EEP Communication
15.6K subscribers
10.8K photos
33 videos
32 files
2.02K links
EEP Communication
Download Telegram
የብቃት ማዕቀፍ ስርዓት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ
……………./////……………
የብቃት ማዕቀፍ ስርዓት እና የዕድገት መሰላል ትግበራ የተቋሙን የአፈፃፀም አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑ የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ካሳ ገለፁ፡፡
ተቋሙ 27 ለሚሆኑ የስራ መሪዎችና ሠራተኞች የብቃት ማዕቀፍ ስርዓት እንዲሁም የዕድገት መሰላል ቀረፃና ትግበራ ላይ ያተኮረ የ5 ቀናት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
ሠልጣኞች በቆይታቸው በብቃት ማዕቀፍ ሞዴል፣ የብቃት ማዕቀፍ አስተዳደር ጥቅሞች ፣ የብቃት ማዕቀፍ ማፒንግ፤ የዕድገት መሰላል ዕቅድ እና ልማት እንዲሁም በሌሎች ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች የፅንሰ ሃሳብና የክህሎት ስልጠና አግኝተዋል፡፡
በተቋሙ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ካሳ እንዳሉት በእያንዳንዱ የስራ መደብ የተለያዩ እርከን ያላቸው የብቃት ማዕቀፍ ደረጃዎች ተዘጋጅተዋል፡፡
የብቃት ማዕቀፍ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ካላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ልምድ መወሰዱን ዶ/ር ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተገኙ ግብአቶችን በማካተት በቀጣይ አንድ ተጨማሪ ውይይት ከተካሔደ በኋላ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ነው ዶ/ር ወንድወሰን ያስታወቁት፡፡

ህዳር 09 ቀን 2013 ዓ/ም
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ
……………….///……………..
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያን ጎበኙ፡፡
የኃይል ማመንጫ ጣቢያው አልፎ አልፎ የሚያጋጥመውን የግብዓት አቅርቦት እና የጥገና ሥራዎች ዙሪያ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ከተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
በማመንጫው በሚከናወን የጥገና ስራ፣ የተረፈ ምርት አወጋገድ እና የኬሚካል አቅርቦት ላይ እየተሰሩ ስላሉ ሥራዎች ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ ተደርጎለታል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከተቋሙ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አረጋግጠዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም መጨረሻ ተመርቆ ከወራት የሙከራና ፍተሻ ሂደት በኋላ ሥራ የጀመረው ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በዓመት በአማካይ 185 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡
የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ባለፈው በጀት ዓመት ከታቀደው በላይ ኢነርጂ ማምረት ከቻሉ የኃይል ማመንጫዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
ምክትል ከንቲባዋ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥፍራውን የጎበኙ ሲሆን ከሠራተኞች ጋርም ተነጋግረዋል፡፡
ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም.