EEP Communication
15.6K subscribers
10.8K photos
33 videos
32 files
2.02K links
EEP Communication
Download Telegram
20210115_105134.jpg
2.3 MB
የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በርካታ የጥገናና የኦፕሬሽን ሥራዎች ማከናወኑን ገለፀ
............/////..............
የጊቤ አንድ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ስድስት ወራት ስኬታማ የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራዎች ማከናወኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ንጉሴ አስታውቁ፡፡
በስድስት ወራት ውስጥ 534 ነጥብ 2 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማመንጨት ታቅዶ 600 ጌጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ በማመንጨት የዕቅዱን 120 በመቶ ማሳካት መቻሉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ጣቢያው 230/132 ኪ.ቮ አቅም ያለው ስዊች ያርድ ባለቤት ሲሆን ለጌዶ፣ ሰበታና ሰኮሩ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኤሌክትሪክ የሚያቀርቡ ሶስት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
ከኦፕሬሽን ሥራዎች ባሻገር በማቀዝቀዣ፣ በዲዝል፣ በስካዳ ሲስተም እና በስዊችያርድ ላይ የጥገና ሥራዎች የተከናወኑ መሆኑን አቶ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡
በብልሽት ምክንያት ለሥራ እንቅፋት ሆኖ የቆየውን የዩኒት አንድ ሰርቨር የኮምፒውተር ሰሌዳ ወይም ስክሪን በመጠቀም እንደገና አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉን ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡
በስዊችያርድ ላይ የሞደፊኬሽን ሥራዎች በማከናወን ስዊች ያርድ ላይ ያጋጥም የነበረውን ተደጋጋሚ የኃይል መቋረጥ ማስቀረት መቻሉንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
ሪጅኑ ባለፉት 6 ወራት ከዕቅዱ በላይ የቅድመ ብልሽት ፍተሻና የጥገና ሥራ አከናወነ
………..////………..
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ ሪጅን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ ባለፉት 6 ወራት የዕቅዱን 102 ነጥብ 38 በመቶ የቅድመ ብልሽት ፍተሻና የጥገና ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
ቢሮው የስድስት ወር አፈፃፀሙን በጅግጅጋ ሲገመግም ዳይሬክተ ሩ አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን ከዛፍ ንኪኪ የማፅዳት፣ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመተካት፣ የመሬት መንሽራተት ምሰሶዎችን እንዳይጎዳ የጋቢዮን ማንጠፍና የተበጠሱ ገመዶችን በሌላ የመተካት ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
የፖርሲሊን ኢንሱሌተሮችን በፕላስቲክ ኢንሱሌተር የመተካት ስራ መስራቱንም ገልፀዋል፡፡
ይህም የሪጅኑን አፈፃፀም 102 ነጥብ 38 በመቶ አድርሶታል ብለዋል፡፡
ከተመሠረተ ሦስት ወራት ያስቆጠረው የጅግጅጋ ንዑስ ሪጅን የተቋቋመበትን ዓላማ መውጣት እንዲችል ተገቢው ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በሪጅኑ ከሪፖርት አቀራረብ፣ የሚሞሉ ዕለታዊ ሎግ ሺቶችን ኦዲት ካለማድረግና ከስልጠና ጋር የተያያዙ የአፈፃፀም ክፍተቶች መታየታቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም
የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ከሁሉም ህብረተሰብ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው
……………../////……………
የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብ ውሀ የማጠጣት ተግባር አከናወኑ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ደርባ ፊንጫ በተባለ አካባቢ በ2012 ዓ/ም የክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብ በወጣው መርሃ ግብር መሠረት ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች በቦታው ተገኝተው ችግኞቹን ውሃ አጠጥተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የቴክኒክ አማካሪ አቶ አንዳርጌ እሸቴ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም ለጽድቀት መጠኑ ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
ችግኞቹ የተተከሉበት አካባቢ በአባይ ተፋሰስ ሥር የሚገኝ በመሆኑ ከወዲሁ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ መሠራቱ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ ያግዛል ብለዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች የሚተከሉ ችግኞች የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከፍ ከማድረጋቸው ባሻገር ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ የግድቦቻችንን ዕድሜ እንደሚጨምር አማካሪው ገልፀ ዋል፡፡
ችግኞቹም ከእንስሳት ንኪኪ ተጠብቀው በጥሩ የዕድገት ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው መደሰታቸውን በመጥቀስ የአካባቢው ህብረተሰብ ላከናወነው ተግባር አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ሀብት አስተዳድር ዳይሬክተር አቶ ተማም አፍደል በበኩላቸው ችግኞችን የመንከባከብና ውሀ የማጠጣት ፕሮግራሙ ከየሥራ ክፍሉ የተወጣጡ አመራሮችና ሠራተኞች የተሳተፉበት በመሆኑ ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ መኮንን ክፍሌ እንደገለፁት ደግሞ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ከሁሉም ህብረተሰብ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው፡፡

ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር ለማሳካት ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ 5 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም
የግድቡ ግንባታ በታቀደለት መርሃግብር እየተከናወነ ነው
...........////.........
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በታቀደለት መርሃግብር እየተከናወነ መሆኑን በስፍራው በመገኘት የፕሮጀክቱን አፈፃፀም የገመገሙት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚሩስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባላት አረጋገጡ፡፡
ሚኒስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታው ሂደት በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ መሆኑን ምልከታ በማድረግ በግንባታው ላይ እየተሳተፉ ካሉት ተቋራጮች፣ አማካሪ ድርጅትና ከባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡
የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በዕቅዱ መሰረት እንዲጠናቀቅና አስቀድሞ በሁለት ዩኒቶች ኃይል ለማመንጨት የተያዘው ዕቅድ እንዲሳካ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠
https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም
ከተቋሙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ውስጥ 33 ነጥብ 1 በመቶዎቹ በራስ አቅም የተገነቡ ናቸው
……………..////……………

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችንና የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን በራስ ኃይል የመገንባት አቅሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን የሲቪል ስራዎች ቢሮ ገለፀ፡፡

የቢሮው ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ኃይለ ጊዮርጊስ እንደገለፁት ተቋሙ ከባለ 45 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በራስ ኃይል መገንባት የጀመረው ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ ነበር፡፡

ቢሮው በሰው ኃይልና በመሳሪያ ተደራጅቶ በአሁኑ ሰዓት እስከ 400 ኪሎ ቮልት ድረስ ያሉ የማስተላለፊያ መስመሮች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አቶ ሰሎሞን ተናግረዋል::

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙት የከፍተኛ መስመሮች ውስጥ 30 ነጥብ 3 በመቶው እንዲሁም ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ውስጥ 33 ነጥብ 1 በመቶዎቹ በራስ ኃይል ቢሮ የተገነቡ መሆናቸውን አቶ ሰለሞን አስታውቀዋል፡፡

እንደ አቶ ሰሎሞን ገለፃ ቢሮው ከአዳዲስ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በ59 ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የማስፋፊያ እና በ37 ማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም የማሳደግ ስራ አከናውኗል፡፡


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠

https://www.facebook.com/Ethioelectric

ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ
www.eep.com.et
ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም