Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ
6.41K subscribers
5.2K photos
69 videos
30 files
2.42K links
ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡
በዚህ ገጽ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡
- የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡
ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMeslene
Download Telegram
እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::
#ሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ
አባቱ ዘብድዮስ እናቱ ደግሞ ማርያም ባውፍልያ ይባላሉ፡፡እናቱ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ነበረች፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ #ስሞች ያሉት ሐዋርያ ነው፡፡እነርሱም፡-
¤ ወንጌላዊ
¤ ሐዋርያ
¤ ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤ አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ ፍቁረ እግዚእ
¤ ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ ቁጹረ ገጽ
¤ ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ ንስር ሠራሪ
¤ ልዑለ ስብከት
¤ ምድራዊው መልዐክ
¤ ዓምደ ብርሃን
¤ ሐዋርያ ትንቢት
¤ ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ ኮከበ ከዋክብት
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
===🔅===🍁===🔅===🍁===
#ሼር
👉 https://t.me/EMislene
👉 https://youtu.be/ARj1QE-ik38
===🔅===🍁
🌻“ፈለግ” ዐምድ ፠፠፠ቅዱስ አዉስግንዮስ አረጋዊ ፠፠፠
በጥር ፭ በዚህ ዕለት የቅዱስ አዉስግንቀስ መታሰቢያ በዓሉ ይህ ቅዱስ አባት በሃይማኖቱ ጽናት በምግባሩ ብዛት ለወጣቶች አብነት መሆን የቻለ አባት ነዉ።በብዛት የሚታወቀዉ በሰማዕትነቱም ቢሆንም በቅዱስ ሰዉነቱ በርካታ መልካም ነገሮች ሠርቷል።በአራተኛው መቶ ክፋለ ዘመን መነሻ አከባቢ(የሰማዕትነት ማቢቂያ አከባቢ )የቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የንጉሱ ወታደር ሆኖ ተቀጠረ።ንጉሱ ወደ መክሲማኖስ ለጦርነት ሲሄድ በሰማይ ላይ መስቀልና"ኒኮስጣጣን" የሚል ፁሑፉ ተመልክቷል።ሁሉም ሰዉ ለመተርጎም ሲፈራ ወጣቱ አዉስግንዮስ በድፍረት ለንጉሱ ክብረ መስቀልና ትርጉም አስረዳ።በቅዱሱ ንጉስ ስርም በወታደርነት ለሃያ አመታት አገለገለ።ከዚያም ሥጋዊ ተግባሩን ትቶ በጾምናበፀሎት ሰዎችም በማስታረቅ በማስተማር ተወሰነ ።ፈጣሪ በረከቱን አብዝቶለትም እድሜዉ መቶ አስር አመት ደረሰ።በግዜዉም የነበረዉ ከሃዲዉ ዑልያኖስ "ሰዎችን አስታርቀሃልና ክርስቶስን አምልከሃልና"በሚል በዚህች ቀን አሰይፎታል።ዑልያኖስን ደግሞ ቅዱስ መርቆሪዮዎስ ተበቅሎቀታል አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን ከበረከታቸዉም ይክፈለን።ጎበዞች ሆይ ብርቱ ስለሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉዉንም ስላሸነፋቹ እጽፋላችኋለሁ ፩ዮሐ ፪:፩፫-፩፬። ወስብሐት ለእግዚአብሔር! @EMislene
https://youtu.be/ARj1QE-ik38
''ደጋግመህ ኃጢያት ብትሰራ ደጋግመህ ንሥኃ ግባ ቤተክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችም..''
✍️ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @EMislene @EMislene @EMislene
((ጥር 06))
💡
#እውነትን ፍለጋ🔎 ዓምዳችን
💥💥💥💥💥
…… ክፍል 2 የቀጠለ .......
(#6). በገነት ውስጥ ስንት ዓይነት ዛፎች ነበሩ?
#መልስ
በገነት ውስጥ ሶስት ዓይነት ዛፎች ነበሩ፡-
ሀ. #ዕፀ መብል፡- እንዲበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ ነው፡
ለ. #ዕፀ በለስ፡- እንዳይበሉት የታዘዙት ነው፡፡
ሐ. #ዕፀ ሕይወት፡- እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቢመገቡት የዘላለም
ሕይወት የሚሠጥ ምግብ ነው፡፡ ሕግን ጠብቀው በገነት ውስጥ 1000 ዓመት ከኖሩ በኋላ ዕፀ ሕይወትን በልተው ከገነት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም (መንግሥተ ሰማያት) እንዲገቡም ለበለጠ ክብርና ፀጋ ሽልማት እንዲሆናቸው ነበር። ግን ያለጊዜው ሳቱ እንጂ።
+ዕፀ በለስን እንዳይበሉ የታዘዙበት ሕግ: አዳም ፈጣሪ እንዳለው የሚያውቅበት፣ ለፈጣሪ ያለውን ፍቅር የሚገልፅበትና ተገዥነቱን የሚያሳይበት ነው፡፡
(#7). እግዚአብሔር ሔዋንን ከአዳም ከጎኑ አጥንት ለምን ፈጠራት? ከግባር ወይም ከእግር ለምን አልፈጠራትም?
#መልስ
+አዳም ለእንስሳት፣ ለሰማይ ወፎች እና ለምድር አራዊት ሁሉ ተባዕትና አንስት ሆነው ሲመጡ ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ለአዳም እንደ እራሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ‘ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት’ አለ፡፡ ዘፍ 2÷18 ከዚያም በአዳም ላይ እንቅልፍ አመጣበትና ፈጽሞ ሳይተኛ ፈጽሞ ሳይነቃ ከጎኑ አጥንት አንስቶ ያቺን ሥጋ አልብሶ የ15 ዓመት ቆንጆ አድርጎ ፈጠራት፡፡ (ዘፍ 2፥18)
አዳምም ስሟንም ሔዋን አላት ሔዋን ማለት ‹ሐይወ› ካለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው፡፡
+ፈጽሞ ሳይተኛ ፈጽሞ ሳይነቃ ሔዋንን መፍጠሩ፡-
-ፈጽሞ ተኝቶ ቢሆን ኖሮ ምትሐት መስሎት ከየት መጣች ብሎ በፈራት ነበር፡፡
-ፈጽሞ ነቅቶ ቢሆን ኖሮ ከአካሉ አጥንት ሲነሣበት ያመው ነበርና በጠላት ነበር፡፡
+ከፍ አድርጎ ከግንባር ዝቅ አድርጎ ከእግር ያልፈጠራት ከጎድን ለምን ፈጠራት?፡-
-ግባርና እግር በልብስ አይሸፈንም ጎድን ግን በልብስ ይሸፈናልና ተሰውራ (ተሸፍና) መኖር ይገባታል ሲል ነው፡፡
-በሌላ በኩልም ግንባር የባለቤት እግር የቤተሰብ ምሳሌ ነው፡፡ እርሷም ከባለቤቷ በታች ከቤተሰብ በላይ ሁና ትኑር ሲል ነው፡፡(1ኛ ቆሮ 12፥19-22)
-እንዲህ አድርጎ አዳምና ሔዋንን እስከ 40 ቀን ድረስ በተፈጠሩበት በማዕከለ ምድር በቀራንዮ አሰነበታቸው፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበትን ቦታ ነውና፡፡ ከዛም በ40ኛው ቀን አዳምን ብርሃን አልብሰው ብርሃን አጎናጽፈው የብርሃን ዘውድ አቀናጅተውት በብርሃን ሰረግላ አስቀምጠውት ወደ ገነት ወደ ገነት አስገቧት፡፡(ኩፋ 4፥12-15)
-አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር የባሕርይ ደግነት የተነሳ እርሱን ለማመስገንና ክብሩን ለመውረስ ተፈጠሩ፡፡ ኩፋሌ 4÷3-5
-እግዚአብሔር ለአዳም ረዳት የፈጠረለት ስለ ሦስት ነገሮች ሲል ነው፡-
👉🏽 ዘርን ለማብዛት፣
👉🏽 ከዝሙት እንዲጠበቅና
👉🏽 ረዳት እንድትሆነው፡፡
(#8). አዳምና ሄዋንን በእባቢቱ ላይ አድሮ ያሳተቸው ሰይጣን ስም ማን ይባላል?
።።።#መልስ።።።
+አዳም በሳጥናኤል ተተክቶ መቶኛ ሆኖ ከመላእክት ጋር ተቆጥሮ ነበር፡፡በዚህ ምክንያት ሰይጣን በእባብ አድሮ አሳሳታቸው ፀጋቸውም ተገፈፈ፤ አዳምና ሄዋንን በእባቢቱ ላይ አድሮ ያሳተቸው ሰይጣን ስም # ጋርድኤል ይባላል፡፡ በመሆኑም አትብሉ የተባሉትን ዕፀ በለስን በሉ፤ ሕጉን አፈረሱ፤ ከገነትም ተባረሩ፡፡ ዘፍ 3 ÷ 1፤ ዘፍ 3 ÷ 22-24 ፡፡ #9. አዳምና ሔዋን ስንት ልጆች ነበሯቸው?
#መልስ
+ከገነት ከተባረሩ በኃላ በደብር ቅዱስ ይኖሩ ነበር፡፡ አዳምና ሔዋን በሰሩት ኃጢአት በመፀፀታቸውና በንስሐ በመመለሳቸው እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም 5 ቀን ተኩል ወይም 5500 ዘመን ሲፈፀም ሰው ሆኖ በመወለድ እንደሚያድናቸው ቃልኪዳን ገባላቸው ዘፍ 3÷15-22 ፡፡ አዳም ግን የራሱን ደም በስንዴ ለውሶ ቢሰዋ ጌታችን በአንተ ደም አይደለም ዓለም የሚድነው በእኔ እንጂ ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡ +አዳምና ሔዋን በምድር ላይ ዘርን ተክተዋል፤ ሚካኤል ፤ ገብርኤል፤ ሩፋኤል ወርቅ፤ ዕጣን፤ ከርቤ አምጥተው ለአዳም ሲሰጡት ወርቁን ማጫ ይሁንሽ ብሎ ሰጣት ከዛም አዳምና ሄዋን በ30 ሩካቤ 60 ልጆችን ወልደዋል፡፡
#10. አዳም በተፈጠረ በስንት ዓመቱ አረፈ?
#መልስ
አዳም በተፈጠረ በ 930 ዓመቱ አረፈ፡፡ አዳም ለሄዋን የሰጣትን ወርቅ ለሴት ሰጠችው ሴትም ለኖህ አስተላለፈው እጣኑንም ኖህ አጽመ አደምን እያጠነ ድኖበታል፡፡
+አዳም በስሙ በሀገራችን የተሰሩት ቤተ ክርስቲያኖች ብዛት 5 ናቸው፡፡
+በአዳም ስም የተቀረፀውን ታቦት ከሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያመጣው ጻድቅ አባ መልአከ እግዚአብሔር ይባላሉ እንዲከበርም ያደረገው ቅዱስና ሊቁ ያሬድ ማህሌታይ ነው፡፡
የዛሬው “እውነትን ፍለጋ” ፈጸምን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
====🔅===🍁===🔅===🍁====
#ሼር
#Share
👉 https://t.me/EMislene
👉 https://youtu.be/ARj1QE-ik38
====🔅===🍁===🔅===🍁====
🌼እንኳን ለ #ጥር_፯_ቅድስት_ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🌼
ነገረ ሥላሴን በበዓል ለመመስከር እና የቸርነቱ፣ የምህረቱ ተካፋይ ለመሆን በዓለ ንግሥም ይከናወናል፡፡ በይበልጥም ሐምሌ 7 ቀን ለአብርሃም በድንኳን ደጃፍ መገለጡን እና ጥር 7 በባቢሎን በሰናዖር የተፈጸመውን ተአምር በማሰብ እናከብራለን፡፡ ዘፍ.18 ዘፍ.11.1-9
በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍት እንደተመዘገበው ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡ በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ› ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡ አለቃቸው ናምሩድ ይባላል ‹‹ ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ ›› አላቸው ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ….›› ይሉ ጀመር ቅድስት ሥላሴ ምንም እንኳ ምህረታቸው የበዛ ቢሆንም በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸው እና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ›› በማለት ቋንቋቸውን ለያዩባቸው የማይግባቡ፣ የማይደማመጡ…… ሆነው ተበታትነዋል፡፡ ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ይህን ያደረጉ ሥላሴ በመሆናቸው በዓሉ ጥር 7 ይከበራል፡፡
በአጠቃላይ ሥልጣን ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑን እና በራስ ደካማ አመለካከት በመታበይ በሥላሴ ሥራ መግባት’ መጠራጠር ….. እንደሚጎዳ እንደዚሁም በጽኑ እምነት በመኖር እና በሥላሴ ስም የተጠመቅን ልጅነታችንን በኃጢአት ሳናሳድፍ በንስሐ ታጥበን እና በምግባር ጸንተን መጠበቅ እንደሚገባ የበዓሉ መልእክት ያስገነዝበናል፡፡ የታማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ እንደሚል ፡፡ ኤፌ. 4÷30
ሰላም ለአእዳዊክሙ እለ ፀሐፋ ኦሪተ
አመ ፆመ ሙሴ አርብዓ መዓልተ
ሥሉስ ቅዱስ ዘትለብሱ ስብሐተ
ከመ አዝነምክሙ በሰዶም እሳተ
በዲበ ፀርየ አዝንሙ መቅሰፍተ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
====🔅===🍁===🔅===🍁====
#ሼር
#Share
👉 https://t.me/EMislene
👉 https://youtu.be/ARj1QE-ik38
====🔅===🍁===🔅===🍁====
🌻💧እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!💧🌻

ለጥምቀት በዓል ከአገልጋዮች ጋር በሕብረት በዝማሬ ያመሰግኑ ዘንድ! መዝሙሮች ይኸው ለእናንተ አዘጋጅተናል፡፡

#አብረን _ተሰብስበን_እያጠናን ግጥሙን እና ዜማውን እየተራዳን እንድናመሰግን ይሁን!

#ከ10 በላይ መዝሙራት አብረን እናጥና፤ እናመስግን!!!

#ዝማሬያችንን ይቀበልልን!
#ሌሎችም_እንዲያገኙ_እናጋራው
#Subscribe
#Share
#Like
#እናድርግ እንዲሁም እናስደርግ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/U5zSEH5wrs8
✥፩✥ -
የከተራ እና የጥምቀት በዓል ዝግጅት!
ጃቴ ኪዳነ ምህረት በአብነት አደባባይ!


https://youtu.be/U5zSEH5wrs8
✥፪✥ -
የከተራ እና የጥምቀት በዓል ዝግጅት!
ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል - በደብረ አሚን አደባባይ!

https://youtu.be/U5zSEH5wrs8
✥ ፫ ✥
የከተራ እና የጥምቀት በዓል ዝግጅት!
ቅዱስ ላሊበላ ከአንድ ፍልፍል ካነፃቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል #ቤተ_ጊዮርጊስ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ

https://youtu.be/U5zSEH5wrs8
🍀 * አንድ ሰው ናችሁ * 🍀
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በዮርዳኖስ ወንዝ ነው፡፡ የዮርዳኖስ ምንጭ ከላይ አንድ ሲሆን ለሁለት ይከፈልና ዝቅብሎ አንድ ይሆናል፡፡ ጌታችን ከመገናኛው ተጠምቆአል ይህም ሕዝብና አህዛብ በጥምቀቱ አንድ እንደሆኑ ያስረዳል፡፡ በጌታ ጥምቀት ሕዝብና አህዛብ አንድ እንደሆኑ «ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና አይሁዳዊ፣ ግሪካዊ፣ ባሪያ፣ ጨዋ፣ ወንድ፣ ሴት የለም ሁላችሁም በክርስቶስ አንድ ሰው ናችሁ» በማለት የሰው ዘር ልዩነት በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉ ተወግዶ ሰው እኩል መሆኑን እና በጥምቀት አንድ ሰው መሆኑን አስረድቶአል፡፡ ገላ. 3፡27፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስስለ ሰው ልጆች ድኅነት ከዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ያደረገውን አምላካዊ ጉዞ ለማሰብ ታቦታቱ በካህናትና በምእመናን ታጅበው ወደባህረ ጥምቀት ተጉዘው አምሳለ ዮርዳኖስ በሆነውናበተዘጋጀላቸው ስፍራ ያርፋሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ በማኅሌትና በቅዳሴ በዓሉ እየተከበረ ያድርል፡፡ ጧት የበረከት ጥምቀት ከተፈጸመ በኋላ በደማቅና በልዩ ልዩ ሥነ ሥርዐት በስብሐተ እግዚአብሔር በዓሉ ይከበራል፡፡ ታቦታቱም በማኅሌትና በእልልታ ታጅበው ወደ መንበራቸው ይመለሳሉ፡፡
ይህ ዕለት ነጻ የወጣንበት የዕዳ ደብዳቤያችንን የተደመሰሰበት ከ እግዚአብሔር ጋር አንድ የሆንበት ዕለት ስለሆነ ልዩ በሆነ ደስታ እናከብረዋለን፡፡ ይህንን ታላቅ በዓል በምናከብርበት ጊዜ በክርስቶስ የተደመሰሰው ኃጢአትን አስወግደን እንደ ልብሳችን ልባችንን በንስሐ አጥበን ንጹሐን ሆነን ፈቃደ ሥጋችንን ለፈቃደ ነፍሳችን አስገዝተን እግዚአብሔር ን ከሚያሳዝን ከኃጢአት፣ ከተንኰል፣ ከዘረሕነት፣ወዘተ ሁሉ ርቀን ለነፍሳችን በሚጠቅም በፍፁም መንፈሳዊ ሥርዓት በዓሉን ልናከብር ይገባናል፡፡
ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡አሜን፡፡
💧ወስብሐት ለእግዚአብሔር
====🔅===🍁===🔅===🍁====
#Share
#Like
#Subscribe
👉 https://t.me/EMislene
👉 https://youtu.be/ARj1QE-ik38
====🔅===🍁===🔅===🍁====
የከተራ በዓል ከደብረ ገሊላ
በከፊል ይህ ይመስላል!

እግዚአብሔር ይመስገን!

በድጋሚ መልካም በዓል!
@EMislene