EEP Communication
15.6K subscribers
10.8K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
የትውውቅ መድረክ ተካሄደ
………../////……………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደተቋሙ ለተቀላቀሉ አዳዲስ የኤሌትሪክ እና የመካኒካል መሐንዲሶች የትውውቅ መድረክ አካሄደ፡፡
በትውውቅ መርሃግብሩ ላይ የተቋሙ የሰው ኃይል ስልጠናና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ካሣ እንደተናገሩት አዳዲሶቹ መሐንዲሶች በኃይል ማመንጫዎች፣ በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎችና የኦፕሬሽን የስራ ክፍሎች የሚመደቡ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል በነበሩት ጊዜያት ሠራተኞች ወደ ተቋሙ ሲቀጠሩ በተደራጀ መልኩ በቂ መረጃ ሳያገኙ ወደ ሥራ መግባታቸው ተቋሙ በፍጥነት ለሚጠብቀው ውጤታማነት እንቅፋት እንደሆነባቸው በመገንዘብ የትውውቅ መድረኩ መዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የትውውቅ መርሃግብሩ ዋና ዓላማ የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ እንዲሁም ተቋሙ ሊያሳካ የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች፣ አደረጃጀቶች እና አሰራር ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ለማሳወቅ ነው፡፡
ከሰራተኞቹ የሚጠበቀውን በመለየት በአዕምሮ ዝግጁ ሆነው ወደ ሥራ ለማስገባት እንደሆነ ዶ/ር ወንደሰን ጠቁመዋል፡፡
በጊዮን ሆቴል በተካሄደው መድረክ ላይ የተቋሙ የሰው ኃይል ሥራ አስፈፃሚ ጨምሮ ከፍተኛ የስራ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማስፈን የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት ትልቅ ሚና እንዳለው ተጠቆመ
…………./////………..
የሠራተኛ ማህበራት የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ከማስከበር ባለፈ የሠራተኛው ማህበራዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር በኢንዱስትሪ ግጭት መነሻ ምክንያቶችና መከላከያ ዘደዎች ዙሪያ ለአባላቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የሀገር አቀፍ የኃይል ማመንጫ፣ ኬሚካልና ማዕድን ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀኃፊ አቶ ፀሐዬ አክሎክ እንደገለጹት በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚፈጠር አለመግባባትን ለመከላከልና የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማስፈን ዘመናዊ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መፍጠር ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡

አሰሪዎችና ሠራተኞች ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ሲሉ አለመግባባት እንደሚከሰት የጠቆሙት አቶ ፀሐዬ በየተቋማት የሚመሰረቱ የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበራት ግጭቶችን ለመፍታት ድርሻቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ማንኛውም ድርጅት ሆነ የሠራተኛ ማህበር የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማስፈን የሚያግዝ መተዳዳሪያ ደንብ ሊኖራቸውና ተፈፃሚነቱን ሊከታተሉ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የሠራተኛ ማህበራት ሲደራጁ ከተፅዕኖ ነፃ በሆነና አንድነትን ባጠናከረ መልኩ መሆን እንዳለበት አንስተዋል፤ ይህም በአሰሪዎች በኩል ተቀባይነት ያለው ማህበር ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

አቶ ፀሐዬ እንዳሉት በየተቋማቱ የሠራተኞችን አንድነትን ለማጠናከርና መብቶቻቸውን በተደራጀ መንገድ ለመጠየቅ ሠራተኞችን በአባልነት ለማቀፍ ማህበራት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል፡፡

የሠራተኛ ማህበራት የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ከመስራት በተጨማሪ የሠራተኛው ማህበራዊ ግንኙነት እንዲጠናከር እና ማህበራዊ ህይወቱ እንዲሻሻል ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያሉት አቶ ፀሐዬ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለማስወገድ ላለመግባባቱ መንስኤ የሚሆኑ ነገሮችን መለየትና በውይይት መፍታት እንደሚገባ ዋና ፀሐፊው አስረድተዋል፡፡

እንደ አቶ ፀሐዬ ገለፃ በድርጅቱ እና በሠራተኞች መካከል የሚፈጠሩ የተለያዩ ግጭቶች በድርድር፣ በሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች በኩል በሚመረጥ 3ኛ ወገን አስማሚ፣ በአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ እና በህግ አግባብ መፈታት ሊፈቱ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም የኢንዱስትሪ ሠላምን ለማስፈን መንግስት፣ አሠሪዎችና ሠራተኞች የየራሳቸውውን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ አቶ ፀሐዬ አሳስበዋል፡፡

ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ፣ በኢንዱስትሪ ግጭቶች መነሻ ምክንያቶችና መከላከያ ዘዴዎች፣ በኢንዱስትሪ ሰላምና ግንኙነት እንዲሁም በግጭት አፈታትና በህብረት ስምምነት ላይ በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ተቋሙ በ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የአማካሪ ግዢ ሥምምነት ተፈራረመ
............./////..........
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለደብባዊ የኃይል ቋት የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ የኢንጂነሪንግ፣ ግዥና ኮንስትራክሽን ሥራዎች የአማካሪ ቅጥር ግዥ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

BYUCKSAN Power Construction የተባለው አማካሪ ድርጅት ተቋሙ በደቡባዊ ግሪድ የሚያሰራውን የኢንጂነሪንግ፣ የግዥና ኮንስትራክሽን ሥራ የሚያማክር ነው፡፡

ሥራውን ለማከናወንም የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻና እና የኩባንያው ተወካይ ሚስተር ጅንግ ውን ጅኦንግ ናቸው፡፡

ህዳር 04 ቀን 2012 ዓ/ም
የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ ተመቷል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው
………………../////…………..
የተከዜ ሀይል ማመንጫ ግድብ በቦምብ ተመቷል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ካለው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ መረጃ ለህዝብ እያደረሰ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ድረገጹ እንዳስታወቀው ተከዜ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ልክ እንደ ሌሎቹ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ሁሉ በፌደራል መንግሥት የተገነባና የሚያስተዳድረውም የፌደራል መንግሥት ነው።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ሚልሻዎች በማይካድራ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሪፖርት ባወጣበት በህዳር 3፣ 2013 ዕለት፣ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የተከዜ ግድብ በቦንብ እንደተመታ የሚያትት ሆን ተብሎ የተቀናበረ፣ የሀሰት መረጃን ህወሓት በቴሌቪዥን አሰራጭቷል ብሏል።
ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችል መሆኑን የመረጃውን ሀሰተኛነት በቀላሉ ያረጋግጣል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል፡፡
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነታቸውን ገለፁ …………………………….///…………………………….
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች ‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› በሚል መሪ ቃል ለሠራዊቱ ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡

በዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

ሁሉም ተሳታፊዎች ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር የገለፁ ሲሆን፤ ለአንድ ደቂቃ ባለማቋረጥ ጭብጨባ በማሰማት ለሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ህግን ለማስከበር ተሰማርቶ ከፍተኛ ድል እየተቀዳጀ ላለው ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ክብር በመስጠት እንዲሁም፤ በህዝብና መንግስት የተጣለባቸውን ግዳጅ ሲወጡ በጁንታው ሀይል ክህደት የተሰዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ተዘክረዋል፡፡

ህዳር 08 ቀን 2013 ዓ/ም
‹‹ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ›› መርሃግብር በፎቶ