የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
2.67K subscribers
1.99K photos
14 videos
294 links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
to view and join the conversation
#እንኳን_ደስ_አሎት

ለፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ እንኳን ደስ አሎት መሰናዶ ተከናወነላቸው።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ በዝንድሮው አመት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በማግኘታቸው በካውንስሉ አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መሰናዶ ተከናውኖላቸዋል።

በመረሀ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፓትሪያሊክ ብጹዕ ካርዲናል ብረሃነ ኢየሱስ ሱራፌል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝን ጨምሮ የካውንስሉ የቦርድ አባላት እና የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በስፍራው በመገኘት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በድጋሜ ለፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
#ካውንስሉ_ድጋፍ_አደረገ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ለስድስት የምገባ ማዕከላት እና በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ ለሚገኙ ተረጂዎች የአልባሳት ደጋፍ አደረገ ።

ካውንስሉ አባል ቤተ እምነቶችን በማስተባበር ቀጣይ የድጋፍ ስራዎችን እንደሚያደርግም የተነገረ ሲሆን ተመሳሳይ ድጋፎችንም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰበታ ከተማም አድርጓል።