የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከግሎባል ቸርች ዲቨሎፐር ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ቤተእምነቶች የደቀመዝሙር አድራጊነት እና የጤናማ ቤተክርስቲያን ግንባታ አገልግሎታቸውን እንዲወጡ ለማስታጠቅ የሚያስችል ስልጠና መጋቢት 9,2014 ዓ.ም በብርሃነ ወንጌል እንግዳ ማረፊያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጥቷል።
በዚህ ስልጠና ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዬጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፅ/ቤት ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ እንደተናገሩት ካውንስሉ ከተቋቋመበት ዋና አላማ አንዱ በወንጌል ስርጭትና በቤተክርስቲያን ተከላ ዙሪያ ከአብያተ ክርስቲያናት ጋር መስራት እንደሆነ ገልፀው በጥናት ላይ የተመሰረተ የቤተክርስቲያን ተከላ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እንደዚህ አይነት መድረኮች ሁሉንም ተደራሽ ያደረገ ስራ ለመስራት እንደሚረዳ ገልፀዋል ። የአይ ሲ ኤም አፍሪካ ወክለው ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የመጡትና ስልጠናው የሰጡት ፍሬድሪክ ሙኬንጂ አይ ሲ ኤም በመላው አለምና በአፍሪካ በደቀመዝሙር ማድረግና በቤተክርስቲያን ግንባታ ዙሪያ ሰፊ ስራ እንደሚሰራና በኢትዮጵያም እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው አሁንም ከካውንስሉ ጋር በመሆን በሰፊው ለመስራት መዘጋጀቱን ተናግረዋል ።
ስልጠናው ሚኒስትሪው ደቀመዛሙርት ማድረግ ተልዕኮውን ለማከናወን በድምፅ የተዘጋጀውን መሳሪያ በአብያተ ክርስቲያናት አማካኝነት በሚቋቋሙ ትንንሽ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖች በማድረስ ተከታታይ ትምህር በመስጠት ደቀመዘሙር ማድረግና ለቤተክርስቲያን ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፅዋል ።
በስልጠናው ላይ ከተለያየ የሀገሪቱን ክፍል የመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች እየተካፈሉ ሲሆን ስልጠናው ቤተክርስቲያን ደቀመዝሙር የማድረግ ዋንኛ ተልዕኮዋን ለመወጣት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል ።
በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የመንፈሳዊ ዘርፍ ሀላፊ መጋቢ ስንሻት ተካ ደቀመዝሙር ማድረግና ቤተክርስቲያን ግንባታ ላይ አይ ሲ ኤም ጥሩ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ከካውንስሉ ጋር በስፋት ለመስራት መዘጋጀቱን ተናግረዋል ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል መንፈሳዊ ዘርፍ ደቀመዝሙር ማድረግና ጤናማ ቤተክርስቲያን ማፍራት ላይ እየሰራ እንደሚገኝና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

#የታላቁ_ወንጌላዊ_የጀርባ_አጥንት_አረፉ
የቢሊ ግርሃም የክሩሴድ ዳይሬክተር የነበሩት ሃርቪ ቶማስ በ82 ዓመታቸው አረፉ።
አብዛኛዎቻችን ፊት ለፊት እንጂ ከጀርባ ያሉትን ሰዎች አናውቃቸውም በመሆኑም የታላቁ ወንጌላዊ ቢሊግርሃም እነዛን ከመሳሰሉ ክሩሴዶች ጀርባ የነበሩት ሰው ከሰሞኑ በ82 ዓመታቸው ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።
በ1960ዎቹ እና 1970ዎቹ ለወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም የስብከተ ወንጌል ሰልፎችን ያዘጋጁ የነበሩት እኚህ ሰው ነበሩ።
የብሪታንያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ የቀድሞ የፕሬስ ኃላፊ የነበሩት እኚህ ሰው እ.ኤ.አ. በ1960 -1975 የቢሊ ግርሃም የክሩሴድ ዳይሬክተር በመሆን በዓለም ዙሪያ ያሉ ዝግጅቶችን ተቆጣጠረዋል።
ቤተሰቦቹ "አባታችን በታማኝነት፣ በይቅርታ፣ በእምነት እና በፍቅር የተሞላ ህይወት መኖር ምን ማለት እንደሆነ ብዙ አስተምሮናል" ሲሉ ስለ አባታቸው ተናግረዋል።
© The Christian News
ምንጭ ዎርዚ ኒውስ

ናኖ መጽሃፍ ቅዱስ ወደ ጠፈር ጉዞ
በዓለም ላይ ትንሹ መጽሐፍ ቅዱስ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ወደ ጠፈር ጉዞ ያደርጋል ተባለ፡፡
የእስራኤል የጠፈር ተመራማሪ የሆነው አይታን ስቲቤ አክስ-1 የተባለው የጠፈር ተመራማሪ ቡድን አባል ሆኖ ወደ አለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ሲነሳ በመጠን እጅግ ትንሽ የሆነውን "ናኖ መጽሐፍ ቅዱስ" ይዞ ይሄዳል ተብሏል።
ይህ በመጠን እጅግ በጣም ትንሽ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ 0.5 ስኩዌር ሚሊሜትር መጠን ሲኖረው በላዩ ላይ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ፊደላት በጨረር አማካኝነት የተቀረጹበት ነው።
ይህ በአይን ሊታይ የማይችል በመጠን በጣም ትንሽ ናኖ መጽሃፍ ቅዱስ የተሰራው ቴክኒዮን ተብሎ በሚታወቀው የእስራኤል የቴክኖሎጂ ተቋም ሲሆን በኢየሩሳሌም በሚገኘው የእስራኤል ሙዚየም ውስጥ ከታሪካዊ የሙት ባህር የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅልሎች ጋር አብሮ እየተጎበኘ ይገኛል።
የመጀመሪያውን የናኖ መጽሐፍ ቅዱስ ያዘጋጀው የቴክኒዮን ተቋም ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኡሪ ሲቫን እንዳሉት "የዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ህዋ ጉዞ ባለፈው ዘመንና እና ወደፊት መካከል ያለውን ርቀት እና ጊዜ ያገናኛል, በጥንት የሰው ልጅ ባህል እና በቴክኖሎጂ ድንበር መካከል ድልድይ ይሰራል."በማለት ተናገረዋል፡፡
ሶስት ጠፈርተኞችንና የግል ተጓዦችን ያካተተው ይህ የአለም አቀፉን የጠፈር ጣቢያን ለመጎብኘት የሚደረግ ጉዞ መጋቢት 30 የሚደረግ ሲሆን ለ10 ቀናት የጠፈር ላይ ቆይታ እንደሚኖረው የዘገበው ካሪዝማ ኒውስ ነው።

ግሬስ ላይፍ ኮሚኒቲ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 5ተኛ ዓመትና የማምለኪያ አዳራሽ ምርቃት
ግሬስ ላይፍ ኮሚኒቲ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 5ተኛ ዓመትና እና የማምለኪያ አዳራሽ ግንባታ ምርቃት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
ከ 5 ዓመት በፊት በፊት በ 30 ምዕመን የተመሰረተችው ቤተክስቲያኒቱ ዛሬ በሺህ የሚቆጠር አባላት ያላት ሲሆን ቀድሞ አምልኮ ታካሄድበት ከነበረው የቦሌ አየር መንገድ ማረፊያ አካባቢ ወደ አትላስ ቴሌ ጀርባ አዲስ የማመለኪያ ህንጻ ገንብታ መጋቢት 10,2014 ዓ.ም አስመርቃለች፡፡
የቤተክርስቲያኒቱ ባለራዕይና ዋና መጋቢ አማረ ሃጎስ ቤተክርስቲያኒቱ በእነዚህ አመታት ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶችን በማለፍ ለ5ኛ ዓመት በአል እንደደረሰች ገልጸው በቀጣይም የመጽሃፍ ቅዱስ ኮሌጅ የመክፈት ፤ የታዳጊዎችና የወጣቶች አገልግሎትን የማስፋፋት ተግባር ላይ በማተኮር እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳና የምርቃት ፕሮግራሙን ያካሄዱት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጽህፈት ቤት ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ ታሪክ የማይረሳ የወንጌል አሻራ ያሰቀመጡት የቀደሙ የወንጌል አባቶች በዱር በገደሉ በብዙ እንግልት፤እስር፤ረሃብና ጥማት ውስጥ አልፈው በገጠር በጫካ በዛፍ ስር አምልከው፤ የህይወት መስዋትነትን ከፍለው ወንጌልን አስረክበውናል፡፡ዛሬ እኛ በተንጣለለ አዳራሽ ቦሌ መሃል ከተማ ላይ ተቀምጠን ማመለክ ችለናል፡፡ለዚህም ዋጋ ለከፈሉ አባቶች ምስጋና እናቀርባለን በማለት ተናግረዋል፡፡
በግሬስ ላይፍ ኮሚኒቲ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 5ኛ ዓመት ክብረ በዓልና የማመለኪያ አዳራሽ ምርቃት ላይ የተለያዩ አብያተክርስቲያናት መሪዎች፤ አገልጋዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አዲሱ ዲጂታል ኤሌክትሮኒክ የመፅሃፍ ቅዱስ ማጥኛ ዲቫይስ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
https://youtu.be/5ViVTNn7ME4
https://youtu.be/5ViVTNn7ME4
YouTube
አዲሱ ዲጂታል ኤሌክትሮኒክ የመፅሃፍ ቅዱስ ማጥኛ ዲቫይስ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
የሴቶችን ውድድር በአሽናፊነት የተቆጣጣረው ወንድ የዋና ተወዳዳሪ ላይ የተነሳ ቅሬታ
የዋና ተወዳዳሪዋ የአንደኝነት ደረጃው ጾታውን ቀይሮ በሴቶች የዋና ውድድር በተሳተፈ የቀደሞ ወንድ ተወዳዳሪ ሰለተወሰደባት ቅሬታዋን ማሰማትዋ ተነገረ፡፡
የቨርጂኒያ ቴክኒዮሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዋና ተወዳዳሪ ሪካ ጆርጂ በዩኒቨርሲቲዎች የዋና ውድድር በተፈጥሮው ወንድ የሆነውና ጾታውን ቀይሮ ከሴቶች ጋር የሚወዳደረው የፔንሲልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ዋናተኛ ሊያ ቶማስ አሸናፊ መሆኑ የአንደኝነት ደረጃዋን እንድታጣ እንዳደረጋት ቅሬታዋን አሰምታለች፡፡
በቅርቡም ለረጅም ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ የዋና ውድድር ባለ ሥልጣን የነበሩት ግለሰብ በተፈጥሮ ወንድ የሆነውና አሁን ጾታውን ቀይሮ ከሴቶች ጋር የሚወዳደረውን ዊሊ(ሊያ) ቶማስን በመቃወም ሥራውን መልቀቃቸው ይታወሳል።
የፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው የቀደሞው ዊል ቶማስ የአሁንዋ ሊያ ቶማስ በ 200 እና 500 ሜትር ነጻ ዋና ተወዳድሮ የሴቶችን ክብረወሰን የሰበረ ሲሆን ዩኒቨረሲቲ በገባባቸው የመጀመሪያ ሶስት አመታት በወንዶች ውድድር ላይ ይሳተፍ እንደነበር ተነግሯል፡፡
"ጾታ መቀየሬ ይህን ስፖርት ለመስራት አቅሜን አልነካውም የሚለው የቀደሞው ወንድ የአሁኑ ሴት የዋና ተወዳዳሪ በዚህ ወር በነበረው የኮሌጆች የዋና ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ መውሰዱ ነው የተዘገበው፡፡
ወንዶች በተፈጥሮ ከሴቶች የበለጠ አካላዊ ጥንካሬ ያላቸው በመሆኑ ጾታ ቀይረው ሲወዳደሩ የማሸነፍ ብልጫ ማግኘታቸው የውድድሩን ፍትሃዊነት ጥያቄ ላይ ይጥለዋል በሚል ብዙ ክርክሮች እየተነሱ እንደሚገኙ የዘገበው ብሌዝ ሚዲያ ነው፡፡
በዚህ ዘመን በስፋት የሚከናወነው ይህ ጾታን የመቀየር ድርጊት ከሚያስከትለው ይህንን መሰል ቀውስ በተጨማሪ እየከፋ ያለውን የአለም የእግዚያብሄርን ህግ የመቃረን አካሄድና ጥፋት ምን እንደደረሰ የሚያሳይ ነው፡፡

#አሜሪካ_በአዲሱ_አለም_ስርዓት
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ 'የአዲሱ አለም ስርአት' ወይም ኒው ወርልድ ኦርደርን መሪ መሆን አለባት ሲሉ መናገራቸውን ላይፍ ሳይት ኒውስ ዘገበ::
ጆ ባይደን ይህንን የተናገሩት በየሶስት ወር በሚደረግ የቢዝነስ የክብ ጠረጴዛ ስብሰባ ላይ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እየተከሰቱ ያሉ ክስተቶች በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ “አንዳንድ የጎሉ ለውጦችን ለማድረግ ጠቃሚ እድሎችን” ፈጥረዋል በማለት መናገራቸው ተገልጿል፡፡
‘ከከፍተኛ ወታደራዊ ሰዎች አንዱ ከ1900 እስከ 1946 ባለው ጊዜ ውስጥ 60 ሚሊዮን ሰዎች እንደሞቱ ነግሮኛል፤ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሊበራል የዓለም ሥርዓትን መስርተናል ፤ነገሮች የሚለወጡበት ጊዜ አሁን ነው። እኛ እየሄድን ነው፣ አዲስ የዓለም ሥርዓት እየመጣ ነው፤ እኛ እሱን መምራት አለብን ፤የተቀረውን ነፃ ዓለም አንድ ማድረግ አለብን በማለት መናገራቸው ተዘግቧል።
አዲሱ የአለም ስርአት ወይም ኒው ዎርልድ ኦርደር የምድር ህዝቦች በአንድ በአለምአቀፍ አገዛዝ ስር እንዲመሩ የሚያደርግ አለም አቀፍ ስርአት ለመመስረት የሚደረግ ሚስጥራዊ እንቅስቃሴ አለ የሚል ንድፈ ሃሳብ ሲሆን በአለም ዙሪያ የሚከሰቱ ክንውኖችን ከዚህ ጋር በማያያዝ የሚተነትን ነው።

የ61ኛው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባዔ የመክፈቻ መርሃ ግብር በጉባዔው አስተናጋጅ ወላይታ ቀጠና ዋና ጽሕፈት ቤት ግቢ በሚገኘው ታሪካዊው ጠረጴዛ አዳራሽ ተካኼደ።
ይኸው ጉባዔ ከመላው አገሪቱ የተሰባሰቡት የጠቅላላ ጉባዔ አባላት እና የክብር እንገዶች የሆኑት የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች፣ የኤስ አይ ኤም ኢትዮጵያ መሪዎች፣ የዞኑ አስተዳደር አመራሮች፣ … በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በመክፈቻ መረሃ ግብሩ ላይ አቶ አቤል ቲማም የወላይታ ቀጠና ሰብሳቢ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የክብር እንግዳው የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ጋብዘዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማም ወደ ወላይታ እንኳን ደህና መጣችሁ የሚል መልእክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን መልካም መኞታቸውን ገልጸዋል።
በጉባዔው ላይ የወላይታ በረከት የሆኑት መጋቢ ዮሐንስ ባሰናና የወላይታ ከተማ አቀፍ መዘምራን በቃል እና በዝማሬ አገልግለዋል። በመጨረሻም የመክፈቻ መርሀ ግብሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች የምስጋና መልዕክት ተጠንቋል። ጉባኤው ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ይጀምራል።
© Ethiopian Kale Heywet Church Communication