EEP Communication
15.6K subscribers
10.8K photos
33 videos
32 files
2.02K links
EEP Communication
Download Telegram
የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ከሁሉም ህብረተሰብ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው
……………../////……………
የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብ ውሀ የማጠጣት ተግባር አከናወኑ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ደርባ ፊንጫ በተባለ አካባቢ በ2012 ዓ/ም የክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብ በወጣው መርሃ ግብር መሠረት ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች በቦታው ተገኝተው ችግኞቹን ውሃ አጠጥተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የቴክኒክ አማካሪ አቶ አንዳርጌ እሸቴ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም ለጽድቀት መጠኑ ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
ችግኞቹ የተተከሉበት አካባቢ በአባይ ተፋሰስ ሥር የሚገኝ በመሆኑ ከወዲሁ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ መሠራቱ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ ያግዛል ብለዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የሚተከሉ ችግኞች የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከፍ ከማድረጋቸው ባሻገር ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ የግድቦቻችንን ዕድሜ እንደሚጨምር አማካሪው ገልፀ ዋል፡፡
ችግኞቹም ከእንስሳት ንኪኪ ተጠብቀው በጥሩ የዕድገት ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው መደሰታቸውን በመጥቀስ የአካባቢው ህብረተሰብ ላከናወነው ተግባር አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ሀብት አስተዳድር ዳይሬክተር አቶ ተማም አፍደል በበኩላቸው ችግኞችን የመንከባከብና ውሀ የማጠጣት ፕሮግራሙ ከየሥራ ክፍሉ የተወጣጡ አመራሮችና ሠራተኞች የተሳተፉበት በመሆኑ ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ መኮንን ክፍሌ እንደገለፁት ደግሞ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ከሁሉም ህብረተሰብ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው፡፡

ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር ለማሳካት ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ 5 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም
የግድቡ ግንባታ በታቀደለት መርሃግብር እየተከናወነ ነው
...........////.........
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በታቀደለት መርሃግብር እየተከናወነ መሆኑን በስፍራው በመገኘት የፕሮጀክቱን አፈፃፀም የገመገሙት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚሩስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባላት አረጋገጡ፡፡
ሚኒስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታው ሂደት በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ መሆኑን ምልከታ በማድረግ በግንባታው ላይ እየተሳተፉ ካሉት ተቋራጮች፣ አማካሪ ድርጅትና ከባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡
የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በዕቅዱ መሰረት እንዲጠናቀቅና አስቀድሞ በሁለት ዩኒቶች ኃይል ለማመንጨት የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም
ከተቋሙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ውስጥ 33 ነጥብ 1 በመቶዎቹ በራስ አቅም የተገነቡ ናቸው
……………..////……………

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችንና የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን በራስ ኃይል የመገንባት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን የሲቪል ስራዎች ቢሮ ገለፀ፡፡

የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ኃይለ ጊዮርጊስ እንደገለፁት ተቋሙ ከባለ 45 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በራስ ኃይል መገንባት የጀመረው ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ ነበር፡፡

ቢሮው በሰው ኃይልና በመሳሪያ ተደራጅቶ በአሁኑ ሰዓት እስከ 400 ኪሎ ቮልት ድረስ ያሉ የማስተላለፊያ መስመሮች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አቶ ሰሎሞን ተናግረዋል::

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙት የከፍተኛ መስመሮች ውስጥ 30 ነጥብ 3 በመቶው እንዲሁም ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ውስጥ 33 ነጥብ 1 በመቶዎቹ በራስ ኃይል ቢሮ የተገነቡ መሆናቸውን አቶ ሰለሞን አስታውቀዋል፡፡

እንደ አቶ ሰሎሞን ገለፃ ቢሮው ከአዳዲስ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በ59 ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የማስፋፊያ እና በ37 ማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም የማሳደግ ስራ አከናውኗል፡፡


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም
በሳይት ላይ መስራት ያለበት ሥራ ተሰርቷል - የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ
………../////……….
የአይሻ II የንፋስ ኃይል ፕሮጀክት ከሚኖሩት 48 የንፋስ ተርባይኖች መካከል የአርባዎቹን ተርባይኖች ተከላና የፍተሻ ሥራ በተያዘው በጀት ዓመት በማጠናቀቅ ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ለማገናኝት እየሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡
ሥራ አስኪያጁ አቶ ሙሉቀን ተሰማ እንደገለፁት በፕሮጀክቱ 120 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ከሚተከሉት 48 የንፋስ ተርባይኖች መካከል የ24ቱ ተከላ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡
ሁሉንም ተርባይኖች ለመትከል የሚያስችል የመሠረት ቁፋሮና የኮንክሪት ሙሌት ስራ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
አራት ተርባይኖችን ለመትከልም ንፋስ የሚቀንስበት ወቅት እየተጠበቀ መሆኑንና ተጨማሪ አራት ተርባይኖች ደግሞ ከወደብ ወደ ፕሮጀክት ሳይቱ እየተጓጓዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ሙሉቀን እንደገለፁት በሳይት ላይ መስራት ያለበት ሥራ የተሰራ በመሆኑ ቀሪዎቹን 16 ተርባይኖች በማምረት ተከላውን ለማከናውን አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
ከተወሰኑ የማጠናቀቂያ ሥራዎች በቀር የፕሮጀክቱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታም ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ብለዋል፡፡
የፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራ 94 በመቶ፣ የተርባይን ጀነሬተሮች ፍብረካ እና ማጓጓዝ 70 በመቶ፣ የፍተሻና ሙከራ ሥራ 47 በመቶ፣ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ደግሞ 70 ነጥብ 25 በመቶ ደርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም
ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃይል ለማቅረብ እየተሰራ ነው
………….///……………
ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለፁት ለምርቃት ዝግጁ ለሆነው ለቡሬ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ሁለት አማራጮች ተይዘው ጥናት ሲካሔድባቸው ቆይተዋል፡፡
ለፓርኩ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ከባህርዳር ማከፋፈያ ጣቢያ በዳንግላ- ቡሬ በኩል 69 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር እንዲሁም ከደብረ-ማርቆስ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ፓርኩ የሚሄድ 92 ኪሎ ሜትር ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር የመዘርጋት አማራጮች ተለይተው የቴክኒክና የፋይናንስ ትንተና እንደተካሄደባቸው ገልፀዋል፡፡
በተደረገው የቴክኒክና የፋይናንስ ትንተና መሠረት ከባህርዳር-ዳንግላ እንዲመጣ የታሰበው የማስተላለፊያ መስመር ባለ 132 ኪሎ ቮልት በመሆኑ ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር የኃይል መዋዠቅ ሊያጋጥም እንደሚችል አመልክቷል፡፡
በዚህም ምክንያት ከደብረ-ማርቆስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ ጀምሮ እስከ ቡሬ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የማከፋፈያ ጣቢያ ለመገንባት መታቀዱን ነው አቶ ሞገስ ያብራሩት፡፡
ፕሮጀክቱን ለማከናወን ዓለምአቀፍ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጓል ያሉት ኃላፊው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን እና የማከፋፈያ ጣቢያውን ገንብተው ለማስረከብ ብቃት ያላቸው ሥራ ተቋራጮች እስከ የካቲት 05 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ክፍት በተደረገው ጨረታ ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
እንደ አቶ ሞገስ ገለፃ የወሰን ማስከበር ጉዳይ ለፕሮጀክት ግንባታ መጓተት ምክንያት እንዳይሆን ከወዲሁ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል በመንግሥትና የግል አጋርነት ይገነባሉ ተብለው ከተለዩት መካከል አንዱ እንደነበር የጠቆሙት ኃላፊው በተለያዩ ምክንያቶች ዕውን ሊሆን አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡
ለቡሬ፣ ለቡልቡላ፣ ለባከርና ለይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃይል ለማቅረብ አሸናፊው ተቋራጭ ከተለየ በኋላ ፕሮጀክቱን በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ፕሮጀክቱ ሁለት አምቡላንሶችን በስጦታ እና በግዥ ማሟላቱን ገለፀ
…………../////………….
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ለሚከሰት የኮቪድ 19 እና ሌሎች የጤና ሥጋቶች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያግዙ አንቡላንሶች መሟላታቸውን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገለፁ፡፡
ለፕሮጀክቱ አንዱን አምቡላንስ በስጦታ ሌላኛውን አምቡላንስ ደግሞ በግዥ እንዲሟሉ ያደረገው የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር መሆኑን ኢንጂነር ክፍሌ ገልፀዋል፡፡
ይህም በግድቡ ግንባታ ወቅት ለሚያጋጥሙ የኮቪድ 19 እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ሥጋቶች ፈጣን የአምቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለናል ብለዋል፡፡
የሁለቱ አምቡላንሶች ዋጋ 2 ነጥብ 63 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጣ በመግለፅ ለተደረገው ድጋፍ የጤና ሚኒስቴርን አመስግነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ተቋሙ በደም ልገሳ በመሳተፉ እውቅና አገኘ
……………./////…………..
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደም እጥረት ላለባቸው ወገኖች እንዲውል በማሰብ ባበረከተው አስተዋጽኦ ከብሔራዊ የደም ባንክ እውቅና አገኘ፡፡
ዛሬ ማምሻውን በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የእውቅና ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ ሰራተኞቻቸውን በማስተባበር በትግራይ በተካሄደው የህግ ማስከበርና በኮቪድ 19 ወረርሽን የደም እጥረት እንዳያጋጥም ደም የለገሱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ተቋማቱ እውቅናውን ከጤና ሚኒስትር ተቀብለዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ በደም ልገሳ መርሃግብሩ ላይ የተሳተፋችሁትንና ደም ለመለገስ ፈልጋችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ሳትለግሱ የቀራችሁ የተቋማችን አመራሮችና ሠራተኞችን የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያመሰግናል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም