ELA TECH💡
195K subscribers
1.29K photos
28 videos
410 files
1.02K links
👋 ሰላም ሰላም እንኳን ወደ ELA TECH በሰላም መጡ

ለማንኛዉም ጥያቄ , አስተያየት እንዲሁም ሀሳብ
በዚ ያገኙናል
👇
@ELA_TECHBOT

በ Youtube ጠቃሚ ቪዲዮችን ለማግኘት የ YOUTUBE ቻናላችንን ይጎብኙ
👇
https://youtube.com/@ELA_TECH
Download Telegram
የጃፓን ስማርት መጸዳጃ ቤቶች!

🔻የጃፓን ስማርት መጸዳጃ ቤቶች አሁን ላይ የጤና ክትትል ማድረጊያ ጭምር ሆነዋል ተብሏል፡፡

🔻ሰዎች ለመጸዳዳት ሲቀመጡ የሽንትና ሰገራ ምርመራ ያደርጋሉ፡፡ ምርመራ ማድረግ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ውጤቱንም ለባለቤቱ ይልካሉ፡፡ ላብራቶሪ ልትሏቸው ትችላላችሁ፡፡

🔻በጃፓን የተሰሩት አዲሶቹ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች የሰገራ ቅርጽን፣ ቀለምንና ኬሚስትሪን የሚመረምሩ ሲሆን፤ ከዚያም ሙሉ የጤና ሪፖርት በቀጥታ ወደ ባለቤቱ የእጅ ስልክ እንደሚልኩ ተጠቁሟል፡፡

🔻ስማርት መጸዳጃ ቤቶቹ የሽንት ምርመራም ያደርጋሉ፤ የምርመራውንም ውጤት በተመሳሳይ መንገድ ያሳውቃሉ፡፡

🔻መጸዳጃ ቤቶቹ በአርቲፊሻል አስተውሎት፣ ሴንሰሮችና የሽንት መመርመሪያ የተገጠመላቸው ናቸው ተብሏል፡፡

🔻እንግዲህ ከዚህ በኋላ ሰዎች ወደ መታጠቢያ ክፍል የሚገቡት ለመጸዳዳት ብቻ አይደለም፤ የጤና ምርመራ ጭምር ለማድረግ ጭምር እንጂ፡፡
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
9😁7👍4👏3
ሳፋሪኮም እና ፔይፓል ኤምፔሳን ከአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ጋር ለማስተሳሰር ተስማሙ

🔻ሳፋሪኮም ከፔይፓል ጋር በመሆን ኤምፔሳን በፔይፓል አለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ውስጥ ለማካተት አጋር ሲሆን በአጋርነቱ መሰረት 35 ሚሊየን የኤምፔሳ ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

🔻በአጋርነቱ መሰረትም ተጠቃሚዎች የፔይፓል አካውንታቸውን ከኤም ፔሳ ጋር በማስተሳሰር የገንዘብ ዝውውሮችን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል።

🔻ለጊዜው አገልግሎቱ በኬንያ በሚገኙ ተጠቃሚዎች ላይ የሚጀመር ሲሆን በሂደት ኤም ፔሳ ወደሚሰራበቸው ሌሎች አካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል።

🔻ሳፋሪኮም በኤምፔሳ ሱፐር አፑ ሰዎች በቀጥታ ከፔይፓል ገንዘብ ማውጣት እንዲችሉ የሚያስችል አማራጭንም አካቷል።

🔻ሰዎች በቀጥታ የፔይፓል ገንዘባቸውን ከኤምፔሳ ማውጣታቸው በተለያየ መንገድ የሰሩትን ገንዘብ ሳይንዛዛ በቀጥታ እንዲያወጡ ያስችላል።

🔻በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ሁለቱን አካውንቶች በማስተሳሰር በቀላሉ የገንዘብ ዝውውሮችን መፈፀም ይችላሉ ተብሏል።

🔻ኤም ፔሳ በአፍሪካ ቀዳሚው የሞባይል ገንዘብ መተግበሪያ እንደሆነ ሲዘገብ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን በማፍራት በየዕለቱ ከ1.1 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ዝውውሮችንም ያሳልጣል።

🔻ፔይፓል በአለም አቀፍ ደረጃ ከ400 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ሲኖሩት በተለይ ለኦንላይን ስራዎች ዋነኛ የክፍያ አማራጭ ሆኗል።

🔻በኬንያ በሚገኘው ኤምፔሳ የሚጀምረው አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያም እንደሚመጣ ሲጠበቅ በርካታ ወጣቶች በኦንላይን ስራዎች ያገኙትን ገንዘብ በቀላሉ እንዲያወጡ ያስችላል።

Source: Tech Point, Tech Africa
══════❁✿❁═══════                                                                           
👍126🔥3
Microsoft ከnvidia ቀጥሎ 4 Triilion የገበያ ዋጋ ሊደርስ ቻለ


ብዙዎቻቹ የምታዉቁት Microsoft የተባለዉ ካምፖኒ የገበያ ዋጋዉ (Market cap) ከትናንት ወድያ 4 Trillion dollar ሊደርስ ችሏል ፣ ይሄም ከNvidia ቀጥሎ የገበያ ዋጋዉ 4 Trillion Dollar ሊደርስ የቻለ ካምፖኒ ያደረገዉ ሲሆን የካምፖኒዉ የገበያ ዋጋ እዚህ ደረጃ ሊደርስ የቻለበት ዋነኛ ምክንያት Microsoft ሰራተኞቹን በመቀነሱ እና በAI ላይ Invest በማድረጉ ነዉ

                     ELA TECH                 
🖱ELATECH GROUP    ELATECH BOT 🖱 
👍2
ህንድ ቻይናን በመብለጥ ስማርት ስልክን ወደ አሜሪካ Export በማድረግ አንደኛ ልትሆን ቻለች


የተለያዩ የስልክ ብራንዶች የሚመረቱባት ሀገር የሆነችዉ ህንድ ስማርት ስልክን ወደ አሜሪካ Export በማድረግ ላይ ከቻይና ልትበልጥ ቻለች ፣ ይሄም የሆነበት ዋና ምክንያት አፕል በህንድ ዉስጥ IPhone ስልኮች ይበልጥ እንዲመረቱ በማስፋፋታቸዉ እና አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችዉ Import Tarrif ዋነኛዎቹ ምክንያት ሲሆኑ ይሄንንም ተከትሎ ስማርት ስልክም በህንድ ዉስጥ ዋነኛ Export የሚደረግ እቃ አድርጎታል

                     ELA TECH                 
🖱ELATECH GROUP    ELATECH BOT 🖱 
👍91
Breaking

🇨🇳Cryptocurrency trading, mining, and related services are now officially banned in China.

🇨🇳 ቻይና Cryptocurrency እና ግንኙነት ያላቸውን አገልግሎቶች ይፋዊ በሆነ መልኩ አግዳለች።

@smart_cryptos1
@smart_cryptos1
👍3👏1
☑️ሁላችንም ስለ Blockchain ሰምተናል 👌ግን ይህ Techinology እያደገ ባለው ልክ ዕያወቅን አደለም
ለዚህም እናንተን ውድ ሜምበሮቻችንን ለማስተማር አዲስ channal ከፍተናል👍

📌ይሄን channal የከፈትነው ሁላችንም  ስለ Block Chain Techinology እንድናቅ እና ለሚመጣው cryptocurrency አለም ዝግጁ እንድንሆን  ነው

ወደድንም ጠላንም crypto የሂወታችን አንድ አካል መሆኑ አይቀርም

ስለ Crypto ብቻ የምንለቅበት አዲስ ቻናል ተቀላቀሉን👍👍

@smart_cryptos1
@smart_cryptos1
1 ቢሊዮን ዶላር አልቀበልም ያለው ሳይንቲስት

🔻የMeta መስራች Mark Zuckerberg አለም ላይ ያሉ የAI ሳይንቲስቶችን በከፍተኛ ዋጋ እየቀጠረ እንደሆነ ይታወቃል።

🔻ከሰሞኑ እንደተሰማው ግን አውስትራሊያዊው የAI ሊቅ Andrew Tulloch 1.5 ቢሊዮን ዶላርና ሌሎች ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች  የሚያስገኝለትን የMeta እንቅጠርህ ጥያቄ እንደማይቀበል ይፋ አድርጓል።

🔻Tulloch በአሁኑ ሰዐት 12 ቢሊዮን ዋጋ ያለው Thinking Machine የተሰኘ የAI startup ሪሰርቸርና co-founder እንደሆነ ተነግሯል።

🔻Tulloch እ.ኤ.አ. በ2023 ወደ OpenAI ከመዛወሩ በፊት በፌስቡክ የAI የምርምር ቡድን ውስጥ 11 ዓመታትን አገልግሏል።

🔻የቀድሞ የፌስቡክ ስራ አስፈፃሚ ማይክ ቬርናል “ Tulloch ባለምጡቅ አዕምሮ ወጣት ነው” ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል።

🔻ከሲድኒ ዩኒቨርሲቲ ከሳይንስ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የተመረቀ ሲሆን በሂሳብ የዩኒቨርሲቲውን ሜዳሊያ ተሸልሟል።

🔻Mark Zuckerberg በግል የWhatsApp አካውንቱ አለም ላይ አሉ የተባሉ የAI ሳይንቲስቶችን በከፍተኛ ክፍያ እሱ ጋር እንዲሰሩ እያግባባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

🔻ዙከርበርግ 50 የሚሆኑ የAI ሪሰርቸሮችንና ኤክስፐርቶችን በማሰባሰብ superintelligence lab ለማቋቋም እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል።

©️
bighabesha_softwares
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
3
ሩሲያ በኤ.አይ የታገዘ ካንሰርን መከላከል የሚያስችል ክትባት ማግኘቷን ይፋ አደረገች::

🔻ክትባቱ የተመረተው በሩሲያ ጋማሌያ ብሔራዊ የወረርሽኝ ጥናት እና ማይክሮባዮሎጂ የምርምር ማዕከል ነው። የካንሰር መከላከያ ክትባቱ በተራቀቁ የኤ.አይ ስልተቀመሮች አማካኝነት የካንሰር እጢዎችን የዘረመል ዳታ በመተንተን ይመረታል።

🔻የእያንዳንዱን ታማሚ ዘረመል (DNA) መሰረት በማድረግ የሚዘጋጀው ክትባቱ የታማሚውን የመከላከል አቅም በማሳደግ ካንሰሩ በታማሚው ሰውነት በፍጥነት እንዳይሰራጭ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ ከዘረመል ጥናት እስከ ክትባት ማምረት ያለው ሂደት በአማካኝ የአንድ ሳምንት ጊዜ እንደሚፈጅ ተገልጿል። 

🔻ክትባቱ በእንስሳት ላይ በተደረጉ የቅድመ-ህክምና ሙከራዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጨውን የካንሰር እጢ እድገትን በመቆጣጠር ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አሳይቷል።

🔻የካንሰር ክትባቱ እ.አ.አ. በ2025 መስከረም ወር ላይ ለካንሰር ታማሚዎች ሊሰጥ ይችላል መባሉን ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
👍52
በነሐሴ 2016፣ከ 9 አመት በፊት

ቢትፊኔክስ፣ በሆንግ ኮንግ የተመሰረተ ትልቅ የክሪፕቶ ልውውጥ፣ በታሪኩ ውስጥ ከፍተኛ ጥቃት  ገጥሞት ነበር

📌ሃከሮች 119,756 ቢትኮይን ሰረቁ፣ በወቅቱ ወደ 72 ሚሊዮን ዶላር የሆነ ዋጋ ያለው ሲሆን

በ2025 የቢትኮይን ዋጋ መጨመር ምክንያት ከ7 ቢሊዮን🫣 ዶላር በላይ ዋጋ ነበረው


@smart_cryptos1
@smart_cryptos1
🤯31😁1
ኦፕንኤ.አይ ኩባንያ አዲሱን ጂ.ፒ.ቲ-5 (GPT-5) ሞዴል ቻትቦት አስተዋወቀ፡፡

🔻የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን አዲሱን ሞዴል የፒ.ኤች.ዲ ደረጃ እውቀትን የያዘ ሲል አሞግሶታል፡፡

🔻ቻትቦቱ ሙሉ ሶፍትዌር ለመፍጠር ከማስቻሉ በተጨማሪ ከቀደምት የኩባንያው ምርቶች በተሻለ ከተጠቃሚዎች ለሚቀርብለት ጥያቄ የስራ ሂደቶችን፣ አመክንዮ እና ግንዛቤን ያማከሉ ምላሾች መስጠት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

🔻ሞዴሉ በተሻለ መልኩ በማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ከማስቻሉ  በተጨማሪ የበለጠ ከሰው ጋር የመነጋገር ያህል ስሜት እንዳለው ኩባንያው ተናግሯል፡፡

🔻ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኩባንያውን ቀደምት ሞዴሎች ከአዲሱ ጋር በማነጻጸር ከቀድሞዎቹ በተጨባጭ የተሻለ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡ ንጽጽሩን ለማጉላት "ጂ.ፒ.ቲ-3 ከሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ጋር እንደመነጋገር ነበር፡፡ ጂ.ፒ.ቲ-4 ደግሞ ከኮሌጅ ተማሪ ጋር የመመካከር አይነት ስሜት ነበረው፡፡ ጂ.ፒ.ቲ-5 ግን በፒ.ኤች.ዲ ደረጃ ካለ ባለሞያ ጋር በማንኛውም ርዕስ ላይ የማውራት ያህል ነው፡፡" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

🔻እንደ ቢ.ቢ.ሲ መረጃ ጂ.ፒ.ቲ-5 ሞዴል ውስብስብ የኮዲንግ ስራዎችን በአጭር ጊዜ እና በከፍተኛ ጥራት ለማጠናቀቅ የበለጠ አስተማማኝ ነው፡፡

🔻ሞዴሉ ውስብስብ ጥያቄዎችን በማገናዘብ እና ረጅም ንግግሮችን በመከታተል የተጠቃሚውን ዐውድ በመረዳት የተሻለ ምላሽ ይሰጣል፡፡
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
29
ታላቅ የማስታወቂያ ቅናሽ አድርገናል !

- በተወዳጁ ቻናላችን ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ ?

▪️ የ ቻናል ማስታወቂያ
▪️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
▪️ የ ድርጅት ማስታወቂያ
▪️ የ ቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
▪️ የ ዩቲዩብና የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
▪️ ትሪትመንቶች
▪️ Consultancy
▪️ Technology accessories
▪️ ማንኛውም የትምህርት ማስታወቂያ እና
▪️ ሌሎችንም ሽያጮች ያስተዋውቁ

- ይሄን ልዩ ቅናሽ በመጠቀም ከ190,000+ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ምርቶን በማስተዋወቅ በእጥፍ ያትርፉ።

አሁኑኑ ያናግሩን
👉 @Its_eliyass
2
ዩቲዩብ በአሜሪካ በሰው ሰራሽ አሰተውህሎት የታገዘ የዕድሜ ማረጋገጫን ሊሞክር ነው።

🔻የዕድሜ ማረጋገጫው ህፃናትን ከአዋቂዎች ከዚህ ቀደም በተመለከቷቸው የቪዲዮ አይነቶች ላይ ተንተርሶ ይለያል ተበሏል።

🔻ማረጋገጫው ተጠቃሚዎች ለምዝገባ ያስገቡትን ዕድሜ ወደጎን በመተው በራሱ መንገድ ዕድሜያቸውን ለማረጋገጥ እንደሚሞክር ተዘግቧል።

🔻ማረጋገጫው ተጠቃሚው ከ18 አመት በታች መሆኑን ካረጋገጠ ዩቲዩብ ከዕድሜ ጋር ተያይዞ የሚጥለውን የቪዲዮ ፖሊሲ ተጠቃሚው ላይ ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

🔻እነዚህ ፖሊሲዎች አንዳንድ ቪዲዮዎችን ካላማሳየት እስከ እረፍት እንዲወስዱ እስከመምከር ይደርሳል ተብሏል።

🔻የሰው ሰራሽ አስተውህሎቱ በማረጋገጫው ወቅት ከ18 ዓመት በላይ የሆነን ተጠቃሚ ከ18 ዓመት በታች ነው ብሎ በስህተት ካረጋገጠ ግን ተጠቃሚው መታወቂያ እና ሌሎች መንገዶችን ተጠቅሞ ማስተካከል ይችላል ተብሏል።

🔻በርካታ ዩቲዩበሮች ይህንን የዩቲዩብ ሃሳብ በመቃወም ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረዋል።

🔻በቂ የተጠቃሚ ጥበቃ ባለበት ወቅት ተጨማሪ የዕድሜ ማረጋገጫ ማምጣት የሰዎችን የመረጃ ነፃነት የተጋፋ ነው ብለውታል።

🔻በተጨማሪ ሰዎች የሚመለከቱትን ሁሉንም ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ታግዞ መከታተል ግለሰባዊነትን መጋፋት ነው ብለዋል።

🔻ዩቲዩብ ይህንን ሙከራ ዛሬ እንደሚጀምረው ተገልጿል።

Source: ABC, Ars Technica
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
8
ሩሲያ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ የሚደረጉ የስልክ ልውውጦች ላይ በከፊል እገዳ ማስቀመጥ ጀመረች።

🔻ሩሲያ ከውሳኔው ላይ የደረሰችው ሁለቱ መተግበሪያዎች ከማጭበርበር እና ከአሸባሪነት ጋር በተያያዘ ለህግ ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ብላለች።

🔻በዚህ የተነሳ ሩሲያ የወንጀል ተግባራትን ለመቀልበስ በመተግበሪያዎቹ የሚደረጉ አንዳንድ የስልክ ልውውጦች ላይ እገዳ ማስቀመጧ ተዘግቧል።

🔻የሩሲያ የዲጂታል ልማት ሚኒስቴር ቴሌግራም እና ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መተግበሪያቸው ላይ የማጭበርበር እና የሽብርተኝነት ተግባራት እንዳይካሄዱ እንዲያደርጉ ተጠይቀው እምቢ ማለታቸውን ገልፀዋል።

🔻የሩሲያ ባለስልጣናት እነዚህ መተግበሪያዎች ሉዓላዊነታችንን የሚጥሱ ስለሆኑ በሃገራችን አግልግሎት አይስጡ ብለው ሲጠይቁ የነበረ ሲሆን ፕሬዚዳንት ፑቲንም በሩሲያ የበለፀገ እና ከደህንነት ተቋሙ ጋር የተሳሰረ የመልዕክት መለዋወጫ እንዲሰራ ማዘዛቸው ይታወሳል።

🔻ሩሲያ ሁለቱ መተግበሪያዎች መረጃ ከሰጡ እና ከህጓ ጋር ከተስማሙ እገዳው እንደሚነሳ ገልፃለች።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮♦️.
@ELA_TECH                         
🎯♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀♦️.
@ELA_TECHBOT      
👍21
📌የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ከሁለት ዓመት በኋላ ዓለምን በመምራት የሰውን ልጅ ሊያጠፋ እንደሚችል የሚተነብይ ጥናታዊ ጽሁፍ መውጣቱን ተከትሎ በቴክኖሎጂው ዓለም ማዕበል ፈጥሯል።

📌በዓለማችን ባሉ ተደማጭነት ባላቸው የላቁ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ባለሙያዎች ቡድን የታተመው 'ኤአይ 2027' የተሰኘው ጥናት ቴክኖሎጂው ከተሠራበት ዓላማ ውጪ ያልተጠበቀ ባህርይ በማሳየት የሰውን ልጅ ጥፋት እንደሚያስከትል ተንብየዋል።

📌ለወደፊቱ በሽታዎችን መፈወስ፣ ድህነትን ማጥፋት እና ሌሎችም ታላላቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል የተባሉት ኤአይ የሰውን ልጅ መግደልን ጨምሮ ጥናቱ ለወደፊቱ ሊፈጠሩ የሚችሉ ሁነቶችን ዘርዘር አድርጎ አካቷል።

የወደፊቱ ሁነቶች ምን ሊመስሉ ይችላሉ?

☑️ጥናቱ በአውሮፓውያኑ 2027 'ኦፕን ብሬይን' የተባለ ምናባዊ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃላይ ልኅቀት (ኤጂአይ) ላይ የሚደርስበት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) እንደሚገነባ ተተንብይዋል።

☑️የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃላይ ልኅቀት ላይ መድረስ ማለት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ምጡቅ ወይም የአእምሮ ተግባራትን ከሰዎች ጋር በእኩል ወይም ከሰዎች በተሻለ ሁኔታ ሲሠራ ማለት ነው።
4👍2😢1
የ75 ዓመቱ አዛውንት በ AI በተፈጠረች ሴት ፍቅር ከወደቁ በኋላ ከሚስታቸዉ ጋር ፍቺ ለመፈጸም ጥያቄ አቀረቡ።

🔻ነገሩ እንዲህ ነዉ  ጂያንግ የተባሉ የ75 አመት አዛውንት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለያዩ ነገሮችን በመጠቀም ላይ ሳሉ  በአይአይ የተፈጠረች ሴት ያያሉ ነገሩ ያልገባቸዉ ጂያንግ ከኤአይ እንስቷ ጋር በፍቅር ይወድቃሉ፡፡

🔻ልጅቷ በግልጽ AI ፈጠራ ነች, ነገር ግን ለጂያንግ ያልሰለጠነ የማህበራዊ አጠቃቀም ሰው አይደለችም ብሎ መቀበል ያዳግታቸዋል፡፡ ከእንስቷ ጋር ማዉራት መሳቅ የሚያምር ፈገግታዋን መመልከት የዘወትር ተግባራቸዉ ይሆናል፡፡

🔻ቀን ቀንን እየተካ ሲሄድ ጂያንግ ቅልጥ ያለ ፍቅር ከኤአይ ፈጠራዋ ሴት ጋር ይይዛቸዋል፤ይሄን የፍቅር ስሜታቸዉን የሚያስታግሱት ከስልካቸዉ ጋር ቀን ከሌት በማሳለፍ መልክቶችን ኤአይ ቴክኖሎጂ ከፈጠራት ሴት ጋር ሲላላኩ መቆየታቸዉን ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

🔻ብዙ ጊዜያቸዉን ስልካቸዉ ላይ ከማሳለፈቻዉ የተነሳ ከባለቤታቸዉ ጋር ግጭት ዉስጥ ይገባሉ፡፡ ባለቤታቸዉ ስልካቸዉ ላይ ብዙ ጊዜ የሚያሳልፉትን ጂያንግ ከተናገሯቸዉ በኋላ ግን ጂያንግ ለብዙ አስርት አመታት ለዘለቀዉ ትዳራቸዉ የፍቺ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ 

🔻ሆኖም ግን የጂያንግ ልጆች አባታቸዉን ወደ አእምሮው ጤና ማእከል እንዲገቡ አድርገዋቸዋል፡፡ ማእከሉም ይህም AI እንዴት እንደሚሰራ እና የበይነመረብ ፍቅር ፍላጎታቸዉ በእውነቱ ውስጥ እንዳልነበረ የማስረዳት ስራ እየሰሩ ነዉ ተብሏል፡፡

🔻በሃገረ ቻይና በብቸኝነት የሚያሳልፉ አረጋዉያን በእንደነዚህ አይነት የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ሰለባ እንደሚሆኑ የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ አስነብቧል ያለው መናኸሪያ ሬዲዮ ነው፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ
)
13😁7
መልካም ቀን family 🫡

GM😳
@smart_cryptos1
@smart_cryptos1
👍94
Forwarded from 🔥አረፍ አሪፍ folder disk channel🔥
🚨እድሜዎ ስንት ነው ?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg
የ 12ተኛ ውጤት ተለቁዋል

ለማግኘት ከስር ADD የሚለውን ተጫኑ!!!