የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.43K subscribers
8.77K photos
131 videos
1 file
1.53K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በደቡብ አፍሪካ ፍርናኬና ፑማላንጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን አደራጅቷል ።
የኢትዮጵያ አንድነት በክርስቶስ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የስራ አመራር ቦርድ ህደር 15/2015 በጉድና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል መደበኛ ስብሰባውን አካሄዷል ።
በዕለቱ የመክፈቻ ፀሎት በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ በእህት ዘነበች ሞሎሮ ከተፀለያ በኋለ የዕለቱ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት በሕብረቱ ጠቅላይ ፀሐፊ ሐዋርያ ተሰማ ሀ/ወልድ "በክርስቶስ አንድ አካል ነን " በሚል ርዕስ ቀርበዋል ።
በመቀጠል የህብረቱ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሐዋርያ ኢዮኤል አብርሃም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ያለውን የህብረቱን የስራ ሂደቶችን እና በቀጣይም ህብረቱ በአገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመስራት እያደረገ ያለውን ሂደቶችን ለሥራ አመራር ቦርድ አብራርተዋል።
በመቀጠል የህብረቱ ም/ፕረዚዳንት ዶ/ር አማኑኤል አብርሃም የህብረቱን መዋቅር እና አዲስ የተጨመሩ የስራ አመረር ቦርድ አባለትን አስተዋውቀዋል ።
በመጨረሻም ቦርዱ በዕለቱ በቀረቡ አጀንዳዎች ለይ ተወያይቶ አጽድቆ የዕለቱ ስብሳባ በፀሎት ተጠናቀዋል።