የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.44K subscribers
8.77K photos
131 videos
1 file
1.53K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል_የኢትዮጵያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች
ቤተክርስቲያንታላቅ የወንጌል ጀማ ስብከት ወንጌል በአዲስ አበባ ስታዲየም l ቀን 3



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://t.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል
#ከdynamic church planting international (DCPI) ጋር በመተባበር በሀዋሳ እና አዳማ ከተማ ስልጠና ተሰጠ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከDCPI ጋር በመተባበር በሀዋሳ እና አዳማ ከተማ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው አላማ ቤተክርስቲያን በተሰጣት ብርቱ አላፊነት ላይ ትኩረት እንድትአደርግ የሚረዳ ስልጠና እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ የመጨረሻው ስልጠና በአምቦ ከተማ የሚደረግ መሆኑንና በ2025 በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በስፋት ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://t.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል_ከሰላም_ሚኒስቴር_ሚኒስትር_ክቡር_አቶ_መሀመድ_እድሪስ_ጋር_ትውውቅ_አደረጉ፡፡

ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቢሮ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡

በትውውቅ ፕሮግራሙ ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ እንደተናገሩት የሃይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነት ለሰላም ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀው በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳይ ሰላማዊና የተረጋጋ ማህበረሰብ እንዲኖር የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ አስተዋፆ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣይ በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ እያከናወነ ያለውን  ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተው የሰላም ሚኒስቴርም በትብብርና በቅንጅት ከካውንስሉ ጋር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ክቡር ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከመገፋፋት ይልቅ በመተባበር እና በመደጋገፍ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሃይማኖቶች ትልቅ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ሲሰራ የቆያቸውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በሀገራችን ሰላም ጉዳይ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነን  ብለዋል፡፡

የካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል እስከ አሁን በተለያዩ ዘርፎች የሰራውን ስራ ገልፃ በማድረግ ማብራሪያ ሰተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ፣የኢትዮጵያ  ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባላት በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://t.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!