EEP Communication
15.6K subscribers
10.8K photos
33 videos
32 files
2.02K links
EEP Communication
Download Telegram
ተቋሙ በ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የአማካሪ ግዢ ሥምምነት ተፈራረመ
............./////..........
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለደብባዊ የኃይል ቋት የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ የኢንጂነሪንግ፣ ግዥና ኮንስትራክሽን ሥራዎች የአማካሪ ቅጥር ግዥ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

BYUCKSAN Power Construction የተባለው አማካሪ ድርጅት ተቋሙ በደቡባዊ ግሪድ የሚያሰራውን የኢንጂነሪንግ፣ የግዥና ኮንስትራክሽን ሥራ የሚያማክር ነው፡፡

ሥራውን ለማከናወንም የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻና እና የኩባንያው ተወካይ ሚስተር ጅንግ ውን ጅኦንግ ናቸው፡፡

ህዳር 04 ቀን 2012 ዓ/ም
የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ ተመቷል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው
………………../////…………..
የተከዜ ሀይል ማመንጫ ግድብ በቦምብ ተመቷል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ካለው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ መረጃ ለህዝብ እያደረሰ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ድረገጹ እንዳስታወቀው ተከዜ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ልክ እንደ ሌሎቹ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ሁሉ በፌደራል መንግሥት የተገነባና የሚያስተዳድረውም የፌደራል መንግሥት ነው።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ሚልሻዎች በማይካድራ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሪፖርት ባወጣበት በህዳር 3፣ 2013 ዕለት፣ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የተከዜ ግድብ በቦንብ እንደተመታ የሚያትት ሆን ተብሎ የተቀናበረ፣ የሀሰት መረጃን ህወሓት በቴሌቪዥን አሰራጭቷል ብሏል።
ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችል መሆኑን የመረጃውን ሀሰተኛነት በቀላሉ ያረጋግጣል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል፡፡
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነታቸውን ገለፁ …………………………….///…………………………….
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች ‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› በሚል መሪ ቃል ለሠራዊቱ ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡

በዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

ሁሉም ተሳታፊዎች ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር የገለፁ ሲሆን፤ ለአንድ ደቂቃ ባለማቋረጥ ጭብጨባ በማሰማት ለሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ህግን ለማስከበር ተሰማርቶ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ ላለው ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ክብር በመስጠት እንዲሁም፤ በህዝብና መንግስት የተጣለባቸውን ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው ሀይል ክህደት የተሰዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ተዘክረዋል፡፡

ህዳር 08 ቀን 2013 ዓ/ም
‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› መርሃግብር በፎቶ