ መፀለያችሁን ትፅፋላችሁ፡፡
@EMislene
ይህ ግን ፀሎት አይደለም!!! ከእግዚአብሔር ከቶ ምን አገኛችሁ? እግዚአብሔርን አጥብቃችሁ ልትይዙት ይገባል አጥብቃችሁ መቼም ቢሆን ካንተ አልለይም መለየትም አልፈልግም ማለት አለባችሁ፡፡ ስለዚህ እኮ ነው ለፀሎት ትእግስት የሚያስፈልገው፤ ያለትእግስት ከእግዚአብሔር አንዳች እንኳን ልትቀበሉ አትችሉም፤ በፀሎታችሁ ትእግስተኞች ልትሆኑ ይገባችሗል፤ እግዚአብሔርን ንገሩት፦ ከእግርህ በታች እንደሆንኩ እቆያለሁ በረከትህንም ሳትሰጠኝ አልነቃነቅም ከእግዚአብሄር በረከትን ካልተቀበልኩ እርሱን መያዜን አልለቅም ካልባረከኝ አልለቅህም እይዘዋለሁ ወዴትም ይሄድ ዘንድ አልተወውም፤ እንግዲህ ይህ ነው በፀሎት ውስጥ ያለው ትግል፤ ሰዎች ፀሎት እንዴት እንደሚፀለይ አልተማሩም እነርሱ የሚያስቡት ፀሎት ማለት ጥቂት ቃላትን መናገር ይመስላቸዋል አይደለም፡፡
ፀሎትን አዘውትሩ፡- ከእግዚአብሔርም አንዳች እስክትቀበሉ ድረስ ታገሉ ፤ አንዳች እንኳን ካልወሰዳችሁ ሳትቀበሉ የትም እንደማትሄዱ ንገሩት ፀሎቴን አልገታም በሉት እንደተፃፈ አንተ ሩህሩህ መሃሪ አምላክ ነህ የለመነውን ሁሉ የምትሰጥ ነህና እንግዲህ እኔም ለምኜሃለሁ እስከምትሰጠኝ ድረስ ወዴትም አልሄድም በሉት፤ በፀሎታችሁ ከእግዚአብሄር ጋር ታገሉ ያን ጊዜ ታርፋላችሁ በፍቅር ትሞላላችሁ በፀሎታችሁም ብርቱ ትሆናላችሁ ከንቱ ነገርንም መደጋገም ትተዋላችሁ እንዲያውም ልባችሁን በእግዚአብሔር ፊት ትዘረጋላችሁ፤ የሳሙኤል እናት ሃና በፀሎቷ ጊዜ ታለቅስ ነበር በልቧም ልጅ እንደምታገኝ ቃል ሳይገባላት ከቤተመቅደሱ ላለመውጣት ወስና ነበር ፤ ንጉስ ዳዊት ከእግዚአብሔር በረከትን እስኪቀበል ድረስ ፀሎቱን አላቋረጠም በመጀመሪያ “ጌታ ሆይ ፦ አስጨናቂዎቼ ምንኛ በዙ” በማለት ፀለየ፤ ቀጥሎም እንዲህ አለ ፦ “ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ራቁ እግዚአብሔር ፀሎቴን ሰምቶልኛልና ፡ ጌታዬ የልመናዬን ድምፅ አድምጧልና ጌታዬ ፀሎቴን ሰምቷልና“፡፡ ኑ ወደእግዚአብሔር ተመለሱ፡፡

@EMislene @EMislene @EMislene