Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ
6.4K subscribers
5.2K photos
69 videos
30 files
2.42K links
ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡
በዚህ ገጽ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡
- የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡
ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMeslene
Download Telegram
🌷🌹🥀🌺🌸🌷🌹🥀🪷🌺
📷የሁለተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል።

http://youtube.com/@EMislene

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ
(መሰባሰባችን እግዚአብሔር ምስሌነን  አንተው!)
🌷🌹🥀🌺🌸🌷🌹🥀🪷🌺
ኃጥአን ጥቅም የሚያገኙት ከቅዱሳን ጋር ሲገኙ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ "ኖኅ ጻድቅ፣ ፍጹም ነበር "ብቻ አላለም፤ በትውልዱ የሚል ጨመረ እንጂ ዘፍ. ፮ ÷፱ ። በዚያ ክፉ እና በተበላሸ ትውልድ መካከል ጻድቅ ሆኖ ተገኘ። ደጋጎቹ ከክፉዎች ጋር በመኖራቸው ያገኙት ጥቅም ይሄ ነው፤ ማለትም ከክፉዎች ጋር ጻድቃን ሆነው በመገኘታቸው በሌሊት በሰማይ ላይ እንደሚያበሩ ከዋክብት ሆኑ። ዛፍ እንኳ በነፋስ ወዲያ እና ወዲህ ሲወዛወዝ ይጠነክራል።

ክፉዎችም ከደጋጎች ጋር ተቀላቅለው በመኖራቸው ይጠቀማሉ። ደጋጎችን ሲያዩ በኃጢአታቸው ያፍራሉ ፤ ይሳቀቃሉ። የመዋረድ ሥሜት ይሰማቸዋል። ከኃጢአት ባይታቀቡም እንኳ በሥውር የሚያደርጉትን በአደባባይ ለማድረግ አይደፍሩም። ኃጢአት እና ነውረኛ ነገር በአደባባይ በግልጥ አለማድረጉም ቀላል ነገር አይደለም። የሌሎቹ መልካም ሕይወት የእነዚህን ክፋት ወቃሽ፣ ምሥክር እና ዳኛ ይኾንባቸዋልና። በደጋግ ሰዎች መኖር ምክንያት በኃጢአት መሳቀቅ እና ራስን መውቀስ ቀላል የማይባል ራስን የመለወጥ የመጀመርያ ደረጃ ነው። በእነርሱ መኖር በሕሊና መሳቀቅ በኃጢአት ከመደሰት እና ከመኩራራት፣ ኃጢአታዊ ምኞትን ሁሉ በዘፈቀደ ከመከተል እንደ ልጓም ያዝ ያደርጋል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

http://youtube.com/@EMislene
የኢትዮጵያ ታላቁ ሀብት ስለሆነው ባህረ ሀሳብ ያውቃሉ

ባህረ ሀሳብ የግእዝ ቃል ሲሆን ከሁለት ቃላት የተወሰደ ነው። ባህር ማለት ዘመን፤ሀሳብ ማለት ደግሞ ቁጥር ማለት ነው። ባህረ ሀሳብ ማለት የዘመን አቆጣጠር ነው። ባህረ ሀሳብን "የጻፈው ማን ነው?" ቢሉ የመንበረ እስክንድርያ ፲፪ኛ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ድሜጥሮስ ነው። ይህ ቅዱስ አባት ቤተክርስቲያን በዘመነ ሐዲስ የምትመራበትን የአጽዋማትና የበዓላትን ቀመር ባህረ ሀሳብን የሠራ ነው።

ድሜጥሮስ ማለት መስታወት ማለት ነው፡፡ ድሜጥሮስ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ትምህርት ባይኖረው ሕገ እግዚአብሔርን አክብሮ የሚኖር ስለነበር በዚህ ቅድስናው ምክንያት መልአከ እግዚአብሔር ለ፲፩ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ዩልያኖስ ተገልጦ በነገረው መሰረት ድሜጥሮስ ፲፪ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ በመንበረ ማርቆስ ተሾሟል፡፡

ኢትዮጵያ የራሷ የዘመን አቆጣጠር እንዲኖራት ያደርገችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናት።ይህ ባህረ ሀሳብ ያለፉትን ዓመታት፣ አሁን ያሉበትን፣ወደፊት እስከ ምጽአት የሚመጡትን አጽዋማት እና በዓላት ለማወቅ ይረዳል።

ቅዱስ ድሜጥሮስ (ከ፻፹ – ፪፻፳፪ ዓ.ም.) በመንበረ እስክንድርያ ላይ ቆይቷል፡፡ ይህም ቅዱስ አባት ቤተክርስቲያን በዘመነ ሐዲስ የምትመራበትን የአጽዋማትና የበዓላትን ቀመር ባህረ ሀሳብን የሠራ ነው፡፡ በተጨማሪም በዘመኑ ብዙ ድርሰቶችን መጽሐፎችን ጽፏል፡፡

በዚህ የዘመን አቆጣጠር ውስጥ የዘመነ ብሉይና የዘመነ ሐዲስ ድምር በጠቅላላው ዓመተ ዓለም ይባላል፡፡

         አዕዋድ:
አዕዋድ የሚለው ቃል ኦደ ከሚል ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ዞረ ማለት ነው፡፡ አዕዋድ ማለት ደግሞ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዞሮ የሚመጣ ማለት ነው፡፡ አዕዋድያት የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም

       ዓውደ ዕለት፡- ከሰኞ እስከ እሑድ ያሉ ቀናት ሲሆኑ እነዚህ ቀናት በየሳምንቱ ተመላልሰው የሚመጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሳምንታት እየተመላለሱ ወራትን ያዋቅራሉ፡፡

        ዓውደ ወርኀ፡-ይህ በሠላሳ ቀን በየወሩ እየተመላለሰ ዓውደ ዓመትን ይሰራል፡፡

        ዓውደ ዓመት፡- በፀሐይ ፫፻፷፭ ቀናት በጨረቃ ፫፻፶፬ ቀን ነው።

         ዓውደ አበቅቴ (ንኡስ ቀመር)፡- ዐሥራ ዘጠኝ ሲሆን በየ፲፱ ዓመቱ ዞሮ የሚመጣ ነው፡፡ ፀሐይና ጨረቃ ተራክቦ የሚያደርጉበት ወቅት ነው፡፡

  ዓውደ ፀሐይ፡- ሃያ ስምንት ዓመት ሲሆን በየ፳፰ ዓመቱ ተመላልሶ የሚመጣ ነው፡፡

  ዓውደ ማኅተም (ማዕከላዊ ቀመር)፡- ሰባ ስድስት ዓመት ነው፡፡ በ፸፮ ዓመት አንድ ጊዜ አበቅቴው እና ወንጌላዊው ይገናኙበታል፡፡

   ዓውደ ዐበይ ቀመር (ዐቢይ ቀመር)፡- አምስት መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ነው፡፡ ዕለት፣ ወንጌላዊ እና አበቅቴ ይገናኙበታል፡፡

        
  በዚህም መሠረት የ2017 ዓ.ም. አጽዋማት መቼ እንደሚውሉ እንግለፅ:-
# ጾመ ነነዌ : የካቲት ፫
# ዐቢይ ጾም: የካቲት ፲፯
# ደብረ ዘይት ፦መጋቢት ፲፬
# ሆሳዕና ፦ሚያዝያ ፭
# ስቅለት ፦ሚያዚያ ፲
# ትንሣኤ ፦ሚያዝያ ፲፪
# ርክበ ካህናት ፦ግንቦት ፮
# ዕርገት ፦ግንቦት ፳፩
# ጰራቅሊጦስ ፦ሰኔ ፩
# ጾመ ሐዋርያት ፦ሰኔ ፪
# ጾመ ድኅነት ፦ሰኔ ፬

http://youtube.com/@EMislene
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን!

ጥቅምት ፭/ ፳፻፲፯ ዓ.ም.

የደብረ ከዋክብት ዝቋላ ጉዞ

በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት አዘጋጅነት ጥቅምት 5  ቀን በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ  ወደ ደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የጋራ ጉዞ ተከናውኗል።

 በዚህ ጉዞ ላይ ለበዓሉ የሄዱ ምዕመናንን ለበዓሉ ይዞ የተጓዘው መኪና አባታችን። አማኑኤል ክብር ይግባውና በዓሉን አክብረው በዛሬው ዕለት በሰላም ይዞ ተመልሷል። የዓመት ሰው ይበለን!ከጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከት ያሳትፈን!
  

"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

http://youtube.com/@EMislene
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን

ለድኩማን ጽንእ ለጽኑዓን ኃይል የሆነ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ያይደል ከልደቱ እስከ ዕርገቱ በነብያት አንደበት ትንቢት አስነግሯል። በጊዜ ኦሪት ነብያት በትንቢት መነጽር ያዩትን አምላክ ሐዋርያት በአካል ዳስሰውታል። እስራኤል ዘሥጋ(አይሁድ) ከግዞት ነፃ ያወጣቸው ዘንድ ውረድ፣ ተወለድ እያሉ በተስፋ የጠበቁትን መሲሕ ሐዋርያት ለእስራኤል ዘነፍስ(ምዕመናን) ከሰይጣን ባርነት ነፃ ሊያወጣቸው በማህፀነ ማርያም መፀነሱን በቤተልሔም መወለዱን ተርከውታል።

ከእግረ መምህራቸው ሳይለዩ ከተጠሩበት ዕለት ጀምረው ሲታዘዙ ምስጢር አልተገለጸላቸውምና ሲጠራጠሩ ጌታችንም ዳግም በአምላካዊ ፍቅሩ ልጆቼ እያለ የልባቸውን እምነት እያፀና የመንግሥትን ወንጌል አስተምሯቸዋል። የእውነት መንፈስ(ጰራቅሊጦስ) ከወረደላቸው በኋላ ፍሩኀን የነበሩት ጥቡዓን፣ ደካሞች የነበሩት ብርቱዎች ሆነው ሐዋርያዊ ሥራቸውን ጀምረዋል። የክርስቶስን ወንጌል እያስተማሩ፣ እረኞች ይሆኗቸው ዘንድ መምህራንን በአንብሮተ እድ በንፍሐት እየሾሙ ቃለ እግዚአብሔርን በዓለም ሁሉ ላይ አዳርሰዋል።

ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከአሣ አጥማጅነት፥ ቅዱስ ማቴዎስን ከቀራጭነት ሌሎች ንዑዳን የሆኑ ሐዋርያትን ከልዩ ልዩ ግብራት ጠርቶ የወንጌልን ዘር እንዲዘሩ ወደ ዓለም ልኳቸዋል። ወደ ተራራም ወጣና የወደዳቸውን ጠራ፥ ወደ እርሱም መጡ። ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክም ይልካቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለቱን መርጦ ሐዋርያት አላቸው። አጋንንትንም ሊያወጡ፥ ድውያንንም እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሰጣቸው። በየስማቸውም ጠራቸው፤ ስምዖንን ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስንም ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፣ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው። እንድርያስንና ፊልጶስን፣ በርተሎሜውስንና ማቴዎስንም ቶማስንና የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንና ቀነናዊውን ስምዖንንም፣ አሳልፎ የሰጠውን የአስቆሮቱን ይሁዳንም" ማር ፫፥፲፫።

"ከመዝ መሐሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ" እያለች ዕለት ተዕለት በቅዳሴዋ የምትጠራቸው እድፈት፣ የፊት መጨማደድ የሌለባት፣ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን ነገርን ከስሩ ውኃን ከጥሩ ነውና፤ እምነቷ፣ ትምህርቷና ቅዱስ ትውፊቷ ሐዋርያዊ እንደሆነ በአፋ ታስተምራለች። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን በላከው መልእክቱ ይህን ሲያጸና "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋልና የሕንጻው የማዕዘን ራስ ድንጋይም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" ኤፌ ፪÷፳ እንዳለ ቅድስት ቤተክርስቲያን የሲኦል ደጆች የማይነቀንቋት ራሷ ክርስቶስ የሆነ በሐዋርያት መሠረትነት የቆመች ጽኑ ዐለት ነች።

ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ እንዲህ ይላል " ቅድስት ቤተክርስቲያን በሃይማኖት መስቀል ላይ የተመሠረተች ናት፤ መሠረቷም ፅኑ ነው። በግራዋ እና በቀኟ ዋናተኞች ያጅቧታል። ከምትንሳፈፍበት ባህር አልፋ ወደ መርሶ መድኃኒት እስክትደርስ ድረስም ከእርሷ አይርቁም። የባህር ምሳሌ ዓለም ነው። በነፋስ፣ በመዋግድና በማዕበል የተመሰሉት ደግሞ ጠንቋዮችና ሌሎችም ናቸው። እነሱ ዓለምን የሚያውኩ ናቸው።"  (በዚኽም ቅድስት ቤተክርስቲያን በጀልባ የምትመሰል ሲሆን ዋናተኞች የሚለው ነቢያትን ያመለክታል። ይኽም ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካል ያልተጨበጠች ስለመሆኗና አንዳንዶቹ ዋናተኞች ዳር ሲደርሱ፣ ሌሎች ደግሞ በድካም ውሃ ውስጥ ጠልቀው ስለሚገቡና ነቢያትም ድካማቸው ጀልባዋ ጋር መድረስ የነበረ ቢሆንም ሳይደርሱባት በሞት ስለመቀደማቸው ነው። በተጨማሪም ሐዋርያት፤ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስለተሳፈሩባትና ዓለምን ስለተሻገሩባት ከማዕበል ውጪ ስጋት በሌለባቸው ጀልባ ቀዛፊዎች ይመሰላሉ። ) መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ
  

ምንጭ ፡ መጽሐፍ ቅዱስ
              መጽሐፈ ቅዳሴ
             መጽሐፈ ቀለሜንጦስ

http://youtube.com/@EMislene
ሽጡኝና ክፈሉ!

ድኾችን እጅግ የሚወድ፣ የተቸገሩትን ለመርዳት ምንም ነገር የማያግደው፣ ከእራሱም አብልጦ ለሌሎችን የሚሞት አንድ ሰው ነበረ ይባላል፡፡ ይህ ሰው በበጎ ምግባሩ የተነሣ ስሙ ተረስቶ "እኁ ቅዱስ" (ቅዱሱ ወንድም) እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ በታሪክ ድርሳናትም የተመዘገበው በዚሁ ስም ነው፡፡ ሠርቶ የሚያገኘውን ምንም ለሌላቸውና ለምነው እንኳን ለማግኘት ዐቅም ላነሣቸው በመስጠት የታወቀ ነበር፡፡
አንድ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አጣ፡፡ ብዙ ችግረኞች ደግሞ መልካም ዜናውን ሰምተው ጥቂት ነገር ለማግኘት ወደ እርሱ ዘንድ መጡ፡፡ ምን ይስጣቸው? የሚያያቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ ብዙዎቹ ገንዘቡን ከጨረሰ በኋላ ከሩቅ ሀገር ሳይቀር በመምጣታቸው አዘኑ፡፡ መመለሻ እንኳን የላቸውም ነበር፡፡ በመጨረሻ እኁ-ቅዱስ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ "እኔን ሽጡኝና ተካፈሉ" አላቸው፡፡ እነዚያ ችግረኞችም ምንም አማራጭ ስላልነበራቸው እርሱን በባርነት ሸጡትና ገንዘቡን ተካፈሉ፡፡

ይህ ታሪክ በታሪክነቱ ሲወሳ የኖረ ነው፡፡ በእኛ ዘመን ግን ተደገመ። በአባ መፍቅሬ ሰብእ።

ይህ ሳምንት በግሸን ደብረ ከርቤ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የኖሩት አባ መፍቀሬ ሰብእ ኪዳነ ወልድ በ96 ዓመታቸው ማግሰኞ  ምሽት ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ሰማን። ለዛሬ ስለ እኚህ አባታችን ከዓመታት በፊት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የቀረበና  ያነበብነውን ልናካፍላችሁ ወደድን።

እኚህ ሰው የትውልድ ቦታቸው ወሎ እንዳልሆነ በቅርበት የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ ምናልባት ወደ ሰሜን ሸዋ አካባቢ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ እስካሁን ግን የተወለዱበትን ቦታና ዘመን በርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡ እርሳቸውም ሃይማኖታቸውንና ምግባራቸውን እንጂ ሰው ትውልዳቸውንና ጎሳቸውን እንዲጠይቃቸውም እንዲያውቅላቸውም አይፈልጉም፡፡ ከድሮ ጀምሮ የሚያውቋቸው የደሴ ከተማ ሽማግሌዎች ግን እርሳቸውን ያወቁበትን ጊዜ በማሰብ ግምት ይሰጣሉ። ወደ ጎንደር ለትምህርት ሲሄዱ ደሴ ደረሱ አሉ፡፡ እዚያ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተጎዱ ሰዎችን አዩ፡፡ እዚህ በተግባር የሚሠራ ሥራ እያለ እዚያ የቃል ትምህርት ለመማር ምን ወሰደኝ ብለው እዚያው ደሴ ቀሩ፡፡
እኒህ ሰው የሚታወቁት በሥራና በፍቅር ነው፡፡ በደሴ ከተማ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት በማሳነጽ፣ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር አሻራ አኑረዋል፡፡ የተቸገረና የተጨነቀ ሰው ካገኙ ግንባር ቀደም ደራሽ ናቸው፡፡ ለእርሳቸው ዘርና ሃይማኖት ሰውን ለመርዳት መመዘኛዎች አይደሉም፡፡ ሰውነት ብቻ ይበቃቸዋል፡፡ ይህ እርዳታቸው ከመከራ ያወጣቸው፣ ከችግር የታደጋቸውና ሕይወታቸውን ያቀናላቸው ሰዎች ስለ እኒህ አባት ሲያወሩ ከማያቋርጥ ዕንባ ጋር ነው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም ከንግግር ይልቅ እርሳቸውን እያሰቡ ዝም ብለው በማልቀስ ይገልጧቸዋል፡፡

የእኒህን አባት ስም የሚያውቀው የለም፡፡ ስማቸው ተረስቷል፡፡ ስማቸው የተረሳው ሕዝብ ሌላ የፍቅር ስም ስላወጣላቸው ነው፡፡ ሕዝብ የንቀት ስም፣ የውርደት ስም፣ የሃፍረት ስም ይሰጣል፤ ለጠላው፡፡ ሕዝብ የፍቅር ስም፣ የክብር ስም፣ የቁልምጫ ስም ይሰጣል፤ ላፈቀረው፡፡ ለእርሳቸውም ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም የሚያስረሳ ስም ሰጥቷቸዋል፡፡ መፍቀሬ ሰብእ (ሰውን የሚወድድ፣ ሰውም የሚወደው) የሚል ስም፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብ ይባላሉ፡፡

ድፍን ደሴ ይታዘዛቸዋል፡፡ ንጽሕናቸውንና ሰው ወዳጅ መሆናቸውን ይመሰክርላቸዋል፡፡ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም እኩል ልጃቸው ነው፡፡ የግሸንን መንገድ ሲያሠሩ በደሴ ከተማ የታወቁት የሙስሊም ባለሀብት "ሃምሳ ሺ ብር ሰጡኝ" ብለው ነግረውኛል፡፡ ቤታቸው ብትገቡ ትደነቃላችሁ፡፡ ወንበርና አልጋ ነው ያላቸው፡፡ አልጋው ላይ መጻሕፍት በክብር ተደርድረዋል፡፡ "አልጋ ለንጉሥ ነው፤ ነገሥታቱ ደግሞ መጻሕፍቱ ናቸው፡፡ አልጋው ላይ የሚኖሩት እነርሱ ናቸው" ይላሉ፡፡ ሰው ለሀገሩና ለወገኑ መልካም ሲሠራ ካዩ የለበሱትንም ካባ ቢሆን አውልቀው ይሸልማሉ፡፡ ስለ እርሳቸው ሲነገር አይወዱም እንጂ ስለ መልካም ሰዎች ተናግረው አይጠግቡም፡፡

አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡፡
የደሴ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጀመረና ለመጨረስ ገንዘብ አጠረ፡፡ ወዲህ ቢባል ወዲያ፣ ገንዘብ ከየት ይምጣ? የደብሩ አስተዳዳሪ አውጥተው፣ አውርደው አንድ ዐሳብ አመጡ፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብ እንደ እኁ-ቅዱስ መሸጥ አለባቸው፡፡ ሄዱና አማከሯቸው፡፡ "አባ! እርስዎን ሸጠን የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ልንጨርስ ነው" አሏቸው፡፡ "እኔ ምን አወጣላችኋለሁ?" አሉ፤ ገርሟቸው፡፡ "በደንብ ያወጣሉ፡፡ ብቻ ለመሸጥ ይስማሙልን!" አሏቸው፡፡ "ካወጣሁ፣ እንኳን እንድ ጊዜ፣ ዐሥር ጊዜ ልሸጥ። አሉ አባ መፍቀሬ ሰብ፡፡

በእርሳቸው ስም የርሳቸው ፎቶና ስም ያለበት ቶምቦላ ተዘጋጀ፡፡ ድፍን ደሴ፣ ሙስሊም ከክርስቲያኑ ተሻምቶ ገዛው፡፡ መፍቀሬ ሰብእ አይደሉ፡፡ ያልተሰበሰበውን ጨምሮ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሸጡ፣ አባ መፍቀሬ ሰብ፡፡ ሌሎቹ የሀገር ሀብት፣ ቅርስና ታሪክ በሚሸጡበት ዘመን አባ መፍቀሬ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን፣ ለእምነታቸውና ለዓላማቸው ሸጡ፡፡ ሌሎች በቤተ እምነቶች ውስጥ ተደብቀው ለጥቅማቸው ሲሉ የምእመናንን ገንዘብ በሚበሉበት ዘመን ለምእመናን ሲሉ አባ መፍቀሬ ሰብ ተሸጡ፡፡ ሌሎች በጎቻቸውን ለራሳቸው ሲሸጡ አባ መፍቀሬ ሰብእ ግን ለበጎች ሲሉ ራሳቸውን ሸጡ፡፡ እልም ባለ በረሃ ውስጥ የምትገኝ ቀዝቃዛ ምንጭ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ እንድታረካ፣ ታማኝነትና ሕዝብን መውደድ፣ በዓላማ መኖርና ለዓላማ መሠዋት እየጠፋ ባለበት ዘመን፣ እርሳቸውን ማየት እንደዚያ ነው፡፡

ነፍስ ኄር

http://youtube.com/@EMislene
🌼መንፈሳዊ ጉባዔ🌼

በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ለማኅበራት የሚዘጋጅ
የአንድነት መንፈሳዊ  ጉባዔ

📆 ጥቅምት 10, 2017 ዓ.ም.
⌚️  ከቀኑ 6:00 እስከ 8:00

የት ነው የሚከናወነው?
    => በጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ

((በዚህ ሰማያዊ ማዕድ ላይ በአንድነቱ ውስጥ የምትሳተፉም ሆነ የማትሳተፉ ማኅበራት ተጋብዛችኋል::))

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ!

የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

📜መልካም ዜና ተከታታይ ትምህርት ተምራችሁ ላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ

        በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት

📝 የ2017 ዓ.ም. የተምሮ ማስተማር ትምህርት ምዝገባ ተጀመረ።

የምዝገባ ቦታ እና ሰዓት

👉 በሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ቢሮ ከምሽቱ 12:00 - 2:00
   
👉 ለምዝገባ ሲመጡ የሦስተኛ ዓመት ትምህርት ያጠናቀቁበት ማስረጃ ይዘው መምጣት አይርሱ!

📌ከዚህ ቀደም በየትኛውም ዓመት በሰ/ት/ ቤታችንም ሆነ በሌሎች ሰ/ት/ቤቶች የተከታታይ ትምህርት /ኮርስ/ ያጠናቀቁ  ተማሪዎች ይህንን ትምህርት መውሰድ ይችላሉ ። 


💥 ትምህርቱ ማግሰኞ ጥቅምት 12/ 2017 ዓ.ም. ይጀምራል።

http://www.debregelila.org
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እንኳን ለዘመነ ጽጌ 3ኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።

በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ሳምንት የጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።

🌸 እንኳን አደረሳችሁ🌸

🏡ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷